ከአዘጋጁ፡ በሚኒሶታ ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ያለው ጉዳይን እየተከታተልን በስፋት የሚደርሱንን አስተያየቶች በማስተናገድ ላይ እንገኛለን። አንዳንድ የዘ-ሐበሻ ወዳጆች በገለልተኛው ወገን ያለውን ብቻ እያቀረባችሁ ነው፤ ይህ ደግሞ ሚዛናዊነታችሁን ሊያሳጣችሁ ይችላል ሲሉ አስተያየት ሰጥተውናል። ዘ-ሐበሻ እንደ ነፃ ሚዲያነቷ የሁሉንም ሃሳብ ታስተናግዳለች። የተላኩላትን አስተያየቶችን ዘ-ሐበሻ ሳታስተናገድ የቀረችባቸው ጊዜያት የሉም። ሆኖም ግን አንዳንዶች የዘ-ሐበሻን በር ሳያንኳኩና ለዘ-ሐበሻ ሳይጽፉ ዘ-ሐበሻን ሊወቅሱ ቢሞክሩ አስተያየታቸው ሚዛን አይደፋም። ልንወቀስ የሚገባው የተላከልንን ጽሁፍ አናወጣም ስንል ብቻ ነው። ዘ-ሐበሻ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አትገባም፤ ሆኖም ግን ዜና የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ታስተናግዳለች። አሁንም ቢሆን በየትኛውም ቦታ አቋማቸውን ያደረጉ ሰዎች በድረገጻችን ሊገለገሉበት ይችላሉ። በግልጽ በዘ-ሐበሻ ኤዲቶሪያል ላይ እንደተቀመጠው በድረገጹ ላይ የሚቀርቡ አስተያየቶች ሁሉ የጸሐፊው እንጂ የዘ-ሐበሻ አቋሞች አይደሉም።
ለዛሬው አቡነ ዘካሪያስ ካህናቱን ያወገዙበትን ደብዳቤዎች ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ አስተናግደናል።