February 17, 2023
9 mins read

ጉዳዩ፤ ኢትዮጵያ እንደ አገር የመቀጠል ወይንም ያለመቀጠል ነው!

አንዱ ዓለም ተፈራ
ሐሙስ፣ የካቲት ፱ ቀን ፪ ፻  ዓ. ም.

 

ETHIOPIAN INTELበቅድሚያ በአገራችን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የተፈጠረው የውስጥ ችግር ተፈትቶ ዕርቅ መደረጉና ውጥረቱ መርገቡ ደስ የሚያሰኝ ነው። ይኼ የጉዳዩ መጨረሻ ነው ወይ? የሚለውን ውለን አድረን የምናየው ይሆናል። ለጊዜው ግን ቢያንስ በቤተክርስትያኗ ውስጥ ሰላም ሰፍኗል። ይህ በፖለቲካው ዙሪያ ባሉት መካከል ምን ያህል ተቀባይነት ይኖረዋል? ሌላው ጥያቄ ነው። ይህ በዚህ እንዳለ፤ የአገራችንና የቤተክርስትያኗ ትልቁ ችግር ይህ የቤተክርስትያኗ የውስጥ አሰራር ብቻ እንዳልነበረ መረዳት አለብን። አሁን በመንግሥት ሥልጣን ላይ ያለው ቡድን ኃላፊነቱን ከተረከበ በኋላ፤ አንድ ጊዜ አንድ ጉዳይ፣ ሌላ ጊዜ ሌላ ጉዳይ እየተነሳ፤ ብዙ ኢትዮጵያዊያን ሕይወታቸው አልፏል። ለምን? ነገ የሚከተለውስ ጉዳይ ምን ይሆን? በዚህ ጽሑፍ ያሰፈርኩት፤ መንግሥት የሠራዉን ወይንም ያልሠራውን መመርመርና ማውገዝ ሳይሆን፤ ጠቅለል ባለ መልኩ ለሌሎቻችን መልዕክት ማስተላለፍ ነው።

እስካሁን የተከሰቱት ጉዳዮች ምንድኖች ናቸው? ለምን ተነሱ? እኔ የምጽፋቸውን ለሚከታተሉ መልዕክቴን መገመት አይከብዳቸውም። ከኔ ክልል ውጣ! ወደ አዲስ አበባ አትገባም! የኔ ክልል ደንበር ትክክል አልተሰመረም! እኛም የራሳችን ክልል ይኑረን! ኡእራሳችን የሃይማኖት ክፍል ይኑረን! በቋንቋችን ይሄ ይደረግልን! ያ ይደረግልን! የኛ የበላይነት ጥግ የለውም! የሥራ ፈላጊው ቁጥር እየበዛ ሥራ ግን አልተፈጠረም! የተነሳንበትን ጉዳይ ሕገ-መንግሥቱ ይፈቅድልናል! የመሳሰሉት ናቸው። እኒህን ሁሉን የሚያያይዛቸው ምንድን ነው? ይህ ነው መታየት ያለበት። እንዲያው እያንዳንዱን እየለዩ ቢያባጥሉት፤ መልሶ መልሶ! ይሆናል። ይህ ሁሉ ባንድ ላይ ሲሰበሰብ፤ የአገርን እንደ አገር መቀጠል ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ጉዳይ ነው። እናም የአገርን ጉዳይ መመልከቱ ዋና የአሁን ጥያቄ ነው። አንዳንዶች በአንዱ ጉዳይ ተጠምጥመው መፍትሔ ለማግኘት ይሯሯጣሉ። ለማንኛውም ጉዳይ መፍትሔ መሻቱና ማግኘቱ አስፈላጊ ነው። ነገር ግን፤ ከላይ የደፈረሰን ፈሳሽ ከታች እናጥራው ቢሉ፤ ለድካም ከመዳረግ ሌላ ትርፉ ባዶ ነው። እናም ከመንግሥት ሥልጣን ውጪ ያለን፣ በአገራችን ያለውን የፖለቲካ ሀቅ የተረዳን፣ አደጋውን ተረድተን የመፍትሔው አካል መሆን የምንፈልግ፣ ኢትዮጵያ ነገ ቀጥላ ለወደፊቶቻን እንድናተርፋት ከፈለግን፤ መምከር አለብን። በኢትዮጵያ ያለው አንገብጋቢ ጥያቄ፤ የአንድ ጎሳ፣ የአንድ ሃይማኖት፣ የአንድ አካባቢ፣ የአንድ ተበዳይ፣ የአዲስ አበባ፣ የወልቃይት፣ የራያ፣ የጉራጌ፣ የኢትዮጵያ ሶማሌ፣ የጉጂ፣ የሲዳማ፣ የተነጣጠለ ጉዳይ አይደለም። የአገር እንደ አገር መቀጠል ወይንም አለመቀጠል ነው።

ይሄ ግራ የሚያጋባ ነው። ኢትዮጵያ አለች! ለወደፊቱም ትኖራለች! በሚል ግትር የተፈጥሮን ሕግ በውል የማይመለከት ጭፍን እምነት የተሰለፉ አሉ። ይሄን በቀላሉ የታሪክ መዝገብን በማገላበጥ መረዳት ይቻላል። ከኢትዮያ የገዘፉ ታላላቅ አገሮችና መንግሥታት ፈርሰው ዛሬ የሉም። ገናናዎቹ የግሪክ፣ የሮማ፣ የሞንጎሊያ፣ ፀሐይ አይጠልቅበትም የተባለው የእንግሊዞች አገር(ከደሴቷ በስተቀር)ና መንግሥታት፤ በታሪክ መዝገብ ብቻ ነው ያሉት። ትናንት ዩጎዝላቪያ ነበረች። ዛሬ ስሟን ከመጽሐፍ በማገላበጥ እንጅ፤ በዓለም ካርታ ላይ አያገኙትም። ኢትዮጵያ የተለየች አገር አይደለችም! እኛ ካልጠበቅናት ሌላ ጠበቃ የላትም። በሃይማኖት ለሚተማመኑት፤ በዓለም ዙሪያ ያሉ አገራት በሙሉ የፈጣሪ አገራት ናቸው። ያዳላል ካላልን በስተቀር ሁሉም አገራት አንድ ናቸው። ኢትዮጵያዊያንንም ከሌሎች አብልጦ ወይንም አሳንሶ አይመለከትም። እናም ኢትዮጵያ ከሌሎች አገር የተለየ ምንም ነገር የላትም። ያሏት እኛ ብቻ ነን። እኔ አንድ እግሬን ወደ መቃብር በመስደድ ላይ ያለሁ ኢትዮጵያዊ ነኝ። ኢትዮጵያን ግን በታትኜ ለማለፍ ዝግጁ አይደለሁም። ሌሎች ሲያፈርሷት ደግሞ፤ እነሱ ናቸው ብዬ እጄን በሌሎች ላይ ልጠቁም አልፈልግም። የራሴ ኃላፊነት አለብኝ። የኢትዮጵያዊነትና የትውልድ ኃላፊነት አለብኝ። ይሄን ከመወጣት አኳያ፤ ኃላፊነቱ ከሚሰማቸው ጋር በኢትዮጵያ እንድ አገር መቀጠል ለመነጋገር ዝግጁ ነኝ።

ከላይ የዘረዘርኳቸውና ሁላችን የምናውቃቸው ጉዳዮች መሠረታቸው፤ ወንበሩን ለሌሎች እንዲለቅ ተገዶ የተባረረው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ጥሎት የሄደው ሕገ-መንግሥትና፤ በቦታው አስቀምጦ እንዲወርስ ያደረገው መንግሥታዊ መዋቅር ነው። ይህ አገራችንን ወደ መፈራረስ እየወሰዳት ነው። በምን መንገድ ይሄ እንዳይሆን መከላከል ይቻላል? ምናልባት በሥልጣን ላይ ያሉት፤ እኛ በትክክል እየመራናት ነው! ብለው ሊምኑ ይችላሉ። አልፈርድባቸውም፤ በሚያውቁት የሚያውቁትን እያደረጉ ነው። ጥያቄው፤ ከነሱ ውጪ ያለነው፤ ያለውን ተጨባጭ ሀቅ ተረድተን፤ ኃላፊነታችንን እንወጣለን ወይ? ነው። የፖለቲካ ፓርቲ፣ የዝመናና ሥልጠና ጉዳይ፣ የልማትና የማደግ ጉዳይ፤ ቦታ ቦታ አለው። አሁን አገር የማዳን ጉዳይ ሁሉን ጨፍልቆ ስለመጣ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ መምከሩ ግድ ነው እላለሁ። በተለያዩ ድርጅቶች የተሰባሰባችሁ ሁሉ፤ ይሄ ዋና ጉዳይ ነው ብላችሁ ካመናችሁ፤ ይሄ ጥሪ ከየትም ይምጣ ከየት፤ የራሳችሁ ጥሪ ነው። እናም እናንተም ጥሩት ሌላው፤ መሰባሰቡ አጣዳፊ ነው። ይህ ለነባር ታጋዮች ወይንም ለነገ ተረካቢዎች የተደረገ ጥሪ አይደለም። ለማንኛውም ኢትዮጵያዊና ኢትዮጵያን ለማዳን ለሚሻ ሁሉ ነው። ይህን ማድረግ፤ የገንዘብም ሆነ የጉልበት አቅም አይጠይቅምና እኔ እገፋበታለሁ። አለን የምትሉ ጥሩኝ፤ እገኛለሁ። ነገ ለመቆርቆር ጊዜ አይኖረንም። ዛሬ ኢትዮጵያ በንጥልጥልም ብትሆን ባለችበት ደረጃ እንድረስላት።

[email protected]

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop