October 2, 2024
12 mins read

ኳሷ ያላችው እስክንድር ነጋ ጋር ነው – ግርማ ካሳ

Eskinder

እስክንድር ነጋ በኢትዮ360 ቀርበ ነበር፡፡ ማስታወቂያውን አስቀድሞ ስለሰማሁ ቃለ ምልልሱን አደመጥኩት፡፡

እንደሚታወቀው፣ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ አንድነት ድርጅት የሚባለውን መቋቋምና፣ የድርጅቱ መሪ እስክንድር ነጋ መሆኑን ተከትሎ፣ ከሶስት ወር በፊት በፋኖ አመራሮች መካከል ውዝግብ ተነስቶ፣ አብዛኛውን ህዝብ አንገት ማስደፋቱ የሚታወስ ነው፡፡

በቃለ ምልልሱ እስክንድር ነጋ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ አንድነት ድርጅት አመሰራረት ሂደት በዝርዝር ለማሳየት ሞክሯል፡፡

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ አንድነት ድርጅት ከተቋቋመ ሶስት ወር ሆኖታል፡፡ አሁንም ከዚህ ድርጅት ጋር በተገናኘ፣ እስክንድር ነጋ በሜዲያ ቀርቦ ማብራሪያ ለመስጠት፣ ህዝቡን ለማሳመን መሞከሩ፣ ድርጅቱ ከህዝብ ቅቡልነት አንጻር ችግር እንዳለበት አመላካች ነው፡፡ ያ ባይሆን ኖሮ በስንት አንገብጋቢ ጉዳይ ላይ አስተያየት መስጠት ሲገባው፣ ከሶስት ወራት በኋላም ድርጅቱን ለህዝብ ለመሸጥ ባልሞከረ ነበር፡፡ አንድ በሉ፡፡

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ አንድነት ድርጅት የግለሰቦች ሳይሆን ድርጅቶች በጋራ የመሰረቱት እንደሆነ እስክንድር ያስረዳል፡፡ ሰባት ድርጅቶች፣ በሻለቃ ባዬ የሚመራው የአማራ ፋኖ በጎንደር፣ በዘመነ ካሴ የሚመራው የአማራ ፋኖ በጎጃም፣ በምሬ ወዳጆ የሚመራው የአማራ ፋኖ ወሎ እዝ፣ በአቶ አሰገድ መኮንን ይመራ የነበረው፣ አሁን በኢንጂነር ደሳለኝ የሚመራው የአማራ ፋኖ ሸዋ እዝ፣ በሻለቃ መከታው የሚመራው የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ፣ በሻለቃ ሃብቴ ወልዴ የሚመራው የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝና ፣ በራሱ በእስክንድር የሚመራው እንድ እዝም ሊቆጠር የማይገባው የአማራ ህዝባዊ ሰራዊት ናቸው፡፡

እነዚህ ሰባት ድርጅቶች አመቻች ኮሚቴ ሲመርጡ፣ የድርጅቱ ስምና መተዳደሪያ ደንብ ሲያጽድቁ በሙሉ ስምምነት ( unanimous consent) እንደሆነ ነው እስክንድር የገለጸው፡፡ ያንንም ተከትሎ ሁሉም የቃል ኪዳን ሰነድ ፈርመዋል፡፡ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ አንድነት ድርጅትም የእስክንድር ድርጅት ሳይሆን ሁሉም ፋኖዎች፣ እነ ዘመነ ካሴን ጨምሮ፣ ያቋቋሙት ድርጅት ነው ማለት ነው፡፡ ከሌሎች ምንጮችም ያሰባሰቡት መረጃ የሚጠቁመው፣ የቃል ኪዳን ሰነድ እስኪፈረም ድረስ የነበረውን ሁኔታ እስክንድር እንደገለጸው ነው፡፡ ሁለት በሉ፡፡

95% የሚሆነውን ጨርሰው፣ ችግር የተፈጠረው መጨረሻ ላይ መሪ ማን ይሁን በሚለው ላይ ነው፡፡ ቀደም ሲል እንደነበረው ሁሉም የተስማሙበት መሪ ቢመርጡ ኖሮ፣ ምርጫ የሚለውን ትተው፣ በ unanimous consent ቢያደረጉት ኖሮ፣ ሁሉም የሚቀበሉት መሪ ከሌለ የቡድን አመራር (collective leadership) ቢያደረጉት ኖሮ ሂደቱ 100% በስኬት ይጠናቀቅ ነበር፡፡ ትልቁ ስህተት የተሰራው እንግዲህ እዚህ ጋር ነው፡፡ ጉዳዩ የህልውና ትግል ሆኖ፣ የቆንጅና ውድድር ይመስል፣ ወይንም በሰላም ጊዜ የሚደረግ የፖለቲካ ፉክከር ይመስል ወደ ምርጫ መኬድ አልነበረበትም፡፡

ለዚህ ስህተት ደግሞ እስክንድር ብቻ አይደለም ተጠያቂው፤ ሁሉም የፋኖ መሪዎች እነ ዘመነ ካሴም ሳይቀር ተጠያቂዎች ናቸው፡፡፡ ሁሉም ተሳስተዋል፡፡ አንዱን ኮንኖ ሌላውን ከፍ ማድረግ አይገባም፡፡ ሶስት በሉ፡፡

ወደ ምርጫ ሲገባ መጀመሪያ ሶስት በኋላ ሁለት እጩዎች እንደቀረቡ እስክንድር ይናገራ፤ል፡፡ ሶስተኛው እጩ ማን መሆኑን ባይገልጽም፣ እኔ ባለኝ መረጃ ሶስተኛው እጩ አቶ አሰገድ መኮንን ነበር፡፡ በኋላ አቶ አሰገድ ራሱን ከእጩነት ያወጣል፡፡ ዘመነ ካሴና እስክንድር ነጋ ብቻ ቀሩ፡፡

ዘመነ ካሴ፣ የዝናቡን፣ የምሬንና የአስገድን ድምጽ ብቻ እንዳገኘ እስክንድር ነጋ ይናገራል፡፡ ከዚያ በኋላ ስብሰባው ይቋረጣል፡፡ ሂደቱ ሊቀጥል አልቻለም፡፡ በሌላ ጊዜ እንደገና ሂደቱ በአዲስ ለማስጀመር እንደተሞከረ መሰብሰብ እንደተቻለ እስክንድር ይናገራል፡፡

ስብሰባው፣ በመጨረሻ የተደረገው ስብሰባ ሲሆን የስብሰባውም ይዘት በሚያሳዝን ሁኔታ እንዲለቀቅ ነው የተደረገው፡፡ በነዚህ በተለቀቁ ኦዲዮውች የፋኖ ስም ነው የተዋረደው፡፡ ህዝብን አንገቱን እንዲደፋ ነው የተደረገው፡፡

መጀመሪያ ላይ እስክንድር ነጋ በሰብሰባው እንዲሳተፍ ሲጠየቅ፣ አቶ አሰገድ መኮንን፣ “የትኛውን ኃይል ነው የሚመራው ? እንደ ፋኖ እዝ አንድ ጠቅላይ ግዛትን ወክሎ ይምጣ እንጂ፣ በራሱ እስክንድር መሳተፍ አልነበረበትም” የሚል ተቃውሞ አስሞቶ ነበር፡፡ እነ አስረስ ማሬ ፣ እነ ምሬ ወዳጆ ፣ ከአቶ አሰገድ ጋር ተስማምተው፣ መጀመሪያዉኑ እስክንድር ነጋ በሰብሰባዎቻቸው እንዲገኝ መፍቀድ አልነበረባቸው፡

በዚህ ስብሰባ እስክንድር ነጋ ለእጩነት ቀረበ፡፡ የእስክንድር ነጋን እጩነት የተወሰኑ መሪዎች ተቃወሙ፡፡ መስፈርት ያሟላል፣ መስፈርት አያሟላም የሚል ክርክር ተነሳ፡፡ ዘመነ ለእጩነት ሲቀርብ ምንም ያላሉ፣ እስክንድር ሲቀርብ ያን ያህል፤ ተቃውሞ ማስነሳታቸውና ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸው ተገቢ አልነበረም፡፡ መጀመሪያዉኑ በምርጫ መሪ እንዲመረጥ መስማማት አልነበረባቸውም፡፡ አራት በሉ፡፡

ከዘጠኝ አመራሮች አራቱ ከተቃወሙ በኋላ፣ ከዚያ በመቀጠል የነበረውን ሂደት እስክንድር ነጋ አላብራራም፡፡ ቃለ ምልልሱ በዋናነት እርሱን ትክክለኛና ዴሞክራሲያዊ ሌሎችን ችግር ፈጣሪ አድርጎ ለመክሰስ ነው የሞከረው፡፡ ይህ በራሱ የእስክንድርን አካሄድ አደገኛነት አመላካች ነው፡፡ በሂደቱ እርሱም ተጠያቂ ነውና፡፡

“እኛ ከፈለግን መሪነቱን ልንሰጣቸው እንችላለን፡፡ የስልጣን ችግር የለብንም፡፡ ግን ህግ መከበር አለበት፡፡ እነርሱ የበላይ እኛ የበታች፣ እነርሱ የፈለጉት ካልሆነ ብለው የፈለጉት እየሆነ እኛ ደግሞ ከነርሱ በታች ሆነን ልንቀጥል አንችልም፡፡ በድርጅቱ ውስጥ ሁላችንም እኩል መሆን አለብንም” የሚል አስተያየት ሰጥቷል፡፡ ይህ ትክክለኛ አባባል ነው፡፡ አንዱ የበላይ፣ ሌላው የበታች ሊሆን አይችልም፡፡

እሺ የስልጣን ችግር ከሌለበት፣ ፍላጎቱ በፋኖ አደረጃጀቶች ውስጥ ማንም የበላይ ሳይሆን፣ በቅንነት፣ በእኩልነት ፣ በመከባበር ትግሉን መምራት ከሆነ፣ ለምን ከመሪነቱ ተነስቶ፣ የቡድን አመራር እንዲኖር ሁኔታዎችን አያመቻችም ? እስክንድርን ተክቶ ዘመነ ካሴ መሪ መሆን አይችልም፡፡ ማንም ዘመነ በእስክንድር ነጋ ይተካ ያለ የለም፡፡ እነ ዘመነ ካሴን የሰሩት ስህተቶች ገብቷቸው፣ ባለኝ መረጃ፣ አሁን እነርሱም፣ መሪ እንሆን እያሉ አይደለም፡፡ የቡድን አመራር መኖሩንም ይደግፋሉ፡፡

እስክንድር ነጋ ወደ ጫካ ስገባ፣ አብረውት ወደ ሰማኒያ ፋንዎች እንደነበሩ፣ ከነርሱ 15 ሕይወታችው እንዳለፈ ገልጿል፡፡ እነዚህ ጀግኖች እግዚአብሄር ነፍሳቸውን ይማር፡፡ታዲያ እስክንድር፣ ለነዚህና ለሌሎችም የተሰው ፋኖች ክብር፣ አሁንም በየጫካው ከዘረኛው አገዛዝ ጋር እየተፋለሙ ላሉ ፋኖዎች ደህንነት፣ ለአገርን ለህዝብ ሲል፣ ለምን ከግትር አቋሙ ፈቀቅ ማለት ተሳነው ? ለምን እርሱንም ያካተተ የቡድን አመራር እንዳይኖር በሩን ይዘጋል ? ለምን በሽማግሌ ወይንም በውስጥ መስመር ከርሱ ጋር ካልተስማሙት ጋር ከመነጋገር በሜዲያስ ወጥቶ ሌሎች የፋኖ መሪዎችን ይኮንናል ?

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ስሙ፣ ህገ ደንቡ ሁሉም በሙሉ ስምንነት ከጸደቁ፣ ችግሩ የነበረው አመራር ላይ ከሆነ፣ ድርጅቱን ማፍረስ ባይገባም፣ የተሰራው 95% እንዳለ ሆኖ፣ ከምርጫ በፊት ወደነበረው ሂደት ብቻ በመመለስ፣ የቡድን አመራር (collective leadership) እንዲኖር ማድረግ አስቸጋሪ አይመስለኝም፡፡ እንግዲህ ኳሷ ያላችው እስክንድር ነጋ ጋር ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop

Don't Miss