September 10, 2022
10 mins read

በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት ‹‹ከኮሎኔሉ ወደ ኮሎኔሉ!!!›› ብዕረኞች እልፍ ጠመንጃን የማረኩባት ሃገር !!!

ሚሊዮን ዘአማኑኤል
ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY

coronel12

ለፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም መታሰቢያ ትሁን……ፕሮፌሰር ዛሬም የጋዜጠኞች እስራት ቀጥሎል!!! የሚጮህላቸውም ጠፋ!!!

  • ከሽህ ሳንጃ በአፈሙዝ ጠመንጃ ያዢዎች፣ አራት ሞጋች ጋዜጦች ይፈራሉ!!! “Four hostile newspapers are more to be feared than a thousand bayonets..” ―Napoleon Bonaparte
  • ብቸናው የደህንነት ዋስትናችን ነፃ ፕሬስ ብቻ ነው!!!“The only security of all is in a free press.” ―Thomas Jefferson
  • ፋሽዝም ሊያብብ የሚችለው ግልፅ ባልሆነና በጨለምተኛነት ጊዜ ነው!!! “Fascism thrives in obscurity and darkness.” ―DaShanne Stokes
  • ነፃ ፕሬስ ጥሩም መጥፎም ሊሆን ይችላል ነገርግን ያለነፃነት ነጻ ፕሬስ መጥፎ ይሆናል፡፡ “A free press can, of course, be good or bad, but, most certainly without freedom, the press will never be anything but bad.” ―Albert Camus………………….(1)

 

ከኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ‹‹ ያነበበ፣ ያስነበበ፣አዋጅ ›› ወደ ኮሎኔል አብይ አህመድ ‹‹የመደንበር ዴሞክራሲ›› ተሸጋግረናል፡፡ እንቁ   ጣጣሽ!!! እንቁ    ጣጣሽ!!!

  • ‹‹…ሃሳብን በጨዋነት የገለፀ እና ገጀራ የነቀነቀን እያነጻጸሩ “ሁለታችሁም ዕረፉ!’’ ዐይነት ምክር ቅንነት የጎደለው ነው’ና ጆሮ አትስጠው፡፡…›› ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሳምንታዊው ፍትሕ መጽሔት አዘጋጂ ሲሆን ከ2014 እስከ 2017እኤአ ከዛም 2018 እስከ 2022 እኤአ መንግስትን በሚተች ምርጥ ስራዎቹ የተነሳ በተደጋጋሚ ዘብጥያ የወረደ እውቅ ጋዜጠኛ ነው፡፡ Temesgen Desalegn is an Ethiopian journalist. As editor of the independent weekly newspaper Feteh, Desalegn went to court many times and was imprisoned from 2014–2017 as a result of his criticism of … Wikipedia
  • ‹‹አጤ ምንሊክና አማራ ለኦሮሞ ባለውለታ ናቸው እንጅ ጡት አልቆረጡም። ጡት ይቆርጡና ብልት ይሰልቡ የነበሩ ራሱ በገዳ ስርአት ውስጥ የነበሩ የኦሮሞ ጎሳዎች ናቸው።›› / tadios tantu ታዲስ ታንቱ ጋዜጠኛና ደራሲ ሲሆኑ በህወሓት ኢህአዴግ እና በኦህዴድ ብልፅግና አገዛዝ ዘመን በወህኒ ቤት በተደጋጋሚ የታሰሩ እውቅ የህዝብ ልጅ ናቸው……..(2)
  • ‹‹ጦርነቱ ኢትዮጵያን የመታደግ ሳይሆን የአብይ አህመድን ስልጣን ለመታደግ ነው፡፡ የማዝነው የአብይ አህመድን ስልጣን ለማስጠበቅ ለሚያልቀው አማራ ነው፤ የአማራ ኢሊቶች ማስብ የምትጀምሩት ስንት አማራ ሲያልቅ ይሆን!›› ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድየሮሃ ቴሌቪዝን መስራች Roha TV founder Meaza Mohammed በምታቀርባቸው የምርመራ  ከገፀምድር እስከ ከርሰ ምድር ዘጋቢ ሪፖርቶች በተደጋጋሚ ልጆን ጥላ ወህኒ ቤት የወረደች ድንቅ ጋዜጠኛ ናት፡፡
  • በኦሮሚያ ክልል ሆሮጉድሩ ወለጋ አሙሩ ወረዳ ውስጥ የሚኖሩ አንድ አርሶ አደር ሲነግሩኝ፡- የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በዚህ መጡ በዚህ ገቡ ብለን ለኦሮሚያ ክልል ልዩ ሀይል ፖሊስ ስንጠቁም‹‹ እነሱ እኮ አገራቸው ነው፡፡ ከፈለጋችሁ እናንተ ወደ አገራችሁ ሂዱ አሉን፡፡›› ……‹‹የመሳሪያ መደብር ተከፍቶ እየተሸጠ ነው!!!›› ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፡፡  ‹‹ከኢሳት አዲስ አበባ ማኔጅመንት የተሰጠ መግለጫ የመስሪያ ቤታችን ባልደረባ የነበረው ጎበዜ ሲሳይ ቤተሰብ ለመጠየቅ 4 የስራ ቀናትን አስፈቅዶ ወደ ሰሜኑ የሃገራችን ክፍል አቅንቶል፡፡ ይሁን እንጂ በስም የተጠቀሰው ጋዜጠኛ በግል የፌስቡክ አካውንቱ ሙያዊ ስነምግባርን ያልተከተሉ መረጃዎችን እያሰራጨ መሆኑን ደርሰንበታል፡፡ በመሆኑም ጋዜጠኛው በፈቃድ ላይ መሆኑን እና በግል የፌስቡክ ገፁ የሚያሰራጨው መረጃ ኢሳትን የማይወክልና የግሉ ሀሳብ መሆኑን እንድታውቁት የኢሳት ማኔጅመንት ይህንን አጭር መግለጫ ማውጣት አስፈልጎታል፡፡ ክቡራን ደንበኞቻችንም ከሃሰተኛና ካልተረጋገጡ መረጃዎች እራሳቸውን እንዲያቅቡ እናሳስባለን፡፡ በዚህ አጋጣሚ የእርሱን መረጃዎች የምትጠቀሙ ሁሉ የኢሳት ጋዜጠኛ ከማለት እንድትቆጠቡ እንጠይቃለን፡፡››

የግንቦት ሰባት ፖለቲከኞችና ኢሳት ብርሃኑ ነጋና አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ ኢህአዴግ ታስረው ህዝብ የጮኽላቸውን  ጊዜ ረስተው ዛሬ ለብልፅግና ፓርቲ ጠቆሚና አሳሪ በመሆን የዴሞክራሲን አብሪ ጥይት በማጥፋትና የነፃ ፕሬስ ነፃነትን በማፈን በታሪክ ተጠያቂ ሆነዋል፡፡ በተመሳሳይ የፕሬስ ነፃነት መታፈን እያዩ እንዳላዩ በመሆን ኢዜማ፣ አብን፣ ኦፌኮ፣ ኦነግ፣ ባልደራስ፣ የመሳሰሉት ፓርቲዎች የጥቂት ሰዎች ስብስብ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ሞግዚት ሳይሆኑ ነን እያሉ በአድርባይነት ዝምታ ውስጥ ለአመታት አሽልበዋል፡፡ የኦህዴድ ብልፅግና ፓርቲ አስራአንድ ሚሊዮን ካድሬዎች አሰማርቶ አስራሁለት ክልሎች አደራጅቶ፣ አዕላፍ ክፍለጦር አስታጥቆ፣ መላ ሀገሪቱን የጦር ሜዳ በማድረግ ለግማሽ ሚሊዮን ወጣቶች ሞት፣ ለሚሊኖች መፈናቀል እያዩ ለፃፉና ለተናገሩ የምእዬ ኢትጵያ ምርጥ ልጆችን ለእስር በመዳረግ ለህዝብ ተቆርቆሪ ጋዜጠኞችን አስረው ይገኛሉ፡፡ ‹‹ዛሬ በእኛ የተፈፀመው በደል ነገ በእናንተም መፈፀሙ አይቀሬ ነው›› እንላለን!!!በብልፅግና ፓርቲ አገዛዝ ወደ አንባገነናዊና ተረና ዘረኛ ስርዐት አገዛዝ እየተሸጋገረ መሆኑን በመካድ ለፈጸሙት አድርባይነት አንድ ቀን ተጠያቂ መሆናቸው አይቀርም እንላለን፡፡

ኢትዮጵያ ከሣህራ በታች ካሉ አፍሪካ ሃገራት ጋዜጠኞችን በማሰር ቀንደኛዋ ሃገር መሆኖን የጋዜጠኞች ተሞጋች ኮሜቴ (ሲፒጄ) አስታውቆል፡፡ ሲፒጄ መግለጫ በጥቅምት 2020እኤአ በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ጦርነት መንስዔ መሠረት በሃገሪቱ የፕሬስ መብትና ነፃነት ቀስ በቀስ ወደ ጨለማው ከርሠ-ምድር መቀመቅ እየሠረገና እየሠመጠ ሄዶል፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ በ2018 እኤአ መንበረ ስልጣናቸውን ከተቆጣጠሩ አራተኛ ዓመት የዶሞክራሲያዊ ሂደቱ በአፍጢሙ መደፋቱና የታለመው ተስፋ  እውን ሆኖል፡፡ ኢትዮጵያ ህወሓት ኢህአዴግ ዘመነ አገዛዝ ከ1991እኤአ እስከ 2018 እኤአ በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀንደኛዋ የፕሬስ ነፃነት አፋኝ አገር እንደነበረች ሲፒጄ ዘግቦል፡፡ ኢትዮጵያ ኦህዴድ ብልፅግና ዘመነ አገዛዝ ከ2018 እስከ 2022 እኤአ ጋዜጠኞችን በማሰር በዓለም አቀፍ ደረጃ ተኮንናለች፡፡

  • ‹‹Ethiopia has been cited as one of the worst jailers of journalists in sub-Saharan Africa, according to the Committee to Protect Journalists (CPJ).››………………..(3)
  • Ethiopia among worst jailers of journalists- Rights Group
  • Ethiopian Army soldiers beat up international journalist while trying to remove their …  –  Copyright © africanews AFP/AFP By Rédaction Africanews with AFP

ተፃፈ ጳጉሜ 5 ቀን 2014ዓ/ም እንቁጣጣሽ…….እንቁጣጣሽ……. መልካም እንቁጣጣሽ……የታሰሩት ጋዜጠኞች ይፈቱ!!!

 

ምንጭ

(1) Free Press Quotes (28 quotes) (goodreads.com)

(2) tadios-tantu | Amhara Fano Movement Support Site – የአማራ ፋኖ ደጋፊዎች ድህረ ገጽ (amharaonline.org)

(3) Ethiopia among worst jailers of journalists – rights group | Africanews

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop