ኢትዮጵያ እና ህዝቧ ዕዉነተኛ መሪ አስካላገኙ ጊዜ ድረስ ኢትዮጵያም ሆነ ህዝቧ በተለይም አስኳል የኢትዮጵያ ዳር ድንበር እና የዓማራ ህዝብ ከተራዘመ መከራ ፣ስደት እና ሞት መታደግ የሚያስችል ነዉ ፡፡
ለአብነት በፀረ ኢትዮጵያ እና ዓማራ ላይ ተደራጂተዉ እና በሴራ ተስማምተዉ ለሚሰሩ ጠላቶች ያደሩ መናጆ የፖለቲካ ድርጂቶች እና አመራሮች ከግማሽ ክፍለ ዘመን ተደጋጋሚ ታሪካዊ ስህተት መማር ካልቻለ መናጆ ምንም ነገር መጠበቅ ሞኝነት ነበር ፤ነዉ ፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ ዴሞክራሲ ንቅናቄ በዋነኝነት በመኃል አገር በተለይም የዓማራ ህዝብን የደም እና የህይወት ዋጋ በመርሳት ሆነ በመካድ የግንባር ቀደምትነቱ ቦታ በ1981 ዓ.ም. ለትህነግ በኢህዴግ ምስረታ ስም አሳልፎ ሰጥቷል፡፡
በክልል ምስረታም ሆነ በኢትዮ ኤርትራ መለየት ብዙሃኑን የዓማራ ህዝብ ማግለል እና እንዲሁም የዓማራ ህዝብ እና አካባቢ የክፉ እና የጠላት ቤተ ሙከራ አድርጓል፡፡
የዓማራ ህዝብ የራሱን የትዉልድ ቅየ እየተነጠቀ ለጠላት ጎጆ መስረታ ( መተከል፣ ሰሜን ጎንደር/ ወልቃይት፣ሰሜን ሸዋ….) ማዋል፣ በራሱ እና በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ኢትዮጵያዉያን /ዓማራ መፃተኛ እና ስደተኛ እንዲሆን እና በማንነቱ እንዲሳደድ እና እንዲሞት ሲደረግ መናጆች ያኔም ዛሬም አሉ ፡፡
በኢትዮጵያ ታሪክ በአደዋም ሆነ በካራ ማራ ጦር የቁርጥ ቀን ልጆች እና የዕድሜ ልክ መሪዎች እና የዘመን ዕንቁዎች እነ ዕምየ ሚኒሊክ ፣ ደጃች በላይ ዘለቀ እና እነ ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም በተፈጠሩባት እና በሞቱላት አገር ዛሬ ላይ ከህዝብ እና አገር በፊት በመከራ ጊዜ ከኋላ እና በሠላም ጊዜ ከፊት የሚበገር አመራር በመናጆነት ቀጥሏል፡፡
በኢትዮጵያ አንድነት እና በዓማራ ህዝብ ሞት እና ስደት ተጠያቂ መናጆ የፖለቲካ ተቋማት አመራር በግንባር ቀደም ተጠያቂ ሲሆን ይህን መናጆ ፖለቲካ አመራር ተስፋ አድርጎ ሲሞት ድረሱልኝ ባይ ህዝብም ካለፉት ረጂም ዓመታት በደል እና መታለል መማር አለመቻል ከተጠያቂነት የሚድን አይደለም ፡፡
የኢትዮጵያ ጀግኖች እና ቁርጥ ቀን ልጆች በደም እና በህይወት ዋጋ ነፃ አገር አስረክበዉናል ነገር ግን ዛሬም እነ ዕምየ ሚኒሊክ ፣ አፄ ቴወድሮስ ፣ ደጃች በላይ ዘለቀ ፣ ኮ/ል መንግስቱ እንዲሞቱለት የሚጠብቅ ህዝብ ዛሬም ከትናንት መማር አልቻለም ፡፡
ዛሬ በህይወት ያሉትን እነ ጀ/ል ተፈራ ፣ ኮ/ል ደመቀ ፣ ዘመነ ካሳ ፣ ማስረሻ ሰጠኝ …….. የመሳሰሉትን ኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን የህዝብ ልጆች በማሳደድ እና በማግለል ለተጠመዱ መናጆች ላይ ዕምነት መጣል ሊቀር ይገባል፡፡
ለህዝብ አንድነት እና ለአገር ሉዓላዊነት የሞቱትን እና እየኖሩ ያሉትን እያገለሉ ዘላቂ የአገር እና ህዝብ ጥቅም እና መብት እንዲጠበቅ የሚፈልግ ቀቢፀ ተስፋ አስተሳሰብ እና ይትበኃል መቆም አለበት ፡፡
ሞኝን ፪ለት ጊዜ ዕባብ በላዉ አንዴ ሳያይ ሌላ ጊዜ ሲያሳይ እንዲሉ ከዚህ ማይማር ዘላለም ሲመረዝ እና ሲደለዝ ይኖራል እና ከበድን የመናጆ ፖለተካ አስተሳሰብ መላቀቅ እና መታጠቅ ይገባል ፡፡
ከረጂም ዓመታት በፊት ዕባቦች ታላቁን የኢትዮጵያን ህዝብ ማንነት ፣ ርስት ፣ነፃነት እና ብሄራዊ አንድነት እና ኩራት የነጠቁት በሶስት አስርተ ዓመታት የሰሩትን ግፍ እና በደል በዕጥፍ አሳድገዉ በሶስት ዓመት ደጋግመዉ ሲፈፅሙበት አሜን ብሎ መቀበል እና ጥቃት መሸከም ለኢትዮጵያ እና ህዝቧ ከዘላለም ባርነት እና ዉርደት ሊያድን ስለማይችል ከማያዉቁት መላክ የሚያዉቁት ሰይጣን ብሎ ሁሉን ዓሜን ላለማለት በጠንካራ ህብረት እና አንድነት መነሳት አለበት ፡፡
ኢትዮጵያ የሚሞቱላት እና የሚኖሩላት እንጂ መናጆዎች የሚኖሩባት ምድር አለመሆኗን በተግባር እና በግንባር የሚገኙ አለኝታዎች የሚያስፈልጓት እና የሚፈለጉበት የታሪክ እና የጊዜ ጠርዝ ላይ የምንገኝ መሆኑን ከዛሬ በላይ የምንረዳበት የላቀ መልካም አጋጣሚ ሊኖር እንደማይችል የኢትዮጵያ ህዝብ እና ሁነኛ የቁርጥ ቀን የመከራ ጊዜ ፈጥኖ ደራሾች ሊገነዘቡት ይገባል ፡፡
“የየትኛዉም አገር ዕጣ ፋንታ ዕዉን የሚሆነዉ በቁርጥ ቀን የህዝብ ልጆች የህብረት ክንድ ነዉ ፡፡”
NEILOSS –Amber