May 21, 2022
9 mins read

 በአማራ ሕዝብ ላይ የሚካሄደውን ግፍና በደል በሚመለከት ከቪዥን ኢትዮጵያ የተሰጠ መግለጫ

Ethiopia 1 1ግንቦት 13፣ 2014
May 21, 2022

ቪዥን ኢትዮጵያ (ራዕይ ለኢትዮጵያ)፣ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ውስጥ፣ በተለይም በአማራው ሕዝብ ላይ፣ በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ መንግሥት እውቅና፣ እየተከሰቱ ያሉትን አስከፊ የግፍና የበደል እርምጃዎችን አጥብቆ ያወግዛል።

ምንም እንኳን አሁን እየተከሰቱ የሚታዩትን ዘር-ተኮር የወንጀል ድርጊቶች የራዕይ ለኢትዮጵያ ድርጅት በተደጋጋሚ ባወጣቸው ፅሁፎች ሲያስጠነቅቅ የቆየ ቢሆንም፣ በአሁኑ ሰዐት በሰላማዊ ዜጎች ላይ፣ ከመቸውም ጊዜ በከፋና በተቀነባበረ ሁኔታ በመተግበር ላይ ያለውን በደል፣ ማንኛውም ለፍትህ የቆመ ግለ-ሰብ፣ ወገን፣ ቡድን፣ መዋቅር ወይም አገር፣ በማያሻማ ሁኔታ ሊቃወመዉና ሊታገለው ይገባል ብለን በጽኑ እናምናለን::

ለ27 ዓመታት የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲገድል፣ ሲያስር፣ ሲበዘብዝና ሲያሳድድ የቆዬው የወያኔ አረመኔአዊ አገዛዝ በኢትዮጵያ ሕዝብ አመፅ ከስልጣን ከተወገደበት ጊዜ ጀምሮ፣ የዐቢይ አሕመድ መንግሥት በዘረኛ አመለካከቱና ፍላጎቱ፥ በአገሪቱ ዙሪያ በአማራ ተወላጆችና ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ በገፍ እየተፈፀሙ የነበሩትን ኢሰብአዊና አሰቃቂ ግድያዎችና ጅምላ የዘር-ፍጅት ድርጊቶች፣ እንዳላየ በማስመሰል፣ ለማስቆም አለመፈለጉን በተግባር ሲያሳይ ቆይቷል::

ከዚህም በባሰ ደረጃ፥ ያለጊዜውና ያለበቂ ምክንያት የመከላከያ ሀይሉን ለወያኔ በሚያመች መንገድ ከትግራይ በማስወጣት የአማራውንና የአፋሩን ህዝብ ለወያኔ የጥቃት ጦርነትና አሰቃቂ የጦርነት ወንጀሎች አጋልጦ ብዙ ከግምት ውጭ የሆኑ ሰብኣዊና ቁሳዊ ጉዳቶች በአማራና የአፋር ህብረተሰቦች ላይ እንዲደርሱ አድርጓል።

ከዚያም አልፎ፣ ብዙ የሚዲያ አባላትን፣ የሰብአዊ መብት ታጋዮችንና ሌሎችን የተራኛነት አላማን ለማራመድ እንቅፋት ይሆናሉ ብሎ የገመታቸውን ግለ-ሰቦችና ቡድኖች፣ በእስራትና በማዋከብ ሲያሰቃይ ቆይቷል:: ቀደም ሲል በመዐዛ መሃመድ፥ ታምራት ነገራ፥ ጎበዜ ሲሳይና ታዲዎስ ታንቱ ላይ የተወሰዱትን፥ ዛሬ ደግሞ መስከረም አበራንና ሰለሞን ሹምዬን በመሳሰሉት ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ መጥቀስ ይቻላል። ይህ የሚዲያ ባለሙያዎች አፈናና የማሕበረ-ሰብ አንቂዎች ጥቃትና ማጎሳቆል፣ ዐላማውና ዉጤቱ ምን እንደሆነ ለማስገንዘብ ቪዥን ኢትዮጵያ ሲታገል ቆይቷል።

ዛሬ እንዲህ በከፋ መልኩ አግጥጦ የወጣውና፣ በአማራውና በኦርቶዶክስ ክርሲቲያኖች ላይ የታወጅው የዐቢይ አሕመድ ጦርነት፣ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ሲታቀድበት የነበረው የኦሮሙማና የወያኔ ፕሮግራም መሆኑ ግልጽ ነው። የእነመስከረም አበራ አፈናና መታሰር፣ የዚሁ የታላቁ የኦሮሙማና የወያኔ ሴራ አካል ነው።

በአሁኑ ጊዜ፣ ሙሉና ይፋ ጦርነት በአማራው ህዝብ ላይ ታውጇል። የአማራ ልዩ ኅይል መሪ የነበረው ጀግናው ጀኔራል ተፈራ ማሞ ታፍኖ በባሕር-ዳር እስር ቤት እየተሰቃየ ይገኛል። የአማራ ፋኖ መሪዎች እየተሳደዱ፤ እንዲሁም የአማራ ፋኖዎች በያሉበት እየተከበቡ፥ እየታደኑና እየተገደሉ ይገኛሉ። ያልታጠቁና ለማንም ስጋት ያልሆኑ ንፁሃን ወጣቶች በጅምላ በጎጃም፣ በወሎ፣ በሽዋና በጎንደር በጠራራ ፀሀይ እየተረሽኑ ይገኛሉ። በአዲስ አበባ ከተማ፣ ወጣቶች በግፍና በጭካኔ እየተለቀሙና ባልታወቁ እስር ቤቶች እየታጎሩ ይገኛሉ።

 

ስለዚህ፥ ቪዥን ኢትዮጵያ፥

  1. እነኝህ ጨካኝና ኢትዮጵያን አፍራሽ የሆኑትን የኦሮሙማንና የወያኔን አረመኔያዊ ተግባሮችን በሙሉ ልቡ ያለምንም ማወላወል ያወግዛል፥ ይታገላል።
  2. በአማሮች ላይ የፍጅት ጦርነት የከፈተው የኦሮሙማ ልዩ ሃይልና አብረውት ያሉት አፋኝ ቡድኖች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከአማራ ክልል በአስችኳይ እንዲወጡ፣ ለሰላምና ፍትሕ ከቆሙ ወገኖች ጋር በመተባበር፣ ያለማቋረጥ ይታገላል።
  3. በተለይም፣ መምህርት መስከረም አበራ ያለምንም ቅድመ – ሁኔታ እንድትፈታና፣ ጨቅላ ልጇን ለማሳደግ እንድትበቃ፣ የሰብአዊ መብቶችን ለመጠበቅ ከቆሙ ድርጅቶች ጋር በመተባበር፣ ያለመትጋት ይታገላል።
  4. ሌሎች ያለህግ፣ በማን ኣለብኝነትና በትእቢት የታሰሩትና የተሰወሩት የሚዲያ ባለሙያዎች፥ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ሌሎችም ንፁሃን ዜጎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ የማያቋርጥ ጥረት ያደርጋል።
  5. መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፥ በተለይም በውጭና በአገር ውስጥ ያሉት የመብት ተቆርቋሪዎች፥ በሙሉ በአንድነትና በመተባበር፣ ይህንን በኢትዮጵያ ህልውና ላይ የመጣውን አደጋ ለመግታትና ለማሸነፍ፣ በጋራ እንዲቆሙና እንዲታገሉ ጥሪ ያቀርባል።
  6. በመጨረሻም፣ የአማራ ብልጽግና በሚል ስያሜ የሚታዎቀው የአብይ አሕመድ ጸረ-አማራ አጀንዳ አስፈጻሚና ተባባሪ ቡድን፣ በታሪክም ሆነ በሀግ ተጠያቂነቱን ተገንዝቦ፣ ክዚህ የወንጀል ተግባር እንዲቆጠብና፣ የአማራ ወገኑን ከተደቀነበት አደጋ ለማዳን በሚደረገው ጥረት ተሳታፊ እንዲሆን ጥብቅ ጥሪ እናቀርባለን።

 

ድል ለተበደለ ሕዝብ

ቪዝን ኢትዮጵያ (ራዕይ ለኢትዮጵያ)

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ

ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ

እግዚኣብሔር ግን ወዴት አለ?

ልዩ ቆይታ ከገዱ አንዳርጋቸው ጋር ! – “ዐብይ ቂም የያዘ የነጣቂ መንግስት መሪ ነው”/ “አማራ እየተዋጋ ያለው ሰላምን ፍለጋ ነው” – ክፍል አንድ ልዩ ቆይታ ከገዱ አንዳርጋቸው ጋር ! –

“ፋኖ የበለጠ ይደራጃል ወደ ኋላ አይልም!”/ “የትግራይን ህዝብን ይቅርታ ጠይቂያለሁ” “ፋኖ በናፍቆት እየተጠበቀ ነው” ገዱ አንዳርጋቸው (ዶ/ር)

December 28, 2024
ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር) (ታህሳስ 19፣ 2017) December 28, 2024 መግቢያ እንደተነገርን ኢትዮጵያን “ከዕዝ ወይም ከሶሻሊስታዊ” ኢኮኖሚ አላቆ ወደ “ ነፃ ገበያ ኢኮኖሚ” እንድትሸጋገር ከተደረገ ይኸው ከ31 ዓመት በላይ ሊያስቆጥር ነው። በጊዜው ስልጣንን የተቆናጠጠው የህወሃት አገዛዝ

ሁለ-ገብ ለሆነ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ዕድገት መሰረት የሚጥል ህግ፣ ወይስ የኢትዮጵያን ሀብት የሚያዘርፍና ህዝብን አቅመ-ቢስ የሚያደርግ አዲስ የባንክ ህግ- ከኒዎ-ሊበራሊዝም ወደ ባሰ ኒዎ-ሊበራሊዝም የዝቅጠት ጉዞ!

ልዩ ቆይታ ከገዱ አንዳርጋቸው ጋር ! – “ዐብይ ቂም የያዘ የነጣቂ መንግስት መሪ ነው”/ “አማራ እየተዋጋ ያለው ሰላምን ፍለጋ ነው” – ክፍል አንድ

ልዩ ቆይታ ከገዱ አንዳርጋቸው ጋር ! – “ዐብይ ቂም የያዘ የነጣቂ መንግስት መሪ ነው”/ “አማራ እየተዋጋ ያለው ሰላምን ፍለጋ ነው” – ክፍል አንድ

December 27, 2024
የሲቪል ማህበረስብ ድርጅቶች ባለስልጣን፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን (EHRDC) “ገለልተኛ ባለመሆን ከተቋቋሙበት ዓላማ ውጭ ተንቀሳቅሰዋል” በሚል ምክንያት ማገዱ ገለጸ። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል (EHRDC)

መንግስት ኢሰመጉ እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን አገደ፤ የታገዱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቁጥር አራት ደረሷል

December 26, 2024
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ ጊዜው ይከንፋል፡፡ ይሄውና ከዘመነ ወያኔ ድቅድቅ ጨለማ ወጥተን ወደ ለዬለት ሲዖል ከገባን ድፍን ስድስት ዓመት ከስምንት ወር ከ11 ቀናት ሆነን – ዛሬ ታኅሣስ 15 ቀን 2017 ዓ.ም፡፡ የሲዖላዊው መርዶ

ሰይጣን አንዳንዴ እውነትን ይናገራል – ከዘመነ ወያኔ ድቅድቅ ጨለማ ወጥተን ወደ ለዬለት ሲዖል ከገባን ድፍን ስድስት ዓመት

Go toTop