December 6, 2022
26 mins read

እንሆ፣ ዕቅድ “ሐ“ (Plan C) ተጀምሯ! ትንቢት ከነገር ይቀድማል! – ሲና ዘ ሙሴ 

“ የእግዚአብሔርም ክብር በሲና ተራራ ላይ ተቀመጠ፥ ደመናውም ስድስት ቀን ሸፈነው፤  በሰባተኛውም ቀን ከደመናው ውስጥ ሙሴን ጠራው። ”

— ዘጸአት 24፥16

ይኽ ፀሐፊ አንድ ጥያቄ የኢትዮጵያ ህዝብንና መንግሥትን ይጠይቃል ? ኢትዮጵያዊያን ሠላም አለ የምንለው እኛ መኖርያ ቤት ውሥጥ ሽፍቶች ፣ ወንበዴዎች ፣ ቀማኞች ፣ ዘራፊዎች ፣ አራጅ ና ገዳዮች ገብተው ቤተሰባችንን በጭካኔ ሥላልገደሉ እና ሥላልዘረፉ ነውን ? መንግሥትሥ “ ሠላም አለ ። “ የሚለን ፣  የተደራጀ ፣ ለሁሉም ግዳጅ ዝግጁ የሆነ የመከላከያ እና የፊደራል ኃይል ሥላለኝ ቤተመንግሥቴን እና ቤተሰቤን እሥከዛሬ ማንም ጫፋቸውን አልነካም ።   ”  በማለት አሳቤ ነውን ? …

አገር በሽብር ኃይሎች እየተናጠች ፤ እንዴት ሠላም  አለኝሥ ይባላል ?  በመንግሥት ውሥጥ ሌላ መንግሥት የመሠረቱ ህቡ ሃይሎች እያሉ እንዴትሥ በዜጎች አእምሮ ውሥጥ  ሠላም ሊኖር ይችላል ? በሙሥና የተዘፈቀ ፣ በምቾትና በድሎት ባህር የሚዋኝ የደህንነት ከፍተኛ ባለሥልጣን እያለ እንዴት አገር ሠላም ትሆናለች ?  እነ ብር አምላኩ በየክልሉ ሥልጣን ይዘው ፤ እግዚአብሔር ተረስቶ እንዴት አገር ሠላም  ትጎናፀፋለች ?

ሥለ እግዜር ሲነሳ ፣ በቅርቡ ፣ አንድ የ19 ዓመት እንቦቃቅላ  ልጃቸውን በዚህ ትርጉመ ቢሥ እምሮ ቢሥ  የወሮበሎች ሥብሥብ   ( ቋንቋን እንደመጨቆኛ መሣሪያ  በማየትሰውን በቋንቋውና በመጠሪያ ሥሙ በሚፈርጅ ከዘመናዊ ሥልጣኔ እና ከዓለም ነባራዊ የኑሮ ዘይቤ እጅግ እርቆ በ15 ኛው ክ/ዘ አሥተሣሠብ እየኖረ ባለ አረመኔ ቡድን ። ያጡ እናትን ላፅናናቸው ቤታቸው ጎራ ብዬ እንዲህ አሉኝ “…እግዚአብሔር  መፍትሄ ያምጣልን ? ‘ እርሱ ያብርደው ! ‘ ትለኛለህ ልጄ !  እርሱም አቅቶታል መሠለኝ … ?  ለዚች አገር ያለመከፋፈል ከእኔ ቤት እንኳን አምሥት ሥጋዎቼን ገብሬለሁ ? እና ምን ተገኘ ? አራቱ በሰሜን ተሰው ። ለዚች ዛሬም ሊከፋፍሎት ከሚጠሩ ሤጣኖች ጋር ተናንቀው ። ዛሬ ደግሞ እትብትህ በተቀበረበት  በቀዬህ ፣ በታዛህ ፣ ‘ እግዜር በፈጠረልህ መሬት  የአግዜሩን መሬት ቀምተውት የእኔ ብቻ ነው ። ‘ በማለት በቋንቋ  ተቧድነው በጅብ መንገድ በሚጎዙ  ኦነግ ሸኔ በተባለ ቅፅል ሥም በሚቀሳቀሱ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች እዚሁ መሐል አገር ልጄን ተነጠቅሁ ። … ጎጆ ቀልሰህ ፣ አፈር ገፍተህ እየኖርክ … ጠፍጥፎ ያልሰራትን መሬት … የኔነው እያለ… ይሄ  ገንዘብ አይኑንን ያወረው ህሊና ቢሥ ቅጥረኛ ንብረትህን አውድሞ አንተን በየቀኑ ሲያርድህ … እንዴት ፈጣሪ ሠላም ያመጣል  ብለህ ታሥባለህ ? ” በማለት በምሬት ጠየቁኝ ።

እኔም ፤ ”  እውነት ብለዋል ። ሰው ከአራት ኪሎ ብዙም ሳይርቅ እየታረደ ነው ። ዕውቁ ጋዜጠኛ  ታምራት ነገራ ፣ ብዙም ባራቀ ወቅት በተራራ ሚዲያ በዩቲየቡ  እንደተነበየው ፤ ‘ ይኽ ፅንፈኛ … ድርጊት በአጭር ካልተቀጨ ጠቅላይ ሚኒሥትራችንን ዶክተር  አብይ አህመድን የሚበላ ነው ። ‘ ምናልባትም  ሰውየው ፣ ‘ ሤጣናቱ ምንም አያመጡም ! ‘ ብለው እጃቸውን አጣጥፈው ፣ በትወራ  ብቻ ‘ አንድነት ! አንድነት ! ‘ እያሉ ከተሞኙ ፣ እርሱ እንዳለው   ‘ አሥከሬናቸው በአራት ኪሎ ቤተመንግሥት ደጃፍ  መጎተቱ አይቀርም ‘  ። ” አልኳቸው ።

ዛሬ ና  አሁን የምናሥተውለው የሤጣን ተግባር ይኽንኑ ቀፋፊ ትንቢት  መልሰን እንድንል  ያሥገድደናል ። ይኽንን ግምት ” የሤጣን ጆሮ አይሥማው ። ” ማለት አይቻልም ። ሤጣን እጅግ  ተራብቶ ጆሮ ብዙ ሆኗልና !  ዛሬ እና አሁን ፣ በኦሮሚያ ባሉ የፊደራል ዩኒቨርስቲዎች እንኳን ጥቂት የማይባል “ የሤጣን ጆሮ አለ ። “  ( አሥደናቂው ነገር የፊደራል ዩኒቨርስቲዎች ዛሬም የሤራ ፖለቲካ መዘውር እና በኦህዲዳዊ ካድሬዎች ፤ በብአዴን ፤ በህወሓት ወዘተ ካድሬዎች መመራታቸው ነው ። ሜሪት አያሠራም ። ከኢህአዴግ እሥከ ግልብጡ ብልፅግና ያውና አንድ ብቻ ሣይሆን የባሰ ካድሬያዊ አመራር  ቀበሌ ድረስ ተዘርግቶ ዛሬም ድረስ እንደ ጭከቃ ሹም ህዝብን ያሰቃያል  ። ህዝብን ለፖለቲካ ወጥመድ የሚያዘጋጅና የምርጫ ማጭበርበሪያ ሥውር መድረክ የሆነው ፤  የካድሬ መናሀሪያ ፈርሶ በትክክለኛው የማዘጋጃ አገልግሎት ካልተተካ ሠላም  በአገር ይመጣል ብሎ የሚያሥብ ጅላንፎ ብቻ ነው ።  ወዳጄ እንደ ኮሮና የሚዛመተው ቫይረሥ መፈልፈያ ቀበሌ  እንደሆነ ህዝብ ያውቃል ። የቫይረሱን በሽታ የሚያሥተላልፈውም ሆድ  አደሩና በዘረፋ የተካነው ከኢህአዴግ ወደብልፅግና የተቀየረው  ካድሬ ነው ። አካፋን ቀለም ብትቀባው ያምራል እንጂ ግብሩን አይቀይርም ። አካፋ አካፋ ነው ።  ካድሬ ሆይ ብጠላኝም ጥለኝ ፣ ‘ መልከ ጥፉን በሥም መደገፍ አይቻልም ።’  እልሃለሁ ። ደግሞም ግማሽ ሉጩ ግማሽ ጎፈሬ መሆን ለተመልካቹ ያሥጠላል ። ያደናግርማል ። በቀኝ በኩልና በግራ በኩል ሲታይ ። ቀኙ ተላጭቷል ግራው ጎፈሬ ነው ። ለእሥታይል ከሆነ ብቻ ይኽ አይነቱ “  በፍላሎታሞች “ የሚወደድ ይሆናል  ። በፍላሎት ዓለም ለሚዎኙ “ አይፈራም ! ጋሜ አይፈራሞች ! “  ይኽ ኖርማል ነው ። ህይወትን በ360 ዲግሪ ለምንመለከት ግን ይህ እብደት ነው  ። ‘ እሥቲ ከባላቶሊ ቁርጥ እና ከሜሲ ቁርጥ የቱ ያምራል ? ‘  ፍላሎታሞቹ ይመልሱ  ። …

ዛሬ ፣ ዛሬ የሤጣን ጆሮ የበረከተበት ፣ ቅዱሣን እና መልዓክት የፈጣሪን ይቅርታ ለማግኘት የሚማልዱበት ወቅት ላይ ደርሰናል ። ሙሴ ያጋጠመው ፈተና በኢትዮጵያዊያን ላይ ተደግሟል ። ኢ _ አማኒያን ሰዎችን ያለርህራሄ እያረዱ ነው ። በሴጣን ፈረሥ እየጋለቡ ። ኦሮሚያ እየተባለች በቋንቋ ነገሥታት በምትመራ ክልል በደም እጃቸውን እየታጠቡ ነው ። ትላንት  እንደ ፊውዳል በትውልድህ ዘርህ ተቆጥሮ ለሹመት እና ለሥልጣን እንደምትበቃ ሁሉ ፣ ዛሬም በኦህዴድነት አሥመሣይ ካድሬነትህ እና በቋንቋህ እንዲሁም ምሥጢር ጠባቂ ሌባነትህ እየተሞላቀቅህ በሰው ደም እየሠከርክ ነው ።  በአማራም ፣ በትግሬም ፣ በአጠቃላይ በሁሉም ክልሎችም በብዙም ሆነ በጥቂት ይኸው እውነት አለ ።  በተመሣሣይ መልከ ነው ፣ ለሹመትና ለሽልማት የምትበቃው ። ህሊና እና የራሥህ እውቀትና እግር ካለህ በጥበብ የላቅህ ፣ ሰው መሆን ብቻ የምትፈልግ ኦሮሞ ፣ ትግሬ ፣ አማራ ፣ ሱማሌ ፣ ሲዳማ ፣ ወላይታ ወዘተ ። ግን ማንም እዚህ ጠባብ እና ህሊና ቢሥ ቡድን ውሥጥ እንድትገባ አይፈቅድልህም   ።

እግዚአብሔር በፈጠራት ምድር ፣ በተለይም በኢትዮጵያ ህግ አሥከባሪ ፀረ _ ዳያቢሎሥ መንግሥት በወጉ ባለመደራጀቱ ነው ህሊና ላለው ለሥጋው ሳይሆን ለነፍሱ ላደረ ጠቢብ የከፍተኛ አመራርም ሆነ በተዋረድ ያሉ የህዝብ ማሥተዳደር ፣ የሥልጣን ክብር የተነፈገው  ። እግዛብሔርን ሥለሚያከብር።  እግዚአብሔር ግን አለ ። ሤጣኖቹ ግን በድፍን ኢትዮጵያ ሰውነትን ቀብረው ቋንቋ ሆነው ፀረ ሰው በመሆን  የሥልጣን ወንበር ላይ  ፊጥ ብለዋል ። በተለይም በኦሮሚያ ከግብፅ በመጡ ፣ በግብፅ በሠለጠኑ ፣ በግብፅ በሚከፈሉ ፣  በነጃዋር በህቡ በሚመሩ እና በወያኔ ፕላን ሲ ( Plan C ) በተካተቱ  እጅግ ምሥጢራዊ በሆነ መንገድ ” ኔት ወርክድ ” በሆኑ ፤ እየተፈፀመ ያለው አገር የማፍረስ እንቅስቃሴ ሀገር ወዳዶች ቸል የማይሉት ተግባር ነው ።

በዚህ በረቀቀ መረባቸው እየፈፀሙት ያለውን ፀረ ሠላም እንቅሥቃሴ የኢትዮጵያ ልጆች ፣ በተለይም የአገር መከላከያ ሠራዊት ከቶም አይረሳውም ። ሣይበቀላቸውም በዝምታ አያልፍም ። የኢትዮጵያ ምሣሌ በመሆኑ ።  መንግሥት ህዝብ  ሠላም እንዳያገኝ ባለማሠለሥ እየጣሩ ባሉት ፤ በገንዘባቸው ኃይል ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ( የመከላከያን ፣ የፓሊሥን እና የደህንነትንም ይጨምራል ። ) በደካማ ጎናቸው ( በተደበቀ ሱሳቸው  ፣ ፀባይ እና ዓመላቸው ) በመግባት  የእነሱ ሎሌ በማድረግ ፣  አገርን በማያባራ ትርምስ ውሥጥ ለማሥገባት ፣ አገር ወዳድ መከላከያውን ፣ ፌደራል ፖሊሥን ለከንቱ መሥዋትነት የሚዳረጉትን በምሥጢራዊ ዕቅድ ማሶገድ ካልቻለ ፣ አገራችንን ጠላቶቻችን እና የውጪ ጅቦች  ተቀራምተው እንደሚበሏት ዛሬ ይበልጥ ግልፅ እየሆነ መጥቷል   ። እንዴት ቢሉ የአገር መከላከያ ሠራዊቱ ና የፊደራል ፖሊሱ እንዲሁም ሙያቸውን የሚያከብሩ የክልል ፖሊሶች በከንቱ ህይወታቸውን አሰየተነጠቁ ናቸውና ! ያልተገባ መሥዋትነት እነዚህ ውድ እና ብርቅ  አገር ወደድ ኢትዮጵያዊያን መክፈላቸው ፣ ነገ የሚያመጣው ጦሥ ደግሞ እጅግ መጥፎ ሊሆን እንደሚችልም መንግሥት ማወቅ አለበት  ። በበኩሌ ክፉው እና አገር አጥፊው ነገር ከመከሰቱ በፊት ፣  ጠቅላይ ሚኒሥቴር አብይ  ኮሶን ለኢትዮጵያ ሲሉ በተገቢው አቅጣጫ በማሾር በህዝብ ቅቡልነት ያለው ማራኪ ግብ ቢያሥቆጥሩ እመርጣለሁ ። ይኽ እድል ለቀድሞው ጠ/ሚ  መለሥ ዜናዊ  በአንድ ወቅት ተሠጥቷቸው ነበር ። ሆኖም አልተጠቀሙበትም ። …

ለጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ ባልተሰወረ መልኩ ፣   በብሔር ብሔረሰብ ሥም ፣ እየተጠቀመ ያለው ህዝብ አይደለም ። የትም ክልል ደሃ ተከባብሮ እየኖረ ነው ። ከ85 % በላይ ህዝብ ደሃ ነው ። የቋንቋዊ ዘረፋም ተጠቃሚ አይደለም ። እድርና ባልትነው አንድ ነው ። ጉልቱ እና መኮመሪያ ጣሳው አንድ ነው ። እርፍ ና ደጋኑ አንድ እና ያው ነው ። ምጣዱ ፣ ድሥቱ ፣ ጀበናው አንድ ነው ። የሚበላው እንጀራ፣ ቂጣው ፣ ቆሎና ንፍሮው ሣይቀር አንድ ነው ። ያም ይኼም በጪሥ የሚጨናበሥ ነው ። ያም ይኼም በብድር መብራት እና በቤት ኪራይ መከራውን እየበላ ያለ ምሥኪን ነው ።  … የተቀረው ጥቂቱ 5% ደግሞ   ለቋንቋ መሥፍንቶች እና መኮንንቶች በማደግደግ እና ጭራ በመቁላት  ሀብት ና ንብረት  ያፈራ ነው ። …

ይኽ የሚያሣብቀው መንግሥት ማወቅራዊ ህመም እንዳለው ነው ። በሽታው እጅግ ጥልቅ እና ጋንግሪን የፈጠረ መሆኑ በግልፅ እየታየ ነው ። እናም አካሉን ጨርሶ ወደ ጭንቅላቱ ጋንግሪኑ ከመዝለቁ በፊት ፣ የተበላሹ እግሮቹን ቆርጦ ሊጥላቸው ግድ ይሆንበታል ።  ይኽ ቱሁት ምክሬ ነው ። ጋንግሪኑ ግልፅ ፣ የማይቀለበሥ አደጋ እያሥከተለ ነው ።  የአገር አለኝታዎች እያሣጣ ያለ የሚያሥቆጭ ብቻ ሣይሆን እጅግ የሚያናድድ አደጋ እየጋረጠ ነው። በየቀኑ አሰያሥሞተ ነው ። ራሳቸውን መከላከል በማይችሉበት ሁኔታ በጠራራ ፀሀይ ለግዳጅ የወጡ አልኝታዎቻችንን በከንተሐ እያጣን ነው ።አዲስ አበባ ባንዲራ አትስቀሉ በሚሉ በግብፅ ወሮበሎች ተከባለች ።  ህዝብ ፣ ገንዘብ በሚከፈላቸው   በታጠቁ ሺፍቶች  በደፈጣ በየቀኑ  ይረሸናል ። ” ወታደራዊ ኦፕሬሽን እና ግዳጅ በጠራራ ፀሐይ ”  ውጡ እየተባለ የአይናችንን ብሌኖች በፈሪ በትር እናጣለን  ። በሞታቸው እንበግናለን ።  እርር ጭሥሥ እንላለን ። ህሊና አለንና ። የሞቱት እንደ እየሱስ ነውና !! ….

ከዚህ ተነስቼ አገር ወዳዱ የመንግሥት ከፍተኛ አመራር ፣  በኦሮሚያ ያለውን ህገወጥ አደረጃጀት ማፍረስ አለበት ። እላለሁ ። ሳይዘገይ ፣ ሚሊሻ የተባለውን ፣ ለመዝረፍ ከየቀበሌው የተመለመለውን በከተመሠም ሆነ በገጠር ያለውን ፣  ማፍረስ አለበት ። ሃምሳ ፐርሰንቱ  ለዘረፋ የተሰማራ ነውና ። ያለአንዳች አሉባልታ ሃምሳ ፐርሰንቱ  ጭለማን ተገን አድርጎ የሚዘርፍ ነው ። ይኽ ሐሰት  እንዳይደለ  የትኛውም የከባድ መኪና አሽከርካሪ ይነግራችኋል ። ከዚህ ይልቀሰ ወጣት የሆነውን የሚሊሻ ሃይል በጥንቃቄ መልምሎ “ የፈጥኖ ደራሽ “ ልዩ ኃይል በማቋቋም ፀረ ሽፍታ ኃይል በፊደራል ደረጃ ማቋቋም ይበጃል ። ይኽ ሃይል በሲቪልም በጋራ ተንቀሳቅሶ የሚሠራ ወይም ግዳጁን የሚፈፅም ሃይል ሆኖ ቢሠለጥንም መልካም ነው ። ካሥፈለገም ከልዩ ኩማንዶ ጋር በማቀናጀት በአጭር ጊዜ የተረጋጋ ሠላም በአገር ማምጣት ይቻላል ።

እንዲህ ዓይነቱን የሠለጠነ እና የነቃ ፣ በምሥጢርም የሚንቀሣቀሥ ልዩ የአገር ደህንነት ኃይል በመፍጠር   የዛሬውን  የፕላን C እንቅስቃሴ  ማሥቆም እንደሚቻል አምናለሁ ። የእሾህ መድሃኒቱ እሾህ ብቻ ነው  ። ነፍሰ ገዳይን ልትገድለው ይገባሃል ። ያለ አንዳች ምህረት ።  የመንግሥት ተመጣጣኝ ይሉሃል ይኼ ነው  ።

ዛሬ በከንቱ የሚሞላቀቅብህን አንተ ዘረኛ እና በዩልንታ የተሸበብክ ካልሆንክ በሥተቀር ቸል ልትለው አይገባም ። ቸልታ ካበዘህ የታምራት ነገራ ትንቢት ይፈፀማል ።  ኦሮሞ ካልሆንክ ብቻ ሣይሆን አንተ “ ሰው ነኝ ። “ የምትል ኦሮሞ ከሆንክ አንተ በረሮ ነህና ትታረዳለህ ። የሚልህ  የግብፅ ቅጥረኛ ከእሥር በለቀቅኸወሰ ሃይል በፕላኒ ቢ የሚመራ ኃይል ነበር ። ዛሬ ወደ ፕላን ሲ ተሸጋግሮልሃል ።…

ይኽ  ኃይልበገንዘብ እጅግ የፈረጠመ በመሆኑ አንተን ገንዘብ በመሥጠት እያነሆለለ ፣ በተቀዳሚ ሥራህ ላይ እንዳታተኩር በማዘናጋት ወደ እርድህ እየገፋህ እንደሆነም እወቅ ። በቤትህ ውሥጥ ያለውን ወታደራዊ ዲሢፕሊንም መርምር ። ሥላለው ገንዘብ መናገር ከጀመረ እጅግ አደገኛ ሁኔታ ውሥጥ እንደምትወድቅ እወቅ ።የአገር መረመ በመሆንህም ጦሥህ ለአገር ይተርፋል ።

ገንዘብ  መንጋ የመፍጠር ችሎታ እንዳለው ጋሼ ጃዋር ትላንት አሜሪካ ሆኖ አሣይቶሃል ። ዛሬ በፕላን ቢ ደግሞ የበለጠ እያሥመሠከረ ወደ ፕላን ሲ ተሸጋግሮልሃል ። የተማረውን ይኸው በመንግሥት ዩኒቨርስቲ በኔት ወርኩ አማካኝነት ገንዘቡን እየረጫ ፣ ሃሺሹን እያሥማገ ያሥጮኸዋል ።  ያልተማረውን ደግሞ ፣ በየጫካው አሠልጥኖ  እና በየከተማው እራሥህ  የሠለጠንከውን ሚኒሻ መልምሎ በሃሰት ፕሮፖጋንዳው ጀንጅኖ ረብጣ ብር ከመክፈል ባሻገር  ሥጋ እያበላ ና አረቄ እያጠጣ  ነፍሰ ገዳይ እንዲሆነ ጫካ ወስዶ ሰው ያሳርዱሃል ።  አሠልጣኞቹም አትዮጰያዊ ናቸው ብለህ በአውሮፕላን ይዘሃቸው የመጡ የግብፅ ሠላየች ናቸው ይባላል ። እነዚህ ፀረ ኢትዮጵያዊያን  ከወያኔም ጋር ነበሩ … ። ተመሬያለሁ ያልከውን በየዩኒቨርስቲ ያለኸውን የዓለምን ተፈጥሯዊ የዘመናት ጉዞ  ፤ ” ከአፈጣጠሮ ጀምሮ ያለውን የቅርቡን የ 5000 ዓመት ጉዞ   ” ያለመረዳትህ በእጅጉ ይገርማል ደ “ ለእዚህ ይመሥላል የታሪክ ትምህርት እንደ አንድ ጠቅላላ እውቀት በየዩኒቨርስቲው እንዳይሰጥ እና ይህ ፍላሎታም ወጣት ዓለምን  ከሣይንሥ እና ከሃይማኖት አንፃር   እንዳያውቃት የተደረገው ?

ዛሬ በመላው ኦሮሚያ የሚስተዋለው ይኸው ታሪክን ያለሠረዳት  ድንቁርና ነው ። የግብፅ እና የቅኝ ገዢዎቻችን ሴራን ከታሪክ እና ከተፈጥሮ አንፃር ያለመረዳት ያመጣውም ጦሥ ነው ። ሙቅ የሚያኝኩት ባለ ረብጣ ብሮች ያሰማሯቸውን ፣ ከመንግሥት በላይ መንግሥት የሆኑትን ፣ ገዳይ እና አሠቃይ  ጋንጊሥተሮች በመፍራት መንጋ ሆኖ መገኘት የከሰተው ችግር ነው ።  …  ትላንት  በነጀነራል ጃጋማ ኬሎ ዘመን ቅኝ ገዢዎች ይህንኑ  የመከፋፈል እና የጭካኔ ሤራ ፈፅመዋል ። በአምሥቱ ዓመት የአርበኞች ትግል ወቅት ይኸው ተንፀባርቋል ። ዛሬ ና አሁን በጠቅላይ ሚኒሥቴር  አብይ አህመድ መዋቅር ውሥጥ   ለፈጣሪ ያደሩ ሰዎች  ሤጣንን ተዋግተው ማሸነፍ እሥካልቻሉ ጊዜ ድረሥ ይኸው ግፍ ይቀጥላል ።

ሆኖም ” ሊነጋ ሢል ይጨልማል ። ” እንደሚባለው ፣ ይህ ሰቆቃ ከፈጣሪ ጆሮ አልደረሰም ማለት እንዳልሆነ ሁሉም ማወቅ አለበት ። ሠላም ያለውም የሚገኘውም በእግዚአብሔር ነው ።  ዛሬ እና አሁን መንግሥት ይኽንን ተገንዝቦ ” ይበቃል ! ” እንደሚል ተሥፋ አደርጋለሁ ። ትላንት “ ፕላን C ይቀጥላል ። ይኽንንም ታዩታላችሁ ።” ብዬ እንደነበርም አትዘንጉ ! ይኽንን ያልኩት ፈጣሪ በሰጠኝ አእምሮ ያለማባራት ፣ የሚከሰቱ ፀረ – ሰው ድርጊቶችን    ገጣጥሜ በማየት ነው ። ይኽንን እውነት ፣ አገር ወዳድ  የመንግሥት የደህንነት ተቋም ዓባላት እና መከላከያ ሠራዊቱ እንዲገነዘብልኝ እፈልጋለሁ ። የኢትዮጵያ ጠላቶች ነገ “ በፕላን ዲ “ ሊከሰቱ እንደሚችሉም ቀድሞ በመረዳት ከወዲሁ መዘጋጀት እንዳለበትም ለማሳሰብ ነው   ። ትላንት ቀድሞ ቢዘጋጅ ኖሮ በኦሮሚያ ዩኒቨርስቲዎች  ፕላን C  በተቀናጀ መልኩ አይከሰትም ነበር ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop