በዘመናችን በአስመሳዮች እና ሆድ አደሮች የአገር አንድነት እና በሄራዊ ደህንነት ፣ ህዝባዊ ስጋት ፣ የህዝቦች በአገራቸዉ የመኖር ተፈጥሯዊ መብት ማጣት፣ ኢትዮጵያ የባህር በር እንድታጣ ሆኗል፣ ዜጎች በማንነታቸዉ እና ኢትዮጵያዊነት ላይ ከፍተኛ ክህደት ፣ጥቃት ፣ ሞት እና ፍጂት ለሶስት አስርተ ዓመታት ተከናዉኗል፡፡
ሆኖም ይህ ሁላ ሲሆን ለዕዉነት እና ለዕምነት ሲል ድምፁን ያላሰማ ዛሬ ላይ ለዜጎች ምድራዊ ሲዖል በሆነች አገረ ኢትዮጵያ ዉስጥ በዜጎች ጉስቁልና መከራ ንዋይ እና ብልፅግና የሚመኙ አድር ባይ በሽምግልና ስም በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ላይ ብዙ ብዙ ክፋት፣ ክህደት እና ጥቃት ተፈፅሟል፡፡
ነገር ግን ዛሬም በኢትዮጵያዉያን እና በኢትዮጵያ ላይ የሚጠነሰሱ እና የሚነሱ የመብት እና የነፃነት ትግል ለማደናቀፍ በተለያየ ጊዜ በአገር ወዳዶች ኢትዮጵያዉያን ላይ ከፍተኛ ሴራ እና መከራ እንዲደርስባቸዉ በማድረግ በህዝባዊ ትግል ዕንቅስቃሴ ላይ መግታት የተጠመዱ ሸምጋይ መሳይ ሸንጋዮች ናቸዉ ፡፡
ሸምጋዮች ሆይ ዋሽቶ ማስታረቅ ቀርቶ ዋሽቶ ማጋደል እና በዉሸት ጠግቦ ማደር ሲዉል ሲያድር መጉደሉ አይቀርም እና በግፈኞች ለርኃብ፤ ለሞት እና ለድህነት የተጋለጠዉን ህዝብ ከምትጎዱ ሀሰት ከመናገር እና ከመመስከር መቆጠብ ለሁሉም እና ለአገር አይበጂም ፡፡
በአገር እና በሰፊዉ ህዝብ ላይ ለዓመታት በደረሰዉ መከራ እና ሰባዊ ጥፋቶች ያልነበሩ እና አንዲት ቅንጣት ዕዉነት ያልተናገሩ እና ያልመሰከሩ ዛሬ ላይ በተለያየ መመሳሰል የቀበሮ ባህታዉያን ሸምጋይ መሰሎች ሸንጋዮች ከሸንጋይነት ማንነት ሊለይ አይችልም እና ሸንጋዮች ሆይ ጥቁር ነጭ አይሆንም እና ከክፉ ድርጊታችሁ ትታቀቡ ዘንድ በዕምነታችሁ ትጠየቃላችሁ ፡፡
ታላቁ መፅሀፍ ቅዱስ “አስታራቂዎች ብፁአን ናቸዉ ፤ክርስቶስን ይመስላሉና ” እንዲል ሽምግልና ክርስቶስን መሆን እንጂ በሽምግልና ስም አገርን እና ህዝብ አለመረዳት እና አለመርዳት መሸንገል ብቻ ሳይሆን በደል እና መደለል ነዉ ፡፡
“ሠዉ ሆይ የኋላ ታሪክህን መርምር ፤ዕወቅ ፤ የተናገርከዉነውን አትርሳ ፤ ያቀቆሰለህ ሳይጨርስህ አይቀርም እና አትመን ፡፡”
“አጥብቀህ ካልያዝከዉ የአባትህን ጋሻ፤
ምን አንበሳ ብትሆን ይነክስኃል ዉሻ፡፡”
“አንድነት ኃይል ነዉ ፡፡”
አለን !