September 2, 2022
7 mins read

ኢትዮጵያዊነት  ከአፋር እና ዓማራ ዉጭ አይታሰብም!  

Ethiopiawinetኢትዮጵያን ለማጥፋት በሠነድ እና በህገ -ጥፋት ስምምነት ኢትዮጵያን እና በደም እና አጥንት መስረተዉ በህይወት ዋጋ ታላቋ ኢትዮጵያን ሠርተዉ እና መስርተዉ ላቆዩን ለዘመናት ክህደት ተፈፅሞባቸዋል ፡፡

በአለፉት የጥፋት እና ሞት ዘመናት ኢትዮጵያን ለማሳነስ ፣ ህዝቡን በዕምነቱ ፣ በማንነቱ ፣ በባህሉ እና በዜግነቱ ጠላት በማድረግ ኢትዮጵያን  እና ኢትዮጵያዊነትን ከምድረ ገፅ ለመፋቅ  የዉስጥ እና ዉጭ ታሪካዊ  ጠላቶች ያልፈነቀሉት ድንጋይ ፤ያልቆረጡት ቅጠል አልነበረም የለም ፡፡

ከዓመታት በፊት ገና ኢትዮጵያን በጥዋቱ ለማፍረስ  አፍራሽ የጥፋት ኃይሎች የጥላቻ መነሻ  ኢትዮጵያዊነት እና ዓማራ ነበር ፡፡

ከሶስት አስርተ ዓመታት  በፊት ጀምሮ በመላዉ አገሪቷ የሚኖሩት ኢትዮጵያዉያን  እና ዓማራ ማሳደድ  ለአንድ ማህበረሰብ ብቻ እንደሆነ አድርጎ አገር የማጥፋት ፀረ-ኢትዮጵያ አቋም እና ሴራ ተስፋፍቶ እና ተንሰራፍቶ ለዛሬ ተደጋጋሚ ጥቃት ፣ ስደት እና ሞት ምክነያት ሆኖ ቀጥሏል፡፡

በፀረ-ኢትዮጵያ ጠላቶች ህብረት  ላለፉት ሁለት ዓመታት የመጨረሻዉን  የአጥፍቶ መጥፋት የክህደት ሴራ ዋዜማ ላይ ለሶስት ተከታታይ ጊዜ ባደረጉት ወረራ እና ምዝበራ  የኢትዮጵያን ዕምብርት የሆኑትን አፋር እና ዓማር ጥቃት የዚህ አካባቢ ጥቃት እና ጉዳት ብቻ እንደሆነ አድርጎ ማስተጋባት ለ ሠላሳ ዓመታት በኢትዮጵያዉያን ላይ የደረሰዉን ክህደት እና ሞት ማሳነስ ነዉ ፡፡

አበዉ በሽታዉን የደበቀ  መድኃኒት የለዉም እንዲሉ  በሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ በትህነግ እና ተባባሪ የጥፋት የክህደት ጌኛዎች በኢትዮጵያዉያን በተለይም በዓማራ እና አፋር ላይ የደረሰዉ ሠባዊ ፣ ቁሳዊ እና ሁለንተናዊ  ጥፋት በኢትዮጵያ ቀርቶ በዓለም የጦርነት ታሪክ ሆኖ አያዉቅም ፡፡

የዓመራን እና የአፋርን ህዝብ እና አካባቢ ላይ የደረሰዉን የሠላሳ ዓመት  ግፍ እና መከራ ማለባበስ እና ማድበስበስ ዳፋዉ እና መከራዉ የኢትዮጵያን ጥፋት  ጊዜ ማፋጠን እና የህዝቧን መከራ ዘመን ማራዘም መሆኑን በመገንዘብ የዓማራ እና አፋር ህዝብ ራሱን እና አገሩን ከህልዉና ጥፋት ለመታደግ የትኛዉንም ዓይነት የአደረጃጀት እና የአንድነት ስልት እንዲከተል ራሱን ማዘጋጀት እና ማብቃት አለበት ፡፡

ዳሩ ሲደፈር መኃሉ እንደማይከበር እየታወቀ  የኢትዮጵያን ብሄራዊ  ዉርደት እና ጥቃት በመከራ ዘመን ለአንድ አካባቢ ህዝብ   መተዉ ፤በሠላም ጊዜ የእኛ ማለት የአድርባይ አስተሳሰብ መገታት አለበት ፡፡

አስካሁን በነበረዉ የህልዉና ተጋድሎ ሠፊዉ የዓማራ እና የአፋር ህዝብ በግንባር ቀደምትነት የተሳተፉበት መሆኑ አስከታወቀ ጊዜ ድረስ ለከፈሉት እና እየከፈሉ ላለዉ  ተጋድሎ ዋጋ መስጠት እና ዕዉቅና መስጠት ያስፈልጋል ፡፡

ከህዝብ ጀርባ ሆነዉ በጭንቅ ጊዜ የሚደበቁ ፤ በሰለም ጊዜ በመከራ ለደረሰዉ ህዝብ እና የህዝብ ልጆች በማሳድ የሚያስጨንቁ ከህዝብ በፊት እስካልቆሙ ህዝቡን እና አገሪቷን ለዳግም ጥቃት እንዳይዳርጉ  ካለፈዉ ጊዜ ለማሩ እና ሊጠነቀቁ ይገባል ፡፡

የዓማራ እና የዓፋር ህዝብ ላይ ደባ የሚፈፅሙ ፀረ-ኢትዮጵያ እና ታሪካዊ ክህደት የሚፈፅሙ መሆናቸዉ  ከግማሽ ክ/ዘመን ያላነሰ ዕድሜ ማስቆጠራቸዉ በህዝብ እና በአገር ላይ ያደረሱት  መጠነ ሰፊ  የአገር ክህደት እና የዘር ፍጂት መኖሩ እየተረሳ እና እየተካደ  የአገር ጉዳይን የአንድ አካባቢ ህዝብ ጉዳይ ማድረግ የትምየሚያደርስ አይሆንም ፡፡

ምንም እንኳ የሁለቱ ህዝቦች በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ጉዳይ የዓመታት የመከራ ገፈት እና የጭቆና ቀንበር ቢሸከሙም በራሳቸዉ እና በአገራቸዉ ጉዳይ ዛሬም እንደትናንቱ በጋለ ብሄራዊ ወኔ እና በጥልቅ አገራዊ ፍቅር በሁሉም ጠላቶች እና ተባባሪዎች ላይ የማያዳግም ርምጃ ለመዉሰድ የአንድነት እና ህብረት ክንዳቸዉ አይዝልም ፡፡

አገሩን የሚወድ እና ራሱን የማይክድ ሁሉ የኢትዮጵያ ዳር ድንበር እና የኢትዮጵያዉያንን ክብር የሚያዋርድ ሁሉ ከዉስጥም ይሁን ከዉጭ ፤ ከሩቅም ይሁን ከቅርብ ……..የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ታሪካዊ ጠላት እንደመሆኑ በየትኛዉም የኢትዮጵያ ሉዓላዊ የግዛት አንድነት እና የዜጎች የመኖር ደህንነት ስጋት የሚሆን ሁሉ ፀረ- ኢትዮጵያ  የሆነ የኢትዮጵያ እና ዜጎች ጠላት መሆኑ በግልጥ ሊሰመርበት እና ሊተኮርበት ይገባል ፡፡

በአገር ጉዳይ ላይ የሚሸከረከር  የዘመናት  ጠላትነት  የአንድ አካባቢ ህዝብ እና የተቃራኒ ጎራ ጉዳይ አድርጎ ማየት ሆነ ማስተጋባት ከችግር አዙሪት አያወጣም እና መቆም አለበት ፡፡

NEILOSS- Amber!

 

“ኢትዮጵያእና ኢትዮጵያዊነት ለዘላም ይኑር ! ”

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop