መጀመሪያ ሁለት መግባባት ባሉብን ጉዳዮች ላይ እንግባባ፡፡ኦሮሙማና ወያኔ የቡድን አባላት እንጅ ህዝብን አይወክሉም፡፡ ዝርዝር እሳቤውን በጣም በአጭሩእንደሚከተለው እንመልከተው፡፡
ኦሮሙማ እሳቤ ነው፡፤ የኦሮሞ የበላይነት የነገሰበት፣ ከሁሉም በላይ ኦሮሞ፣ ሁሉም የኦሮሞ የሚል አመለካከትን የሚያቀንቅን (አይዶሎጅ) ነው፡፡ መነሻቸው የበታችነት የሆነ የጥቂቶች የማይሳካ ቅዠት ነው፡፡የትምና መቼም ሊሳካ አይችልም፡፡ ስለሆነም ኦሮሙማ የጥቂቶች የተሳሳተ አይዶሎጅ እንጅ ሰፊውን የኦሮሞ ህዝብ አይወክልም፡፤ በተመሳሳይ መልኩም የወያኔ አስተሳሰብ ከትግራይ የበቀሉ ጥቂት ከሀዲወች በማኒፌስቶ ላይ አስፍረውት በይፋ ይዘዉት ወደስልጣን ያመጡት የዘር ፖለቲካ እሳቤ ነው፡፡ሰውን በሰውነቱ ሳይሆን በዘሩ ከፋፍሎ ህዝብን ወዳጅና ጠላት ብሎ ፈርጆ፣ ክልል መድቦና እርስ በርስ አናክሶ አገሪቱን ለዚህ ያበቃት መርዘኛ የወያኔ እሳቤ ነው፡፡ ስለሆነም ለኢትዮጵያ አገርነት የጀርባ አጥንት የሆነውን ሰፊውን የትግራይን ህዝብ አይወክልም፡፡
በርእሱ ስለተጠቀሰው ጉዳይ እንመለስ፡፡
በመርዘኛው ወያኔ ጊዜ በ27 አመታት ውስጥ ያልታዩና ይደረጋሉ ተብለው ሊገመቱ የማይችሉ የአገርና ህዝብ ውርደቶች አሁን በኦሮሙማ ጊዜ ተፈጽመዋል፡፡ በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ሰቅጣጭና ግፉ ሞልቶ የፈሰሱባቸውት አያሌ ወንጀሎች በአምስት አመት የኦሮሙማ አገዛዝ ውስጥ ተካሂደዋል፡፤
ስፍር ቁጥር የሌላቸው ዝርፊያወች፣ አሰቃቂ ግዲያወች የጦር ወንጀሎች፣ በሰው ልጅ ላይ የተፈጸሙ አረመኔያዊ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች …ወዘተ በንጹሀን ላይ ተፈጽመዋል፡፡ የተንሸዋረረውን ወያኔና ኦሮሙማወች ተናበው የፈጠሩትን ህገ መንግስት ኦሮሙማወች በመተላለፍ ኦሮሙማ ዘግይቶ እንዲውጣቸው ለማስቻል ለዚሁ ሊጠቅሙ የሚችሉ ክልሎችን ፈጥረዋል፡፡ በከተማ ላይ ከተማ ይመሰርታሉ፡፤ ከኦሮምያ ክልልም ከአዲስ አበባ አስተዳደርም ከሁለቱም ጎን ተካላዮች ሆነው ቀርበው ድንበሩን በአሻቸው መንገድ ከልለን ተፈራረምን ያሉት የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባላት ናቸው፡፡ይህ ከሆነ ማግስት ጀምሮ የአዲስ አበባ ከተማን ስልቀጣው ጫፍ ደርሷል፡፤
የአዲስ አበባን ጉዳይ ካነሳን ዘንድ ከነጻ ገበያ መርህ ውጭ መንግስት ተብየው የዱርየወቹ ስብስብ ህዝቡን ከፋፍዬ ብዙ ደጋፊ አገኛለሁ በሚል ከንቱ ስሌት በአከራይና ተከራይ መካከል ገብቶ የሚያቦካው “ጭቃ” በአለም ባንክና በአለም አቀፍ ገንዘብ ድርጅቶች ዘንድ አልትወደደለትም፡፡ራሱኑ ጠልፍ ሊጥለው ጫፍ ደርሷል፡፡በሌላ በኩል ደግሞ በኢትዮጵያ ብር ላይ ”ለአምጭው እንዲከፈል ህግ ያስገድዳል”” የሚለው ጽሁፍ በራሱ በብሩ ላይ አለ፡፡የዚሁ አሰራር ትክክለኛነትም በአሜሪካውም ዶላርም ላይ “THIS NOTE IS LEGAL TENDER FOR ALL DEBTS PUBLIC AND PRIVATE” የሚለው ተጽፎ ይገኛል፡፡የእኛው የዱርየወች ስብስብ ከእውቀት ማጣት ይሁን ከጥቅም ፍለጋ አዲስ አበባ ውስጥ ለመኪና ነዳጅ ለመሙላት ዲጂታል ካርድ ካልሆነ በስተቀር ብር አንቀበልም ማሰኘቱ የቱን ያህል ጥጋብና ከዲጂታል ካርዱ ጋር የተገናኘ የልዩ ጥቅም ተገዥ እንደሆኑ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ ይህ የመንግስት ብልግና ብቻ ሳይሆን የስብስቡ ፍጹም ህገወጥነት ማሳያ ነው፡፤
በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ጉድ እናንሳላችሁ፡፡ እስኪ ይታያችሁ የአንዲት አገር ዋና ከተማ ለተወስነ ቡድን ልዩ ጥቅምን ትሰጣለች የሚል ህገ መንግስት የት አገር ነው ያለው?? የአሜሪካ ዋና ከተማ የሆነችው ዋሽንግተን ዲሲ ከሜሪላንድና ከቨርጅኒያ ግዛቶች በወቁቱ የነበሩት የአገሪቱ መሪወች መሬት አውጣጥተው ነው የፈጠሯት፡፤ ታዲያ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ልዩ ጥቅም የሚባል ነገር የለም፡፡ ይህ በወያኔ የተተከለ መርዝ አጎምርቶ አሁን ለኦሮሙማ ፍሬ የሚሰጥበት ጊዜ ላይ ደርሷል፡፡ ለነገሩኮ አይሳካላቸውም እንጅ አሁን ላይ ሁለቱ ጸረ አማራ ህብረትን ፈጥረው የለምን?? አማርኛ ቋንቋንም በየክልሎቻቸው እንዳይነገር ለማገድ “ስምምነት”የፈጸሙ መሆኑን በሚጠሉት በአማርኛ ቋንቋ ይፋ አድርገውልንስ የለምን? እፍርታሞች!!!
ይህ ሁሉ ሲሆንና ሲፈጸም ጭንጋፉና ዱሮም የወያኔ አሁንም የኦሮሙማ አሽከር ሆኖ ለጭነት አህያነት የተፈጠረው 46 ሚሊዮኑን አማራን “እወክላለሁ” የሚለውና በተግባር ግን በሁሉም አማራወች ተንቆ የተተፋው ብአዴን(የአማራ ብልጽግና) የትም መድረክ ላይ የአማራን ህዝብ ጥቅም ወክሎ ወይንም የአማራን ህዝብ እልቂቱን ተቃውሞ ቅንጣት የመናገር ስልጣን አላሳየም፡፤ አፈጣጠሩም አይፈቅድለትም፡፡ የአማራ ህዝብ በአዲስ አበባም ላይ ሆነ በአማራ ርስቶች ላይ ያቀዱትን የወያኔንም ሆነ የኦሮሙማን የቀን ቅዠት ያለጥርጥር ያመክነዋል፡፡ ትንቅንቁንም በርሱ ቆራጥ ልጆች ጀምሮታል፡፡
ወደ አብይ አህመድ ስብእና ስንመለስ ከግለሰቡ መገለጫወች ውስጥ በውሸት መቀደዱ፣ መርህ፣የለሽነቱና ከእውቀት የጸዳ መሆኑ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ግልጽ የሆነ ሀቅ ነው፡፡ በውሸት ከመቀደዱና ከማታለል ችሎታው አኳያ፣ ከማጭበርበር ልምዱና ከማጨናበር ብቃቱ አኳያ በብዙሀኑ ኢትዮጵያዊያን አይን አብይ አህመድ ይሰራቸዋል ተብሎ በማይጠረጠርና በማይታሰብ ደረጃ ሁሉንም የግዲያና የዝርፊያ ድጊቶችን እርሱ ራሱ አቅዶና ፈቅዶ ፈጽሟቸዋል፡፡ አስፈጽሟቸዋልም፡፤ ይህ ነው እርግጡ፡፡ አብይ ሳያወቅና ሳይፈቅድ አንዲትም ነገር አንደማትፈጸም መረዳት አለብን፡ዘረፋም ትሁን ጭፍጨፋ ግዲያም ትሁን ማፈናቀል ወይንም ወረራ ..ወዘተ ያለእርሱ እውቅና አትካሄድም፡፡ ለዚህ ነው አብይ አህመድ በሆኑት አረመኔያዊ ድርጊቶች ላይ ሁሉ ጸጥ እረጭ የሚለው፡፡ይህም 18 ባንኮችን ከማዘረፍ ጀምሮ ፤ ኢንጂነር ስመኘው በቀለን ዶ/ር አምባቸው መኮንን፣ ጀኔራል አሳምነው ጽጌን ጀኔራል ሰአረ መኮንን …ወዘተ ግዲያወችን ያጠቃልላል፡፤
የአገር መሪ ሆኖ ብር እያተሙ የዶላር ጥቁር ገበያ ንግድን በስውር ማጧጧፍ የራሱ የአብይ አህመድ የማይጠረጠር የዘረፋ ቁማር ነው፡፡ የጥቁር ገበያ ሰንሰለቱንና የራሱን ሰወች በውጭ አገራት በገንዘብ አስተላላፊነት ከመመደብ ጀምሮ ዶላሩን ወደራስ ወይንም ወደ ተወካይ ነጋዴ ኪስና(ሂሳብ) እዚያው እያስቀሩ ኢትዮጵያ ውስጥ በይፋ በባንክ በየቀኑ በሚሊዮኖች ብሮች ለተላከላቸው ሰወች ክፍያ እንዲፈጸም እያስደረገ ነው፡፤ በዚህ ድርጊቱም በህጋዊ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ የአለም አቀፍ ሂሳቧ (country account) መግባት የነበረበትን ሬሚታንስ ወደ ጥቁር ገበያ ንግድ እያዞረው ነው፡፡ ይህንኑ የአገሪቱ ገንዘብ ሚኒስቴርና ብሄራዊም ሆነ ንግድ ባንኮች አያውቁትም ማለት ለቀባሪው ማርዳት ነው፡፤ ዱሮስ በማን ተመድበው ለማን እየሰሩ ነውና????
ታዲያ ማን ይሙት ከየዋሁ የኢትዮጵያ ህዝብ እይታ አኳያ አሁን አብይ አህመድ ይህንን ሁሉ ያደርጋል ብሎ ማን ይጠረጥራል??
የዶላሩና የዩሮው( የውጭ ምንዛሬው) የገዥው መደብ አደገኛና ድብቅ ቁማር ላይ ትንሽ ላቆያችሁ፡፡ በአሁኑ ሰአት ኢድስ አበባ ውስጥ በቀነ ከ50 እና 100 ሽህ ብር በላይ ከባንክ ማውጣት በማይቻልበት ጊዜ ወደ ሌላ ሰው ሂሳብም በቀን ከተወሰነ ብዛት (በየቀኑ እንዳመቻቸው ይለዋውጡታል) ውጭ ማዛወር ወይንም ማስገባት ለህዝቡ ፈተና በሆነበት ጊዜ በአብይ አህመድ ሰወች በኩል ከውጭ አንድ ዶላር በ110 ብር ሂሳብ ለተላከለት ገንዘብ ተቀባይ በቀን በብዙ መቶ ሚሊዮኖች ብሮችን ወደተቀባዮቹ ሂሳብ ማዞርና ገንዘብ በባንክ ቀርቦም መክፈል ምንም ችግር የለውም፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፡፡ በህገወጥነት የሁሉንም ኢትዮጵያዊያን የባንክ ሂሳቦችንና ባለቤቶችን መረጃ በእጁ አጠቃልሎ የያዘው ይህ ቡድ ብሩን ለተቀባዩ ሰው የሚያስገባው ላኪው ዲያስፖራ ውጭ አገር ሆኖ ዶላሩን ለዘመዶቹ ሲልክ ብሩ የሚገባው ወደተጠቀሰው የተቀባይ ሂሳብ ብቻም አይደለም፡፡ ተረኞቹ የሁሉም ባንኮች ዝርዝር መረጃ ስላላቸው <<በራሳቸው ምክንያት>> እነርሱ ወደመረጡት የትኛውም በንክ ተቀባዩ በዚያ ባንክ ውስጥ አካውንት እንዳለው በስሙ ፈልገው በማግኘት በታዘዙት ሳይሆን እነርሱ በመረጡት የባንክ ሂሳብ ብሩን ያስገቡለታል፡፡ፈጣሪ አምላክ ያሳይችሁና ታዲያ እኛ ኢትዮጵያዊያን በማን እጅ ውስጥ ነው ያለነው?? ይህንንስ ማድረግ ማለት ምን ማለት ነው??
“ኢትዮጵያ አትፈርስም” እያለ እየተበጠረቀ ከላይ ሆኖ ወንጀሎቹን ዝርፊያወቹን ግድያወቹን ያዘዘው፣ የመራውና ያስፈጸመው የኦሮሙማው ቁንጮ አቶ አብይ አህመድ አሊ ነው፡፤
አገራትን በማፍራረስ ብዙ ልምድ ያላቸው “ልማደኞቹ” የውጭ ሀይሎች ኢትዮጵያንም ለዘመናት ጥርስ ነክሰውባት ሲያደቡ ስለነበርና ለእነርሱ ቅጥረኛ መሪ ሆኖ የሚሰራላቸው ወኪል ሲፈልጉ የኖሩ ስለነበረ ይሄዉና አሁን ያንን ሰው አግኝተዋል፡፡ “ከወንጀል ተጠያቂነት ነጻ እናወጣሀለን” ብለው እንደሻቸው የሚያዙት ይህ ከንቱ ሰው አቶ አብይ አህመድ አሊ ይባላል፡፡ እንጭጩ አብይም ቃላቸው እውነት መስሎት አገሪቱን አሳልፎ ሰጥቷቸዋል፡፡የላይቤሪያውን ፕሪዝዳንት የሳሙኤል ዶን አጨራረስ ቢያጤነው ይሻለው ነበር፡፡
እንዳው በፈጠራችሁ አምላክ እስኪ አስቡት፡፡ ይህ አይነት አውሬነት፣ ይህ አይነት ጭካኔ፣ ይህ አይነት ተረኝነትና ዘረፋ ግድያና ጭፍጨፋ የአገር መሪ ነው በተባለ ሰው በገራሙ፣ በየዋሁ፣ በጎስቋላው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ መፈጸም ነበረበትን???
ወላጆቿን ገድለውባት እሷንም ሊደግሟት ሲሉ “ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም” ብላ ስላለቀሰችው ታዳጊ ልጅና ነፍሰ ጡራን ሴት አንገቷን አርደውና ሽሉን ከሁዷ ሸልቅቀው አውጥተው በእቅፏ ላይ ስላደረጉት ሴትዮ ስናስብ መጠሪያ ስማቸው ምንም ይሁን ምንም ድርጊታቸው ምን ያህል አውሬ ምን ያህል ከእንሰሳነት የወረደ ስራ እንደሆነ እገንነዘባለን፡፡ ሰውን ገድሎ ዘቅዝቆ በስልክ እንጨት ላይ መስቀልስ ምን ይሉታል?? ሰውን አርዶ ፎቶ አብሮ (selfie)መነሳትስ ምንነትን ያመለክታል?? ከጀርባ ሆኖ የነዚህ ሁሉ ሰቅጣጭ ግፎችና ጭፍጨፋወች መሪና አዛዥ ሴረኛው አብይ አህመድ አሊ ሲሆን በተዋረድም ጡንቻ ራሱ ሽመልስ አብዲሳ ምርኮኛው አስር አለቃ ብርሀኑ ጁላና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡
አቶ አብይ አህመድ የንጹሀንን አስክሬን በቴሌቪዥን ቀርቦ በዘር ከመቁጠር ጀምሮ ለሙታኑ መቃብር ዛፍ መትከል ጥላ ይሆናቸዋል ብሎ እስከማሾፍ የሄደ ወደርየለሽ እቡይ ነው፡፤
በወያኔ በኩልም እንዲሁ ብዙ አሰቃቂ ድጊቶች ተፈጽመዋል፡፡ አንድቷን ጉድ ብቻ ነቅሼ ልጥቀስላችሁ፡፤ እየተፈራረቁ ለአራት ሲደፍሯት የነበረችውን አንዲት እናት “እባካችሁ ተውኝ የሰባት ልጆች እናት ነኝ” ብላ ስትለምናቸው ሌሎች ሶስት ደፋሪወችን ጨምረው በድምሩ ለሰባት እንደትደፈር ሲያደርጉ ድርጊታቸው ምን ያህል አውሬወች መሆናቸውን ያስረዳል፡፡
በወያኔም ሆነ በኦሮሙማ በኩል በአማራው ዘር ላይ ብዙ አሰቃቂ ወንጀሎች ተፈጽመዋል፡፤ አማራ የገዥ መደብ ሆኖ በመራባቸው አመታት ውስጥ ወንጀሎችና ግፎች በአማራ የገዥው መደብ አባላት ተፈጽመው ሊሆን ይችላል፡፡ ተፈጽመዋል የሚለውን እንያዝ፡፡ ያንን ግፍና ወንጀል የስሩት ግን በወቅቱ የነበሩት የአማራ የገዥ መደቦች እንጅ የአማራ ሰፊ ህዝብ አይደለም፡፡ ታዲያ አሁን ላይ ይህንን ከማንም የባሰ ጎስቋላ ኑሮ የሚመራን የአማራ ህዝብና ገበሬ እንደ ህዝብ ከማየትና እንደ ህዝብ አብሮ ከመኖር ውጭ በአማራነቱ እያደኑ ተረኞች ስለሆኑ ብቻ መጨጨፍና ማሳደድ ምንን ያስከትላል ብሎ አለማሰብ ነውር ነው፡፤ ኦርሙማ ለሰራው ግፍ ቆይቶ ጊዜው ሲደርስ ኦሮሞ ዋጋ መክፈል አለበት እንደማለት ነው፡፤ ወያኔ ለሰራው ግፍ የትግራይ ህዝብ ቆይቶ ይሰቃይ እንደማለት ነው፡፤ ይህ ጸረህዝብነት ነው፡፤ ይህ አጉል ጀብደኝነት ነው፡፤ ይህ አፓርታይድ ነው፡፤ ይህ አረመኔነት ነው፡፡
ላለፉት አመታት አማራው በወያኔም በኦሮሙማም የተሰራበት ግፍና መከራ ጽዋው ሞልቶ ስለፈሰሰና አሁንም ድረስ ግፉ ቀጥሎ እየተካሄደበት ስለሆነ አማራው ዝም ብዬ ሞቼ አላልቅም ብሎ ወስኖ፣ ጠንክሮና አንድ ሆኖ በአማራነቱ ለአማራነቱ የሚያስፍልገውን ዋጋ ከፍሎ ራሱን ከግፈኞቹ አገዛዝ በአስተማማኝ ነጻ በማውጣት በአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ የ46 ሚሊዮኑ አማራ ወሳኝ ሀይል ሆኖ ለመቆም ቆርጦ ወደ ወደ ተጋድሎና ወደ አመጻ ገብቷል፡፡ ጠላቶቹ ገፍተው ገፍተው ለዚህ ስላበቁት ተጋድሎው ላይቀለበስ አሁን ላለበት ደረጃ ደርሷል፡፡ ወደ ኋላ አይመለስም፡፤ ምንን ተስፋ አድርጎ ነው አማራው ከእንግዲህ ተጋዶሎውን የሚያቆመው?? የአማራው ነጻነት ጥርጊያ መንገድ ሆዳም አማራወችን በያሉበት ከማስወገድ ይጀምራል፡፡
የኦሮሙማ አፓርታይድ በክልሉ የሚኖሩ የሌሎች ብሄር ብሄረስቦች ላይ በይፋ የሚፈጸመው ማሳደድ መግደልና መጨፈጨፍ ሲሆን ይህ ድርጊትም በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ መንደሮችና ከተሞች ዙሪያ ይኖሩ የነበሩ ከ11 ሽህ በላይ አባወራወችን ማለትም በትንሹ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኗሪወች በላያቸው ላይ ቤት በማፍረስ ህጻናትን ጅብ በማስበላትና በመግደል ህዝብ እያየ፣አለም እየታዘበ መንግስት ተብየው የኦሮሙማ ስብስብ እያየና እያወቀ ሆን ተብሎና ታቅዶ በይፋ የተደረገ የአፓርታይድ ድርጊት ነው፡፤ የትምና መቼም የተፈጸሙት መሰል ግፎች በልዩ ሁኔታ በአማራው ላይ ያነጣጠሩ ናቸው፡፡ መንግደ ዘግይቶ ሚሊዮኖችን ከመጠየቅ ጀምሮ ስንቱ አፓርታይዳዊ ድርጊት ተዘርዝሮ ያልቃል??
የኦሮሙማ ፋሽዝም የተለየ መግለጫ አያስፈልገውም፡፤ አለም ያወቀው ጽሀይ የሞቀው ሀቅ ነው፡፡ሚሊዮኖች ንጹሀን በዘራቸው አማራ በመሆናቸው እየተለዩ በኦሮሚያ ክልል በጭካኔ ደማቸው እንዲፈሥ መደረጉ በሚገባ ይታወቃል፡፡ተመዝግቦም ተይዟል፡፤
የኦሮሙማ የባሪያ ፍንገላ አዲስ ክስተት ነው፡፡ ሴት እህቶቻችን ወደአረብ አገሮች ለስራ እየተላኩ ግፍ እንደሚፈጸምባቸውና ብዙወቹም እዚያው ራሳቸውን እንሚያጠፉ አያሌ መገናኛ ብዙሀን ዘግበውታል፡፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞ አሁን በቅርቡ አንድ አሳፋሪና አዋራጅ የባሪያ ፍንገላ ድርጊት በመንግስት እውቅና ተፈጽሟል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ወደሊባኖስ ለስራ የሚሂዱ ኢትዮጵያዊያን ፓስፖርቶቻቸው በአሰሪወቻቸው እጅ እንዲያዝ አውቆና ፈቅዶ በይፋ ውል ፈጽሟል፡፤ ታዲያ ይሄ በታሪክ ከምናውቀው የባሪያ ፍንገላ በምን ይለያል??
የኦሮሙማ ወንጅሎች ብዙ ናቸው፡፤ በግፎቹም አስገዳጅነት ህዝቡ ለአመጻ ወጥቷል፡፡አሁን ላይ በተለየ መልኩ አማራው ቆርጦ ወደ ትግሉ ሜዳ ገብቷል;፡፡ አብይ አህመድም የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒፎርምን አስለብሶ የኦሮምያን ጦር ወደ አማራ ክልል አዝምቶ ትንቅንቁ ቀጥሏል፡፡ ትጥቋን ያልፈታችው ወያኔም ራያንና ወልቃይትን በኦሮሙማ ትከሻ ታዝላ ከአማራው ነጥቃ ለመውሰድ ድብቅ ዝግጅቷን አድርጋለች፡፡የውጮቹም ይህ እንድሳካ እየተሯሯጡ ነው፡፡
ከእንግዲህ ሜዳውም ፈረሱም ይሄዉና፡፡ የኦሮሙማ መንጋ የአማራ አሽከሮቹን አስከትሎ ከወያኔ ጋር የፈጠረው ጸረ አማራ ጥምረት የአማራውን ህዝብ የነጻነት ትግል ሊያስቆሙት ከቶም አይቻላቸውም፡፡ በአገር ደረጃ ኦሮሙማን ለመደምሰስ አማራው ፋና ወጊ ሆኖ ትግሉን እያጧጧፈው ነው፡፤ ከሁለቱ አንዱ የግድ ይፈጸማል፡፡ ወይ ኦሮሙማ ተሽቀንጥሮ አገር መልሳ ትቀጥላለች ወይንም አገር ትፈራርስና የእርስ በርስ ጦርነቱ በሁሉም አካባቢ ተጋግሎ መፈራረሱ እውን ይሆናል፡፡
በመሀል ግን በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ተረኞቹ ከብቶች “ልዩ ጥቅም አለን” እንደሚሉት ጅላጅልነት ለኦሮሚያ ልዩ ነጻነትና ልዩ ሰላም ለብቻው ፈጽሞ አይመጣም፡፤
የኦሮሙማ አፓርታይድ ፋሽዝምና ባሪያ ፍንገላ በተግባር ሲገለጽ (እውነቱ ቢሆን)
Latest from Blog
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ
ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )
“ገብርዬ ነበረ የካሳ ሞገሱ…..” በጋዜጠኛ እና መምህርት መስከረም አበራ አብይን የሚያንዘፈዝፉት የእንስቷ ንግግሮች አድምጡት
“ገብርዬ ነበረ የካሳ ሞገሱ…..” በጋዜጠኛ እና መምህርት መስከረም አበራ
ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ
ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)
ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ
እግዚኣብሔር ግን ወዴት አለ?
ልዩ ቆይታ ከገዱ አንዳርጋቸው ጋር ! – “ዐብይ ቂም የያዘ የነጣቂ መንግስት መሪ ነው”/ “አማራ እየተዋጋ ያለው ሰላምን ፍለጋ ነው” – ክፍል አንድ ልዩ ቆይታ ከገዱ አንዳርጋቸው ጋር ! –
“ፋኖ የበለጠ ይደራጃል ወደ ኋላ አይልም!”/ “የትግራይን ህዝብን ይቅርታ ጠይቂያለሁ” “ፋኖ በናፍቆት እየተጠበቀ ነው” ገዱ አንዳርጋቸው (ዶ/ር)
ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር) (ታህሳስ 19፣ 2017) December 28, 2024 መግቢያ እንደተነገርን ኢትዮጵያን “ከዕዝ ወይም ከሶሻሊስታዊ” ኢኮኖሚ አላቆ ወደ “ ነፃ ገበያ ኢኮኖሚ” እንድትሸጋገር ከተደረገ ይኸው ከ31 ዓመት በላይ ሊያስቆጥር ነው። በጊዜው ስልጣንን የተቆናጠጠው የህወሃት አገዛዝ
ሁለ-ገብ ለሆነ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ዕድገት መሰረት የሚጥል ህግ፣ ወይስ የኢትዮጵያን ሀብት የሚያዘርፍና ህዝብን አቅመ-ቢስ የሚያደርግ አዲስ የባንክ ህግ- ከኒዎ-ሊበራሊዝም ወደ ባሰ ኒዎ-ሊበራሊዝም የዝቅጠት ጉዞ!
ልዩ ቆይታ ከገዱ አንዳርጋቸው ጋር ! – “ዐብይ ቂም የያዘ የነጣቂ መንግስት መሪ ነው”/ “አማራ እየተዋጋ ያለው ሰላምን ፍለጋ ነው” – ክፍል አንድ
ልዩ ቆይታ ከገዱ አንዳርጋቸው ጋር ! – “ዐብይ ቂም የያዘ የነጣቂ መንግስት መሪ ነው”/ “አማራ እየተዋጋ ያለው ሰላምን ፍለጋ ነው” – ክፍል አንድ
የሲቪል ማህበረስብ ድርጅቶች ባለስልጣን፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን (EHRDC) “ገለልተኛ ባለመሆን ከተቋቋሙበት ዓላማ ውጭ ተንቀሳቅሰዋል” በሚል ምክንያት ማገዱ ገለጸ። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል (EHRDC)
መንግስት ኢሰመጉ እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን አገደ፤ የታገዱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቁጥር አራት ደረሷል
“መካር የሌለው ንጉስ እንዳይሆኑ” ፤ ግልጽ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የተፃፈ አቶ ያሬድ ሀ/ማሪያም