ከኢሳያስ ከበደ
1. ሳይረን
በሰው ልጅ የኋልዮሽ ታሪክ ወንዶች ሁል ጊዜም ኃላፊነት መውሰድ፣ መቆጣጠርና ምክንያታዊ መሆን ይፈልጋሉ፡፡ ታዲያ ሳይረኗ ሴት ይህንን የወንዶች ስሜት ጥንቅቅ አድርጋ የምታውቅ እውነትም ሴት የምትባል ናት፡፡ ይህቺ ሴት ታዲያ ወንዱ ያለበትን በነገሮች መገደብ አስረስታ ሁሉም ነገር በሱ ኃላፊነት እንደሚደረግ የምታሳስበው ናት፡፡ ታዲያ ይህቺን ሴት አንተ ከሌሎቹ ሁሉ ነጥለህ ልትለያት ትችላለህ፡፡ በአብዛኛው በአካላዊ ሁኔታዋ ጥንቃቄ ያለው አለባበስ፣ ለስለስ ያለ ሽቶ፣ እርጋታ ያለው አካሄድ፣ እፍረትና መሽኮርመም ያለበት የሚመስል ፈገግታ ቢነኩት ተሰባሪ የሚመስል ስስ ስሜትና ወደ ፊት በድፍረት ወደኋላ በመሽኮርመም መሀል ያለችና አንተንም ሙሉ ወንድነት እንዲሰማህ የምታደርግልህ ናት፡፡
2. እሳቷ
ሴት ልጅ ምንም ጊዜ ቢሆን የመደነቅና የመወደድ ስሜቷ አይረካም፡፡ ሁሌም ቢሆን የነገሮች ማዕከል ሆና መገኘት ትፈልጋለች፡፡ ታዲያ እሳቷ ሴት ሁሌም ቢሆን ተውባ ተሽቀርቅራና በወንዶች ተከባ መገኘት የምትፈልግ ናት፡፡ በህይወቷ የምትፈልገው ነገር ሁሉ በነፃነት ማውራት፣ ጮክ ብሎ መሳቅ፣ ፍቅር በመስራት መደሰት በአካባቢው ውስጥ ገኖ መታየትን ነው፡፡ ይህችን ሴት ለማግኘት ታዲያ ይህን ስሜቷን ማወቅ ይኖርብሃል፡፡ ስሜቷ መፈለግ ስለሆነ የተለየች ሆና እንዲሰማት ማድረግ ይገባሃል፡፡ ግን ደግሞ እንቅስቃሴህ በዚህ ብቻ ሳይገታ ሁሌም ይህን ጉዳይ ሁሉም ሰው የሚነግራትና የምታየው ስለሆነ ያለአንተ አብረሃት መኖር እሷ ጎልታ እንደማትታይ እንዲሰማትና ሁሌም አንተን እንድትሻ የማድረግ ከባድ የቤት ስራ አለብህ፡፡ መሳሳት የሌለብህ እሳቷ ሴት ሁሌም ቢሆን በወንዶች መከበብ ፀጋ የታደለች ነች፡፡ የቤት ስራህን ለመጀመርም መጀመሪያ አንተ እንደሌሎች ወንዶች ሁሉንም ነገር በፀጋ መቀበል የለብህም የራስህ አቋም ካለህ የሷ እሳትነት አንተን የማይሞቅህ እንዲመስላት ማድረግ ከቻልክ በእርግጠኝነት ከመሞቅ አልፎ እንደምታቃጥል ልታሳይህ ትጥራለች፡፡ ያኔ ታዲያ ለሷ ማማር ያንተ ከጎኗ መሆን እንደሚያስፈልግ ታሳያታለህ፡፡
3. ህልመኛ
ማንኛውም ሰው በአፍላ የፍቅር ዘመኑ ወደ ፊት ስለሚያፈቅረውና/ስለሚያፈቅራት ሰው የራሱ የሆነ የባህርይ፣ አካላዊ፣ ሃይማኖታዊና የስራ ህልም ይኖረዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ታዲያ እያደግን ስንመጣ እየተሸረሸረ ይመጣል፡፡ በዚህ በህልመኛ አፍቃሪ መደብ ስራ ያለች ሴት ታዲያ አሁንም በዛ ህልም ውስጥ የምትኖር ፍቅርን ልክ በልጅነቷ የፍቅር ተረቶች ውስጥ እንዳነበበችው በፅጌረዳ አልጋ የተሞላ፣ በደመና ውስጥ የሚንሸራሸሩበት አንዱ ላንዱ የሚሰዋበት አድርጋ የምትወስድ ናት፡፡ በዚህም የተነሳ የሰማችውን ሁሉ የምታምን፣ በትንሽ በትልቁ የምታዝን፣ ማንኛውንም ነገር ስለ ፍቅር ብላ የምታደርግ፣ ሁሌም በፍቅር ቃላት መሞገስን የምትወድ፣ ላፈቀረችው ሰው ታማኝ የሆነችና የልጅነት ንፅህና የሚታይባት ናት፡፡ ታዲያ አንተ ያፈቀርካት ሴት እነዚህ ባህሪዎች ካሏት ከላይ እንደገለፁት ሳይረንና፣ እሳት አለመሆኗን ተረድተህ ልታፈቅራትና ልትታመንላት ይገባል፡፡ ይህቺው ሴት ፍቅርን በገንዘብና በአካላዊ ገፅታ የማትለካ ናት፡፡ ግን ደግሞ ከአንተ ማፍቀርህን ከማወቅ ጀምሮ ጥቃቅን ስጦታዎችን አበባ፣ ቸኮሌት፣ ዳያሪ… ትጠብቃለች፡፡ ስለዚህ ተዘጋጅ፡፡
4. አብዮተኛዋ
አብዛኞቻችን የምንኖርባት ዓለም ውስጥ በነገሮች ተገድበንና ታጥረን እንዳለን ይሰማናል፡፡ በዚህም የተነሳ ከኛ የበለጠ ነገሮች ላይ በራስ መተማመን የሚሰማቸው፣ ባህሪያቸው አሻሚ በነገሮች ለየት ያሉ ሰዎች ሲያጋጥሙን በቀላሉ እንማረካለን፡፡ አብዮተኛዋ ሴት ታዲያ ሁሌም ቢሆን ከተለመዱት ሴቶች ለየት ያለ አለባበስ፣ አስተሳሰብና ድርጊትን ታራምዳለች፡፡ ይህቺ ሴት እንደ ወንድ ልትለብስ፣ ፀጉሯን ድሬድ ልታደርግ፣ አይኗን ከተለመደው የሴቶች እስታይል ውጪ ልትኳል፣ ወይም ደግሞ ለየት ባለ ሁኔታ የባህል ልብሶች ወይም የራሷን ቅድ የሆነ ልብስ ልታደርግ ትችላለች፡፡ በምታወራበትም ጊዜ በነገሮች እንደማትመሰጥ ሁሉም ነገር ምንም የማይመስላት መስላ ትታያለች፡፡ ይህችን ሴት ታዲያ እንዳለች መቀበልና ካንተ ጋር ስትሆን እንደፈለገች እንድትሆን ነፃነት መስጠት ሀሳብ በሚነሳበት ጊዜም አንተም የራስህን ወጣ ያለ ነገር ይዘህ መከራከር እሷን በእጅህ ለማስገባት ቀላሉ ዘዴ ነው፡፡
5. ትንሿ
ይህቺ ሴት ህፃናዊ ባህሪ የሚታይባት ቅብጥብጥ፣ በኃይል የተሞላች፣ ስሜታዊ፣ አኩራፊ፣ ንፁህና ተወዳጅ ናት፡፡ አብረሃት ስትሆን ሁሌም በሆነ ነገር እንደተመሰጥክ ነው፡፡ ልክ እንደ ህፃን ልጅም ሁሉን ነገርህን የራሷ ማድረግ ትፈልጋለች፡፡ ወደ ልጅነት ወርቃማ ጊዜህ ትመልስሃለች ጥላህ ትሮጣለች፣ ጣፋጭ ነገሮች እንድትገዛላት ታስቸግርሃለች ቶሎ ደርሶ ኩርፍ ልትል ወይም ልትመታህም ትችላለች፡፡ ታዲያ ይህችን ሴት ከሷ በልጠህ በመገኘት ተንከባካቢ፣ ሁሉን ቻይ፣ ተቆጪና አፍቃሪ ከሆንክ ልታሸንፋት ትችላለህ፡፡ አስታውስ ልጆች ሁል ጊዜም የሚመራቸው ይፈልጋሉ፡፡ አንተም ታዲያ ኃላፊነት ወስደህ መምራት መጀመር አለብህ፡፡
6. ሚስጢራዊ ጥላ
ጥላዋ ሴት በአማካይነት ህግ ውስጥ ንግስት ልትላት ትችላለህ፡፡ ልክ በፀሐይ ላይ እንዳለ ጥላም ስትቀርባት እየራቀች ስትርቃት እየቀረበች ትታህ እንዳትተዋት ታደርግሃለች፡፡ እንደማትፈልግህ ትነግርሃለች ግን ደግሞ መልሳ በአይኗ ታባብልሃለች፡፡ በዚህ ፈታኝ በሆነ ወቅት ማድረግ ያለብህ እሷን ልክ እርግብ ጥሬ እየተሰጠ እንደሚለምደው እንድትለምድህ ማባበልዋን የበለጠ እንድትገፋበት ማፍቀርህን እየገለፅክ ማበረታታት ነው፡፡ ቀስ በቀስም ልክ እራሷን የበለጠ በነፃነት መግለፅ ስትጀምር አንተ ደግሞ በተራህ ጥላ ሆነህ መራቅና የበለጠ መፈለግ ይኖርብሃል፡፡
7. መስታወት
በዚህች ሴት ውስጥ አንተ መልሰህ እራስህን ታየዋለህ፡፡ ስሜትህ ይሰማታል ህመምህ ያማታል ሳቅህ ያስቃታል፡፡ አንተ ወደሃት እሷን ማግኘት ከፈለክ ልክ አንተ እራስህን እሷ ውስጥ እንዳገኘኸው እሷን ደግሞ ውስጥህ ፈልጋት፡፡ እሷስ የውስጥ ህመሟ ምንድን ነው? ከልቧ የምትደሰተውስ መቼ ነው? ብለህ ጠይቅና ድረስበት፡፡ ያኔ አንድ እኩል ስለምትሆኑ ሁሉም ነገር የሰመረ ይሆናል፡፡ ግን ደግሞ እራሷን ከፍታ እስክታሳይህ ታገስ፡፡
8. ብርሃን
ከውስጥ የሚመነጭ በራስ መተማመን፣ እርጋታ፣ የአማላይነት ኃይል፣ ምክንያታዊነት የሚታይባትና ልክ እንደ ብርሃን የምትታይ እንጂ የማትነካ የምትመስል ሴት ናት፡፡ በፍቅር ውስጥ ይህቺን ሴት እንደማማለል ከባድ ነገር የለም፡፡ ሁሉ ነገሯ ሙሉና የማትደፈር ትመስላለች፡፡ ታዲያ አንተም ልክ እንደ እሷ በነገሮች ምክንያታዊነት የምታምን፣ ምስጢራዊ አጓጊ፣ በራስ መተማመንህ ኃይል ሆኖ መገኘት ይኖርብሃል፡፡ በምክንያታዊነት የምታምነው ይህቺው ሴት ብርሃኗን የሚያይላት ሰው ስለምትፈልግ ያላትን ነገር ልታበረታታላት ይገባል፡፡ መረሳት የሌለበት ግን ማስመሰልን ብጥርጥር አድርጋ የምታይ ሴት ስለሆነች የምታደርገው ነገር ሁሉ ከልብህ የመነጨ መሆን አለበት፡፡ በንግግርና በበጎ አድራጎት ትማረካለች ሁሌም ቢሆን የሚበልጣትን ወንድ ስለምትፈልግና በእውቀትም፣ በገንዘብም በማህበራዊ ግንኙነትህም ከሷ የተሻለ ነገር ይዘህ ተገኝ፡፡
9. ኮከብ
ኮከቧ ሴት በሁሉም ነገር ብልጫ ያላት በቁንጅና፣ በሀብት፣ በእውቀት በማህበራዊ ግንኙነት የላቀች በነገሮች በጎ አተያይ ያላትና ይህ ቀረሽ የማትባል ናት፡፡ ሁሌም በየሄደችበት ቦታ በሁሉም ጎልታ የምትወጣ በወንዶችም በሴቶችም የምትከበብ ናት፡፡ ሁሉም ሊያገኛት የሚጥርባትና ሽሚያ የበዛባት ናት፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥም ተስፋ የሌለህ ሊመስልህ ይችላል፡፡ ግን ደግሞ ተሳስተሃል ኮከብ ስለሆነች ኮከብ ትፈልጋለች ብለህም ካሰብክ አሁንም እደግመዋለሁ ተሳስተሃል፡፡ አንድ ነገር አስተውለህ ከሆነ በጣም የምትገርም ያልካት ሴት ከአንድ ተራ ሊባል ከሚችል ሰው ጋር በፍቅር ልትወድቅ ትችላለች፡፡ ስለዚ ህ አንተም ከቻልክ ከሷ የበለጠ ኮከብ ካልቻልክ ደግሞ የሷን ኮከብነት የሚያጎላ ብርሃን ሆነህ መቅረብ ይኖርብሃል፡፡ S
ዘጠኙ የአማላይ ሴቶች ባህሪይና እነሱን መልሶ ማማለያ ምስጢር
Latest from Blog
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤ 15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን
ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር
የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!” አቶ ቡልቻ ደመቅሳ
ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
ሀገሪቱ እኮ የለችም…. የጄነራሎቹ ጉድ…. የአብይ አህመድ ነገር…ሀገሪቱ እኮ የለችም…. የጄነራሎቹ ጉድ…. የአብይ አህመድ ነገር…ሀገሪቱ እኮ የለችም…. የጄነራሎቹ ጉድ…. የአብይ አህመድ ነገር…
ሀገሪቱ እኮ የለችም…. የጄነራሎቹ ጉድ…. የአብይ አህመድ ነገር…
ቴዲ አፍሮና ጃዋር መሐመድ፤ ”ንጉሥ አንጋሹ ፖለቲከኛ” የዘመኑ ፖለቲከኞች መካከል አንዱ የሆነው ጃዋር መሐመድ ‘አልፀፀትም’ በሚል ርዕስ ያዘጋጀውን መጽሐፍ 🔴What separates Jawar and Abiy is their measure of how much non-Oromos
ቴዲ አፍሮና ጃዋር መሐመድ፤ ”ንጉሥ አንጋሹ ፖለቲከኛ”
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ
ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )
“ገብርዬ ነበረ የካሳ ሞገሱ…..” በጋዜጠኛ እና መምህርት መስከረም አበራ አብይን የሚያንዘፈዝፉት የእንስቷ ንግግሮች አድምጡት
“ገብርዬ ነበረ የካሳ ሞገሱ…..” በጋዜጠኛ እና መምህርት መስከረም አበራ
ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ
ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)
ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ