የሰው ልጅ በማህበራዊ ህይወት ውስጥ ዘልቆ ሲያልፍ የተለያዩ ባህላዊ እና ሳይንሳዊ ፎኩሎሪስቶችን ወግ ማዕረግ የሚሉትን ያልፋል፡፡ ይህ ወግ ማዕረግ እድሜና ሁነቶችን ተከትሎ የሚመጣ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ አንዲት ለአቅመ ሄዋን እና አዳም የመድረስ ወግ ማዕረግ ነው፡፡
ይህ የዕድሜ ክልል ደግሞ ከዛ በፊት የማይታወቅ አዲስ ምዕራፍ የሚገለጥበት ነው፤ ከተቃራኒ ጾታ ጋር በፍቅር የመተያየት የመፈላለግ ስሜት በብርቱ የሚከሰትበት ስለሆነ አንዳድ ሴቶች ከተቃራኒ ጾታ ጋር በቀላሉ የመግባባት ችሎታ ሊኖራቸው ይችላል። ሆኖም ግን ይህ ብቻውን የሚፈልጉትን ወንድ በመሳብ በእጃቸው ለማስገባት አይቻላቸውም፡፡
በተለይም (single partner) በአባት ወይም በእናት ብቻ ያደጉ ሴቶች በመግባባቱ በኩልም ችግር ገጥማቸዋል ይላል የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያ የሆነው ሮበርት ሲልዲኒ፡፡
ለመሆኑ ሴቶች ምን አይነት ወንድ ይወዳሉ? ብለን ለራሳችን ገራገር ጥያቄ ልናነሳ እንችላለን የተለያዩ ምላሽ ልንሰጥም እንችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን አብዛኛው ህብረተሰብ ይስማማባቸዋል፡፡ እነሱም ሴቶች በብዛት የሚወዱት ወንድ ወንዳወንድ ሰውነት ያለው ቆንጆ፣ ሀብታም ከሆነ አለቃ ምኞታቸው ተሳካ ይባላል፡፡ ነገር ግን የሴቶች እውነተኛ መግለጫ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ምክንያቱም ካሉት ወንዶች ዕድለኛ የሚሆኑት ከመቶ አንድ ፐርሰንት ይሆኑ ነበር፡፡ ሌሎች ይህንን አላየንም አልሰማንም፡፡
በመሆኑም ሴቶች የሚመኙት የሚመርጡት ወንድ የራሳቸው የሆነ መመዘኛ አላቸው ማለት ነው፡፡ በእርግጥ የሁሉም ሴቶች መመዘኛ አንድ ነው ማለት አይቻልም፡፡ እንግዲህ ሴቶች በግል መመዘኛቸው የመረጡትን ሰው በእጃቸው ለማስገባት ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል? ይላል የስነልቦናው ሊቅ ሮበርት ሲልዲኒ። ለዚህም ተለያዩ ጥናቶች አግዘውኛል፡፡ በተለይም ይላል ባለሙያው “አምስቱ መሪ ተግዳሮቻችን በሚገባ የተወጣች ሴት የፈለገችውን ወንድ በእጇ ለማስገባት አይሳናትም”ይላል፡
አብዛኞቹ ሴቶች ወንዶችን በመሳብ የራሳው ለማድረግ የሚጠቀሙበት ብልሃት ይኖራቸዋል፡፡ ነገር ግን ብልሃታቸው ግብታ እንጂ ሳይንሳዊ ባለመሆኑ አንዳንዴ በወንዶቹ ዘንድ ሌላ ትርጓሜ ሲያስጥባቸውና ከመሳብ ይልቅ ሲርቁት ይገኛል፡፡ ለዋቢነት በቀጠሮ ሰዓት አሳልፎ መምጣት፣ ቁጥብ መሆንና ኮራ ማለትን እንደ ማጥመጃ ወይም ተፈላጊነትን የማግኛ መንገድ አድርገው የሚጠቀሙ አሉ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ሌላም አሉታዊ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩ ሙከራዎች ሴቶች መታቀብ ይኖርባቸዋል። ይልቁንም ቀጥረው ቀጠሮውን ተግባራዊ በማድረግ ወንዶችን ለማማለል እና በእጅ ለማስገባት ሁነኛ መንገድዎን ዛሬውኑ ይሰንቁ፡፡ ከዚያ በኋላ እራስዎ መካሪ ይሆናሉ፡፡
በርካታ ሰዎች የሚሉት አንድ አባባል አለ “Don’t judge a body by its cover” አባባሉ መጽሃፍን በሽፋኑ ጥሩና መጥፎ መሆኑን መወሰን እንደማይቻል አጽንኦት የሚሰጥ ነው፡፡ የስነ-ልቦና ባለሙያው ግን አንድን ወንድ ለመሳብ አካላዊ መስህብን ተቀዳሚ የወንዶች ማማለያ መንገድ ይላል፡፡ ለዚህም አካላዊ መስህብን አንቀው (subconscious) የአእምሯችን ክፍል ይመኘዋል ይላል፡፡
እንስቷ የምትፈልገው ወንድ ጋር በምትቀርብበት ጊዜ ለእይታ ጥሩ ሆና መቅረብ አለባት፡፡ ይህም ሲባል በምትለብሰው ልብስ ከተክለ ሰውነቷ ጋር የተስማማ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርባታል፡፡ ምክንያቱም አንዳንዶች ሌሎች ሴቶች ለብሰውት በማየታቸው እና ስለወሰዱት የዛ አይነት አለባበስ ሊመርጡ ይችላሉ፡፡ ከዚህ በፍጹም መጠንቀቅ ይኖርባታል፡፡ ተክለ ሰውነታቸው እና የቆዳ ቀለማቸው ለሚለብሱት ልብስ ወሳኝ መሆኑን ሴቶች ሊገነዘቡት ያስፈልጋል፡፡