እዌጥን በስመ ሥሉስ ቅዱስ
ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ [email protected]
ጥቅምት 3 ቀን 2915 ዓ/ም
የነ ቄስ በላይን እሬቻ እንዴት ተረዳሀው? ብላችሁ ያቀረባችሁልኝ ጥያቄ ኢትዮጵያ ያለፈችባቸውን አራቱን የስርአታት ዘመናት፦ የዳሰሳውን ስርአት ፤ የአራዊቱን ስርአት፤ የኦሪቱን ስርአትና የወንጌልን ስርአት እንድቃኝ አደረገኝ፡፡ የእሬቻን ባሕርያት ጥቅሙንና ጉዳቱን በጥልቅ ለመረዳት ከዳሰሳው ስርአት በመጀመር ኢትዮጵያ ያለፈችባቸውን ሁሉንም ሥርአቶች ኦርቶዶክሳውያን አባቶች በነገሩን ስልት መቃኘት ይረዳል፡፡
የዳሰሳው ዘመን
ሰሞኑን እሬቻ ስለሚባለው ነገር ሰወች እየደጋገሙ ሲያወሩ ሰማሁ፡፡ ስርአተ አምልኮ ተብሎ የተዘጋጀለትንም ልከውልኝ አነበብኩት፡፡ በዚህ ዘመን ይህን ያህል ወደ ኋል የቀረ ቡድን በኢትዮጵያ መኖሩ በጣም አሳፍረኝ፡፡ ሰው እሬቻን የመሳሰሉትን የእውቅት የስልጣኔና የእምነት እንቅፋት የሆኑትን ከፊቱ እያስወገደ እዚህ በደረሰበት ዘመን ኢትዮጵያ እሬቻ ከተባለው ጸረ ተፈጥሮ ስራት ውስጥ መግባቷ በጣም አስደንግጦኛል፡፡
በቻይና በህንዱ በዓረብና አውሮፓውያን ሁሉ በጥቅሉ የሰው ልጅ ታግሎ የማያሸንፈው ገፍቶ ፈቀቅ የማያደርገውንና ጫፉን ሊደርስበት ያልቻለውን ተራራ፤ ሊያጠፋው ያልቻለውን የእሳት ነበልባል፡፡ ሊገድበው ያልቻለውን ጎርፉንና ሊገታው ያልቻለውን ነፋሱን ሲያመልክ መኖሩን የታወቀ ነገር ነው፡፡
Jhon Mibiti የተባሉት አፍሪቃዊ African Traditional Religion and Philosophy በሚል ርዕስ ባቀረቡት መጽሐፍ ላይ ቀኝ ገዥወቻቸው ወደ ክርስትና እስኪመልሷቸው ድረስ አፍሪካውያንም በየመንደሮቻቸው ያምልኳቸው ስለነበሩት ስርአቶች በሰፊው ገልጸውታል፡፡ የሰው ልጅ የተሻለ ለማግኘት በሚያደርገው ዳሰሳ የተሻለ በመሰለው እየተካ ካለበት ደርሷል፡፡ ይሁን እንጅ የሰው ጸር የሆነውን ሁሉ ቀፋፊና ዘግናኝ ነገር ተሸክሞ ዛሬ በዘመን መጨረሻ በአገራችን ኢትዮጵያ እሬቻ የሚባለው ብቅ ማለቱ የኢትዮጵያን ታሪክ በየዩንቨርሲቲወች ሲያነቡና ሲያስተምሩ የኖሩትንም ሁሉ አስገርሟቸዋል፡፡
እሬቻ የተባለውን ጉድ አዝላ ብቅ ያለችው ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ ዛሬ ከደረሰችበት እሬቻ ላይ እስክትደርስ፡ በሕገ አራዊት በታቀፈ የዳሰሳ ጉዞ ተጉዛለች፡ ሕገ አራዊትን ታቅፋ በዳሰሳ ላይ ሳለች ህገ ኦሪት ማጅራቷን ያዛት፡፡ ከሕገ ኦሪት በፊት የነበሩት ኢትዮጵያውያን በዳሰሳውና በህገ አረሚ (አራዊት )ዘመናቸው የህይወት መፍለቂያ ነው በማለት የወንድ አባለ ዘር አስመስለው ሐውልት ቀርጸው በመካከላቸው በማቆም ሲሰግዱለት እንደነበር አበው ነግረውናል፡፡ ዘግይተው አምላክ አለመሆኑን ሲረዱ ያቀርቡለት የነበረውን አምልኮት ገፈው በውስጡ ላጠናቀረው ጥበበዕድ ሲሉ ሐውልቱን በቅሬት መልክ እንድንጠብቀው አውርሰውናል፡፡
በህገ አረሚ (አራዊት )የዘመን ጉዟቸው ላይ ሳሉ በሐውልቱ ብቻ የተወሰኑ አልነበረም፡፡ የመግደል የማዳን ኃይል አለው ብለው የእንስሳትንና የሰውን ልጅ በኩር ሳይቀር ይገብሩለት የነበረው በንግሥት
1
ማክዳ አባት ተቃጥሎ አመድ እስኪሆን ድረስ ጤፍን እንደ ቅሬት የተወለንን ዘንዶውንም አምልከዋል፡፡ ተቃጥሎ አመድ ሆኖ ከጠፋው ምድር የተገኘ መሆኑን ለማስረዳት ጤፍ ብለውታል ይባላል፡፡
ዳዊት በዘመኑ ኢትዮጵያ የነበረችበትን አሻግሮ በመመልከት “ወቀጥቀጥከ አርዕስቲሁ ለከይሲ ወወሀብኮሙ ሲሳዮሙ ለህዝበ ኢትዮጵያ” ማለትም “የዘንዶውን ራስ ቀጠቀጥክ ለኢትዮጵያውያንም ምግባቸውን ሰጠሀቸው” መዝ 73፡ 13_14 ብሎ ተናገረ፡፡ ይህን ከተናገረበት ከዛሬ ሶስት ሽ ዘመን በፊት ኢትዮጵያውያን በዘንዶ ያመልኩ ነበር፡፡ ዘንዶው ከኢትዮጵያ እንደሚጠፋና ቋሚ ምግባቸውም ዘንዶው በተቃጠለበት ቦታ በቅሎ ያገኙትን ጤፍ ብለው እንጀራ አድርገው በቅርስ እንደሚጠብቁት ዳዊት በትንቢት አያይዞ ተናገረው ይላሉ፡፡
ነገሩን ግልጽ ለማድረግ የዘንዶውን ነገር በመጠኑ መግለጹ ተገቢ ይመስለኛል፡፡ ዳዊት ኢትዮጵያን በጠቀሳት ዘመን፡ ኢትዮጵያውያን ከሰው እስከ እንስሳ መጀመሪያ የተወለደውን የበኩር ልጅ ለዘንዶው ይገብሩለት ነበር፡፡ የማክዳ አባት የነቃ ነበርና ሰው ሁሉ እንደተታለለ ተረዳ፡፡ ያካባቢውን ሰው ሰበሰበና “በኩራት (የመጀመሪያ) ልጆቻችሁን ለዘንዶው መገበራችሁን አቁሙ፡፡ ገድየ አሳርፋችኋለሁ” አላቸው፡፡ ያካባቢው ሰወች ለዘመናት ባደረባቸው ተጽእኖ ኃይሉን አጋነው በመፍራት የኛ አምላክ እሱን ለማጥፋት ስታስብ ከህሊናህ ቀድሞ በተቀመጥክበት ይገልሀል ተው ብለው መከሩት፡፡
የማክዳ አባት ምክራቸውን ሳይቀበል ዘንዶው ተጠቅልሎ የተኛበትን ቦታ በደረቅ ቁጥቋጦ ከበበና እሳት ለቀቀበት፡፡ ዘንዶው ተቃጠለና አመድ ሆነ፡፡ ከጥቂት አመታት በኋል ያካባቢው ሰወች ትዝታቸውን እያወጉ ዘንዶው በተቃጠለበት አካባቢ ሲያልፉ ሳር በቅሎበት አገኙና የሳሩን ቅጠል ሸምጥጠው አሹት፡፡ ደቃቃ ፍሬ እጃቸው ላይ ረገፈ፡፡ ከጠፋው ዘንዶው የተገኘ መሆኑን ለመጠቆም እጃቸው ላይ የረገፈውን ፍሬውን ጠፍ አሉት፡፡ ከብዙ ዘመን ልምምድ የጤፉን አጠቃቀም ካሻሻሉ በኋላ ወደመደበኛ ምግባቸው ቀይረው እንጀራ ብለው ስም አወጡለት፡፡ ይህም ማለት “ኧረ እንጃ! ኧረ አላውቅም!” ማለት ነው፡፡ ከብዙ ዘመን ዳህጸ ልሳን ጠፍ ይባል የነበረው ጤፍ ተባለ እያሉ ይነግሩናል፡፡
እንግዳ ነገር ሲከሰት ክስተቱን የሚጠቁም ስም መሰጥቱና ከብዙ ዘመን ዳህጸ ልሳን ተጽእኖ ፊደሉን እንደሚለውጥ በሌላውም ኅብረተሰ የተለመደ ነው፡፡ ለምሳሌ እስራኤላውያን በበርሀ በነበሩበት ጊዜ መና ከደመና ዘነበላቸውና በሉት፡፡ እንዴት እንደተከሰተ ስላላወቁ አለማውቃቸውን ለመጠቆም ስሙንም ምንድነው ለማለት መና ብለው ሰየሙት፡፡ መና ማለት በግዕዙ “መኑ” ማለትም ነው ዘጸ 16፡15 የዳሰሳው ዘመን አቅፎት የነበረውን ሕገ አረሚ(የአራዊት ሕግ) ለመዳሰስ እንሞክር፡፡
በሥርአተ አረሚ (ሕገ አራዊት) የነበረችው ኢትዮጵያ
በህገ አረሚ ወይም በአራዊት ዘመን የነበሩ ሰወች ፈቃዳቸውን የማይቆጣጠሩ ከዱር አራዊት የከፋ ባሕርያት ነበሯቸው፡፡ ይህም ማለት ማነኛውም ቆሞ የሚሄድ አውሬም ሆነ እንስሳ እያሳደድክ በጦር እየወጋህ ግደል ደሙን ጠጣ፡፡ ሞቶ ያገኘኽውንም አትለፈው ብላው ፡፡ “ለእመ ሐልቀ ላሕም ሡዑ ሰብአ” ማለትም፦ እንስሳ ካለቀብህ ሰው ሰዋ፡፡ ደሙንም ጠጣ፡፡ ሰውም ትሁን እንስሳም ትሁን ሴት ሆና ካገኘሀት ያለፈቃዷ ሰረራት ማለትም ጥቃት፡፡ ፈቃደ ሥጋህ ከፈለገ ወንዱንም ስረረው ማለትም ድፈረው፡፡ ጉልበት ካለህ መንፈስህ የፈለገውን ሁሉ ስጠው፡፡ አትንፈገው፡፡ አትግታው፡፡ ኃይልህን ያለገደብ ለፈለከው ሁሉ ተጠቀምበት የሚል ነው፡፡ እሬቻ የተባለውን ጉድ አዝላ ብቅ ባለችው ኢትዮጵያ የነበሩት ኢትዮጵያውያንም፤ ከሰባዊ ኑሮ እድገት ውጭ ስላይደሉ ህገ ኦሪትን እስኪቀበሉ ድረስ በሕገ አራዊቱ ስርአት ሄደውበታል፡፡
በሥርአተ ኦሪት የነበረችው ኢትዮጵያ
2
ሥርአተኦሪት ከላይ የተገለጸውን አሰቃቂ ተግባር በሰውና በእንስሳ ላይ ይፈጽም የነበረው ሕገ አራዊት እየተቃወመ የተሻለ ቅርጽና ይዘት ሰጠው፡፡ ወድቆ ያገኘኽውን፤ ሥጋ ተሽክሞ የምታገኘውን አውሬ አትብላ የምትበላቸውንም የእንስሳት አይነት ለይ፡፡ ደሙን አትጠጣ፡፡ ሴት ሆና ባገኘሀት ሰውም ትሁን እንስሳ ላይ መንጠልጠልህን አስወግድ 18 ፡7_፡፡ አትስረር ወንድም አትድፈር፡ ዘሌ 18፡22 23 ሰማይና ምድር የፈጠረውን አንድ አምላክ ብቻ አምልክ፡፡ ለራስህ ሊደረግልህ የምትፈልገውን ለሌላ አድርግ፡፡ ሊደረግብህ የማትፈልገውን በሌላው አታድርግ አካልህን ስሜትህን ከአረመኔው ልማድ ግረዝ፡፡ እንዳትገደል አትግደል፡የሚለው ሥርአተኦሪት ተተካ፡፡ ዘጸ 21፡23_25፡፡ኢትዮጵያ ይህንንም ተቀበላ፤ በተቀበለችው ሥርአተ ኦሪት እየታገዘች በህገ አረሚ ወይም በሕገ አራዊት ያሉትን ወገኖቿን አካታ ለመያዝ በትግል ሳለች ወንጌል ተደረበባት፡፡
በሥርአተ ወንጌል የነበረችው ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ ከሕገ አራዊት ርዝራዥ ራሷን ጨርሳ ሳታጸዳ በሕገ ኦሪት ላይ ሳለች ወደ ወንጌል መሻገሯ የእመርታዋ ፍጥነት ለምሳሌነት በታሪክ እንድትወደስና እንድትደነቅ አድርጓታል፡፡ ይህም ሲባል ከዳር እስከዳር የነበሩት ሕዝቦቿ በተመሳሳይ መረዳት፤ በተመሳሳይ ዘመንና መጠን በተመሳሳይ እርከን ላይ እየደረሱ የቀደሙትን ሥርአቶች እኩል ተሻገሩት ማለት አይደለም፡፡
ሕገ ወንጌል ከህገ ኦሪት ጉያ ወጣ እንጅ “ልፈጽም እንጅ ልሽር አልመጣሁም” (ማቴ 5፡17 ) በሚለው ክርስቶሳዊ ድጋፍ የመጣውን ኦሪትን መደምሰስ ሳትሞክር ይልቁንም ሙሉ ኀላፊነቱን ለቤተ እስራኤል ወገኖች በመተው ለሰውና ለእንስሳ ጠንቅ የሆነው ጨርሶ መጥፋት ያለበት ህገ አረሚ(ህገ አራዊት ) ከምድሯ ጨርሳ ለማጥፋት በትግል ላይ ሳለች ወንጌልን ደረበች፡፡
በመጨረሻ የተቀበለችው ሥርአተወንጌል፡ ክርስቶስ ሲጠመቅ “ጽድቅን ሁሉ መፈጸም አለብን”
(ማቴ 3፡15) ብሎ በዮርዳኖስ ያወጃት ጽድቅ ናት፡፡ በህገ አረሚ ላይ እንዳለ ከህገ ኦሪት ላይ ሳይደርስ ተቆርጦ
የቀረባትን ህዝቧንንና በህገ ኦሪት ላይ ያለውን ህዝቧን ከዳር እስከዳር አስተካክላ ወደ ወንጌል መርከብ
ማለትም ወደ ጽድቅ ወደ ቅድስና ለማምጣት ከራሷ ህዝብ ጋራ በመታገል ላይ ሳለች፤ በራሳቸው አገር
በአረመኔወች በመሳደድ ላይ ያሉትን ተሳቱ ቅዱሳን የሚባሉትን ክርስቲያኖችን በመሰብሰብ ሕገ አራዊትን
የምትፋለሙባቸውን ገዳማት (ምሽጎች) በየቦታው ሠራች፡፡
በዚህ ላይ እያለች ሌላ ተጨማሪ ኃይል ያገኘችበት አዲስ ክስተት ገጠማት፡፡ በነቢዩ መሐመድ ትምህርት ከሕገ አረሚ ተላቀው አንድ ፈጣሪ ማምለክ የጀመሩትን ዐረቦችን በሕገ አራዊት የነበሩት አረመኔወች ዘመዶቻቸው ሲያስድዷቸው ኢትዮጵያ ወደራሷ ሰበሰበች፡፡
በወቅቱ ባመራር ላይ የነበሩት አባቶቻችን ሶስቱም የእምነት ተቋማት ማለትም የቤተ እስራኤልም የክርስትናም የሙስሊምም የእምነት ተቋማት ሰማይንና ምድር በፈጠረ ባንድ አምላክ የተመሰረቱ ስለሆኑ ወደ ዝርዝር የነገረ መለኮት ሐተታ ሳይገቡ ጸር ተፈጥሮን ማለትም ህገ አረሚን በጋራ ታግሎ ለማጥፋት ያንድነት ኃይላቸውን አጠናከሩ፡፡
አውሮፓውያን በክርስቶስ እናምናለን ቢሉም፤ በሕገ አራዊት ወረራ ስለመጡባቸው የኦርቶድክስ ተዋህዶ እምነታቸውን ጠብቀው ባንድ አምላክ ከሚያምኑት ከቤተ እስራኤልና ከሙስሊሞች ዜጎቻቸው ጋራ ተባበረው የጋራ አገራቸውን ተከላከሉ፡፡ ዓረቦችም ባንድ አምላክ እናምናለን እያሉ በወረራ መልክ ሲመጡባቸው ከጥቂት ሙስሊም ዜጎች በቀር ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከክርስቲያንና ከቤተ እስራኤል ዜጎቻቸው ጋራ ተሰልፈው ኢትዮጵያን ተከላክለዋል፡፡ ይህም ማለት፡ ጠላት ከተለያዩ አቅጣጫወች በህገ
3
አራዊት በመጣበት ጊዜ ሁሉ ከቤተ እምነቶች ካሉት ዜጎች በአራዊቱ መንፈስ ሕሊናቸው ተሰርቆባቸው ከጠላት ጋራ የተሰለፉ ዜጎች አልነበሩም ማለት አይደለም፡፡
ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ልፈጽመው መጣሁ እንጅ ልሽረው አልመጣሁም ያለውን 10 ቃላት የተጻፈበትን ጽላት ተሸክማ ወደ አደብባይ በመውጣት “ድንበር አታፍርስ” የሚለውን ሽራችሁ ውቅያኖስ አቋርጣችሁ የሰው አገር የምትወሩ አረመኔወች ናችሁ አቁሙ! እያለች በክርስትና ስም ከውጭ የሚመጡትን አውሮፓውያን መገሰጿን ቀጠለች፡፡ ሶስቱም ቤተ እምነቶች፦ ቤተ እስራኤል፡ ቤተክርስቲያንና ቤተመስጊድ በጽላቱ ላይ በተጻፈው ሕግ ላይ ልዩነት ስለሌላቸው በየበዓላቷ በተለይም ክርስቶስ ጽድቅን በፈጸመባት በጥምቀት በዓል በአውሮፓውያን ወራሪወች ላይ የምታስተላልፈውን የተቃውሞ አዋጅ ተባብረዋል፡፡
የሁሉም ቤተ እምነቶች ዜጎች ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ላይ ያለቸው አንድነት ለወራሪወች ስላስቸገረ፡፡ ወራሪወች በእምነት ልዩነታቸው እየገቡ ሊከፋፍሏቸው ሞክረዋል፡፡ አገር በቀል አረመኔወች ግን በቀላሉ እየተታለሉ የራሳቸውን ህዝብ በመሸጥ በመለውጥ ከመጣው ሁሉ ጋራ በመተባበር አገራቸውንና ህዝባቸውን ከመጉዳት አላቆሙም፡፡
እነአጼ ምንይልክ፤ እነሀብተ ጊዮርጊስ፤ እነ ባልቻ አባ ነፍሶ፤ እነራስ ጎበና እነ በላይ ዘለቀና ሌሎችም ኦርቶዶክሳውያን አርበኞች “የተዋረዱትን ከፍ አደረጋቸው ትቢተኞችን በተናቸው” ብላ ስለ ሰው ልጅ ልዕልና በተናገረቸው በቅድስት ድንግል ማርያም እርስ በርሳቸው ቃል እየገቡ ከውጭ ወራሪ ጋራ መቆምህን ባታቆም “ማርያም አትለመነኝ” አለቅህም እያሉ ከውጭ ወራሪ ጋራ የተሰለፈውን ተወላጅ አረመኔ እያስተካከሉ ኢትዮጵያን እሰከ ወያኔወች ዘመን አደረሷት፡፡
እንደ በርሀ ቋያ ዛሬ በመግለብለብ ላይ ያለውን እሬቻን ኢትዮጵያ ባለፈችባቸው ስርአቶች ስፈትሸው፡ ኮረብታ ተራራ ውሀ በሌበት በተንጣለለ ሜዳ ላይ በቀትር ጸሐይ፤ ነፋስ እየሰበቀ የሚያግለበልበው የተንጣለለ የባሐር ወለል የሚመስል፡ ሲቀርቡት ምንም የሌለው ዋዕይ(mirage) ብቻ ሆነብኝ፡፡ በኢትዮጵያ አገራችን እሬቻ ገኖና ተጋግሎ በተቀሰቀሰበት ወቅት ጎን ለጎን በሰው ላይ የሚፈጸሙትን ቀፋፊና ዘግናኝ ተግባርት፤ ማረድ፤ በጦር፤ መውጋት፤ ማቃጠል፤ ሴቶችን መስረር፤ ወንዶችን መድፈር፤ ስመለከት ከሬቻ ጋራ የማይላቀቁ እንደ ነፍስና ሥጋ የተዛመዱ እንጅ ባጋጣሚ የተከሰቱ አይደሉም፡፡ይህም ማለት ኢትዮጵያ በዘንዶው መንፈስ ወደነበረችበት ወደ ሶስት ሽ ዘመን የተመለሰች መሰለኝ፡፡
ወደ ሶስት ሽ ዘመን የተገለበጠችው ኢትዮጵያ
የማክዳ አባት ያቃጠለውን ዘንዶ የትግራይ ወያኔወች ቀሰቅሰው በመንፈሱ አሰከራቸው፡፡ ዘንዶው ያደርገው የነበረውን መዋጥ ከትግራይ ልጆች አስጀመራቸው፡፡ አክርራ በታገለችው በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንና በአማራው ላይ ኃይሉን ሁሉ አሰባስቦና አጠናክሮ አፉን ከፍቶ የመዋጥ ሥራውን በስፋት ቀጠለ፡፡ በመጨረሻም ወደ ኦነግ ሸኔዎች መንፈሱንና ሱሱን አሻገረው፡፡
የእሬቻ ንክኪ ባለባቸው ቦታወች በተወለዱት ላይ ባሰፈነባቸው የቂምና የጥላቻ መንፈስ ድሮ የተቃወሙትን የነ አጼ ምንይልክን ሐውልት እንዲያፈርሱ አጽማቸውን ከመቃብር እየቆፈሩ እንዲያቃጥሉ አስገደዳቸው፡፡ አርበኞች ለነጻነት ምሳሌነት የሚጠሯትን ቅድስት ድንግል ማርያምን የኦርቶዶክሱን አርበኝነት የሰበርን እየመሰላቸው የማይመጥናትን ነገር መናገር ጀመሩ፡፡ አትውረር የሚለውን 10ቱ ቃላት የተጻፈበትን ጽላት ማጣጣል ጀመሩ፡፡ “ጽድቅን መፈጸም ይገባናል” እያለች ስትዋጋቸው የነበረችውን
4
ፍአ5፡ቁ130
ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለትምህርትና ለተግሳጽ የጻፈቻቸውን ለአምላክ ስነ ባህርይ መለኪያ አደረገቻቸው እያሉ ለማዋረድ ታጥቀው ተነሱ፡፡
ከኦርቶዶክስ ክርስትና ካማራው እና ካጼ ምንይልክ ጋራ ንክኪ አለው ብለው በገመቱት ሁሉ ላይ ማለትም በቋንቋው በፊደሉ ላይ ሳይቀር ዘመቻቸውን አወጁ፡፡ የመግደልና ጡት የመቁረጥ ባህርይ የዘንዶው መንፈስ የተጠናወተው የራሱ የእሬቻ ባህርይ መሆኑ እየታወቀ፤ የእሬቻን መንፈስ ሲቃወም ወደነበረው ወደ ምኒልክ ገልብጠው የተቆረጠ ጡት የተሸከመ ሀውልት አሩሲ ላይ ተከሉ፡፡ የዘንዶውን መቃጠል ለመበቀል አብያተ ክርስቲያናትን፤ ገዳማትን መስጊዶችን አቃጠሉ፡፡ አማራውን አማረኛ ተናጋሪውን አማረኛ ፊደል ተጠቃሚውን ሁሉ አሳራጅ ወደ ሆነው እሬቻ ኢትዮጵያ ስትገለበጥ ቤተ ክህነቱ ቆሞ በዝምታ በመመልከቱ ተመልካቹን ሁሉ አስደነገጠ፡፡
አስደንጋጩ የቤተ ክህነታችን አቋም
ባንድ አምላክ የሚያምኑት የሶስቱ ታላላቅ እምነቶች የይሁዲ የክርስትናና የሙስሊም ቤተ እምነቶች እሬቻንና መነፈሱን በሚቃወሙበት ወቅት በቤተ ክህነታችን አመራር ላይ ያለው ከእሬቻው ጋራ ተሰለፈ፡፡ በዘንዶው መንፈስ ስክሮ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ያጠመቀቻቸውን ልጆቿን የዋጠውን ያስዋጠውን ድርጅት ለፍርድ ለፍትህ ይቅረብልኝ ብሎ ለሚመለከው ሁሉ ድምጽ ከማሰማት ይልቅ የዋጠውና ያስወጣው ድርጅት እንዳይወቀስ እንዳይከሰስ ጋረደ ተባበረ፡፡ ሕገ አራዊትን ደገፈ፡፡
በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ቀኖና በግልጽ የተሳሳቱትን ማቀፍ ቀርቶ፡ አንድ ሰው ተሳስቶ ስሕተቱን ተቀብሎ ንሰሐ ከተቀበለ በኋል ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ቁርባኑን ከክርስቲያኖች ጋራ አይካፈልም፡፡ የንስሀ ፍሬ እስኪያሳይ በአመክሮ ገለል ብሎ ይቆይ ነው የሚለው “ወለእመ ነስሐ ወተመይጠ
እምነ ስሕተቱ ዓዲ ኢይደልዎ ይሳተፍ ቅድሳተ ምስለ ክርስቲያን እስከ ይትከሠት እምኀቤሁ ፍሬ ንስሓ” ፡፡
የዘመናችን ቤተ ክህነት ይህን ቀኖና ረግጦ አቋሙን ቀይረ፡፡ “በኦሮምያ ክልል የተገኘ አማራና ኦርቶዶክስ የምንይልክ ሰፋሪ ነውና መታረድ ይገባዋል ብለው የፈረዱት እነጀዋር ያዘጋጁትን ገጀራ ከባረኩ ቄሶች ጋራ ተስማማ፡፡ ከፈረደው አረመኔ ጋራ ተሰከፈ፡፡
ከነ ፓስተር ቶሎሳ ይልቅ የከበደ ህላፊነት ያለባቸው እነ አጼ ምንይልክን አጥምቃ አረመኔወችን እንዲታገሉ ባደረገቻቸው ኢትዮጵያዊት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የተሰየሙት ፓትርያርክ ነበሩ፡፡ እነአቶ ለገሰ ሌንጂሳ “የሰው ደም የተጠማ የዘንዶው መንፈስ ነው፡ እኛም በሱ ከመዋጥ ያመለጥን ነንና ከእሬቻ ሽሹ” እያሉ ለአካባቢው ሕዝባቸው ድምጻቸውን ማስተጋብት ጀመሩ፡፡ ወደ ቤተክህነቱ የገባው የዘንዶው መንፈስ በእነሱ ላይም የሠራዊቱን አፍ አስከፈተባቸው ፡፡
ፓትርያርካችን በስራቸው ያለነውን ቄሶቿንና አማኞቿን አስተባብረው ከነ ፓስተር ቶሎሳ በላቀና በተጠናከር ሬቻን መታገል ሲገባቸው የሬቻው መንፈስ አይሎ በተነሳበት ወቅት ፍልሰታን አቋርጠው ለህክምና ብለው ወደ አሜሪካ መጡ፡፡ ከነማን ጋራ ሰነበቱ? ምን ተነጋገሩ? ወደ ኢትዮጵያ ሲመልሱ እንዴትና በእነማን ረድኤት ተሸኙ? ወደ ኢትዮጵያ የተሸኙበትን የእሪቾችን ቄሶች የጸሎት መሸኛ ከፎቶው ግርጌ አንብቡ ፡፡
5
አሜሪካ ላይ ሲደርሱ የቀረበላቸው አቀባበልና ሲመለሱም የተሸኑበት መንገድ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ሊቀርብ የማይገባ በሬቻው መንፈስ የተዘበራረቀና መንገዱን የሳተ ተመልካቹን ያስደነገጠ ነበር፡፡
መንገዱን የሳተ ድጋፍና ተቃውሞ
“ወንድሞች ሆይ የባሰ ፍርድ እንዳንቀበል ከእናንተ ብዙወች መምህራን አይሁኑ” (ያዕቆ 3፡1) የሚለውን መመሪያችንን ስተን በዚህ ዘመን ያበዛናቸው ስፍር ቁጥር የሌላቸው መምህራን በእሬቻ ላይ የሚያሰሙት ተቃውሞ ለባሰ እልቂትና ፍርድ ኢትዮጵያን እየዳረጓት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችንንም በእሬቻው መንፈስ እንድትዋጥ እያደረጓት ንው፡፡
ኦርቶዶክሳዊውን የተቃውሞ መንገድ ስተው ተቃውሟቸውን በፖለቲካው መንገድ በማድረጋቸው የዘንዶውን መንፈስ እያጠናከሩት ነው፡፡ በተቃዋሚ መልክ የተሰለፉ መስለው ተቃዋሚ ያለ በማስመሰል በግልጽ የሚቃወሙትን የቤተ ክርስቲያን ልጆችን ለማዘናጋት ተጽእኖ እንዳይፈጥሩ ለማደረግ ለመሳሪያነት የሬቻው መንፈስ እየተጠቀመባቸው ነው፡፡
ተቃዋሚ መስለው የቀረቡትን ሰዎች አውቀውም ይሁን ሳያውቁ የሬቻው መንፈስ ለአቡነ ማትያስና ለእነ ቄስ በላይ ደጋፊወች አድርጓቸዋል፡፡ ቄስ በላይን ለምን ገባ እያሉ በሌላ በኩል ቄስ በላይን አቅፎ የያዘውን መደገፍ በተዘዋዋሪ መንገድ የሚቃወሙት የሬቻውን መንፈስ ሳይሆን ቄስ በላይን ነው፡፡
6
የእሬቻው መንፈስ የተቀደሰውን ተቃውሞ በቄስ ባላይ ብቻ ገድቦ፡ ደጋፊወችን ብትነካ በቄስ በላይ አማካይነት ባዘጋጀሁት አካል እውጥሀለሁ እያለ በማስፈራራት ለአቡነ ማትያስ ዘበኞች አድርጓቸዋል፡፡ ዘንዶውን በሙሉ ኃይላችን በኅብረት ታግለን እንዳናሸንፈው በአባዜው በተውረሩ ዜጎች በኩል ተቃውሟችንን ወደራሱ በመገልበጥ አፍኖናል፡፡
በተቃውሞ ተሰልፈናል የሚሉ ወገኖች ክርስቶስ፤ ጳውሎስ፤ አትናቴወስ፤ ዮሐንስ አፈውርቅና ሌሎችም የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባቶች የጠቀሙበት መንገድ መጠቀም በተገባቸው ነበር፡፡
ክርስቶስ ብቁ ሳይሆን የገባውን “ወዳጄ ሆይ የተመረጡ ጥቂት ሰወች ብቻ በሚገቡበት እንዴት ገባህ እጁንና
እግሩን አስራችሁ አስወጡት “ማቴ 22፤ 11_13 ፡፡ ብሎ እነደነ ቄስ በላይ ሰርጎ የገባውን እንዲያስወጡ አዘዘ፡፡ እነ አቡነ ማትያስ ከክርስቶስ ይልቅ ወያኔንና ብልጽግናን የሚከተሉ በመሆናቸው የክርስቶስን ትእዛዝ ሽረው እነ ቄስ በላይን ታቀፉ፡፡ መምህራን የሚባሉትም የክርስቶስን ትእዛዝ በመሻራቸው አቡነ ማትያስን በግልጽ መገዳደር ሲገባቸው ያሳዩት ድጋፍና ተቃውሞ መንገዱን የሳተ ሆነ፡፡
ተቃዋሚወቹና ደጋፊወቹ ቅዱስ ጳውሎስ “በውስጥ ባሉት ሰወች ላይ አትፈርዱምን ክፉውን ከመካከላችሁ
አውጡ ” (1ኛ ቆሮ 5፡12_13) ብሎ ያስተማረውን ሐዋርያዊ ትውፊት መከተል ባለመቻላቸው በሐዋርያዊት ትውፊት ላይ ያመጹትን ደገፉ፡፡
ጴጥሮስ የተሳሳቱትን ከመቃወም ይልቅ ፈርቶ አፈገፈገ፡፡ ከተሳሳቱት ጋራ ተሰለፈ፡፡ እንደ ወንጌል እውነት ራሱን አዘጋጅቶ በቅንንት መንገድ አለመቃወሙን ቅዱስ ጳውሎስ ሲያይ ይፈረድበት ዘንድ የገባዋል ብሎ ጴጥሮስን ዘለፈው (ገላ 2፡11_14) ፡፡ ተቃዋሚወቹ ይህን ሐዋርያዊ ትውፊት ባለመከተላቸው ተቃውሟቸውም ድጋፋቸውም ከኦርቶዶክሳዊው ትውፊት አፈነገጠ፡፡
አትናቴዎስ “ሕቱ እምውስቴትክሙ በአበይኖ፡፡ ገሥጽዎ ወዝልፍዎ በግሀድ ለዘጌገየ ኢይቁም ወኢይኅበር ምስሌክሙ” (216፡ቁ 8_9) ያለውን በመከተል ከፖለቲካዊ አድልወ በራቀ ሚዛናዊ ፍርድ የተሳሳተው ከራሱ ስህተት ተጸጽቶ እንዲመለስ ሌላውም እንዲማርበት በግልጽ ውቀሱት ዝለፉት ብሎ ያስተማረውን ሰምተውት የሚያውቁ አይመስሉም፡፡
“ወለኩሎሙ እለ ይትቃረንዋ ለሕግነ ሠሩ እምድር ዝክሮሙ ስቅል ጋጋ ዘእሳት ውስተ ክሣውዴሆሙ ኀበ ቦቱ
ይሰሀቡ ውስተ ዐቢይ ሰይል” ገጽ 235 ቁ 135_136 ህገ ወንጌልን ክደው ሕገ አራውትን የሚደግፉትን ስም አጠራራቸውን ሰርዝ፡፡ ባንገታቸው ያደረጉትን የእምነት አርማ አስወልቀህ በምትኩ የተለዩበትን ምክንያት የሚገልጽ ምልክት እሰርባቸው፡፡ የሚለውን ቀኖናችንንም ሳቱት፡፡
“ለብዙ ዘመናት ለረዥም ወራት ” (ሥ. ቅ. ገጽ 77 ቁ18 ) ጠብቅልን እየተባለ እንዲጸለይ በቀኖናችን የታዘዘው፡ አምላክ ከኢትዮጵያ ምድር የእሬቻውን መንፈስ አስወግዶ የመከራውን ዘምን እንዲያሳጥርልን ለሚታገሉ መንፈሳውያን መሪወች ነበር፡፡ ዛሬ ግን የተቃውሞውም የድጋፉም መንገድ አቅጣጫውን በመሳቱ ሬቾችንና ደጋፊወቻቸውን ለረዥም ዘመን እንዲያኖርልን አምላክን በመማጸን ላይ ነን፡፡ ህዝቡንም በዚህ አይነት የጥፋት ተማህጽኖ አፍዘንና አደንዝዘነዋል፡፡ ታዲያ በዚህ ዘመን ኢትዮጵያ ወደ ሕገ አራዊት አልተገለበጠችም ማለት ይቻላልን?
ይቆየን
7