November 5, 2022
16 mins read

የፕሪቶሪያ ስምምነት:- ውጫሊያዊ ወይስ አልጄርሳዊ? (ከአሁንገና ዓለማየሁ)

ስምምነቱ ከሀገራዊ ዘላቂ ሰላም አኳያ  

በዚህ ጽሑፍ የፕሬቶሪያውን ውል አጠቃላይ መንፈስ፣ ዓላማና መዘዝ ለማሳያ አንድ አንቀጽ ላይ ብቻ እናተኩራለን።

የሥልጣን ውዝግቡ ማእከል የተደረገውና ጦርነቱ ሁለንተናዊ ጉዳት ያደረሰበት፣ የሰላም ስምምነት ተብዬውም ሌላ ዙር አደጋ የጋረጠበት የአማራ ሕዝብ በድርድሩ ሊወከል ይገባል ብለው የሚከራከሩ አካላት ትክክል መሆናቸውን ከሚያሳዩት የፕሬቶሪያ ውል አናቅጽ ውስጥ አንቀጽ 10 ቁጥር 4 ዋነኛው ነው።

ይህ አንቀጽ በወያኔ በጉልበት ተወስደው በጭቆና ሥር የኖሩትን የአማራ (የጎንደርና የወሎ) መሬቶች ተመልሰው ለወያኔ የሚተላለፉበትን አግባብ የሚያመቻች ነው። ታድያ ተማስሎሹ ነጻነትን አሳልፎ እንደሰጠውና ለጦርነት በር እንደከፈተው የውጫሌ ውል (አንቀጽ 17) ነው ወይስ ጦርነትን ድል አድርገው አልጄርስ ሄደው ድሉን በሽንፈት እንደለወጡበት የአልጄልርስ ስምምነት? የሚል ጥያቄ ይጭርብናል።

አወዛጋቢ አካባቢዎችን በተመለከተ የተጻፈው የፕሪቶሪያ ውል አንቀጽ እንዲህ ይለናል።

Article 10

  1. The Parties commit to resolving issues of contested areas in accordance with the Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia* ወያኔ ሆን ብሎ የፈጠረውን ችግር ለመፍታት ችግሩ እንዳይፈታ አድርጎ በቋጠረበት በራሱ በወያኔው ሕግ ይዳኝ ብሎ የመፍረድን ነገር፣ ተንኮል፣ ክፋት ወይስ ንቀት እንበለው? በቀላል  ቋንቋ  ዘራፊ ተዘራፊ በተዘረፈው  ንብረት ሲጣሉ ውዝግቡ በዘራፊው  ሕግ ይዳኛል እንደማለት ነው።

 

Where are the chimps
Kenyan President Uhuru Kenyatta (L), Redwan Hussein (2nd L), Representative of the Ethiopian government, African Union Horn of Africa envoy and former Nigerian president Olusegun Obasanjo (2nd R) and and Getachew Reda (R), Representative of the Tigray People’s Liberation Front (TPLF), look on after the signing of a peace agreement during a press conference regarding the African Union-led negotiations to resolve conflict in Ethiopia at the Department of International Relations and Cooperation (DIRCO) offices in Pretoria on November 2, 2022. (Photo by PHILL MAGAKOE / AFP)

አፍሪካ ጫፍ ሄደው አጽራር በጠያራ

ወልቃይት ጠገዴ ራያና ሁመራ፣

ነጻ እንደማይቆዩ ነገሩት ላማራ

የተዋለበትን ውሉን ሳያጣራ 

ሰላም መጣ ብሎ አያብዛ ዳንኪራ

ሰከን ብሎ ያስብ ሁሉም ኢትዮጵያዊ

ውጫሌ ነው ውሉ ደግሞ አልጄርሳዊ*

 

(*የውጫሌ ውል ከጦርነት በፊት የተዋዋሉት የባርነት ውል ሲሆን፣ የአልጄርስ ውል ደግሞ ከድል በኋላ የተዋዋሉት የሽንፈት ውል ነው) ውሉ በአማራ ሕዝብ ላይ ባርነትን፣ ጭቆናን፣ ከርስት መፈናቀልን የሚያስከትል ነው ስንል ለትግሬ ሕዝብ ይጠቅማል ማለት አይደለም። ከአማራ ርስት ቀምታችሁ ወደ ትግራይ ከልሉልን፣ እኛን እየወሰዳችሁ፣ እያስታጠቃችሁ በአማራው መሬት ላይ አስፍሩን ብሎ ሕወሃትን ጠይቆ አይደለምና የተስፋፊነቱ ክሥተት የተፈጸመው።

እርግጥ የጎሳ አፓርታይዱ ሥርዐት ፈርሶ አንቀጽ 39ኝም ተወግዶ ሌላ የፖለቲካ አከላለል ቢተገበር፤ ወልቃይትም ሆነ ራያ ወደ ሱዳን እና ኬንያ አይካለሉ እንጂ በሌላ በየትኛውም ኢትዮጵያዊ አስተዳደር ሥር ቢደረጉ ብርቱ ተቃውሞ አይነሳም። የጎሳ አፓርታይዱ ሥርዐት ግን አንድም ክልሎቹ ተገንጥለው ሀገር ለመሆን የሚንደረደሩ በመሆናቸው ከትግራይ ጋር መገንጠል የማይፈልጉትን እነዚህን አካባቢዎች በግድ ትግራይ ውስጥ ማካለሉ አግባብ ስለማይሆን፤ ሁለተኛም በማንነት ፖለቲካ ላይ በተመሠረተው በዚህ ሥርዐት ማንነታችንን ይበልጥ የሚገልጸው የጎንደርና የወሎ አማራነት ነው እያሉ በትግሬ ማንነት በግድ ተጨፍለቁና ለተጨማሪ የባርነት አገዛዝ ተንበርከኩ ማለቱ ግፍ ስለሚሆን ፍትሐዊ ሰው ሁሉ በጽኑ ሊቃወመው የግድ ይላል።

ለሥልጣን ሲባልና ማን ጌታ ማን ሎሌ እንደሆነ ለማሳየት ይህን ያክል ደም አፋሳሽ ጦርነት ከተካሄደ ለፍትሕና   ለነፃነት   ሲባል ጦርነት አይካሄድም   ብ ሎ ማሰብ የዋህነት  ነው።  የድርድሩ ውጤት ቅጽበታዊ ሰላም የሚያመጣለት ሰውና አካባቢ፣ የተወሰነ እፎይታ የሚሰጠው አካል አይኖርም ማለት አይደለም። በዋናነት ግን ዛሬን ለመሻገር ብቻ እና ድርድሩን ካባሸሩና ከተሳተፉ አካላት ጥቅም አኳያ ብቻ የተደረገ የሰላምን መሠረት የሚያናጋ “የቀጠሮና የቋጠሮ ውል” ነው።

ስለዚህ እንደ ኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ወይም እንደ ውጫሌ ውል ብዙ ደሳስ በሚሉ ቃላትና አናቅጽ የታጀበው   የሰላም ስምምነት ተብዬው የፕሪቶሪያ ሰነድ፣  የድሉን  የነጻነት  እድል ያመከነ፣   ለሌላ ግጭትና  ጦርነት መሠረት የጣለ አልጄርሳዊ ሰነድ ነው።  በትግራይና በአማራ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በቀጠናው ሌላ ዙር ቀውስ የሚጠራ እንጂ እንደተደሰኮረለት ለዘላቂ ሰላም መሠረት የሚጥል አይደለም።   ስምምነቱን  በተመለከተ  መልካም አናቅጹን እየጠቀሱ  ጉንጭ  አልፋ ክርክር   ማንሳቱ ቁም  ነገር የለውም።  ከላይ እንደተባለው  የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትም የውጫሌ ውልም ቁልፍ የባርነት እና የሀገር ክህደት አናቅጾቻቸውን እጅግ ብዙ በሆኑ በሚያማምሩና በሚያማልሉ አናቅጽ ነው የመሸጓቸው፣ የሸፋፈኗቸው፣ የከበቧቸው።

ምናልባትም መጀመሪያስ ከአደራዳሪዎቹ ኢትዮጵያ ጠል (ራስ ወዳድ) ባእዳን ስፖንሰሮች እና እነሱ ካሳደጓቸው አሸባሪና ባንዳ ተደራዳሪዎች ዱለታ  እውነት የዘላቂ ሰላም ውል ሊገኝ  ይችላልን? ብለን መጠየቅ ይኖርብናል። ምእራባውያን  በሰላም ድርድሮች፣ በሕገመንግሥት ረቂቆችና በመሳሰሉት ውሎች ውስጥ ቆይተው የሚፈነዱ ፈንጂዎችን ቀብረው  ሀገሮችን በእርስ በእርስ ጦርነት የመዝፈቅ የበሰለ ልምድ ያላቸው ናቸው። በድርድርና በማረጋጋት ስም የገቡባቸው ሀገሮች ወይ ይፈርሳሉ ወይም ለማያባራ እርስ በእርስ ጦርነትና ውዝግብ ይዳረጋሉ። ይህም በአብዛኛው የሚተገበረው በስምምነት ውል ተብዬዎቹ ሰነዶች ውስጥ በተንኮል ጥበብ በሚቀመመው ቋንቋ ነው።  በአደራዳሪነት ስም ገብተው ያፈረሱት ሀገር ሁለት ደርዘን ይሞላል።

እዚህ ላይ ሳይጠቀስ የማይታለፈው የምእራባውያን የተንኮል ጥበብ ድርድሩን ያቀናበሩት እነሱ ሆነው እያሉ ፎቶው ላይ አንድም ቦታ አለመታየተቻው ነው። ሁሉም የድርድር ፎቶ አፍሪካውያንን ነው የሚያሳየው። አንድ የሶሻል ሚዲያ ኮመንት ይህን የድርድሩን ፎቶ እንቆቅልሽ “ዝንጀሮዎቹ ብቻ ፎቶ የተነሱት ቺምፓንዚዎቹ የት ሄደው ነው?” ብሎ በትክክል ገልጾታል። እኔ በመጨመር “ገመሩ ዝንጀሮስ የት ነበር?” እላለሁ። የማያጠያይቀው ጉዳይ ግን ራሱ አቢይ አህመድም በቃሉ እንደመሰከረው የድርድሩ  ውል  ኦህዴድ  ላይ የማይፈልገውን  ነገር የጫነበት  ሳይሆን  በሚፈልገው  ልክ  የተሰፋ  ከረጢት  ነው።  ለዚህም ኦህዴድ/አቢይ አህመድ  የወልቃይት፣  ጠለምት፣  ሁመራና  ራያን  መሬት  ለወያኔ  ለማሰረከብ   አመቱን  ሙሉ  ሲፈጥረው  የከረመውን  መደላድልና  ያካሄደውን መንገድ ጠረጋ ልብ ይሏል።

  1. አረቂያሙን የወያኔ ቡችላ አገኘሁ ተሻገርን  ይህ ውሳኔ ሄዶ ሄዶ የሚወሰንበት የፌደሬሽን ምክር ቤት ወንበር  ላይ መሰየሙ
  2. ይህንንውሳኔ በብርቱ ይቃወማሉ ተብለው የሚታሰቡትን የአማራ ፋኖዎች ሲያሳድድ፣  ሲያስርና ሲገድል መክረሙ  (ዛሬም እያሳደደ መሆኑ)
  3. በዚህምአይቀሬው ድርድር ሲመጣ አማራን የሚወክል ሐቀኛ ተቋም እንዳይኖር አበክሮ መሥራቱ
  4. ነጻለወጡት አካባቢዎች የማንነት ጥያቄ ሕጋዊ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን መቆየቱ
  5. ከሕወሃትነጻ የወጡትን የአማራ አካባቢዎች የባጀትና የመንግሥት አገልግሎት መንፈጉ
  6. ወያኔ ጠለምትና ራያን ይዛ እንድትቆይ በማድረግ በነዚህ አካባቢ ያሉ አማራዎችን እንድታወድም  ማመቻቸቱ
  7. ሕገመንግሥቱ የሚሻሻልበትን እድል ዘግቶ መቆየቱ

እናም ወገኖች እፎይታን አብዝተን ስለናፈቅነው ብቻ አይናችንን ጨፍነን ልንሞኝ አይገባም። ደርግ ሲወድቅ እፎይታን ከመናፈቃችን ብዛት የባርነት እና የሀገር ፍርሻ ወጥመዱ ሲዘረጋ ሁሉ ልብ አላልነውም። አቢይም ሥልጣን ላይ ሲወጣ በእፎይታ ፍለጋ ማእበል ውስጥ እጅግ ብዙ ወጥመዶች ሲዘረጉብን ሳናስተውል ቀርተናል። “ዘላቂ ሰላም ምንትሴ” በሚል አስመሳይ ሰነድ የዘላቂ ሰላም መሠረት በክህደት ሲናድም እንዲሁ በእፎይታ ፍላጎት ብቻ እየናወዝን ሳንመረምር እንዳለ መቀበል አይገባንም።  ጦርነት  መቆሙ  ደስ ይላል።  ለሌላ ጦርነት  መሠረት የሚጥል፣ የትናንቱን የሀገር ፍርሻ መንገድ የሚያስቀጥል ከሆነ ግን ርቀት አያስጉዝም።

እውነት ግን ኢትዮጵያችን ከነዚህ አሸባሪ ስታሊኒስት ድርጅቶች (ኦህዴድ፣ ኦነግ፣ ሕወሃት፣ ብአዴን ወዘተ) እና ከሕገ አራዊቱ የእልቂትና የፍርሻ ሰነዳቸው ነጻ የምትሆንበት ዘመን ቅርብ ይሆን?

______

*ሞገስና ኤርምያስ ኢትዮ 360 ላይ በዚህ ዙሪያ ባደረጉት ሰፊና አስተማሪ ውይይት ይህን አንቀጽ 10.4 በተመለከተ ግን የተሳሳተ አተረጓጎም (ከቋንቋው አቀማመጥ ውጭ) ሲያንጸባርቁ ነበር። ይኸውም resolving issues of contested areas የሚለው “ውዝግብ የሚነሳባቸውን ጉዳዮች ማለት ነው፣ መሬትን በቀጥታ አይመለከትም ወይም አወዛጋቢ ጉዳዮችን ሁሉ መሬትንም ጨምሮ ማለቱ ነው” ብለዋል። እንደዚያ እነሱ እንዳሉት ቢሆን የቃላቱ አቀማመጥ የሚሆነው እንደሚከተለው ነበር

The parties commit to resolving contested issues in accordance with….. ወይም= The parties commit to resolving contested matters in accordance with…..

በውጫሊያዊው የፕሬቶሪያ ውል የተቀመጠው ግን በቀጥታ የመሬት ውዝግብን የሚመለከት ነው። ይሁን እንጂ ትርጉሙ አሻሚ ከሆነም እንደሚመቸው አጣምሞ የመተርጎም መብት የሚኖረው ሥልጣን ላይ ያለው ነው። ሥልጣን ላይ ያለው ደግሞ ፍላጎቱን በግልጽ ቋንቋ ሲያስቀምጥ እና እንዳልነው ለትግበራውም መንገድ ሲጠርግ የከረመ ነው። ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያን በተመለከተ።

እዚህ ላይ የቦርከና ኤዲቶሪያል የፕሬቶሪያን ስምምነት “postponing the war” ብሎ የገለጸበትን ቋንቋ ዘላቂ መፍትሔ ብሎ እስካቀረበው የመደምደሚያ ጥቆማ ጭምር ወድጄለታለሁ።

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop