አሁን፣ አማራጭ የሌለው የአማራና የኢትዮጵያ ሕዝብ እጣ ፈንታ፣ ነጻነትን “በሕዝባዊ አመጽ” ማስከበር ብቻ ነው።
የአማራን ሕዝብ አፋኙ ፍሽስታዊና አምባገነናዊ የኦህዴድ ብልጽግና በሕዝብ ትግል ይደመሰሳል።
የኦህዴድ ብልጽግና ዛሬ በአማራ ብሄር ላይ የሚያደርገውን የጥፋት ዘመቻ ነገ ደግሞ ብሁክሉም ብሄሮች ላይ ያካሂደዋል። እያካሄደም ነው። ወንጀለኛ እስር ቤት እንጂ መንግሥት ሊሆን አይችልም።
#PutCriminalsInJail_NotInGovernment
ለአስተማማኝ ህልውና፣ ሰላምና እድገት አማራ የራሱን እድል በራሱ የሚወስንበት ምዕራፍ ላይ ደርሷል።
የአቢይ አህመድ የኦህዴድ ብልጽግና ፓርቲ፣ የመከላከያ ሠራዊታችን ላይ የሲኖ ትራክ የነዳውን የአማራንና የአፋርን ክልል ከወረራና ከዘረፋ ወንበዴ ጋር ድርድር ገጥሟል። ለምን ቢሉ፣ ወያኔ እስከ አፍንጫው ድረስ ሰለታጠቀና (ባለ አፈመዝ መሆኑ) ይህን የፈረደበትን የትግራይን ሕዝብ ደግሞ አስገድዶ ከጀርባው እንዲቆም በማድረጉ ነው። ነገም የአማራን ሕዝብ ከወለጋና ከመተከል ለአራት ዓመታት ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በግፍ ሲጨፈጭፉና ሲያፈናቅሉ ከነበሩት ወንበዴዎች ጋር እንደራደር ማለቱ አይቀርም። አሁንም ለምን ቢባል፣ አፈሙዝ ስለታጠቁ ነው። ዋናው ቁም ነገር፣ ከወያኔም ሆነ ከሸኔ አሸባሬዎች ጋር ድርድር ያስፈለገው የአቢይ አህመድ ኦህዴድ ብልጽግና በአፈመዝ ለማሸነፍ አቅም ስለሌለው ብቻ ነው። ስለዚህ፣ ወያኔ የአቢይ አህመድ የኦህዴድ ብልጽግና ለአራት ዓመታት ድርሽ ባላለባት መቀለ ተቀምጦ የድረድሩን ቅድመ ሁኔታ በመሪነት እየመራ ይገኛል።
ታድያ፣ 40 ሚልዮን የሚሆነው፣ መንግሥት አለኝ የሚለውና ሕግ አክባሪው የአማራ ሕዝብ (ከአማራ ክልል ውጭ ያለውን 10 ሚልዮን የሚጠጋ የአማራ ሕዝብ ሳይጨምር። ይህ ቁጥር እንዳየታወቅ የአንድ ሳንቲም ግልባጭ የሆኑት ኢሃዴግም ሆነ ብልጽግና የሕዝብ ቆጠራ በየምክንያቱ እያሳበቡ ማግድረግ አይፈልጉም። አማራውን ገድለው እስኪጨርሱ ድረስ) ነጋም ጠባም የሚጨፈጨፈው፣ የሚፈናቀለውና የሚታፈነው ስላለተደራጀና ነፍጥ ስላልታጠቀ አይደል? ያኔ በጄኔራል አሳምነው ጊዜ፣ አማራ ገና መታጠቅ ሲጀምር (ወያኔ እስካፍንጫው ድረስ ታጥቆና እስከ 500 ሺህ ጦረኛ አለኝ እያለ በገሃድ በሚደነፋበት ወቅት) አቢይና የኦህዴድ ብልጽግና ባቀናጁት ሴራ በፍጥነት አኮላሽተውታል። ታድያ እንዳይታጠቅና እንዳይደራጅ የተፈረደበት አማራ በአምስት ወራቶች የወያኔ ወረራ ጊዜ ሲገደል፣ ሰደፈር፣ ሲዘረፍ፣ ንብረቱ ሲወድም፣ የጤናና የኢንደስትሪ ተቋማት ሲደመሰሱ ወደኋላ ሰፈረጥጥ የነበረው የአቢይ አህመድ የኦህዴድ ብልጽግና፣ ዛሬ የአማራ ፋኖ (ሕዝብ) ህልውናውን ለማስከበር ነፍጥ ሲታጠቅ፣ ከአሸባሪ አባቱና ከአሸባሪ ታናሽ ወንድሙ ጋር ገጥሞ የአማራን ሕዝብ ለማፈንና ለማንበርከክ “ሕግ ማስከበር” በተባለ ሲራ እየተሯሯጠ ይገኛል። አሁንስ ቢሆን የአማራ ክልል ወረዳዎች በወያኔ ቁጥጥር ሥር አይደሉም እንዴ? ታድያ ተላለኪው ብአዴንም ሆነ የኦህዴድ ብልጽግና ለምን “የሕግ ማስከበር” እርምጃ ወራሪውና ገዳይ ወያኔ ላይ ለመውስውድ ፈሩ? ዋናው ጠላት አማራ (ፍኖ) በመሆኑ?
ለዚህ፣ የአቢይ አህመድ የኦህዴድ ብልጽግና ላለው የአማራ ሕዝብ ንቀትና ጥላቻ፣ የተቀናጀና ነፍጥ የታጠቀ ሕዝባዊ አመጽ ብቻ ነው። የአማራ ሰፊና ታላቅ ሕዝብ መንግሥት ያለ መስሎት፣ ፍርድ ያለ መስሎት፣ መሪዎች ያሉት መስሎት፣ ከነገ ዛሬ ይሻላል በማለት በትግስት እስካሁን የደረሰበትን ጭካኔና በደል በቆሰለው ትከሻው ላይ ተሸክሞ ቆይቷል።
አሁን፣ አማራ ከኢትዮጵያውነቱ በፊት በአማራነቱ እራሱን አስከብሮ ለመኖር ቆርጧል። በአማራነቱ መኖር ካልቻለ ኢትዮጵያዊነት ህልም/ምኞት መሆኑን ተረድቶታል። ማንኛውም ኢትዮጵያ ወስጥ ያለ ብሄር እራሱን በራሱ ማስተዳዳደር እንዳለበት ሁሉ፣ ለአማራ ሕዝብ እራሱ እንጂ ማንም ብሄር መሪዎቹን ሊመርጥለት አይችልም። አማራ ለራሱ ክልል እንጂ የማንም ተላላኪና ጉዳይ አስፈጻሚ አይደለም። አማራ የየትኛውም የክልል ሕዝብ በማንኛውም ጉልበተኛና ባለጊዜ ነኝ በሚል የክልል መንግሥት ጭቆናና አድልዎ እንዲደርስበት አይፈቅድም፣ አይደግፍም። የአማራ ሕዝብ፣ ይህ በግልጽና በመርህ ተደግፎ አሁን የሚካሄድበትን የህልውና ማጥፋት ዘመቻ በፍጥነት እልባት ካላገኘ፣ ህልውናውን ጠብቆ፣ ከትውልድ እስከ ትወልድ በሰላም ለመኖር እንዲችል፣ የራሱን ሐገር መንግሥት መመስረት ቅድሚያ አማራጩ መሆን እንዳለበት ተገንዝቧል። ስለዚህ፣ ከ40 ሚልዮን ሕዝባዊ አመጽ ካቀጣጠለና ህልውናውን ለማስከበር ከታጠቀ ሕዝብ ጋር ከመሸ ብኋላ ከመደራደር ይልቅ፣ አፈናው ይቁም። የታፈኑት በአስቸኳይ ይፈቱ። ፋኖ የአማራ ሕዝብ ነው። የታሰሩት በሙሉ ይፈቱ። ፋኖ የአማራ ሕዝብ በመሆኑ ብሎ “የተደራጀ ሃይል” የሚባል ሥም የለውም፣ ሊኖረውም አይችልም። የአማራ ሕዝብ (ሴቱም፣ ወንዱም፣ ሽማግሌውም፣ ሼኩም፣ ቄሱም) አብሮ ህልውናውንና ሐገሩን የሚጠብቅበት ዘይቤ ነው። ይህንን የማያውቅ መሪ ባንዳ ካልሆነ በቀር ሌላ ሥም የለውም። የአማራ ልዩ ሃይል አባልና መሪዎቹም በአሰቸኳይ ይፈቱ። የሕዝቡ ዋልታና ጠባቂዎች ናቸው።
የአማራ ሕዝብ መሪዎች ነን የምትሉ፣ የኦህዴድ ብልጽግና ሹሞች ግን ቆም ብላችሁ አስቡ። ለራሳችሁ ሳይሆን ለልጆቻችሁ፣ ለቤተሰቦቻችሁና ለዘመዶቻችሁ። ዛሬ ታልፋለች። ትላንት እንደአቡነ ጴጥሮስ የተሰዋው ጄኔራል አሳምነው ጽጌ፣ ሥጋው ሞተ እንጂ ከትንሽ ሳምንታት በኋላ የትውልድ አርበኛና (ፍኖ) የአማራ ሕዝብ ኩራት ሆኗል። ፈሪና ባንዳ የአማራ ሕዝብ አረም ነው። ሥጋውም ሥሙም የሞተ ቀን አብሮ ይቀበራል። ዛሬ የአሳምነው ጽጌን ፈለግ ያነግቡ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የአማራ ወጣቶች በየከተማው ተሰማርተዋል። በሚልዮን የሚቆጠሩ ትናንሽ ፋኖዎችም በየመንደሩ በቅለው የአሳምነው ጽጌን ገድል ለመድገም ጊዜያቸውን እየጠበቁ ነው። “ያንቀላፋህ ካለህ ንቃ”። “የት ይደርሳሉ” ብለህ አትዘናጋ። ሕዝብ አይናቅም። የጊዜ ጉዳይ ነው። ትግሉ ተቀጣጥሏል። የአማራ ሕዝብ በቁርጥ ልጆቹ ጠላቶቹን ደምስሶ ሕልውናውን ያስከብራል።
የአቢይ አህመድ የኦህዴድ ብልጽግና ቁማር።
የዛሬ ወር አካባቢ ጄነራል ጻድቃን ገ/ተንሳይ በግልጽ ነግሮን ነበር። “ከአቢይ መንግሥት ጋር ድርድር ኢያደረግን ነው። ብርሃኑ ጁላ ስለ ኤርትርና ስለ አማራ ፍኖና ልዩ ሃይል አታስቡ በቀላሉ እናጠራላችኋለን” ብሎ ነግሮናል በማለት የድርድሩን አንደኛ ሚስጢር ለሰበሰባቸው ወታደሮቹ በኩራት ተናግሮ ነበር።
አሁን ይህ የጻድቃን ሚስጥር እውን ሆኗል። ምዕራባውያን የራሳቸውን ሀገር ጥቅም ለማሟላት፣ ታዛዥና አጎብዳጅ የእንደራሴ መግሥት ኢትዮጵያ ውስጥ መመሥረትና በአፍሪካ ውስጥ ተሰሚነትን ማስፋፋት ቀዳሚ አላማቸው ነው። ስለዚህ ለኦህዴድ ብልጽግና ዳጎስ ያለ የኢኮኖሚና የልማት እርዳታ በማድረግ (በምጽዋት የሚኖር ለማኝ ስለሆነ)፣ ጻድቃን እንዳለው ከወያኔ ጋር ለድርድር አሰልፈውታል። ለዚህም ማረጋገጫ የሰሙኑ የ$300 ሚልዮን ዶላር ቀብዲ እንደምሳሌ ሊቆጠር ይችላል።
የትላንቷ የአቢይ ወዳጅ ኤርትራ።
ምዕራባውያን የኤርትራን መንግሥት ለመጣል (Regime Change) ይፈልጋሉ። አንደኛው የምዕራባውያን አጀንዳ ኢትዮጵያ የባህር በር እንድትከፍት አለም አቀፍ (በተባበሩት መንግሥታት በኩል) እውቅና መስጠት ነው። ይህ ሁለት ጠቀሜታ አለው። የመጀመሪያው ኤርትራ ለብቻዋ ይዛ ከቻይናና ከራሺያ ጋር ከምትደራደርበት ቀይ ባህር፣ አሰብን ቆርጦ በኢትዮጵያ ሥር ማድረግና ለአሜሪካ የጦር ሰፈር መገንቢያ ማመቻቸት ነው። ሌላው ደግሞ፣ ምዕራባወያን ለበኩር ልጃቸው ለወያኔ ወልቃይት እንዲሰጠው ካደረጉ በኋላ፣ በሱዳን በኩል ከፍተኛ የጦር መሳሪያ እንዲያስገባ ተደርጎ፣ በቀድሞው ማኒፌስቶው ላይ እንዳሰፈረው ሁሉ፣ በአፋር በኩል (በቅርቡ በተከታታይ እየወረረ የሎጂስቲክ ቅድመ ሁኔታዎችን የሚለማመድባቸው ወረዳዎች) አሁን በኢትዮጵያ ሥም እንዲገኝ የታሰበውን አሰብ በመቆጣጠር “ታላቋን የትግራይ መንግሥት” ማወጅና ከዚያም መገንጠክል ነው። ስለዚህ የኦህዴድ ብልጽግናም፣ በምዕራባውያኑ ቃል ኪዳን መሰረት፣ ይህንን የባህር ወደብ ጥያቄ አጀንዳ በኦፊሴል ባለፉት ሁለት ሳምንቶች ማራመዱን ጀምሯል። ኢርትራን የማጽዳት ዘመቻ “ወርቅ ላበደረ ጠጠር”።
አማራን የማጽዳት ዘመቻ።
ለወያኔ መመለስ ቅድመ ሁኔታ ለማመቻቸት፣ የኦህዴድ ብልጽግና አማራውን የማጽዳት ዘመቻውን በይፋና በስፋት ጀምሯል። የአማራ ሕዝብ በአሁኑ ወቅት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል። ዙርያውን በጠላቶቹ ተካቧል። ህልውናውን ለማዳን በመደራጀት ላይ ያሉት የበኩር ልጆቹ እየታፈኑና እየተረሸኑ ነው። አፈሳውና ጭፍጨፋው ተጠናክሯል።
የኦህዴድ ብልጽግና ክህደት
በመጀመሪያው ምዕራፍ፣ ወያኔ እስታሊን “መብረቃዊ” ያለውን ጥቃት አካሂዶ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ሊያንበረክክ ሲሯሯጥ፣ የአቢይና አህመድና የኦግዴድ ብልጽግና ከመጥፋት የዳነው በኤርትራ፣ በአማራ ልዩ ሀይልና በፋኖ እርብርቦሽና ጀግንነት ነው። ኤርትራ እራቁታቸውን የመጡትን ወታደሮቻችንን አልብሶ፣ መሳሪያ አስታጥቆ መልሶ ላካቸው። የአማራ ልዩ ሀይልና ፋኖ ከአፋርና ከተረፈው የመከላከያ ሰራዊት ጋር ሆነው ጠላትን መቀለ ድረስ አሯሩጠው መቱልህ። እነዚህ ጀግኞች ለኦህዴድ ብልጽግና አዲስ ህይዋት ሰጡ። በሰራህው አሳፋሪ የጦርነት ስህተት የተነሳ፣ እንደዱቄት በትኜዋለሁ ያልከው ጠላትህ ተመልሶ እስከ ደብረ ሲና ድረስ አሯሩጦ ለአምስት ወራቶች አዳሸቀህ። በሁለተኛው ምዕራፍም ቢሆን አሁንም የአማራ ልዩ ሀይልና ፋኖ ከአፋር ድሮኖች ጋር ከመከላከያ ጎን ተሰልፈው ለአቢይና ለኦህዴድ ብልጽግና ሁለተኛ ህይወት ዘሩ። በዚህ ዘመቻ ላይ የዳያስፖራውም አክቲቪስቶች ከአቢይና ከኦህዴድ ብልጽግና ጎን ተሰልፈው ነበር። አቢይ አህመድ ግን፣ ያለፈው ሳይበቃው በድጋሜ፣ በራሱ ጀግንነት ብቻ ድሉን እንዳገኘህው ቆጠረው። እስከ ደብረሲና ድረስ እየሸሹ የመጡት ጄኒራሎች ሲሸለሙና ሲሾሙ፣ ጀብድ የሰራው ልዩ ሃይልና ፋኖ ተካደ። አቢይ አህመድ ከአንድም ሁልቴ ህይወታቸውን የሰጡህን ባለውለትዎች ከዳሃቸው።
ለአራት ዓመታት የኦህዴድ ብልጽግና አራት ኪሎ ከገባ ጀምሮ በገሃድ የዘር እልቂት (ጄኖሳይድ) የተካሄደበትና ከምድር እንዲጠፋ የተፈረደበት የአማራ ሕዝብ፣ ዛሬ ከአብራኩ የወጡት አንጡራ ልጆቹ ሊታደጉትና ህልውናወን ሊጠብቁለት መደራጀት ሲጀምሩ፣ ለዓመታት ቁጭ ብሎ እልቂቱ ከቀን ወደ ቀን፣ ከወር እስከ ወር፣ ከዓመት እስከ ዓመት እየተባባሰ እያየና እየተባበረ ያስፈጀ መንግሥት፣ አሁን በገሃድ የአማራ ሕዝብን እልቂት (ጄኖሳይዱን) ለማፋጠን ይባስ ብሎ ግልጽ ወረራውን ጭፍጨፋውን ጀምሯል።
ይህ የኦህዴድ ብልጽግና ክህደት ልክ አጥቷል። ሁለት ህይወት የሰጠህን የአማራ ፋኖና ልዩ ሀይል በገሃድ እያፈንክ መግደልና ማሰር ጀምረሃል። የአማራን ልዩ ሀይል መኮንኖችና ጀግናውን ጄኔራል ተፈራ ማሞን፣ መሸለም ቀርቶ፣ ያለ እፍረት ወህኒ ከተሃል። በኢትዮጵያ ውስጥ የታወቁትን ጋዜጠኞችና ማሕረሰብ አንቂዎች በሞላ ሰብሰበህ ወደከርቸሌ ወርወረሃል። በሁለት ሳምንታት ብቻ ያሰርካቸው አሥር ሺህ ሊጠጉ ደርሰዋል። ነገር ግን ባሰርካቸው ልክ በሺዎችና በመቶሺዎች ተባዝቶ የሀገር አንቂዎችና ጠበቆች በፍጥነት መተካት ይጀምራሉ። አብዮቱ የሕዝብ አመጽ ይፋጠናል። የፋሽስታዊና የአምባገነናዊ መንግሥት እርካብና መንበር፣ በሰፊው ሕዝብ አብዮት ይሰበራል።
ለነጻነት የመረረ ትግል ያስፈልጋል። አሁን የአማራ ሕዝብ “ለነጻነቱ ህይወቱን መገበር ያለበት ወቅት ነው”። አማራ በክብር እንጂ በባርነት የሚኖር ትውልድ ሆኖም አያውቅም ወደፊትም አይሆንም።
ዳያስፖራው “ኢትዮጵያን ለማዳን” በሚል ሰበብ ሳያውቀው በኦህዴድ ብልጽግና የሚበላው ቁማር።
ችግሩ ይህንን አማራን እያሳደደ የሚያስጨፈጭፍ መንግሥት “ኢትዮጵያን ለመታደግ” በሚል ሰበብ በውጭ ያለው ዳያስፖራ ከኦህዴድ ብልጽግና ጎን መሰለፉ ነው። በጣም ትልቅ ቁጥር ያለው የአማራ ዳያስፖራ በገንዘብም፣ በዲፕሎማሲም፣ በጽሁፍም “ኢትዮጵያን ለማዳን” በሚል መርሆ ተታሎ፣ ይህን የአማራን ሕዝብ በገሃድ ለማጥፋት የተሰለፈውን የኦህዴድ ብልጽግና እየደገፈ ነው። በተለያዩ የዳያስፖራ ድርጅቶች ሥር በዚህ ሥራ የሚሳቱፍትን በውጭ ሐገር ይሚኖሩ አማራዎችን ጠጋ ብሎ መመልከቱ ይበቃል። ለምንድነው ይህ ሁሉ ዳያስፖራ አማራ “በሆዱ እያወቀ እንዳላወቀ” በመሆን “ኢትዮጵያን ለመታደግ” በሚል ስንኩል ወጥመድ ታስሮ ወገኑን የሚያስጨርሰው? በሞኝነት? ለስልጣን? ለገንዘብ? HR660 እንዲያልቅ ለተፈረደበትና ቀዬው ድረስ ለሚጨፈጨፈው የአማራ ሕዝብ ምንድነው? ይልቁንም የኦህዴድን ብልጽግና በንዋይም ሆነ በመሳሪያ ለማጠናከር ይረዳል እንጂ። በአሁኑ ሰዓት የሚደረገውን የአማራ ግልጽ ጭፍጨፋ አይንህ እያየ፣ ጆሮህ እየሰማ፣ ልብህ እያወቀ፣ በ “ኢትዮጵያን ለመታደግ” ሥም የኦህዴድ ደጋፊነትህን የምትቀጥል ዳያስፖራ አማራ “ከጠላትም የባስክ መሰሪና ወገንህን አስገዳይ ነህ”። የኦህዴድ ብልጽግና ክዶሃል። ፋኖን (ህዝብን) እየገደላነ እያፈነ ነው። አላመንከውም እንጂ ሽመልስ አብዲሳ ያዛሬ ሁለት ዓመት ነግሮሃል “እስከ ባህዳር ድረስ ተመላልሰን ቁማሩን በልተናል። በያለበት ክልል ዲሞግራፊን እንለውጣለን። እኛ የምንመራው ሌላው ደግሞ ተላላኪ ይሚሆንበትን መንግሥት እንመሰርታለን። ኢትዮጵያን እንድምንፈልገው አድረገን ጠፍጥፈን እንሰራታለን። ላሚቷም ወደክልልላችን ገብታለች” ።
ዳያስፕራውም ተሸውዷል። ልትሰበርና ልትንኮታኮት በደረስክ ጊዜ፣ ዳያስፖራው በገንዘቡና ባካሄደው ታላቅ የዲፕሎማሲ፣ ቃQየትዊተርና የፌስቡክ “ኢትዮጵያን ለማዳን” በሚል ዘመቻ ምዕራባወያን ከቃጡብህ ታላቅ ጥፋት አድኖሃል። አሁንም በዚሁ “ኢትዮጵያን ለማዳን” በሚል ስንኩል ዘይቤ አንዳንዶቹ ያንተንው የአምባገነንና የፋሺስት ሥርዐት በማገዝ ይገኛሉ።
ውሸትህና ጥጋብህ ልክ አጥቷል። ጭካኔህ መጠን የለውም። አንተ መንበርና እርካቡን በተቆጣጠርክባቸው አራት ዓመታት ብቻ በወለጋና በመተከል የተጨፈጨፈው የአማራ ብሄር በሺዎች ይቆጠራል። የተፈናቀለው ደግሞ በመቶ ሺዎች ይገመታል። በአራት አመታት ይህን ያህል ጭፍጨፍ በአማራ ብሄር ላይ ሲካሄድ፣ አንዴም የሕግ ማስከበር ዘመቻ ወስደህ አታወቅም። እንኳን የሕግ ማስከበር፣ በአንድ ቀን ብቻ ከሁለት መቶ አማራዎች፣ ታይቶ በማይታወቅ ጭካኔ ሲጨፈጨፉ፣ እንደ ሕዝብ መሪ የሃዘን መግለጫ እንኳን አልሰጠህም። የጭካኔህን ጥግ ለማሳየት ግን ስንዴ እርሻ ወይንም ፓርክ ትጎበኛለህ። ዛሬ ታድያ ሁለት ጊዜ ነፍሰህን ያተረፈውን የአማራ ልዩ ሃይልና ፋኖ፣ በሕዝብም ሆነ ባንተ ላይ አንዲት ጥይት ሳይተኩስ፣ ለአማራ ሕዝብ ህልውና በመቆሙ ብቻ “ሕግ ማስከበር” በሚል ሴራ በገሃድ መጨፍጨፍ ጀምረሃል።
ወደ ላይ ስትወጣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከውስጥም ከውጭም (ዳያስፖራው) መሰላል ሆነውልህ ነበር። ልብ በል፣ ይህ የወጣህበት መሰላል ከታችህ አሁን መንሸራተት ጀምሯል። ማንም አምባገነን፣ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ፣ መንኮታኮቱ አይቀሬ ነው። ያንተ ደግሞ ጊዜ አይወስድም፣ እያፋጠንከው ነው። ገና በለጋነትህ ሕዝቡ አንቅሮ ተፍቶሃል። በቋፍ ላይ ነው ያለህው።
ድል ለአማራና ለኢትዮጵያ ሕዝብ።
የማንም ብሄር ሕዝብ፣ በቁጥር በዛም አነሰም፣ ለማንም ብሄር ተላላኪ አይሆንም።
ደረጀ አያኖ