October 14, 2022
11 mins read

ለኢትዮጵያ ትንሳዔ ከኢትዮጵያዊነት ዉጭ አማራጭ አይኖርም !

በጭለማ እና ድንግዝግዝ በበዛበት የፖለቲካ እና የታሪክ  ሽሚያ ትንቅንቅ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ከየትኛሙም ጊዜ በላይ በታሪካዊ ጠላቶች ጥርስ ዉስጥ ገብተዋል ፡፡

የሶስት አስርተ ዓመታት የግፍ እና የሰቆቃ ዓመታት ትሩፋት የሆነዉ የጊዜዉ የጦርነት ፣ የድህነት ፣ ስደት እና ሞት ጣር በዕለት ተዕለት የዜጎች ህይወት ከንጋት አስከ ምሽት በልቶ ለማድር የሚጨነቅባት ኢትዮጵያ የምድር ሲኦል ወደ መሆን  ተቃርባለች ፡፡

ይህ ሁሉ የሚሆነዉ ደግሞ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ከሚገኙበት የታሪክ ስብራት እና የጠዉልድ ዝቅጠት እና ዉድቀት ወደቀደመ ማንነት እና አብነት ከፍታ ማማ ለመመለስ ከሚሰሩት ኢትዮጵያዉያን እና በተቃራኒዉ ኢትዮጵያን ከከከፍታዋ ለማዉረድ እና ለማዋረድ በኢትዮጵያዊነት  ማንነት ላይ የጥፋት ነጋሪት በሚጎስሙት ታሪካዊ የዉስጥ እና የዉጭ ጠላቶች መካከል ነበር ፤ነዉ ፡፡

ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ሆና እንድትቀጥል ለዛሬ መሰረት የጣሉትን ኢትዮጵያዉያን በማንነታቸዉ እና የዚህ መገለጫ በሆነዉ ሁለንተናዊ ነባር ዕሴቶች ላይ የበታችነት በወለደዉ ጥላቻ በመነሳት የጥፋት ሴራ ለሚያራምዱ ጠላቶች በአመለካከትም ሆነ በተግባር ለሚፈፅሙት በደል አይቶ እንዳላየ የሚያልፍ አካል ሁሉ ኃላፊነቱን መወጣት አለመቻሉም ከጠላትነት ጎራ ስላለመሆኑ የሚታወቅ ነገር የለም ፡፡

ዜጎች በማንነታቸዉ ተለይተዉ ለሚደርስባቸዉ መጠነ ሠፊ አስከፊ መከራ ሞት ፣ዉርደት ፣ስደት ፣ ሠባዊ እና ቁሳአካላዊ የመብት ገፈፋ  ተፈጥሯዊ ራሳቸዉን እና አገራቸዉን ለመታደግ እና ለመከላከል የሚያስችል ህብረት እና አደረጃጀት እንዳይኖራቸዉ በቀጥታም ሆነ በስዉር የሚደረግ ሴራም ኢትዮጵያዊነትን እና ብሄራዊ አንድነትን አምርረዉ የሚጠሉት ፀረ-ህዝብ እና ኢትዮጵያዉያን የጥፋት ኃይሎች ፍላጎት ነዉ ፡፡

ለዚህም በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ ላለፉት የጥፋት እና ዉድመት ዓመታት ከህገ -ኢህአዴግ የጥፋት ስምምነት (የ1968 ዓ.ም. እና የ1987 ዓ.ም) የሚነጨዉ የኢትዮጵያን ማዕከላዊ ፤ብሄራዊ አንድነት ከሚሸረሽር  ፤ ህዝብን ከህዝብ አባር እና ገባር ከሚያደርግ ፤ የብሄራዊ ሉዓላዊነትን በደብዛዛዉ የሚንድ፤ ብዙኃኑን ኢትዮጵያዊ ዓማራ ህዝብ በራሱ አገር እና ምድር በሁሉም በፖለቲካዉ ፣በማህበራዊ፣ በታሪክ ፣ በምጣኔ ሀብት  …በባህል  የበይ ተመልካች ከማድረግ በላይ መፃተኛ እና ስደተኛ በማድረግ ዛሬም በራሱ ጉዳይ እንዳይመክር ፤እንዳይዘክር የማይበጠስ ቅጠል ፤የማይፈነቀል ድንጊያ የለም ፡፡

ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት በማይኖሩበት እና በማይከበሩበት ኢትዮጵያን በግዞት የግል እና የቡድን የግዞት ምድር የሚያደርጉ ጠላቶች ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ አስከምንገኝበት ጊዜ ብሄራዊ አንድነትን የሚያስከትለዉን ትስስር እና ህብር በመፍራት እና በመጥላት ኢትዮጵያዊ መዓዛ በሚታይበት ሁሉ ሳታክቱ ይህን ለመቀጨት የሚሰሩ ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ቅርፅ እና መልክ በመቀያየር እዚህ ጋ ተደርሷል፡፡

ኢትዮጵያን ለማዳከም እና በሚፈልጉት ልክ ለማዋረድ ከቅድመ 1983 ዓ.ም አስካዘሬ  ጠላት ለሚጎነጉነዉ የጥፋት ሴራ ያልተነበረከኩ ኢትዮጵያዉያን ለነፃነታቸዉ እና ለማንነታቸዉ ለመታገል የተለያየ አደራጃጀት መፈጠር ታግለዋል ፤ ይታጋሉ ፡፡

ለአብነት ዕዉቁ እና ታላቁ የአገራችን የህክምና ሊቅ ፕ/ ር ኢህአዴግ ሽግግር  ጀምሮ አስከ ኢትዮጵያዉያን  ሠባዊ እና ተፈጥሯዊ መብት ጥሰት በተለይም ኢትዮጵያን ለማክሰም ፤ ኢትዮጵያዉያንን / ዓማራን ማዉደም በሚል የጥላቻ  መንፈስ አጥብቀዉ በማዉገዝ የዓማራ ህዝብ ለራሱ እና ለአገሩ  ከብር እና አንድነት በኢትዮጵያዊነት አንድነት እና ህብረት እንዲደራጂ እና እንዲታገል አድርገዋል ፡በዚህም የኢትዮጵያን ዉድቀት እና የዓማራን ዕልቂት አይቀሬነት በጥዋቱ  የተረዱ የኢትዮጵያ ሙሴ ነበሩ ፡፡

የርሳቸዉን ወኔ እና የትግል ዓርማ ከፍ በማድረግ ትልቅ ተጋድሎ የፈፀሙ እንደ እነ አስማረ ዳኜ ያሉ ጀግኖች  ትናንትም እንደዛሬዉ በፀረ-ኢትዮጵያዉያን ኃይሎች ሴራ ህይወታቸዉ ቢያልፍም የተነሱለት ዓላማ እና ብሄራዊ የጀግንነት እና የነፃነት የትግል ፍሬ የሆነዉ ተጋድሏቸዉ በዘመን እና ትዉልድ ጅረት ህያዉ ሆኖ ቀጥሏል ፤ ይኖራል፡፡

የዚያን ጊዜዉ የዓማራ አደረጃጀት ዓማራን መታደግ  ኢትዮጵያን ከዉድቀት እና ከጥፋት መታደግ መሆኑን የተረዱት ብሄራዊ ጀግኖች ለህዝብ እና ለአገር አንድነት መቀጠል ለትግል ሲነሱ ፍላጎታቸዉ ዕዉነትን ለማስተማር እንጂ በግል ጥቀም በመነሳት የሚፈልጉትን ለማግኘት እና የነበራቸዉ አንሷቸዉ አልነበረም ፡፡

ያ መራር ትግላቸዉ ጎምርቶ በፖለቲካ አብን እና በኃይል አደረጃጀት ፋኖን  እንደገና እንዲያብብ እና እንዲነበብ አድርጎታል፡፡

የዓማራ ህዝብ እንደ ሠዉ ተፈጥሯዊ መብቱ እና ክብሩ ፤ ሠባዊ መብቱ ፤ ኢትዮጵያዊ የአገር ባለቤትነቱ እና ትዉፊቱ  በፖለቲካም ሆነ በኃይል ሚዛን ፍትኃዊነቱ አስካልተረጋገጠ ጊዜ ድረስ የኢትዮጵያን እንደ አገር መቀጠል ለሚሹ ሁሉ አሁን ኢትዮጵያ ከምትገኝበት ታሪከዊ ስብራት ለማዳን በአንድነት እና ህብረት ለራሳቸዉ እና ለአገራቸዉ ዘብ መቆም አለባቸዉ ፡፡

ያለኢትዮጵያዉያን ኢትዮጵያ ፤ ያለ ዓማራ ህዝብ ተሳትፎ ኢትዮጵያዊ አንድነት እና ዕድገት “ወንዝ/ ዉኃ ሳይኖር መስኖ ”ማሰብ ነዉ  ፡፡

ራሱን የሚወድ ሌላዉን ይወዳል ፤ ሌላዉን የሚወድ አገሩን እና ማንነቱን አጥብቆ ይወዳል ፡፡ ዛሬ ላይ ከ ፴  ዓመታ በፊት የተጠመደዉ ኢትዮጵያን የማጥፋት  ወጥመድ እና ጉድጓድ አንዱ እና ዋነኛዉ ኢትዮጵያዊነት ድር መቆራረጥ ሲሆን ይህም ፀረ -ዓማራ ዘመቻ መከፈት እና ማስፋፋት ነበር ፡፡ ለዚህም ነዉ ዛሬም ከዉጭ እና ዉስጥ የኢትዮጵያ ጠላቶች ፀረ-ኢትዮጵያዊነታቸዉን በማቡካት ፣በማሟሸት እና የሚጋግሩርት ዓማራ ጠል  አረም በመዝራት ነዉ ፡፡ ይህን አማረ ጠል ዓረም በተለያየ መልክ ኢትዮጵያዊነትን በመዋጥ እና በመለወጥ ፀረ-ኢትዮጵያዊነት ጥድፊያዉ ቀጥሏል፡፡

ለዚህ ነዉ ኢትዮጵየዉን ሁሉ “ኢትዮጵያዊነትን እየናዱ ፤ዓማራን እየካዱ ፤እያስወገዱ ኢትዮጵያ ለሚሉ የኢትዮጵያ ቀንደኛ ታሪካዊ ጠላቶች ” በጋራ እና በተባበረ ክንድ ለመመከት እና ለማጥፋት የትብብር ጊዜ አሁን ነዉ  ፡፡

የኢትዮጵያን ትንሳኤ የሚመኝ እና ከምትገኝበት የታሪክ ስብራት እንድትድን የሚመኝ ኢትዮጵያዉያን ብቻ መሆኑን አዉቀን ከዚህ ዉጭ መሃል ሠፋሪ እና የጠላት ተባባሪ ሆነ የታወቀ ጠላት ለኢትዮጵያዉን ድህነት አማራጭ እንደማይሆን ዛሬም እንደትናንቱ በቁርጥ እና በግልፅ መረዳት ይገባል፡፡

 

“ለነፃነት እና ለህልዉና በሚያስፈለገዉ ተጋድሎ መዘናጋት ፍሬዉ ዉርደት እና ሞት ነዉ ፡፡”

“አንድነት ኃይል ነዉ ”

 

NEILOSS Amber!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop