የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ
“ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!” አቶ ቡልቻ ደመቅሳ
አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፦ ‘አጼ ምኒልክና ራስ ጎበና አብረው ነው ያደጉት። አብረው ነበሩ፣ ይነጋገሩ ነበር። አሁን እኔና አንተ እንደምንነጋገረው። አጼ ምኒልክ ራስ ጎበናን “ማንም የለም ከጎኔ መጥተህ እርዳኝ” ባሏቸው ግዜ “እኔ ኦሮሞ ነኝ ካንተ ጋር መስራት አልችልም” ብለዋል ራስ ጎበና? አላሉም፡፡
ምኒልክ ከራስ ጎበና ጋር ፈረስ ጉግስ ይጫወቱ ነበር፣ የአጼ ምኒልክን ችግር አዩ፣ ገባቸው። እሽ እከተልሃለሁ አሏቸው። ምን ስራ ትሰጠኛለህ አላሉም፣ “እሽ እከተልሃለሁ ነው” ያሉት፡፡ እሳቸው እንግዲህ አጼ ምኒልክ ሸዋን ይዘዋል፣ ወለጋ፣ ሃረር ከእርሳቸው ኮማንድ ውጭ ነው። ኦሮሞ ግን እንደተበታተነ በየአገሩ ቀረ፣ ይህንን ለማሰባሰብ አጼ ምኒልክ ጎበናን መረጡ። ተስማሙ አብረው መጡ፣ ወደ አዲስ አበባ፡፡ ‘ይገለኛል፣ ይጠላኛል’ ለምን አልተባባሉም? እንደዛሬው ልዩነት አለን ብለው አላሰቡም፡፡ “አንድ አገር ነን” ብለው ነው ያሰቡት፡፡ ልዩ ልዩ አገርም አለን ብለው አላሰቡም። ጎበናም ምንም ሳይጠይቁ ከእርሳቸው ጋር ገቡ አብረው በሉ ጠጡ ተጋቡ፡፡ ይህንን ነው የማውቀው። ሁለቱም አይፈራሩም አብረው ነው ለዘመናት የኖሩት። ተጋብተው ተዋልደዋል።”
አጼ ምኒልክን ለኦሮሞ የተለየ ጥላቻ አንዳላቸው አድርገው የሚያነሱ ሰዎች አሉ፡፡ ይህ ነገር እንዴት ያዩታል?
አቶ ቡልቻ፡- ‘በፍጹም ዳግማዊ ምኒልክ ለኦሮሞ ጥላቻ የላቸውም። “አሮሞ የሚባል ስም አልወድም እገላቸዋለሁ፣ ወላይታን አልወድም እፈጃቸዋለሁ፣ አደሬን አልወድም….” ብለው አንድን ህዝብ መርጠው ጠላቴ ነው ብለው አያውቁም፡፡ አስበውትም አያውቁም። አገር እንዲሰለጥን፣ ህዝብ ሁሉ እንዲሰለጥን ነው የተቻላቸውን ሁሉ ያደረጉት። ለአንድ ህዝብ የተለየ ጥላቻ ኖሯቸው ይህንን ህዝብ እንውጋው ብለው ይነጋገራሉ ብዬ መገመት እንኳን አልችልም፡፡ እሳቸው ለአገራቸው ስልጣኔ ነው የለፉት፤ ማንንም አይጠሉም ነበር።’
ጌጡ ተመስገን
እነ በቀለ ገርባ፤ጁዋር መሃመድ ሌሎች ደም የጠማቸውም በስጋ አልሞቱም እንጅ ሙተዋል