አይተህ ተመልክተህ የሚደርስብህን፣
ተምድር ሊያጠፉ የሸረቡብህን፤
ግማሽ ክፍለ-ዘመን የቆመሩብህን፣
አማራ ቃል ግባ አጣምረህ ክንድህን፣
ሰፈርን መንደርን ድርምስ አርገህ ጎጥን፡፡
እንደነዚያ አርበኞች እንደ ቅደመ አያትህ፣
ከሰሜን ከደቡብ ተምዕራብ ተምስራቅም ያለህ!
ክብር ወይም ሞት በል አሞት ኮስተር አርገህ፡
እርስትህን ላትለቅ በመላው አቅጣጫ፣
የቅደም አያትን ውርስ ውሀ ላታስበላ፣
እጅ ለእጅ ተያይዘህ አማራ ቃል ግባ!
ንቅንቅ ላለማለት ተአያቶችህ ማማ፣
ታሪክና ቅርስህ ተፍቆ እንዳይጠፋ፣
አማራ አንድ ሆነህ ክንድህን አበርታ!
በውጩም በውስጡም ቁማርና ሴራ፣
ዘርህ ሙጥጥ ብሎ ተምድር እንዳይጠፋ፣
እምቢኝ ዘራፍ ብለህ ፎክርና አቅራራ!
እንኳን ስድሳ ሚሎን አንድ ሰውም ብትቀር፣
እርስት ላመስጠት ክብርን ላለመጣል፣
በአገርህ ታቦቶች በመስጊዶችህ ማል፡፡
እንደ አድዋው ፋኖ እንደ አምስቱ ዘመን፣
ቆርጦ ለመፋለም ፋሽሽትን ወራሪን፣
አማራ ቃል ግባ አስታውስ አርበኞቹን፡፡
አሚካላና እሾህ እንቅፋት ቢገጥምህ፣
ወድቀህ ለመነሳት ድልን ሰንደቅ አርገህ፣
ወደ ሁዋላ ላትል ከቶ ተስፋ ቆርጠህ፣
አማራ ቃል ግባ ልክ እንደ አያቶችህ!
በአውሬዎች በጅቦች ወገን ላታስበላ፣
ልፍስፍስ ጅላጅል ላትሆንም ባንዳ፣
ከልብህ ከአንጀትህ አማራ ቃል ግባ!
ተራስህም አልፈህ ሌሎችን ልትረዳ፣
ክንድን ፈርጠም አርገህ አማራ ቃል ግባ!
እንኳን በምድር ያለህ ሁሉን የምትሰማ፣
በማርስ በጁፒተር የምትኖር አማራ፣
በድል ለመመከት ዘር አጥፊ ወረራ፣
ተቃቅፈህ ተማማል አማራ ቃል ግባ!
አማራ ቃል ግባ! አማራ! ቃል ግባ! አማራ ቃል ግባ!
በላይነህ አባተ ([email protected])
መስከረም ሁለት ሺ አስራ ስድስት ዓ.ም.