June 29, 2024
13 mins read

ገንቢ ፀፀትንና ልባዊ ይቅርታ መጠየቅን እየሸሸን ፈፅሞ የትም አንደርስም!

June 29, 2024
ጠገናው ጎሹ

በዚህ ሂሳዊ አስተያየቴ ከሰሞኑ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት በኢትዮጵያ የአሚሪካ አምባሳደር ጋር ስለ አደረጉት ውይይት በፎቶ ግራፍ ተደግፎ የቀረበ ዜናን መነሻ ያደረገ ነው። ይህንን እንደ ምሳሌ/እንደ ማሳያ ተጠቀምኩበት እንጅ በዚህ ረገድ ያለብን ፈተና ዘርፈ ብዙና ሥር የሰደደ (wide and chronic)  የመሆኑን መሪር እውነትነት ዘንግቸው አይደለም።

በመሠረቱ  እጅግ አስከፊ በሆነ ፖለቲካ ወለድ መከራና ውርደት ወስጥ የሚጓጉጠው  (የመከራ ዶፍ ሰለባ የሆነው) ህዝብ  የሚያሳስበውና የሚቆጨው ማነኛውም ኢትዮጵያዊ በግልብም ሆነ በቡድን በየትማኛውም ጊዜና ቦታ አወንታዊ አስተዋፅኦ የማድረጉ አስፈላጊነት የሚያጠያይቀን አይመስለኝም።    ይህ ማለት  አስፈላጊና ገንቢ የሆነ ሂሳዊ  አስተያየት  (ትችት)  አያስፈልግም  ወይም ይህንን ማድረግ አላስፈላጊ ተጠራጣሪነትን እንደ ማራመድ ተደርጎ መወሰድ አለበት ማለት አይደለም።።

ከዚህ አንፃር ነው የሁለቱ  ግለሰቦች ከአሚሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማት ጋር የመነጋገራቸውን ዜና በመልካም ዜናነት መቀበል ትክክል ቢሆንም ጥያቄ ማንሳትም ተገቢ የሚሆነው። ያለምንም ጥያቄና ሂሳዊ አስተያየት ወይም ያለምንም እንከን አልባነት ማለፍ ግን ትክክል አይሆንም። ፈፅሞ አይጠቅምም።

እንደ መግቢያ ይህንን ካልኩ ወደ ጥያቄ አዘል አስተያየቴ ልለፍ።

1) መቸም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወለድ መከራና ውርደት ያሳስበኛል ከሚል አካል/ወገን ጋር ስንነጋገር የአማራ ፋኖ እና የሌሎች የትግል ባለድርሻዎችና ተጋሪዎች  ጉዳይ መነሳቱ አይቀርምና በዚህ ረገድ ተገቢው ጥንቃቄና ፖለቲካዊ ጥበብ ሊኖረን ይገባል።ምክን ቱም  ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ አደረጃጀቱና ፍኖተ ካርታው ወደ ዴሞክራሲያዊ  የአንድነት ብስራት አዋጅና የተግባር ውሎ ተሸጋግሮ ለዚህ የድል ግስጋሴው ያግዝ ዘንድ ማንዴት/ይፋዊ ሃላፊነት ካልተሰጠን በስተቀር በግል ወይም በቡድን  ደጋፊነት ከምናደርገው አስተዋፅኦ አልፈን መሄድ ያለብን አይመስለኝም። የአነዚህ ሁለት ወገኖች (የገዱና የይልቃል) የጥረት ይዘትና አቀራረብ ከዚህ አንፃር ስለ መሆኑ ወይም ስላለመሆኑ እርግጠኞች ነን ይሆን?

2) ሀ/ በተለይ ደግሞ እንደ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አይነት ከወጣትነት እስከ ባለ ግራጫ ፀጉር የእድሜ ርዝማኔ የህወሃት ኢህአዴግ እጅግ እኩይ ዓላማ  አስፈፃሚ እና ራሱን ብልፅግና ብሎ የሰየመው እጅግ ሴረኛና ጨካኝ የኦህዴድ-ኢህአዴግ ጉልቾች አንዱ በመሆን “እኛ ለሥልጣን ሳይሆን ለአገር ስንል ነው” የሚል እና የፖለቲካ ሥልጣን ከመያዝ እውነታና ወሳኝነት አንፃር ሲታይ እጅግ የወረደ ዲስኩር የደሰኮረ እና በአብይ አህመድ በቅጡ እንኳ ሳይነገረው ከወንበር ወንበር እያቀያየረ መናገር የሚችል አሻንጉሊት አድርጎ ሲገለገልበት የነበረ ሰው ሌላው ቢቀር ከምር የሆነና ገንቢነት ያለው ፀፀትና ይቅርታን ለመግለፅ የሞራል አቅም የተሳነው ምን አይነት ትርጉም ያለው ግብአትነት እንዳለው መጠየቅ በደምሳሳው ማግለል የሚሆነው እንዴት ነው? ለ/ ከምንም በፊት ከምር የሆነ ፀፀትንና ይቅርታን በግልፅ እና መሪር አስተማሪነት ባለው የፖለቲካና የሞራል ሰብእና ለመግለፅ ወኔው ከሌለን ለግዙፉና ለመሪሩ የነፃነትና የፍትህ ተጋድሎ አስተዋፅኦ የምናደርገው እንዴት ነው?  ሐ/ በፊትም የህወሃት እኩያን የፖለቲካ ኢሊቶችን እና በኋላም የኦህዴድ/ብልፅግና ተረኞችን እኩይ ዓላማና አጀንዳ እጅ እያወጡ በማፅደቅ እንደ ደመ ነፍስ እንስሳት ከርሳቸውን ከመሙላት ያለፈ ሚና የሌላቸው የፓርላማ አባላት (ካድሬዎች) ስብሰባ ላይ  ዘመናት ያስቆጠረውን የህዝብ መከራና ውርደት የሚያንፀባርቅ ዲስኩር ማስማትን በአወንታዊነት ማየት ተገቢ ቢሆንም እውነተኛ በሆነ ፀፀት እና ገንቢ በሆነ (ከምር አስተማሪ በሆነ ይቅርታ) ካልታጀበ በእጅጉ ጎደሎ የሆነ የፖለቲካ ሰብእና አይሆንም እንዴ? መ/ እንዲህ አይነት የፖለቲካና የሞራል ግልፅነትና ልዕልና የሚጎላቸው ወገኖች  አያድርገውና የሥርዓት ለውጥ ትግሉ ቢከሽፍና እኩያን ገዥ ቡድኖች የካድሬነት የመመለሻ በር ቢያዘጋጁ  ሰንካላና ወራዳ የሰበብ ድሪቶ እየደረቱ የመጀመሪያ ተሰላፊዎች ሊሆኑ እንደማይችሉ ምን ያህል እርግጠኞች ነን? ሠ/ የፖለቲካ ባህላችንና ታሪካችንም የዚህ አይነት አሳፋሪና መሪር ተሞክሮ ደሃ ነው እንዴ?  ረ/ ለመሆኑ እንደ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የመሰለ የእኩያን የጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ፈጣሪና አስፋፊ ሥርዓትን በፍፁም ካድሬነት ከልጅነት እስከ ግራጫ ፀጉር እድሜ   አገልግሎ   በቃኝ ብሎ የተሰናበተን  ፖለቲከኛ የታሰበበት፣ የተደራጀና የተቀነባበረ፣ አካፈን አካፋ ብሎ ለመጥራት የማይገደው፣ ምን መደረግ አለበት የሚለውን ጥያቄ ቀጥተኛና ግልፅ በሆነ አቀራረብ ለመመለስ የሚችል ፣ እና እውነትም ከልብ በመፀፀት  ለነፃነትና ለፍትህ ትግሉ ጉልህ አስተዋፅኦ እያደረገ ነው  የሚያሰኝ ያላሳለሰ ጥረት ሲያደርግ አላየንም/አልሰማንምና እንዲህ አይነቱን ፖለቲከኛ ምነው ብቅና ጥልቁ? ብሎ መጠየቅ ፖለቲካዊ ነውር  ነው እንዴ?

3)  ለብዙ ዓመታት በካድሬነትና በባለ ሥልጣንነት ተዘፍቀው የኖሩበትን ሥርዓት በሆነ ምክንያት ለቀው ሲወጡ ምንም ስህተት እንዳልሠሩ ያለምንም  ፀፀትና ይቅርታ ስለ ነበሩበት እኩይ የፖለቲካ ሥርዓት እንደ አዲስ ሲነግሩንና ሲተነትኑልን እኔስ/እኛስ ? ለማለት ፈፅሞ ወኔ የሌላቸው አቶ ገዱ አንዳርጋቸውንና አንዳርጋቸው ፅጌን የመሰሉ ወገኖችን በግልፅና በቀጥታ ፖለቲካዊው አመጣጣችሁና አኳኋናችሁ በእጅጉ ጎደሎ ነውና ህሊናችሁን ከምር መርምሩ ማለት  ካልቻልን ስለ የትኛው እውነተኛና ዘላቂ የነፃነትና የፍትህ  ሥርዓት ነው የምናወራው? ይህንን ከምር ወስደውና መርምረው በትክክለኛው ፍኖተ ነፃነትና ፍትህ ላይ ለመገኘት ፈቃደኞችና ዝግጁዎች የማይሆኑ ወገኖችን (ግለሰቦችን) ማባበል ግዙፍና መሪር ዋጋ የተከፈለበትንና እየተከፈለበት ያለውን መሠረታዊ የሥርዓት ለውጥ ትግል ይጎዳል እንጅ ፈፅሞ አይጠቅምም ብሎ መከራከር ትክክል ካልሆነ ሌላ ምን?

4) አንዳንድ ሁኔታዎችን (አጋጣሚዎችን) እየጠበቁና እያመቻቹ አደረግን ወይም እያደረግን ነው ለማለት ከሚያስችሉ ዜናዎችና ምስሎች (ፎቶ ግራፎች ወይም ተንቀሳቃሽ ምስሎች) ጋር ብቅና ጥልቅ ማለት ከጠቀሚታው ይልቅ አሳሳችነቱ (አዘናጊነቱ)  ያመዝናልና  ከዚህ አይነት ጋግርታም (chronically poor) የፖለቲካ ባህል ለመውጣት በግልፅና በቀጥታ መነገጋገር ይኖርብናል።

5) በዚህ ረገድ ህልውና፣ ነፃነት፣ ፍትህ፣ እኩልነት፣ ሰላምና የጋራ እድገት የሚሰፍንባትና የሚረጋገጥባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በአንፃራዊነት እጅግ አበረታችና ተስፋ ሰጭ ተጋድሎ በማካሄድ ላይ ከሚገኙት ከአማራ ፉኖዎች እና ከሌሎች የዴሞክራሲ አርበኞች ብዙ ይጠበቃል። ጋግርታሙ የፖለቲካ ባህል ማለትም የወንበር ሽሚያ፣ የአድርባይነት ደዌ፣ የጎጠኝነት አባዜ፣ በግል ኩርፊያ የአንድነት ስንጥቅን ከመድፈን ይልቅ የማስፋት፣ የግልብና የግል ስሜት ሰለባ የመሆን፣ መከራና ውርደት መቀበልን እንደ ፅድቅ መንገድ አድርጎ የማመንን (ራስን የማታለልን) ፣ የሥርዓት ለውጥ ሳይሆን የጉልቻ ለውጥ ባለ ድርሻ የመሆን  ወራዳነትን፣ በራስ ውድቀት ትግሉ ቢቀለበስ ” ፈጣሪ ባይለው ነው” የሚለውን ጨምሮ ሰንካላ የሰበብ ድሪቶ የመደረትን፣ ወዘተ  አስቀያሚ ፈተና የጊዜን ወርቃማነት እና ሌሎች የትግል ግብአቶችን ግምት ውስጥ ባስገባ ሁኔታ የፖለቲካና የወታደራዊ አንድነት ሃይልን (አደረጃጀትን) እውን በማድረግ ካላለፍነው እዚያና እዚህ የምናያቸው የብቅና ጥልቅ የፖለቲካ ጨዋታዎች ጠልፈው እንደማይጥሉን ዋስትና የለንም።

እናም ልብ ያለው ልብ ይበል!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ “ይድረስ ለእገሌ” ማለቱ ሰለቸኝና ተውኩት እንጂ ዛሬም መጻፍ የፈለግሁት የአማራን ዕልቂት ለመታደግና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር እየተዋደቁ ላሉት ወገኖቼ ነው – በፋኖም ይሁን በሌላ ስም፡፡ ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ የነገድና

ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

Go toTop