July 14, 2014
9 mins read

ግልፍተኛነት

በስራም ሆነ በሌሎች ማህበራዊ ህይወታችን ውስጥ ግልፍተኛ የሆኑ ሰዎች ይገጥሙናል፡፡ ምናልባትም እኛ ራሳችን በሌሎች እይታ ግልፍተኛ ልንባል እንችል ይሆናል፡፡ ግልፍተኝነት ተራ በሚባሉ ጉዳዮች ሳይቀር በቁጣ መገንፈልና ይህንንም ተከትሎ ለአላስፈላጊ ውሳኔ ወይም ድርጊት መጋበዝን ያመለክታል፡፡ በዚህ በግልፍተኝነት ምክንያትም ለዓመታት የተገነቡ ጓደኝነቶች፣ ትዳር ወይም እቅድ ሊከሽፍና ሊበላሽ የሚችልበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ግልፍተኝነት መቅረፍ የሚቻልባቸው እና የተረጋጋና ሰላማዊ ህይወት መኖር የሚያስችሉ ሳይንሳዊ ስነ ልቦናዊ መንገዶች እንዳሉ ማስታወስ ያሻል፡፡ ከግልፍተኝነት ለመላቀቅ የሚበጁ ተብለው በተለያዩ የስነ ልቦና ምሁራን ከሚጠቀሱት ምክሮች በፊት ‹ግልፍተኝነት› በምን ምክንያት ይከሰታል የሚለውን ነጥብ እንመልከት፡፡

ግልፍተኝነት እንዴት ይከሰታል?

ግልፍተኝነት ከጭንቀትና ከውጥረት ብዛት እንደሚከሰት ብዙዎች ቢስማሙበትም፣ አታካች በሆነ የህይወት ሂደት፣ በቤተሰብ፣ በከባድ ኃላፊነቶች ምክንያት ሊመነጭ ይችላል፡፡ በተደጋጋሚ ሲነገረው አልሰማም ባለ ልጅ አባት/እናት ግልፍተኛ ሊሆኑ ይችላሉ፣ የጠበቅነው ነገር ሳይሆን ሲቀር ለግልፍተኝነት ሊዳርገን ይችላል፡፡

አና የተሰኘች የ25 ዓመት ወጣት ስለ ፍቅር ጓደኛዋ እንዲህ ስትል ትናገራለች፡፡ ‹‹እኔና ጓደኛዬ ላለፉት ሁለት ዓመታት በጓደኝነት ኖረናል፡፡ ይህ ጉድኝታችን ግን በጓደኛዬ ግልፍተኛነት ምክንያት አንዴ ሲቋረጥ አንዴ ሲቀጥል ነበር የቆየው፡፡ በጣም ተራ በተባሉ ጉዳዮች ከመጠን ባለፈ የሚበሳጭ ሲሆን ሲበሳጭ ደግሞ አጠገቡ ያለውን እቃ ከመስበር አንስቶ ግድግዳ በቦክስ ሲደበድብ ሊታይ ይችላል፡፡ እንደውም በአንድ ወቅት ራሱን ለማጥፋት እስከመሞከር የደረሰበት ሁኔታ ነበር፡፡ እርሱ መናደድ በጀመረበት ወቅት ለማረጋጋት መሞከር ንዴቱን ይበልጥ ማባባስ ስለሆነ ቆሜ ከማልቀስ ውጭ ምንም ማድረግ አይቻለኝም›› ስትል ትገልፀዋለች፡፡

ይህን አስመልክቶ መልስ የሰጡ አንድ የስነ ልቦና ባለሙያ ግልፍተኛነት ማንኛውም ሰው በህይወት ዘመኑ ሊገጥመው የሚችል ስሜት ሲሆን ይህ ስሜት ግን በአንዳንድ ሰዎች ላይ በተደጋጋሚና ጠንከር ባለ ሁኔታ ሊከሰትበት የሚችል እድል እንዳለ ያስረዳሉ፡ ፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች ማለትም ክብራችን ሲደፈር፣ ጥቃት ሲደርስብን ወይም አይነኬ ያልነው ድንበር ሲጣስ ግልፍተኝነት ጠቃሚ ሊሆን ይችላል የሚሉት እኚህ ባለሙያ ግልፍተኝነት ጤናማ የማይሆነው የተፈጠረው ችግር ለግልፍተኛነት የማይጋብዝ ሁኔታ ላይ ሲከሰት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

ከዚህ ቀደም በመልካም ባህሪያቸውና በትህትናቸው የምናውቃቸው ሰዎች ድንገት ቁጡና ግልፍተኛ ሆነው የሚገኙበት አጋጣሚም አለ፡፡ ይህ አይነቱ ግልፍተኛነት ‹secondary emotion› ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን ሰዎች በህይወታቸው ውስጥ በሚከሰቱ የስራ ወይም የሌሎች ማህበራዊ ህይወት ጫናዎች ለዚህ ባህሪ ሊዳረጉ የሚችሉበት እድል ሰፊ ነው፡፡ አንድ ሰው በዚህ ሁኔታ ለግልፍተኛነት ሲጋለጥ ምንም አይነት ደስታ ላይኖረው ሲችል የፍቅር ቃላትና ሰላምታ ሳይቀር ለቁጣና ለብስጭት ሊዳርገው ይችላል፡፡

ግልፍተኛነት የረጅም ጊዜ ባህሪያችንንም ሆነ የአጭር ጊዜ በተለያዩ ሳይንሳዊ መንገዶች ተጠቅመን ልናስወግደው የምንችለው ባህሪ መሆኑ ግን ሊታወቅ ይገባል፡፡ ተግባቢና ተጫዋች ሆኖ ከመገኘት የበለጠ ምን አለ? ግልፍተኛ ከሆኑ ወይም ‹ግልፍተኛ ነዎት!› የሚባል ከሆነ እስቲ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ነጥቦች ለመተግበር ይሞክሩ፡፡

የግልፍተኛነት መፍትሄዎች

ቁጡነትንም ሆነ ግልፍተኛነትን ለመቅረፍ የሚያስችሉ የተለያዩ ስትራቴጂዎች በተለይ በሰለጠነው ዓለም በስፋት ይገኛሉ፡፡ ጭራሹኑም በግልፍተኛነት ችግር የሚፈጥሩ ሰዎች በህግ ታዘው ከግልፍተኛነታቸው የሚገላገሉበት ስልጠና እንዲወስዱ ሲደረግም ይታያል፡ ፡ ከእነዚህ የግልፍተኛነት መቅረፊያ መንገዶች ውስጥም ለቁጣ /ለግልፍተኛነት የሚዳርጉንን ነገሮችን ለይቶ ማወቅና ከእነርሱም መራቅ፣ ለግልፍተኛነት የሚዳርጉ ስነ ልቦናዊ ችግሮች ማለትም ጭንቀትና ውጥረት ካሉብን ለእነርሱ መፍትሄ መፈለግ፣ ከአልኮልና ከሌሎች ሱስ አስያዥ ነገሮች መቆጠብ፣ የመግባቢያ /Communication/ መፃህፍትን ማንበብ ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ እርስዎ በቤትዎ ግን እነዚህን ምክሮች ሊተገብሩ ይችላሉ፡፡

– ከግጭቱ፣ ከተበሳጩበት ሰው ወይም ቦታ ዘወር ማለት፡- ከአንድ ሰው ጋር በአንድ ጉዳይ እየተከራከሩና በሰውዬው ንግግር /ድርጊት ብስጭት የሚሰማዎ መስሎ ከተሰማዎት ምንም መልስ ሳይሰጡ ከሰውየው ይራቁ፡፡ ብቻዎትን ይሁኑናም ‹ብቻዬን ሆኜ ራሴን ማረጋጋት እችላለሁ› ይበሉና ለራስዎት ይንገሩት፡ ፡ ወይም ክፍልዎ ይግቡና ግድግዳ ይደገፉ፡፡ ሁለት እጅዎንም ግድግዳው ላይ ይለጥፉና 5 ጊዜ በጥልቀት አየር ወደ ውስጥ እየሳቡ ይተንፍሱ፡፡ ውስጥዎ ሲረጋጋ ተሰማዎ? ‹አዎ! አሁን ተረጋግቻለሁ› ሲሉ ለራስዎ ይንገሩት፡፡

– ቁጣዎን ያስወጡት፡- በብስጭት ውስጥዎ ሲነድ ግድግዳ በጡጫ ይነርታሉ? ዕቃ ይሰብራሉ? ግድግዳውም ሆነ ዕቃው ከብስጭትዎ ጋር በምን ይገናኛሉ?

በእርግጥ ሰው ሲበሳጭ ይህን ብስጭቱን ቢያስወጣው ለመረጋጋት እንደሚያስችለው ይታመናል፡ ፡ እርስዎም ብስጭትዎን ቢያስወጡት መልካም መስሎ ከተሰማዎ ለምን እንዲህ አያደርጉም?! አንድ ሞቅ ያለ ሙዚቃ ድምፁን ከፍ አድርገው ይክፈቱና በደንብ ይደንሱ፡፡ ለዳንስዎ ህግ አያውጡ፤ እጅዎም ሆነ እግርዎ እንደፈለጉት ይንፈራገጡ፡፡ ይህችን ነገር ከ2 እስከ 3 ደቂቃ ካደረጉ ብስጭትዎን ድራሹን ለማጥፋት በቂ ነው፡፡

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ

ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ

እግዚኣብሔር ግን ወዴት አለ?

Go toTop