የኢትዮጵያ አንድነት እና የሕዝቦች ሉዓላዊነት ከፈተና አልፎ ኢህአዴግ መጋኛ ከሆነባቸዉ ግንቦት ሀያ ቀን ሽ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት ጀምሮ አስከዛሬ ተደርሷል ፡፡
ዛሬም ብአዴን ላለፉት ሶስት አስርተ ዓመታት የሚያዜመዉ የሕዝብ መብት እና የአገር አንድነት ከመከራ ወደ መከራ በተሸጋገረ ቁጥር አለን ለማለት የህዝብን ቁስል እና በደል ችላ በማለት ሲነፍስበት እኔ ላሻግር ሲል ግማሽ ምዕተ ዓመታት አለፉ ፡፡
በለፈለፉ ….አንዲሉ አበዉ ብአዴን ኢትዮጵያ የግዛት አንድነቷን የሚጎዳ አደረጃጀት ሲመሰረት ፣ ዓማራ እንደ ህዝብ በጠላትነት ተፈርጆ ሲሳደድ እና በመላዉ አገሪቷ በሶስተኛ ደረጃ ዜግነት ሲቆጠር ፣ በማንቱ የፖለቲካ ዉክልና እና የህግ ከለላ ሲነፈገዉ በዚህም በማንት ፍጂት እና ዕልቂት ሲካሄድበት ከዚህ በላይ በአማራ ህዝብም ሆነ ከኢትዮጵያ አንድነት አደጋ መግባት ምን ይኖራል ብሎ ነዉ ብአዴን በየጊዜዉ ከዕንቅልፉ ሲነሳ ከፈተናዎች ለማሻገር ብሎ ማደናቆር ፡፡
አስኪ ክልሎች ሲደራጁ በስያሜም ይሁን በይዘት እንደ ዓማራ እና ኢትዮጵያ የተጎዳ ወይም ቤተ ሙከራ የሆነዉ የትኛዉ ክልል ነዉ ፡፡
ዓማራ ክልል ዓማራ ከተባለ የብሄር ብሄረሰብ የአዉራጃ መስተዳደር መኖር ለዓማራ ክልል እና ህዝብ ሲሆን እና በሌለች የአገሪቷ ክፍል ግን መንገድ ላይ ዕግር ለመታ ዕንቅፋት ለማንሳት የቦታዉ ብሄረሰብ መሆን በሚጠየቅባት አገር ብሄራዊ አንድነት እና አብሮነት የሚፀናዉ በዕኩልነት አስከሆነ በመላ አገሪቷ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ሆኑ ዓማርያን የፖለቲካ ዉክልና እና ራሳቸዉን በራሳቸዉ የማስተዳደር ህጋዊ ዋስትና ሲነፈጋቸዉ እና የዘመናት አድሎ እና መድሎ ሲደርስባቸዉ እያየ ያለፈ አሻጋሪ ዛሬ እንዴት ይሆን ኢትዮጵያን የሚሻግር፡፡
ኢትዮጵያ እንደ አገር ኢትዮጵያዉን እንደ ህዝብ በተለይም ዓማርያን በፀረ-ኢትዮጵያዉን ጠላቶች በተጠነሰሰ የጥላቻ ፖለቲካ በአገራቸዉ የመኖር እና ሰርቶ የማግኘት ተፈጥሯዊ መብተቻዉ በማን አለብኝነት ተገፎ ያለከልካይ አሁን በሚገኙበት ቀዉስ ዉስጥ መድረሳቸዉ እየታወቀ ይህ ፈተናዎችን ወደ ድል ከማለት በህዝብ እና በአገር ላይ እየደረሰ ያለዉን የጨለማዉ ዘመን መከራ እና ግፍ ላንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ባለበት ለማስቀረት የዚህ ሁሉ አስኳል የሆነዉን ኢህአዴግ ማክሰም እና አገሪቷን ወደ ቀደመ አንድነቷ እና ታላቅነቷ ፤ ኅዝቡንዳ ተሟላ ሉዓላዊ ነጻነት እና ክብር ሊያደርስ ወደ ሚችል ብሄራዉ እና ህዝባዉ መንግስት ቢባል በጥቂቱም ቢሆን በሽግግር ስም ከማደነጋገር ወደ ወደ ዕዉነተኛ ቁም ነገር ይለወጥ ነበር ፡፡
የኢትዮጵያም ሆነ የዓማራ ህዝብ ችግር የመሰሪ እና የአደንቋሪ ዕንቅፋት መኖር እንጂ ከመሻገር አልፎ በራሱ መብረር የሚችል ህዝብ መሆኑን መረዳት ከመደነቋቆር ወደ መተባበር ያደርሳል ፡፡
ዝንተ ዓለም በአገር እና ህዝብ ህመም የፖለቲካ ትኩሳት ለማስታመም ሽግግር እና ተሀድሶ መልሶ መላልሶ የሞኝ ለቅሶ ለህዝብ እና ላገር ችግር አይሆንም ፡፡
Allen Yet men!
Unity is strength!
https://youtu.be/f88ze8pGfO0