ት-ኢኮኖሚ/ET- ECONOMY
(ክፍል ሦስት)
ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ)
ከ1928 አስከ 1933ዓ/ም በጣልያን ፋሽስቶች ወረራ ዘመን በኢትዮጵያ ‹‹መሬቱ ውኌው ተመረዞ ነበር፣ የተማሩ ኢትዮጵያኖች ከአራቱ ሦስቱ ተገደለው ነበር፣ እናም ንጉሱ አሁን በሃገረ- መንግሥት ግንባታ (State Bulding) ተግባር ላይ ይገኙ ነበር፡፡ ቀ.ኃ.ሥ. በሁለተኛ የዓለም ጦርነት ኢትዮጵያን ለደገፉ ወዳጆች እንደተናገሩት ‹‹እውነተኛ ጎደኛ የሚፈተነው በውድቀታችንና በከባድ ፈተና ውስጥ ሆነን ነው፣ ወዳጃችንንና ጠላታችንን የምንለይበት ፈታኝ ጊዜ ውስጥ ሆነን ነው፡፡ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ አሜሪካኖች በተለይም ጥቁር አሜሪካኖች ላደረጉልን ውለታ፣ ላበረከቱልን አስፈላጊውን ድጋፍና የፖለቲካ ቅስቀሳ ሥራን ሳንጠቅስ ማለፍ አንችልም፡፡›› በ1948 እኤአ ግርማዊ ቀ.ኃ. ሥ. ጥቁር አሜሪካዎቹ ላበረከቱት ውለታ ሻሸመኔ ውስጥ አምስት ጋሻ መሬት የኢትዮጵያ ዓለም ፊዴሬሽን አንዲያስተዳድረው መሬቱን አበረከቱ፡፡ አስታውሱ፣ጣሊያኖች ኢትዮጵያን በወረሩ ጊዜ ከአፍሪካ የመጨረሻዋ ነፃ ሃገርና በአፍሪካ ያልተሸነፈች ሃገር ነበረች፡፡ ኢትዮጵያኖች ተሸንፈው ቢሆን ኖሮ፣ በአፍሪካ ነፃ የወጡ አገራቶች ዛሬ አይኖሩም ነበር፡፡›› ሳሊቪያ ፓንክረስት
“The land and waters had been poisoned, three out of four educated Ethiopians were killed, and the Emperor now had the task of rebuilding his nation. Commenting on the support given to Ethiopia during the war, HIM Haile Selassie said, “ As it turns out, a genuine friend is tested in times of crisis, and the heavy challenge We encountered has enabled Us to distinguish between a friend and foe. We cannot afford passing without mentioning the substantial support and political agitation which millions of Americans, particularly Black Americans, have made.”
Thus, as a reward for their support in 1948 HIM Haile Selassie I granted 5 gashas of land in Shashemane to be administered through the Ethiopian World Federation, Incorporated.
REMEMBER, WHEN THE ITALIANS INVADED ETHIOPIA WAS THE LAST FREE, INDEPENDENT AND UNCONQUERED NATION IN AFRICA. HAD THE ETHIOPIANS BEEN DEFEATED, THERE WOULD BE NO INDEPENDENT AFRICA TODAY.”……..(1) Sylvia Pankhurst: Citizen of the World
- ‹‹ክብርናኩራታችን የለም ከንጉሱ ጀምሮ፣ በተወሰነ ደረጃ የቀረው ኤርትራ ውስጥ ነው፡፡ኢሳያስ በእርዳታችሁ በምናችሁም እንደዚህ አንገዛም አትገዙንም፡፡ አልፈልግም ብሎ እራሱን ነፃ አድርጎ፣ እሱንም እንደዚህ ስቃይ የሚያበሉት ትዕቢት ነው፣ እንዴት የእኛ አሽከረ አልሆነም፣ እንዴት የእኛ ታዛዢ አልሆነም ለምን ለዶለር አልስገደም ነው፡፡…አንድ ጥቁር ክብሩን ኩራቱን ይዞ አለሁ፣ ከእናተው እኩል ሰው ነኝ፣ብሎ ፊት ለፊት ትክክል ዓይናቸውን የሚያይ ሰው አይፈልጉም፡፡ ይሄ ነው የእሱ ችግሩ አንዱ፣ በዚህ ላይ ወያኔ ተጨመረለት የሚያሳጣ!!!›› (Professor Mesfin Woldemariam on President Isaias Afeworki – BRANA PRESS)
- ‹‹ኢሳያስከመለስ ዜናዊ የበለጠ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡›› ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም
- “ወያኔንምጃዋርንም ያባለገዉ አብይ ነዉ!”|ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም | Professor Mesfin Weldemariam | Ethiopia.YouTube
- ‹‹ብዙ ሰው ያልተረዳውና የመያስደንቀው የአሜሪካ ዶላርና የአሜሪካ ጫና ኤርትራን ማንበርከክ አለመቻሉ ነው፡፡…ሎሌ ሆኖ ጌታ ከመምሰል፣ደሃ ሆኖ መከበር ይሻላል፡፡›› ፕ/ርመስፍን ወልደማርያም
- ‹‹ይህ ሁሉ የሚሆነው ባለተራ ነን የሚሉ ስለነገሡ ነው›› ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ
- ‹‹የቌንቌው ውዝግብ መነሻው ጥላቻ ብቻ ወይስ አገር የማፈረስ አካል?›› ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ
አዲስ የጅኦ-ፖለቲካል ውልድ እያበበ መምጣት በቀጠናው ተለዋዋጭ ሁኔታ መከሰት ታሪካዊ ሂደትና የሚና ሽግግር በኢትዮጵያና በሱዳን ዋነኛ የቀጠናው የፖለቲካ ተለዋዋጭና ተቀያያሪ ሁኔታ በትውልዱ ስር ተካቶል፡፡ አሜሪካ ሱዳንን ከሽብርተኛነት ሊስት በመሰረዝ አዲስ አጋር ሃገር ሆናለች፡፡ የመካከለኛ ምስራቅ አገሮች በአፍሪካ ቀንድ አገሮች የፖለቲካ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ፡፡ የሁለቱ ልዕለ ኃያላን ሃገሮች በአፍሪካ ቀንድ አገሮች ጣልቃ መግባት ራሽያ በኤርትራ እንዲሁም አሜሪካ በኢትዮጵያ እጃቸውን ማስገባት በቀጠናው የማያባራ ጦርነት ሊቀሰቀስና የውክልናው ጦርነት ከውኃው ፖለቲካ ጋር ተሸርቦ የታላቁን የኢትጵያ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን ማጨናገፍ ላይ ተልእኮ እንዳለው የፖለቲካ ሀሁ ነው እንላለን፡፡ የአሜሪካ መንግስት የትኛውን ፈረስ እንጫነው? በማለት ምክክር ላይ ይገኛሉ፡፡ አንደኛው ፈረሳቸው ህወሓት ለሃያ ሰባት አመታት ያገለገላቸው በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ በመሆን የአሜሪካኖቹን ጦርነት የታደገ፣ ደረቱን ለጥይት፣ ግንባሩን ለድሽቃ፣ የሰጠላቸውን የቀድሞ ባለውለታ ዳግም ለማንገስ የማያገላብጡት ድንጊያ የለም፡፡ የአሜሪካ ጦር በሱማልያ ከአልቃይዳና አይሲስ ጋር ባደረገው ጦርነት ሬሳቸው በአደባባይ ተጎትቶል፣ መለስ ዜናዊ አሜሪካኖቹን ለመታደግ ሠላም አስከባሪ በመላክ የኢትጵያኖች ሬሳ እንዲጎተት አድርጎል፡፡ የአሜሪካና የህወሃት ወዳጅነት ለሦስት አስርት በላይ የቀጠለ ሲሆን ዳግም ለማስቀጠል ወያኔ ፈረስ ሆኖ ለመጋለብ ቀርቦል፡፡ ሁለተኛው ፈረስ ደግሞ ኦዴድ ብልፅግና ፓርቲ የአብይ አህመድ መንግስት ሲሆን ልዩ ልዑካን ወደ አሜሪካ በመላክ ያላችሁትን ሁሉ አደርጋለሁ አንድ እድል ስጡኝ ተማፅንኦ አቅርቦል፡፡ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተፈፀሙ የስብዓዊ መብት ጥስት ወንጀል፣ የጦር ወንጀልና የዘር ማጥፋት ወንጀል በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት (International Criminal Court) አብይና ባለሰልጣናቱን ለፍርድ ማቅረብና H-R-6600 እና S-3199 ረቂቅ ህግጎች እንዳይጠየቁ በማድረግ አሜሪካ አንደኛ የወልቃይት፣ሁመራ፣ ራያ ወዘተ ግዛቶች ወደ ትግራይ ክልል እንዲመለስ፣የአማራ ልዩ ፖሊስ፣ ፋኖ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሽያ ከነዚህ ቦታዎች እንዲለቁ አብይ መንግስት ተስማምቶል፡፡ ከኤርትራ መንግስት ጋር ግንኙታቸውን እንዲያቆርጡ ተነግሮቸዋል፡፡ የአብይ አህመድ መንግሥት አሜሪካኖቹ እግር ላይ ወድቆ ትዕዛዛቸውን ለማስፈፀም በሃገር ውስጥ ፋኖ የአማራ ልዩ ኃይል ትጥቅ ለማስፈታትና ለማሰር ሥራ ጀምረዋል፡፡ የአማራን ልዩ የፖሊስ ኃይል አመራሮች ከስራ በማባረር ጀነራል ተፈራ ማሞና ሌሎቹም ላይ አፈና ወንጀል መፈፀም ፣ የአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ አባሎች ይህን የአፈና ስራ እንዲሰሩ በማድረግ ፀረ ህብነታቸውን በተግባር አስመስክረዋል፡፡ አብይ ዳግም የሥልጣን ኮርቻው ላይ ለመፈናጠጥ የአማራን ህዝብ እንቢተኛነት ትግል አሸንፎ ከወጣ ከአሜሪካኖቹ ለመጋለብ ሁለተኛ ፈረስ ሆኖ ይወጣል፡፡ የኦህዴድ አብይ አህመድ መንግሥትና ብአዴን ብልፅግና ካቢኔዎች የአማራ ህዝብ ትግልን መሪዎች ከፋኖ የአማራ ልዩ ኃይል፣ የአማራ ልዩ የፖሊስ ኃይልና የአማራ ሚሊሽያ ጋር በጦርነት ተሸንፎ ከአማራ ክልል ፈርጥጦ ከወጣ የአማራ ክልል ሁለተኛው ከአብይ አህመድ የማይገዛ ተገዳዳሪ ኃይል ሆኖ በመውጣት ታሪክ ይሰራል፡፡ ‹‹የአማራ ጊዜያዊ ህዝባዊ የሽግግር መንግሥት›› በማቆቆም የአማራን ክልል ማስተዳደር ይቻለዋል፡፡ የትግራይ ክልል ህዝብም ህወሓት አስወግዶ ‹‹የትግራይ ጊዜያዊ ህዝባዊ የሽግግር መንግሥት›› ‹‹የአፋር ጊዜያዊ ህዝባዊ የሽግግር መንግሥት›› የኦሮሞ ህዝብና የቄሮ ህዝባዊ ኃይል ኦህዴድ ብልፅግናና ኦነግ ሸኔ አስወግዶ ‹‹የኦሮሞ ጊዜያዊ ህዝባዊ የሽግግር መንግሥት›› ወዘተ በማቆቆም የአብይ መንግስት በህዝባዊ እንቢተኛነትና አመፅ ከስልጣን መንበሩ ወርዶ ከሁሉም የተወጣጣ ‹‹የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ህዝባዊ የሽግግር መንግሥት›› በ2015ዓ/ም ይመሠረታል፡፡ ፋኖ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ለኦሮሞ ቆሮ የትግሉ አጋር ሆኖ እንዲወጣ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ በማሰልጠንና በማስታጠቅ ጭምር የድሮ በደም የተፃፈ ህዝባዊ አጋርነታቸውን ዳግም መመለስ አስፈላጊ ነው፡፡
{1} በአባይ ውኃ አጠቃቀም ተፎካካሪ አገሮች፡- ግብፅ፣ ሱዳንና ኢትዮጵያ መቼም ላይስማሙ መስማማታቸውን ወስነዋል፡፡ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ በሃይድሮ ፓወር ኤሌትሪክ አመንጭታ ሰባ በመቶ የሚሆነውን በጨለማ ውስጥ የሚኖር ህዝብዋን ብርሃን እዳትፈነጥቅባቸውና ተጠቃሚ እንዳትሆን እንቅፋት የሆኑ የሚታዩና የማይታዩ ስውር እጆች ውስጥ ግብፅና ሱዳን ዋና ተዋናዩች ሌላ አሜሪካ፣ አውሮፓ ህብረት፣ የአረብ አገሮች፣ የአረብ አገሮች ማህበር፣ እስራኤል በኢኮኖሚ ሴራው ተካፋዬች ናቸው፡፡ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በ1300 (አንድ ሽህ ሦስት መቶ) ሜጋዋት ቀንሶም ግድቡ እንዳይሞላ በሃገር ውስጥ ተላላኪዎቻቸውና ዓለም አቀፍ ደላሎቻቸው ተፈፃሚ እንዳይሆን በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ የዓለም ህብረተሰብና ምሁራን በኢትዮጵያ ላይ የሚፈጸመውን የኢኮኖሚ አሻጥር በመታዘብ ላይ ይገኛሉ፡፡
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ‹‹ፕላን ኤ›› ሃይድሮ ፓወሩን ለኤሌትሪክ ማመንጨት መጠቀም መሆኑን በመግለፅ እንዳይሳካና እንቅፋት ከሆኑ በ‹‹ፕላን ቢ›› ወደ ህዳሴው ግድብ የሚፈሱ ወንዞችንና ጅረቶችን ለመስኖ አገልግሎት ለመጠቀም በየክልል መንግሥቶች ወንዞቹ ተጠልፈው ሥራ ላይ እንደሚውሉ ወዳጅም ጠላትም እንዲያውቅ ማድረግ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ቃል ሆኖ እንደ አስርቱ ትእዛዛት የአባይ ትእዛዛትን ማወጂ ይጠበቃል፡፡ የክልል መንግሥቶቸ በክልላቸው ውስጥ የሚገኙ ወንዛችን ጠልፈው ለመስኖ እርሻ ካናሎቹን ከአሁኑ እየቆፈሩ በማዘጋጀት ማስጠንቀቂያ በመስጠት የግብጽንና ሱዳንን የኢኮኖሚ አሻጥርና ሴራ በመበጣጠስ በፖለቲካው አሸናፊ በመሆን የእኛን አጀንዳ ዓለም አቀፋዊ ማድረግ እንችላለን፡፡
{2} በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት፡- እንዳይሳካ በማድረግና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጣልቃ በመግባት የውስጥ ተቃዋሚ ታጣቂዎችን በማስታጠቅና በማሰልጠን ትልቅ ሚና የሚጫወቱት የግብጽንና ሱዳንን የህወሓትን ሠላሳ ሽህ የሳምሪ ታጣቂዎች በማስታጠቅ፣ የኦነግ ሸኔ ታጠቂዎች፣ የጉሙዝ ሸማቂዎች፣ወዘተ በማሰልጠንና በማስታጠቅ ወደ ሃገር ውስጥ የሚያሰርጉ፣ ህገወጥ የጣር መሳሪያ ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት፣ ህገወጥ ገንዘብ በማሰራጨት፣ የስለላ ስራ በመስራት፣ በግድቡ ላይ የሳይበር ጥቃት በመፈፀም ሃገሪቷ በእርስ በእርስ ጦርነት እንድትዳክር የሚያደርጉትን ግብፅና ሱዳንን ማስቆም እንችላለን፡፡ የአባይ ወንዝ ገባሮች የሆኑትን፣ ወደ ግብጽንና ሱዳን የሚፈሱ ወንዞችን ጠልፈን ውኃውን ለመስኖ እርሻ ሥራ ተጠቅመንበት እንደምናስቀር በማስጠንቀቅ ለሽምቅ ተዋጊዎች የሚያደርጉትን ድጋፍ ማስቆም ይቻላል፡፡ ግብፅና ሱዳን በሃገራችን ላይ ለሚፈፅሙት የተወሳሰበ የፖለቲካ ሴራ ከነሰንኮፉ በመንቀል በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ማድረግ ይቻላል፡፡ ሱዳን መንግሥት ከኢትዮጵያ ወርሮ የያዘውን ቦታዎች በአስቸኮይ ለቆ እንዲወጣ ማስጠንቀቂያ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ የእኛ አሸናፊ አጀንዳ የወንዞቹን ወኃ በመገደብ ሁሉንም የፖለቲካ ሴራ የሚከላከልልን እውኑን የውኃ ሳይበር ጥቃት (water cyber attack ) ኢትዮጵያ መጀመር አለባት እንላለን፡፡
{3} የዓለም ፖለቲካ ሁኔታ ተለዋውጦል፡- የጦርነት ግጭት ቀጠና በሱማሌያ፣ በደቡብ ሱዳን፣ በሱዳን፣ በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ፣ በትግራይ ወዘተ በቀይ ባህር ዳርቻ ባሉ አገራቶች ተሳትፈውበታል፡፡ በአፍሪካ ቀንድ አገሮች ፖለቲካ ጉዳይ ጣልቃ ገብነት፣ የመካከለኛው ምስራቅ አገራቶች ዋና ተዋናዬች ሲሆኑ፣ የልዕለ ኃያሎች ሃገራትም አሜሪካ፣ ራሽያና ቻይና በብሄራዊ ደህንነታቸው ጉዳይ ዙሪያ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡
የዓለም ፖለቲካ ሁኔታ ተለዋውጦል፣ ገናና ታሪክና የጥንት ሥልጣኔና ቅርስ ያላቸው የሰሜን አፍሪካ ሃገራት ውስጥ ሊቢያ፣ ሲሪያ፣ ኢራቅ፣ የመን፣ሱዳን፣ ሱማሌ፣ ሊባኖስ፣ ማሊ፣ ናይጀሪያ ናይጀር፣ ሴንትራል አፍሪካ ሪፓብሊክ ወዘተ አገሮች የጦርነት ቀጠና በመሆን በተለይ ሊቢያ፣ ሲሪያ፣ ኢራቅ፣ የመን፣ ሱማሌ ወዘተ ሃገሮች መሠረተ ልማቶቻቸው በጦርነት እንዲወድም ተደርጎል፡፡ ፀረ አሜሪካ ኢምፔሪያሊዝምና ፀረ-እስራኤል የነበሩ አገሮች ተራ በተራ ወደ ትቢያነት ተቀይረው የስው ልጆች የእናቶችና የህጻናቶች ስቃይና ሞት ለሠለጠነው የአንደኛው ዓለም መንግሥትና ህዝብ ከሚያኖሮቸው ውሻዎችና ድመቶች ህይወታቸው የረከሰ የምድር ጎስቆሎች ሳይፈጠሩ ቢቀሩ በተሸለ ነበር፡፡ አሜሪካና የአውሮፓ ህብርት አገሮች የሦስተኛው ዓለም ህዝብ ስቃይን በማራገብ የደም ገንዘብ በማግበስበስ ላይ ተጠምደው ይገኛሉ፡፡ የሚያመርቱት ሰው ጨራሽ የጦር መሣሪያ በአፍሪካና እስያ አህጉራት የብዙ ሰው ህይወት ቀጥፎል፣ ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ መንገዶች፣ ኤርፖርቶች፣ ወደቦች መሠረተ-ልማቶች በእነሱ የጦር መሳሪያና ጅምላ ጨራሽ መሣሪያዎች፣ የጦር አውሮፕላኖች፣ ድሮዎኖች፣ ታንኮች፣ ፀረ ሰው ፈንጂዎች ሚሊዮን ወጣቶች እጅናና እግራቸውን አጥተው አሰቃቂው ህይወት በመግፋት ላይ ናቸው፡፡ በእነዚህ አገሮች የሚኖሩ የአካል ጉዳተኞች በየአገሮቹ ከተሞች እንደ የህያውያን እግዚቢሽን በጎብኝዎች ይታያሉ፡፡ ለእነዚህ የአካል ጉዳተኞች መቆቆሚያ የጦር መሣሪያ አምራቾች ገንዘብ እንዲከፍሉ የሳሻል ሚዲያዎች እንደ ልእልት ዲያና አርዓያ ሆነው መታገል ይገባቸዋል፡፡
{4} አስታጣቂው ማን ነው? የገንዘቡ ምንጭስ?
‹‹የሱማሌ ክልላዊ መንግሥት ልዩ ኃይል የአልሻባብ አባሎችን ህገወጥ የጦር መሣሪያዎች በሱማሌ ክልል በአፍዴራ ዞን ኢልከሬ ወረዳና በቡላ ቀበሌ ውስጥ ሲያዞዙሩ አግኝቶ እንዳሰረ ኢቢሲ አስታውቆል፡፡ የአልሻባብ አባሎች የሽብር ጥቃት በክልሉ ውስጥ ለመፈፀም በዝግጅት ላይ ነበሩ፡፡ የአልሻባብ አባሎች አስራ ስምንት የኤኬ አርባ ሰባት ጥይቶች፣ ስድስት አርፒጂ፣ ሁለት ማሽን ጋን ከጠርጣሪዎቹ ጋር ተይዞል፡፡ በወርሃ አፕሪል ሠላሳ አራት የአልሻባብ አባሎች አዲስ አበባ ውስጥ ሽብር ለመፈፀም ሲያሴሩ መያዛቸው ተዘግቦል፡፡ ኢትዮጵያ ባሳለፈችው ደግ ዘመኖ አይታ የማታውቀው የኃይማኖት ግጭት በመላ ሃገሪቱ ውስጥ ለመለኮስ የውጭ ሀገር ጠላቶቾ በማሴር ላይ ይገኛሉ፡፡›› “Somali region special forces said it has arrested Alshabaab members who were attempting to smuggle arms to the Somali region of Ethiopia. According to a report from EBC, state media, they were arrested in Afdere zone, Elkere District, and Bula Kebele. They were planning to carry out terrorist activity, it was said. The planned targets were in the region. 18 boxes of AK 47 ammunition, six RPGs, and two machine guns were seized from the suspects. In late April this year, Ethiopia announced that it has arrested 34 Al-Shabaab members as they were moving to implement terror plants targeting places in Addis Ababa, the Oromo region of Ethiopia, and the Somali region. Ethiopia has recently been experiencing challenges in relation to religious violence and the Ethiopian government has been claiming that enemies to the Ethiopian state have been attempting to exploit religion as a cover to bring about prevalent religious violence in the country.”………………………………………..….(7)
አርሶ በሌው፣ በወሮ በሌው ተተክቷል!!! ህወሓት ኢህአዴግ በሃያ ሰባት አመታት በሃገሪቱ ውስጥ የፈለፈለው ወሮበላ ቡድኖች አሊባባና አርባዎቹ ሌቦችን ያስንቃል፡፡ በህወሓት የጦር አበጋዞች የሚመራው የተቃዋሚው ህብረት ኃይል አሰላለፍ ተዋጊ ኃይል ብዛት፤ የትግራይ መከላከያ ኃይል ሦስት መቶ ሽህ (300,000) ተዋጊ ኃይል ፣ የኦሮሞ ነጻ አውጪ ሠራዊት ሃያ ሽህ (20,000)፣ የአገው ነጻ አውጪ ሠራዊት አምስት ሽህ (5,000)፣ አፋር ሦስት ሽህ (3,000)፣ ጉሙዝ ነጻ አውጪ ሠራዊት አስር ሽህ (10,000)፣ ጋምቤላ ነጻ አውጪ ሠራዊት አምስት ሽህ (5,000)፣ ቅማንት ነጻ አውጪ ሠራዊት አምስት ሽህ (5,000)፣ ሲዳማ ብሔራዊ የነፃነት ግንባር አምስት ሽህ (5,000) የተደራጀ አራጅ ወንጀለኛ ቡድንየኢትዮጵያን ህዝብ በመጨፍጨፍ ላይ ናቸው፣ የአማራውን፣ የአፋሩን፣ የኦሮሞውን ወዘተ ህዝብ በመጨፍጨፍ ላይ ናቸው፡፡ ኦዴፓ ብልፅግና የአብይ መንግሥት ‹‹ታጣቂው ከአራሹ ቁጥር በዝቶ የእህል ምርት ሲጠፋ አልገባውም፣ ችግኝ ይተክላል!!! ፓርኮች ያስፋፋል፣ መንግሥቱ እየወደቀ እያየ፣ የፀና መስሎት!!! ለአሳራጁ መንግሥት ፍርድ እንዲሠጥ መጠየቅ ጊዜው አሁን ነው!!! አንድ መንግስት ዋነኛ ሥራው የህዝቡን ደህንነትና ፀጥታ ማስከበር፣ ድንበር በማስጠበቅ ህገወጥ የመሣሪያ ዝውውርን፣ የገንዘብ ዝውውርን፣ የሰው ዝውውርን መቆጣጠርና ማስቆም ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ግብርና ታክስ የሚከፍለውና መንግሥት ደሞዝ ከፍሎ ቀጥሮ የሚያሠራው የምድር ጦር፣ አየር ኃይል፣ አየርወለድ፣ የፖሊስ ሠራዊት፣ የደህንነት ሠራተኞች ወዘተ ዋነኛ ሥራቸው የሃገሪቱን ዳር ድንበር ማስከበርና የህዝቡን ደህንነት መጠበቅ ነው፡፡ በአብይ አራት አመታት አገዛዝ አዲስ የመከላከያና የፖሊስ ሠራዊት መመሪያ ወጣ በተባለበት ማግስት መከላከያው ኃላፊነቱን በመዘንጋት ዜጋው በየቀኑ እንደከብት ሲታረድ እያዩ እንዳላዩ መሆን እንቆቅልሹ ያልተፈታ ችግር ሆኖል፡፡ አብይ በኢትዮጵያን ህዝብ ላይ ኦሮሙማን ለመጫን ከኦሮሚያ ክልል ውስጥ አማራውን አሳርዶ ማስወጣት የኦህዴድ፣ ኦነግ ፣ ኦነግ ሸኔ፣ ኦፊኮ በአጠቃላይ የሁሉም ኦሮሞ ድርጅቶች ሰው ሰው ያልሸተተ የእርኩስ መንፈስ ተሸካሚዎች ጠመንጅ ተሸካሚዎች አረመኔ ሥራ የጊዜ ጉዳይ እንጅ በኢትዮጵያ ህዝብ ይመከታል፣ በአማራ ፋኖ ሽብሩ ይገታል፣ በአፋር አናብስቶች ሽብሩ ይከላል፡፡
የዓለም ፖለቲካ ሁኔታ ተለዋውጦል፣ የአንደኛው ዓለም መሪዎች በኮኪየን፣ ማሪዋና፣ ወዘተ ድራግ የተመረዙ እየሆኑ በመምጣቱ ዓለምን የሚያስተዳድሩ የእብዶች መንግስታት የኒውክለር ጦርነት ውስጥ መግባታቸው አይቀሬ ነው፡፡የዓለም ህዝብ ቁጥር በጦርነት፣ በበሽታ ቨይረስ በማሰራጨት (ኮቪድ፣ ሳርስ ወዘተ) ከእራሳቸው ላብራቶሪ ተፈብርከው የወጡ ፀረ ሰው ቫይረሶች እንደአሸን ተፈብርከዋል፡፡
{5} ‹‹የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ህዝባዊ የሽግግር መንግሥት›› ፍኖተ–ካርታ
በኢትዮጵያ የሚገኙ ክልሎች ድንበርና ወሰን የሃሳብ መስመር እንጂ ምድር ላይ የሌሉ ልዩነቶች ናቸው!!! ኢትዮጵያ፣ በኤርትራ፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ ፣ ወዘተ የሚገኙ ክልሎች ካርታ ድንበርና ወሰን የሃሳብ መስመር እንጂ ምድር ላይ ያልተሰመሩ ምናባዊ መሥመሮች ናቸው!!! መንግሥት ይሄዳል ይመጣል፣ የኢትዮጵያ ህዝብና ምድሪቷ ህልውና ግን ይቀጥላል!!! በዚህ የልብ ወለድ ታሪክ ካቻምና ሻብያና ወያኔ በህብረት ኢትዮጵያን በጦርነት ወግተው ድል አደረጉ፡፡ አምና ወያኔና ኢትዮጵያ በህብረት ሻብያን ወጉ፡፡ ዘንድሮ ደግሞ ሻብያና ኢትዮጵያ በህብረት ወያኔን ወጉ፡፡ የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብ በካርታው ላይ የተሳለውን የሃሳብ መስመር ጥሰው ከሃያ አመታት መለያየት በኃላ በፍቅርና በነፃነት ድንበርና ወሰኑን ጥሰው አንድ ሆነዋል፡፡ የትግራይ ህዝብም ከዚህ ጦርነት በኃላ ከኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብ ጋር በካርታው ላይ የተሳለውን የሃሳብ መስመር ጥሰው በፍቅርና በነፃነት ድንበርና ወሰኑን ጥሰው ዳግም አንድ ቀን አንድ ይሆናሉ፡፡ የሻብያ የወያኔ የብልፅግና የጦር አበጋዞች መንግስት ልብ ወለድ ታሪክ፣ ልብ ወለድ የካርታ የድንበርና ወሰን የሃሳብ መስመር ድርሰት፣ ምክንያት በትንሹ አንድ ሚሊዮን ዜጎች ሞተዋል፣ አንድ ሚሊዮን ዜጎች ቆስለዋል፣ ሚሊዮኖች ተሰደዋል፡፡ በኢትዮጵያ የጦር አበጋዞች መንግሥት የድንበርና ወሰን ግጭት ወደ ማያባራ ጦርነት ውስጥ አገሪቱን ስለሚከታት ከወዲሁ ህገመንግሥቱን ማሻሻል፣ የዘር ፌዴራሊዝምን ድንበርና ወሰን በማጥፋት እውነተኛ ፌዴራሊዝም በመገንባት ራስን በእራስ የማስተዳደር መብቶች የሚከበርባት ኢትዮጵያን በሠላም መገንባትና ሳይንሳዊ የሠለጠነ መንገድ ችግራችን እንዲፈታ ማድረግ ዘለቄታዊ መፍትሄ ያመጣል እንላለን፡፡ የኢትዮጵያ በሰሜን በደቡብ፣ በምስራቅና በምዕራብ የሚያዋስኖት አገሮች ብቻ ካርታ ሲኖር፣ ውስጣዊ በዘር ላይ የተመሰረተ ድንበርና ወሰን አይኖርም፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ህዝባዊ የሽግግር መንግሥት›› ዋና ሥራዎቹ ውስጥ፡-
- ‹‹ማንኛውምሰው ስብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰሰ በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነትና፣ የነፃነት መብት አለው፡፡›› አንቀጽ 14
- ‹‹ማንኛውምሰው በሕይወት የመኖር መብት አለው፡፡ ማንኛውም ሰው በሕግ በተደነገገ ከባድ የወንጀል ቅጣት ካልሆነ በስተቀር ሕይወቱን አያጣም፡፡›› አንቀጽ 15
- ኢትዮጵያ ባጸደቀችው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና በሌሎች የኢትዮጵያ ሕጎች በሰው ልጅ ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች ተብለው የተወሰኑትን ወንጀሎች ፣ የሰው ዘር የማጥፋት፣ ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ የመውስድ፣ በአስገዳጅ ሰውን የመሰወር፣ ወይም ኢስብዓዊ የድብደባ ድርጊቶችን በፈጸሙ ሰዎች ላይ ክስ ማቅረብ በይርጋ አይታገድም፡፡ በሕግ አውጪውም ክፍልም ሆነ በማንኛውም የመንግሥት አካል ውሳኔዎች በምሕረት ወይም በይቅርታ አይታለፍም፡፡›› አንቀጽ 28
- ‹‹ማንኛውምኢትዮጵያዊ ወይም በሕጋዊ መንገድ ሀገሪቱ ውስጥ የሚገን የውጭ ዜጋ በመረጠው የሀገሪቱ አካባቢ የመዘዋወርና የመኖሪ ቤት የመመስረት፣ እንዲሁም በፈለገው ጊዜ ከሀገር መውጣት ነፃነት አለው፡፡ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወደ ሀገሩ መመለስ መብት አለው፡፡››አንቀጽ 32
- ‹‹ማንኛውምኢትዮጵያዊ ዜጋ የኢትዮጵያ ዜግነት በሕግ የሚያስገኘውን መብት፣ ጥበቃና ጥቅም የማግኘት መብት አለው፡፡›› አንቀጽ 33 (የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ ሕገ መንግሥት)