September 13, 2022
28 mins read

ጅሉ ፓሰተር፣ ጅላጅሉ ዶክተርና ጅላንፎው ኮሎኔል- ጠ/ሚ አብይ አህመድ – አስቻለው ከበደ አበበ

የዛሬ ሶስት ሰምንት ገደማ ጠ/ሚ አብይ ከመላው ኢትዮጵያ የተሰባሰቡ ወጣቶችን(የብልጽግና ፓርቲ ደጋፊዎችን) ሰብሰበው ጅል፣ጅላጅልና ጅላነፎ ትርጉም ሲያሰጠኑ ነበር፡፡ እኔ እነደሚመስለኝ ይህ የራሳቸው ሃሳብ አድርገው ያቀረቡት ብያኔ ከአልበርት አንስታይን የተዋሱት ነው፡፡

“ማነኛውም አዋቂ ሞኝ፣ ነገሮችን ትልቅ፣ ውስብስብና በጣም አደገኛ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ነገሩን ለመቀልበስና በተፃራሪው ለመሄድ  በጣም የምጡቅ አእምሮ ባለቤትን ዳሰሳና ብዙ ድፍረትን የሚጠይቅ  ነው፡፡” ጠ/ሚ በቢሮቸው ከተደረደሩ መጽሐፍት ውስጥ ድነገት ያነበቧትን ይህችን ጥቅስ ይመስለኛል በእራሳቸው አባባል አቀነባብረው ያቀረቡት፡፡

ጠ/ሚ እውነት ነው ለህዝብ የሚታዩበት ፊታቸው ቆዳው ጅል ነው፡፡ ትልልቅ አይኖቻቸውን ቁልጭ ቁልጭ እያደረጉ ገራገር መስለው ነው የሚታዩት፡፡ ይህ እንግዲህ የእሳቸው ምስል ክሰታ መሆኑ ነው፡፡

ጅል የሚለውን ቃል መዝገበ ቃላቱ ሲተረጉመው፣ ሞኝ ሆነ ተቂቃለ ይለዋል፣ ይህም በውሳኔ ላይ መታለልን የሚያመላክት ነው፡፡ ጠ/ሚ ጅል የሚለውን ቃልና እርቢዎቹን ለመሐበራዊ ሚዲያ አንቂዎቻቸው ሰይመውና አጠቃለው የሰጡት ነገር ነው፡፡ በዚያ ንግግራቸው የሂስ ድጋፍ(critical support) የሚሰጡቸውን ሁሉ ጨፍልቀው ተናግረዋል፡፡ በዚህም አነጋገራቸው ከእኔ ጋር ካልሆንክ ጠላቴ ነህ የሚል ኢትበሃልን ተጠቅመዋል፡፡ የእሳቸው እይታ እንደ ወያኔ ግዜ እንደነበረው ሁሉ በጥቁርና ነጭ መሃል ያለ ፍልሚያ አድርገውታል፡፡ በመሃል ያለውን ግራጫ ቀለምን ወደ ጥቁሩ ቀለም አጠቃለውታል፡፡

አንስታይን አዋቂ ጅሎች(Intelectual Fools) ያላቸው ኤይ. ኪውአቸው ከፍ ያለ ነገር ግን እኔ አዋቂ ነኝ ስለሚሉ ራሳቸው አታለው ከውድቀት ላይ የሚያረፉትን ነው፡፡

ጅል ፓስተር

ጠ/ሚ አብይ ራሰቸውን በአስታራቂነትና በመካከለኝነት በእስልምና፣ ኦርቶዶክስ ክርስትናና በፐሮቴሰታንት እምነት ውስጥ ለመግለጥ ቢሞክሩም ያው የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ናቸው፡፡ የሚገረምው ነገር ከሞስሊሞች ጋር ውይት ሲያደረጉ ሰይድናና ረሱል የሚል ቃል ይጠቀማሉ፡፡ ግን ለምን? ጌታዬ እንትና እያሉ ለምን የሱፊያ ሞስሊም ትልልቅ ሰዎች ይጠራሉ? ለምንስ ነብዩ ሞሃመድን መልክተኛው ይሏቸዋል? ይህ ነገር ፎግረህ ብላ ካልሆነ ምን ሊባል ይችላል?

ትግሬዎቹ እሳቸው ወደ ስልጣን እንደመጡ ደግፈዎቻቸው ነበሩ፡፡ መጀመሪያ ተቃውሞ ያነሱባቸው የቤተ ክህነት ሰዎች ነበሩ፡፡ ያም ደግሞ ስለ አክሱም በተናገሩት ነገር ነው፡፡ እሳቸው አክሱም ላይ መስጊድ መስራት ይችላል አሉ፡፡

ለዚያም ደግሞ ዱባይ ላይ ቤተ ክርስቲያን ተሰርቶ አይደለምን ሲሉ መለሱ፡፡ ትግሬዎቹ ከዚያ በፊት አክሱም ላይ መስጊድ ይሰራን ጥያቄ የመለሱበት አግባብ፣ ለምን መካ መዲና ላይ ቤ/ክርስቲያን እንዲሰራ አትፈቅዱም ነበር፡፡

ጠ/ሚ ይህን እውነታ ቢያውቁምና፣ የዚያኔ ይህ በተነገረበት ግዜ የስለላ መዋቅሩን መሪ ነበሩ፣ አክሱምን በዱባይ ሰፈሯት፡፡ የዚያኔ 96% ኦርቶዶክስ የሆነውና ለአፍሪካ ክርስትና አምብርት ነኝ ብሎ የሚያሰበው ትግሬውን ማሌሊት – ወያኔ በሐይማኖት ስም ቀሰቀሰው፡፡ ጠ/ሚ ያወቁ ሲመስላቸው እዚያ ላይ ነጥብ ጣሉ፡፡ ይህን አለማድረግና ሞስሊሙንም ክርስቲያኑንም ወደ ላቀ ህሊና የሚውድን ንግግር መጠቀም ይችሉ ነበር፡፡

አድብቶና አስልቶ የመስቀል አደባባይን ለኦርቶዶክስ፣ሞስሊሙና ፕሮቴሰታንቱ ሻሞ ያሉ ቀን፣ የውም ከጎኑ የኢሬቻን አደባበይ ፈቅደው፣ የይዞታ ማረጋገጫ ሲሰጡ፣ ኦርቶዶክስ እምነትን ከምንም እንደማይቆጥሯትና መጥፋቷን ነፋቂ እንደሆነ አረጋገጠ፡፡

በፕሮቴስታንት መድረክ ላይ ሲሰብኩ የምናያቸው ጠ/ሚ አብይ፣ ለብልጽግና ወንጌል ሰባኪዎች የትምህርት ቤት ይዞታ ቦታን እስከመስጠት ደርሰዋል፡፡ አሁን ደግሞ ወጣቶቹን ሰብስበው አእምሮዬነም እጄንም ንጹህ አድርጌ በመስራቴ ብሞት እንኳን ገነት ነው የምገባው እያሉ ይናገራሉ፡፡ እጅዎ በእውነት ሐይማኖት ውስጥ ገብቶ አልፈተፈተምን?

እዚያው የወጣቶቹ ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ፈጣሪንና መጥላትና ማናናቅ ለኢትዮጵያ ስኬታማ አለመሆን ጋር አገናኝተው ተናገሩ፡፡ እኚህን ጅል ፓስተር ምን እንበላቸው? እርሶ ሄደህ የተወሸቁባት ቻይና የእርስዎን እየሱስ አታውቀውም፡፡ ግና በኢኮኖሚም ሆነ በወታደራዊ አቅሟ ትልቅ ሃገር ነች፡፡ እነ ጃፓን፣ ህንድ…መጥቀስ ይቻላል፡፡

ነገር ግን ጠ/ሚ ይህን ያሉበት ምክነያት አንዳንድ ፕሮትሰታንት ጸሐፊዎች፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ለኢትዮጵያ ውድቀት ተጠያቂ አድርገው የጻፉበትን መነሻ አድርገው ነው፡፡ በእህአዲግ ግዜ አንድ በቀለ ወ/ኪዳን የሚባል ፓስተር አስታውሳለሁ ስለ ኢትዮጵያ ሪቫይቫል በጻፈበት መጽሐፉ፣ የአንድነታችን ሰባት አንዶች፣ በሚል ርእስ የካቶሊኩንም የኦርቶዶክሱንም ቤ/ክ በአወንታዊ መልኩ ጠቅሶ ጽፏል፡፡ አንድ ሌላ  መጽሐፉን ሲያሰመርቅ ሙሉ ወንጌል ቀጠና ሁለት ታዳሚ ነበርኩ፡፡ በ77 አመቴ ጌታ ሊወስደኝ ነው ብሎ ሲጸለይለት አዚያው ነበርኩ፡፡ ነገር ግን አሁን ሰማኒያ አመት አልፎት የብልጽግናን ወንጌል እያገለገለ ይገኛል፡፡

መቼም አመት በአል በደረሰ ግዜ ሁሉ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ አዝንላታለሁ፡፡ የገናውም፣የፋሲካውም…በአላት የብልጽግና ፖለቲካ ማዳመቂያ አድርገው ነው ጠ/ሚሩ የሚተርኩት፡፡ እስኪ የጠ/ሚ አብይ የመስቀል በአል ንግግር ምን እነደሚሆን ልገምት፣

የንጉስ ቆስጠንጥኒዮስ እናት ነግሰት እሌኒ ደመራውን ደምራ ብታጨሰው፣

ጭሱ ወደ ላይ ወጥቶ ወደታች ተመለሰ፡፡ እውነተኛ የሆነውን የክርስቶስ

መስቀል የተቀበረበትን ቦታም አመላከተ፡፡ ይህ በአባቶች ኢትባህል የሚነገር

ታሪክ ነው፡፡ እንደ እውነተኛው መስቀል የኢትዮጵያ ትንሳኤ የሚበሰርበት

ብልጽግና በመደመር ውስጥ የሚገኝ ስለሆነ…

መቼም ጠ/ሚ አብይ ሞስሊሞቹን ይቅርታ እየጠየቁ ሁሉ ስለክርስቶስ ፓርላማ ውስጥ የሚሰብኩት፣ በአምላካቸው ሃሴትን ሰለሚያደርጉ ነው ብዬ መገመት ይከብደኛል፡፡ ነገር ግን ዘፋኟስ ብትሆን  ”ስለማርያም ሲሉት አንጀቱ የሚራራ…” አይደል ያለችው፡፡

እሳቸውም ቢሆኑ ህዝብን ወደ እሳቸው ያቀርባል ብለው ካመኑ ዞር ዞር ብለው ሞስሊሞቹንና ፕሮቴሰታነቶቹን ካዩ በኋላ “ማሪያምን!” ከማለት አይመለሱም፡፡ አንድ ግዜ እነደውንም፣ እንደው አፋቸው ላይ መጥቶ አይመስለኝም፣ እናቴ “ማሪያምን” ካለች ወይ ፍንክች አሉን፡፡ እንዲህ ነው እንግዲህ፣ በልጅ አመካኝቶ ይበላል እንኩቶ ማለት፡፡

 

ጅላጅሉ ዶክተር

ጠ/ሚ አብይ አህመድ የዶክትሬት ጽሑፋቸውን በግጭት አፈታት ላይ እንደጻፉ ይነገራል፡፡ ካለተሳሳተኩ ሐይማኖታዊ ግጭቶች ላይ ይመስለኛል፡፡ ታዲያ ይህ ዶክትሬት እውነት ከሆነ ለምን አክሱምን የዱባይ ትይዩ መድረግ ተፈለገ?

ካይሮ ሄደው ሳለ፣ ምንም እንኳን ቁራን የቀሩ ቢሆንም አረብኛ አይችሉምና፣ አልሲሰን ተከትለው በአረብኛ የሚናገረውን እየደገሙ፣ ወላሒ፣ ወላሒ የግብጽን ጥቅም የሚነካ ነገር በአባይ ወንዝ ላይ አናደርግም ምን አሰባለቸው? ተረጓሚ ቱረጁማኑን ጠርተው ፣ ምን ይላል ማለት የአባት ነው፡፡

ኋላ ላይ ግን ቆራጥ ወታደራዊ አቋም አሳይተዋል፡፡ ያውም ኖቤል ሽለማቱን ከተቀበሉ በኋላ፡፡ እኔ እራሴ አሰዋን ግድብ ላይ ሄጄ አጥፍቼ እጠፋለሁ ነበር ያሉት፡፡ ወኔው ደስ ቢልም፣ በግጭት አፈታት ላይ ፒ.ኤች.ዲውን ከሰራ ፖለቲከኛ ይህ ንግግር አይጠበቅም፡፡ ጅላጅሉ(ሞኛ ሞኝ) ዶክተር ይሉሃል ይሄ ነው፡፡

ጠ/ሚ በጣም ጥሩ የሚባል የመናገር ችሎታ አላቸው፡፡ አንዳንዶቹ “ምላሱን ተነቅሶ ነው ቤተ መንግስት የገባው” ይሏቸዋል፡፡ እኔ ግን ከልጅነት ግዜያቸው ጀምረው እራሳቸውን ስላዘጋጁ ነው ብዬ ነው የማምነው፡፡ አለ መታደል ሆኖ ነው እንጂ፣ በፈለገበት መንገድ ይመን፣ እራሱን በእንደዚህ ደርጃ የዘጋጀ ሰው ማጣት፣ ብኩን ሆኖ ማየት ያሳዝናል፡፡

እናት ኢትዮጵያ አንድ ሰው ሳይሆን በጋራ አካፋይ የሚያምኑና አንድ ሰው የሚመራቸው ፖለቲካል ኤሊትስ ያስፈልጓታል፡፡ አማካኙን ደግሞ በብሔር ማስላት አይቻልም፡፡ ብሔርን ሐይማኖት፣ አስተሳሰብና ጾታ እንኳን ሳይቀር ዜሮ የወጡታል፡፡

ዶ/ር አብይ ደግሞ ይሄንን ሰው መሆን አልቻሉም፡፡ ቲሙ ተተምትሟል፡፡ በሁሉም ቦታ እኔ እኔ ሆኗል ነገሩ፡፡ ያደግሞ ብዙ የወዳጅ ጠላት እየፈጠረላቸው ነው፡፡ አድፍጠው እየጠበቋቸው ይገኛሉ፡፡ ያገኟቸው ግዜ ደግሞ አይኗ እንደጠፋ አይጥ በድመትኛ ይጫወቱበቸዋል፡፡

ከእናቱ መሃጸን ሲወጣ የመደመር ምልክት እነደተመለከተ ሰው ሁሉ፣ መደመር መደመር የሚለውን የግል አባዜ ትተው በጋራ አካፋ ላይ የተጠና ስብስብ አድርጎ መንገዳቸውን ቢያስተካክሉና ቲሙን ይዘው ቢጓዙ ይሻላቸው ነበር፡፡ ይሻላል ስል ታሞል መለቴ እንዳለሆነ አይታወቅልኘ፣ ምናልባትም በሞት ጣር ላይ ስላለ ነገር አያወራን ይሆናል፡፡

 

ጅላንፎው ኮረኔል

የሞነጎሉ መሪ ለነበረው ጄነጂስ ከሃንን ያማክረው የነበር አንድ ቻይናዊ እንዲህ ብሎት ነበር “መላው ቻይናን በፈረስ ላይ ሆነህ መውረር ትችላለህ፡፡ ነገር ግን እፈረስ ላይ ሆን መምራት አትችልም፡፡”

ጠ/ሚ አብይ በወታደራዊ ማዕረጋቸው ኮሎኔል ናቸው፡፡ የስራ መደባቸውም መገናኛ ነበር፡፡ጠ/ሚሩ  የወያኔ መጀመሪያ ወረራ ላይ፣ ወያኔ ከደደቢት ተነስቶ መቀሌ ለመግባት አስራ አምስት አመት የፈጀበትን  በእስራ አምስት ቀን መቀሌ መግባት ችለናል ያሉበትን ጦርነት፣ የፌድራሉ መንግስት በተሳሳተ መንገድ የገመገመው ይመስለኛል፡፡ የትግራይን ሁሉም ከተሞችን መያዝ ተችሎ ነበር ግን ታንክ ላይ ተቀምጦ መግዛት አልተቻለም፡፡

ያሁላ የጀነራሎች ሙገሳ፣ እነ ድል ቁርሱ፣ ሳተናው…ስምንት ወር ያህል እንኳን መቆየት አልተቻለም፡፡ ከዚያም ለትግራይ የጽሞና ግዜ ተሰጣት ተባለ፡፡ የሆነውና ተከትሎ የመጣው ግን አማራና አፋር ክልሎችን በከፍተኛ ሁኔታ ያወደመ ነበር፡፡

ፈረንጆቹም እነ አጼ ቦካሳን፣ ዮናስ ሳቢንቢን በተሸከሙበት ትከሻቸው ወያኔን በአንቀልባ አዘሉት፡፡ኢትዮጵያም የዲፐሎማሲ ጦርነቱን ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ አጣች፡፡ ይህ የሆነው በጠ/ሚሩ ስህተት ጭምር ነው፡፡ አሜሪካንን የአባይ ግድብ አደራዳሪ አድርገው በመጋበዛቸው፣የኦሮሚ ባለስልጣን የሆኑና የእሳቸው ቀኝ እጅ የሆኑ ሰዎች ምእራባዊያን እያወገዙ በግልጥ በመናገራቸውና በአጠቃላይ ለሚያገለግሉት ህዝብ (ብሔር) የቆሙ በመምሰል ብልህነት የጎደለውና ክህሎትን(statemanship) ያጣ አቀራረብ ለምእራባውያኑ በማሳየታቸው ነው፡፡

ዘመኑ የሚጠይቀው ነገር ቢኖር አለምንም እራስንም ሆኖ መኖር ሆኖ ሳለ በኦሮሙማው ልዋጥህ ተደበልበል መንፈስ የሚመራው ብልጽግና ይህን ለማሰተናገድ ቸግሮታል፡፡ የዚህ ፓርቲ መሪ የሆኑት ጠ/ሚ ጠላትን በማቀለልና በአዋራጅነት መንፈስ ሲጋለቡም ይታያሉ፡፡

ጀነራል አሳምነው ጽጌን በሁለት ሰዓት ከምናምን ደቂቃ ኦፕሬሽን ጸጥ አደረግነው፡፡ ወያኔን በአስራ አምስት ቀን ጠራረግነው፡፡ ኦነግ ሸኔን ከስፈለገ አንድ ሂሊኮፍተር አስነስተን እንለቅመዋለን፡፡ ከአሳምነው ፅጌና ደ/ር አምባቸው ሞት በኋላ ስንት የአማራ ክልል ፕሬዝደንቶች ተቀያየሩ፡፡ ይህ የሚያሳየው ለአምባቸው መወገጂያ ሞትን የመረጠለት ቡድን እንቅልፍ እንዳልተኛ ነው፡፡

የሚገርመው ነገር ጠ/ሚ አብይ ለሰበሰቧቸው ወጣቶች፣ ለዚያ ህልመኛ ትውልድ ቦታ እነዳትሰጡ ስልጣን የናንተ ብቻ ነው አሏቸው፡፡ ህልመኛ የሚለው ደግሞ ሽማግሌዎቹን ማለት ነው፡፡ እሳቸው እራሳቸው ግን የኢዜማውን ሽማግሌ ዶ/ር ብራሃኑና የኦነጉን ኦቦ ቀጀላን ስልጣ መስጠታቸው ተጠየቅ እነደሚያቀርብባቸው ውልም አላላቸውም፡፡ ሽማግሌዎቹን ያገለለ ፖለቲካ በተደመረ ወጣት ሊያተካኩ ሲቃትቱ ነው ያናቸው፡፡ አይ ኢትዮጵያ፣ ፖለቲካ የፍልፍል ወጣቶች ብቻ እንዲሆን ከአለም ተለይታ የተፈረደባት ሃገር፡፡

መቼም የፋኖ ነገር ያሳዝናል፡፡ መንግስት እራሱ ድረስልኝ ብሎ ከጠራው በኋላ ወደ እስር ቤት አጋዘው፡፡ ዘመነ ካሴ ጠላት ተደርጎ የተወሰደው ከሃብታሙ(ኢትዮ 360) ጋር ቃለ መጠይቅ ስላደረገ ነው፡፡ ይኸውላችው የአብይ መንግስት ግራጫውን ቀለም ረስቶታል፡፡ እንደ ወያኔ ግዜ ከእኔ ጋር ከልሆንክ ጠላቴ ነህ መርህ ላይ ተቀርቅሯል ባይ ነኝ፡፡

ለግራጫው ቀለም ማለትም በነጭና ጥቁሩ መካከል ላለው ቀለም ቦታ የማይሰጥ የመደመር አብዮት፣ የአንድ አመት እድሜ የለውም፡፡ አማካሪ የሌለው ንጉስ፣ አለ አንድ አመት አይነግስ አይደል የሚለው ተረቱ፡፡

 

ብልጽግና ቢጫ ደመና፣ ህልም እልም፣ ጉም ብትን፡፡

ከእንጦጦ ተራራ ከሽንቁሩ ሚካኤል ማዶ ስላለ ስፍራ ልንገራችሁ፣ የግመል ውለታ በመባል ይታወቃል፡፡ ነገሩ የሆነው በአፄ ኃይለስላሴ ዘመን ነው ይባላል፡፡ ሽማግሌዎቹ እንደነገሩኝ፣ ንጉሱ ከስደት መልስ በሱዳን በኩል እነ ጄነራል ዊነጌትን ይዘው ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ በግመል ላይ ተቀምጠው ነበር፡፡

ንጉሱን ብዙ ኤርትራዊያንና፣ ከጥሩመቡሌ (ተሪፖሊ፣ ሊቢያ) የመጡ ሶማሌዎች…እንግሊዞች አጅበዋቸው ነበር የመጡት፡፡ እኔ በግሌ የማውቃቸውን ሐማሴኑን ባላንባራስ አቦይ አስፋውን ልጥቀስ ፡፡ ታዲያ ንጉሱ አዲስ አበባ ሊገቡ ሲሉ ግመሎቹ ይወገዱና በፈረስ ላይ ይጫናሉ፡፡

የቱለማው ኦሮሞና የሸዋ አማራው ፈረስ ነዋ የሚያውቀው፡፡ ይህን ግዜ ሞስሊም ተከታዮቻቸው የነበሩት ግመሎቹን አርደው እነደሚሆን አንዲያደርጓቸው ትእዛዝ ተሰጠ መሰል እነደሚሆን ሆኑ፡፡ ከዚያን ግዜ ጀምሮ ያቦታ “የግመል ውለታ” ተብሎ ይታወቃል፡፡ ምነው ጠቅላያችን የፋኖን ውለታ የግመል አደረጉትሳ? ለነገሩ ዳፍንታም አይን ባይኖሮዎት አሁን ጦርነት እንደሚነሳ ቢያውቁ ኖሮ ፋኖን፣ መካላኪያን ወጊ የጥቁር ክላሽ ሌባ ብለው አይበይኑትም ነበር፡፡ በሃገሪቷ ላይ ሰለሰፈነው ጦረኝነት መንፈስም ሊነግሩን ይዳዳዎታል፡፡

እርሰዎን ያገኘሆት አቋመቢስ የኔ ስልጣን ብቻ ባይ አድርጌ ነው፡፡ በመጀመሪያው የእርስ በእርስ ጦርነት ግዜ፣ ሴችዬሽን ሩም ውስጥ  የጦረነቱ ዋና አዋጉ በመምሰል ቁጭ ብለው ታዩ፡፡ ፕሬዚደንት ኦባማ የአልቃይዳ መሪ ኦሳማ ቢላደን ሲገደለ የነበረውን ኦፕሬሽን ተመለክቷል ግን አዋጊ አልነበረም፡፡ስራውን ለጄነራሎቹ ነው የተወው፡፡ ታዲያ እርስዎ ምን ነው ሁሉ ነገር በእኔ ስር ነው የተደረገው ፐሮፓጋንዳ የተጠናወትዎት?

እናውቀለን ማን እንደነበሩ፡፡ እርስዎ እራስዎ የኦነጉ ሰው ለገሰ እንዳይገደል እኔ ለኦነግ ነግሬው ነበር ብለውናል፡፡ ቀጥሌ ደግሞ በአንዳጋቸው ጽጌ በኩል ያኔም ለአርበኞች ግንቦት ሰባት የመንግስትን ሚስጥር አሣልፈው ይሰጡ እንደነበር ሰምተናል፡፡ አበሻ ስማ ደብል ኤጀንት ሰላይ ይሉሃል ይሄ ነው፡፡ ግን ተሪፐልም ሆኖ ለወያኔ ይሰራ እንዳልነበር ማረጋገጫውነ …

አሁን ስለድርድር እየተወራ ነው፡፡ ወያኔ ጌታቸውንና ጻድቃንን ወክሏል፡፡ ሁቱም በጣም ጥሩ እንግሊዘኛ ተናጋሪዎች ናቸው፡፡ በድርድሩ ውስጥ አማራ ይወከል ሲባል የጠ/ሚ መልስ ደመቀና ተመስጌን አሉበት ነበር፡፡ እንግሊዘኛቸውስ እንዴት ይሆን? ሌላ የግሩፑ አባላት ጥሩ የይናገራሉ ብንል እንኳን የሚሆን አይደለም፡፡ ዋናው የዚህ ጦርነት ተጠቂ አማራው የት አለና ነው፡፡ ለነገሩ ጠ/ ሚ ጥሩ እንግሊዘኛ ተናጋሪ ቢሆኑ ኖሮ እራሳቸው ነበር የተባበሩበት መንግስት ላይ ሄደው ንግግር የሚያደረጉት፡፡ የኖቤል ሽልማት ግዜ አንድ ጋዜጠኛ ቀርቦ ሊጠይቃቸው ሲል በእንግሊዘኛ በደረቅና የተቆጣ በሚመስል ቶን “ምን ፈለግክ? ” ነበር ያሉት፡፡ ይህን ይዘን ነው እንግዴህ ጦርነትና ድርድ ውስጥ እምንገባው፡፡

 

ማጠቃልያ

ዘመኑ እየተቀየረ ስለሆነና ምናልባትም ትንሳኤ ሙታኑን ለኛ ከደረገልን፣ እንሆ አንድ ቀልድ ላጫውታችሁ፡፡

አንድ ግዜ አንድ ጥሩ ሰው በምድር ላይ ይኖር ነበር፡፡ ድብልቅልቅ ያለ የብሔር ማንነት ቢኖረውም በጽንፈኛ ብሔረተኞች ተገደለና ወደ ሰማይ ቤት ሄደ፡፡ እዘም እንደ ደረሰ  ሁለቱንም ስፍራዎች እንዲጎበኝ እድል ተሰጠው፡፡

መጀመሪያ ወደ ገሃናም  ተጓዘ፡፡ እዚያም  እንደደረሰ አንድ የመዋኛ ስፍራ ያያል፡፡ እዚያ ውስጥ ምድር ሳለ የሚያውቀው ሰው ይመለከታል፡፡በለው፣ግደል የሚል ጽንፈኛ ብሔርተኛ በዋናው ገንዳው ውስጥ ያያል፡፡ ሰውዬው ሁለት እርቃናቸውን የሆኑ ቆንጆ ሴቶች ከጎንና ከጎኑ አድርጎ በእጁ ልዩ ልዩ መጠጦች ይዞ ይጨፍራል፡፡

ደጉ ሰው፣ ይህ እኮ መሬት ላይ ያስገደልኝ ሰው ነው፡፡ ልክ እነደዚሁ ምድር ላይ በነበርንበት ግዜ ሚሰቶቻችንን ያሰነውር ነበር፤፤ በየቀኑ ህሊናው ሰለሚዋቀሰው አራሱን የሚሸነግለው በመጠጥ ነበር ሲል ይናገራል፡፡

ይሄኔ ያሰጎበኘው የነበረው መልአክ ቅጣቱ ይሄው ነው‹፣ እዚያ ጋር የምታያቸው ሴቶች ከታች ቀዳዳ የላቸውም፣ ጠርሙሶቹ ግን ሁሉም ቀዳዳ ናቸው፡፡

የሁለት አለም ስደተኛው የብሔር ፖለቲካ!

አስቻለው ከበደ አበበ

ሜትሮ ቫንኮቨር ካናደ

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop