ሐሙስ መጋቢት 25 ቀን 2006 ዓ.ም.
ግርማ ሞገስ
የዚህ ጽሑፍ ግብ በመንግስት ስልጣን ሽሚያ የተነሳ በአንድ ወገን በዮሐንስ እና በአሉላ ትውልድ በሌላ ወገን በምኒልክ እና በጎበና ትውልድ መካከል የነበረውን የፖለቲካ ባላንጣነት፣ ለስልጣን ሲሉ የተደራረጉትን እና የፈጸሙትን ስህተት መተረክ አይደለም። በመካከላቸው የነበረው ጸብ ዙፋኑ ለእኔ ይገባ ነበር የሚል ጸብ ነበር፡፡ የስልጣን ጸብ ነበር። በእርስ በርስ ጦርነት የሚፈጸመው ስርዓት አልባው የመንግስት ሽግግር ባህላችን የፈጠረው ጸብ ነበር። ይህ የቀድሞ አባቶቻችን የፖለቲካ ባህል ችግር ዛሬም አብሮን አለ። ያን ችግር ለማስወገድ ሰላማዊ ትግል ጀምረናል። የኢትዮጵያን ህዝብ የመንግስት ስልጣን ባለቤት ለማድረግ ጉዞ ላይ ነን። ወደ ዴሞክራሲ ለመሸጋጋር በቁርጠኛነት ተነስተናል።
ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ