March 29, 2014
21 mins read

ለጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ብራቦ ብለናል (ከሥርጉተ ሥላሴ)

የወያኔ ማናቸውም የፖሊሲ አይነት ለነፃነት ትግሉ ምኑ ነው?

መልስ —– ምንም!  ከሥርጉተ ሥላሴ 29.03.2014 ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ

ይድረስ ለማከብርህ ወንድሜ ለጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም። ብራቦ ብለናል። ጥሩ መጠጋጋት ነው እንላለን እኔና ወዷ ብዕሬ። ወያኔን የምትደግፍበት አንድ ነገር መገኘቱ ሸጋ ነው – የሙያዊ ግዴታህ መንፈስ ካላስፈነጠረው። እኔ ደግሞ ይገርምሃል ወንድምዬ የዚህ ተቃራኒ ነኝ። በመጀመሪያ ነገር „ኢህአድግ“ የሚባል ነገር የለም። ኖሮም አያውቅም። ያለው ቲፒኤልፍ የትግራይ ሀዝብ ነፃ አውጪ ነው። ይህ „ኢህአድግ“ የምትለው ማላጋጫ ልባጅ ነው ወይንም ለጠፍ። ወይንም እቃ እቃ መጫወቻ የእንቦይ ካብ።  ለዚህ አቀብት ቁልቁለት የሚያስወርድ ነገር የለውም። በነቂስ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የሚውቀው ጠሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው። በአንተ በታላቁ የተግባር አክቲቢስት ይህ ዕውቅና ወያኔ ማግኘቱ እጅግ ዕድለኛ ነው። በተከታታይነት ጭራዋን ይዞ በትጋት አፍኖ በያዘው ሰፊህ ህዝብ እዬሰረሰራ የሚገባ መርዝ አሳምሮና አስማምቶ ይረጭበታል። ለቀፎው የወያኔ ሚዲያና የጎሳ ጥመኞች ጥሩ አልጋ አዘጋጅተኽላቸዋል። በደሉ እራሱ፣ አስከዛሬ የፈሰሰው ደምና ዕንባ ሁሉም አፍ አውጥቶ ቢናገር ፍርዱ ዬት ላይ ሊሆን እንደሚችል ማዬት በተቻለ። …. ለነገሩ ትክለኛው የህሊና ዳኝነት ያለው በህዝብ የህሊና አደባባይ ስለሆነ ልተወው።

 

የማከብርህ ወንድሜ ጋዜጠኛ ፋሲል እንዲህ የቤታችሁ ሥራና ውጥረት መፈናፈኛ ሰጥቷችሁ ነው የወያኔ የመሬት ፖሊሲ አስጨንቆህ ድፍት ብለህ ስትጽፍ ያደረከው? ለዛውም ለማይመለከተን፣ ላልመከርንበት፣ ብስል ከቀሊል ለሚለይበት፣ ላልወሰንበት፣ በባይታወርነት ለምነቀጠቀጠበት የኢትዮጵያን ሙሉ የክብር አካል ለሚፈቀፍቅ ፖሊሲ። አጀብ ነው። ከቶ እኛን ምን አገባን?!

ጨዋታን ጨዋታ ያነሳዋል የሚል አንድ ብሂል አለ። አንድ ጊዜ ጠ/ ሚ ሃይለማርያም ደስአለኝ የሟቹን ሄሮድስ መለስ ዜናው ግዛታዊ ግቢ ሊረከቡ በነበረው የመሰናዶ ወቅት ጸሐፊ ተስፋዬ ገብሬ ድምጽ ሆነ ምስል በሚስጥር የሚቀርጽ ነገር በቤተመንግስቱ ወያኔ እንደሚያሰቀምጥ ማጠቀሻ መረጃ ጨምሮ ጽፎ ከረንት ከቤቴ አንብቤ ነበር።

ታዲያ እኔ እህትህ ያን ጊዜ እኛን ምን አገባን?  ….. ብዬ ከሥር ጠንከር ያለ ትችት መጻፌን አስተዋሳለሁ። አሁን ደግሞ አንተ መሰሉን ነው የምትነግረን። ግልጽነትህ መቼም የሚገዛ ቢሆን ቀዳሚ ተሰላፊዋ እኔ በሆንኩ በነበረ። ለዚህ ከልብ ለጥ ብዬ አስግዳለሁ – አመሰግናለሁ። ውስጥህን ፈቅደህ ማሳዬትህ የማይገኝ ነው። ወደ ዋናው ጉዳዬ ስመጣ ግን  እኛ ስለ አይሁደ የመሬት ስሪት ምን ዶል አደረገን? ስለ በቀለኛው ባንዳ የፖሊሲ አፈጻጸም ሳይጠሩንስ የምን ዝንቁል ነው? ለምንስ መቀላቀል አስፈለገ?

ግን መሬት የኢትዮጵያ የእኛ የምንለው አለን?! አሱን አጥተን መስሎኝ የተሰደድነው። መቼም አንተም እንደምታወቀው 90 ሚሊዮን ህዝብ ልሰደድም ልሸፍትም ቢል አይችልምና አሁንስ መፈናፈኛ አጥቶ ከቀዩ ስለሚፈናቀለው፤ ሞት ለተፈረደበት ሚሊዮን ወገንህስ ታሰረኸለት – ተሰደኸለት – መሰደድህ አልበቃ ብሎ የመጨረሻውን ፍርድ ተቀብለኸበት እንዴት ነው ነገሩ ….. ወንድምዬ? እኔ እህትህ እንድ ሥርጉተ ሥላሴ መንፈስና አቋም ግን የወያኔ ማናቸውም ፖሊሲ በለው፤ ህግ በለው፤ የአፈጻጻም ደንብ በለው፤ ህግ አርቃቂ አካል – አስፈጻሚ ተቋም፣ የዳኝነት ውሎ ድል ምንጥርስ ቅብጥርስ ከነምናምንቴው  ወዘተ ምኔም አይደለም። ቆራጣ ጊዜ አላባክንም። እኔይቱ ላለተርፍበት እማባክናት ብጣቂ ጊዜ የለችኝም። ወያኔ ታጥቆ ስለተናሳበት የጥፋት፤ የንደት፤ የውርስና ቅርስ ፍልሰት ጥብቅናም ልንቆምለት ይገባል ባይም ነኝ። የ40 ዐመቱ ጉዞና ግብዕቱ መሰረቱ አንድ ነው። የቲፒኤልኤፍ የጎጥ ማኒፌስቶ። በቃ! ከዚህ የሚያመልጥ የሰናፍጭ ታክል ነገር የለም። ሁሉም የሚመነጨው ወያኔ ከተነሳበት አላማ ነው። ማናቸውም ህግ በለው ፖሊሲው መርዝ ነው። ከዚህ በተረፈ ማንፌስቶውን የፈጠረውን „ብርቱ ሚስጢር“ እንደ እኔ እንደ ደንቆራዋና ምስኪን ሳይሆን እንደ ታሪክ ሙሁርነትህ፤  እንደ ጋዜጠኝነትህ እንደ ታላቅ የሚዲያ አስተዳዳሪነትህና ኤዲተርነትህ እባክንህን እናትዬ  ብትን አድርገህ መንፈስ ሰሌዳ ላይ አደላድላና ብልቱን አውጣው። መልሱን ታገኘዋለህ። ባለፈም እንደ እኔ ላላ ማህይም ህሊና ዘባ ሲል ጎባጣውን አቃንተህ ትገራበታለህ።

 

ወንድምአለም ቀድሞ ነገር ኢትዮጵያ ዕውን አለችን ነው ጥያቄው? ለመቶ አመት እኮ እየተቸበቸበች ነው? ከመቶ አመት በኋላም መሬቱ ዘር ስለመሰጠቱ መዳህኒአለም ይወቀው። ዛሬ እንዲህ ቅዱሳኑ ይከላተማሉ። ይሄውልህ ልጁህ ግልገሉን ይዞ መድረሻ አጥቶ እንዲህ ይንከራተትልሃል። ውሎ አድሮም ለትውልዱ ይህን ተከትሎ የሚመጣው ፍልሰትና ቀውስም ዕዳ ነው ልትሸከመው የማትችለው። ረመጥ እያደረ እዬፋመ እያገላበጠ የሚቀጣ ይህ ነው የተዶለተልህ።

ወይ ጉድ! ዘር እንዳይራባም እኮ ወያኔ መላ መቷል።   በታላቋ ትግራይ ህልም ደግሞ ከአፋር የደካ ጎንደርን ወሎም አለፍ ብሎ የአባይን ኣናት ጭምር ለመቆጣጠር እንዲያስችል ሌትና ቀን እዬተሰራበት ነው። መንገዱ ከጁቡቲ ትግራይ፤ ከሱዳን ትግራይ ጦፏል፤ እና …. ከአሲድ ጋር የሚያደራድረን ከቶ ምን ብናኝ  ነገር አለና?! — ቅድሚያ ነጻነት —- ንጹህ አዬር። ከሥጋት የጸዳ ባዕት —–

 

በወያኔ ፖሊሲ ለኢትዮጵውያን ለዛ መሬት ለተደፋበት ብዙኃን ተቆርቋሪ የሆነው የትኛው ተቋም፤ ድርጅት ከቶ የትኛው ነው? የትኛው ይሆን ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊ  የሚሸተው? ሰንደቅን የሚያደምጥ ፍላጎትና ዝንባሌ እስረኛ እኮ ነው። – በጠቅላላ የወያኔ ፍትረት የጠላትነት ነው። ለእኛዎቹ እኮ መስቀል አደባባይ የታጠረ ነው። ስለ አፓርታይድ የመሬት ፖሊሲ እንደ ፍጥርጥሩ እሱ ይፈናጠርበት ጎጠኛው ወያኔ … ለምርጫም – ለበጎ ነገርም – ለድርድር የሚያበቃን ነገር ቅንጣት የለም? የውጭ ባዕዳን ፍላጎት አስፈጻሚ የባንዳነት ተልዕኮ እኮ ነው የወያኔ ተግባር።

እርግጥ ነው እንደማንኛውም የጥበብ ሰው ቀድመው የሚያሰጉትን ነገሮች ማመላከት የተገባ ነው። ይህን አከብርልኃለሁ። ነገር ግን ሰለ ነገ የመሬት ድርሻ ወይንም የባለቤትነት ይዞታ አስጨንቆህ ከሆነ የምንፈልገው አይነት የዴሞክራሲ ሥርዓት ሲዘረጋ በህዝብ ድምጽ አዎንታዊ ይሁን አሉንታዊ ምላሽ ያገኛሉ። ድምጽ የሚመራት ሀገር ስትኖርን። የማትቦጫጨቅ የእኩልነት እናት ምድር ስትኖረን። ለዚህ ቢያበቃንም ችግሩ የአዬለ ስለሆነ በቂ ጊዜ፤ የሰከነ ጥናትና ተግባርን ይጠይቃል። እፍ ብላህ ከምድረ ገጽ የምታበነው ችግር አይጠብቅም …. ዳገት ነው -።

እናቴ እመቤቴ ልዕለቴ የሚል እረኛ ሲኖረን፤ ይህ ዝበትና አድሎዊነት ሁሉ ታርቆ በሂደት መልክ ይይዛል። ይስተካከል። ፕሬዚዳንት ክርሰቲና ክሪሸርን የአርጀንቲናዋን፤ ጠቅላይ ሚኒስተር አንጅላ ሜርክልን የጀርመኗን፤ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን ለሥልጣን ያበቀው ሥርዓቱ ስለተዘረጋ ብቻ ነው።

… የድካሙ የትግሉ አቅጣጫም ይህ መሆን አለበት እንጂ ይሄኛው ያኛው እያልን በሳቢያዎች ላይ የምናጠፋውና የምናባክነው ጊዜና ጉልበት ሊኖር አይገባም።  ዘላቂ የመፍትሄ ቁልፍ ሊሆን ከቶውም አይችልም። እንዴት ነው ነገሩ ኢትዮጵያ እራሷ አኮ እስረኛ ናት – የምን ቀልድ ነው!? ከወገብ በላይ ከወገብ በታች ብሎ ትግል የለም። የነፃነት እርቦ ሆነ ሲሶም የለም። ግድ የለህም ወንድምዬ እንስማማ። ምክንያትን እንፈልግ፤ የምክንያትን አቅጣጫ እንመትር በዛ ላይ አቅም የሚመትን ተግባር እንከውን …. ሳቢያን እንዝጋው – ቅርቅር አድርገን።

 

የማከብርህ ጋዜጠኛ ፋሲል እኔ በአቀረብካቸው የመሬት ይዞታ የፖሊሲ ትንታኔና አቅጣጫ ደንቆሮ ስለሆንኩኝ ባለሙያዎቹ እንደ አመጣጡ ይመክቱህ። ግን ጠላቴ ማን እንደሆን አውቃለሁ። የጠላቴ ፍላጎት እንብርት ምን እንደሆን ጠንቅቄ እረዳለሁ። ጠላቴ ለሀገሬ ኢትዮጵያ ያለውን ጠናና አመለካከት አሳምሬ እረዳለሁ። የበሽታው አጠቃላይ አስኳል ዬት ላይ እንዳለ ይገባኛል። በቀዶ ጥገናም ፈውስ እንደማይገኝ አምናለሁ። የመፍትሄው ቁልፍ ሂደት ወሳኙ አካል ምን ስለመሆኑም መንፈሴ በቂ ጥግ አለው።

በተጨማሪም አቅም ምን ላይ ሊፈስ እንደሚገባ ሆነ እንዲሁም ጉልበትና ሃይል ሊፈጥሩ የሚችሉ የመንፈስ ሃብቶች መሰናዶ  ምንና ምን  ሰለመሆናቸው ጠንቅቄ አውቃለሁ። ስለዚህም እላለሁ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ትንሳኤ የወያኔ ማንፌስቶና ፖሊሲ እሰከ ዝክንትል ጓዙ መነቀል አለበት የሚል ጽኑ እምነት አለኝ። ለቅርጥምጣሚ መላሾ የሥርጉተ መንፈስ አያደገድግም …. ኢትዮጵያ የመተንፈሻ ቧንቧዋን አፍኖ በጠላትነት እዬታገላት ያለው መጋኛ ወያኔ ሲወድቅ የቀደሙ ይሁን አሁን ያሉ፤ ወደፊትም ዘምን ሊፈጥራቸው የሚችሉ ችግሮች ሁሉ በመመካካር – በመደጋጋፍ – በመደማማጥ ፈቃዱ ሲሆን የተባረከው ቀን ሲመጣ ሁሉም ያለውን ይዞ እናቱን ከወደቀችበት ማጥ ለማውጣት በቅንነት ወስጥጡን ሰጥቶ የሚሳተፈበት ሥርዓት ሲፈጠር በጣም በእርግጠንነት ከኢትዮጵያውያን አቅምና ቁጥጥር በላይ የሚሆን አንዳችም ችግር አይኖርም።

 

የሚያስደስኝ በወያኔ ቅንጥብጣቢ መንፈሳቸው የማይደለል ጀግኖች ወጣቶች ኢትዮጵያ ላይ መኖራቸው። አይገርምህም ወያኔ ሲገባ ያልተወለዱ ልጆች የፈካ የተስፋ እርምጃ፤ የጎለበት አቅም፤ የራዕይ ጉልበት፤ የጸደቀ መንፈስ፤ የቁርጠኝነት ትንታግነት፤ የጥራት ልዕልና፤ የአስተሳሰብ ሥልጡነት፤ የመንገድ መረጣ ስልታማነት፤ የፈጠራ እርካብን – የአፈጻጻም ሂደቱ ለምነት፤ የሀገር ፍቅርና የአብሮነት ሰማዕትንት፤ እርግጠኝነትና በራስ የመተማማን ሙሉ ብቃት ሙቀቱ ከበቂ በላይ አጥጋቢ ነው። እነዚህ የትናንት እንቡጡች ወያኔ ሲገባ ታቱ ዥግራ ወይንም በእምዬ ትክሻ አንቀልባ የነበረቱ፤ ወይንም የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የነበሩት ራህብ ላይ ሆነው፤ አንጀታቸው ጠግቦ ሳያድር  „ሰንድቅአላማ“ በተሳረበት ዘመን አድገው፤ ትምህር ቤት ዜግነታቸውን የሚሸረሽር ሥልጠና እዬተሰጣቸው፤ ነገር ግን ያነን ሁሉ አሸንፈው „አትከፋፍሉን፤ አትለያዩን፤ አንድ ነን፣ አንድ ህዝብ፣ አንድ ሀገር“ ይላሉ ለዚህም ይታሰራሉ – ይገረፋሉ – ይሰደዳሉ፣ ይገለላሉ- ይወቀሳሉ – ተነጥለው ይጠቃሉ። ግን መከራውን እያሸነፉ ወደፊት እዬገሰገሱ ነው —- ከዚህ መርዛማ የወያኔ ዶክትሪን አምልጠው እኛን በተግባር እያስተማሩን ይገኛሉ። የትውልዱ መንፈስ ይህ ነው አድምጡን ይላሉ ጆሮም ህሊናም ከኖረን …..

በዚህ በምታዬው የክልል ሽንሸና የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ለመቅበር የተዶለተበት ነበር። ግን ኢትዮጵያዊነት ጠፍቶ የማይጠፋ የነገ ፍቱን መዳህኒት በመሆኑ የተጫነውን ድንጋይ ፈንቅሎ እዬፈካ በቀንበጦቻችን ታዬዋለህ …..

እኔ ውጪ ላላውም ወገኔ ቢሆን የተፈጠረበት ሚስጥር ነፃነት በመሆኑ ያገባኛል ባላበት ጉዳይ ሁሉ ተግቶ መሳተፉ፤ ሀገሩ ኢትዮጵያን በዬትኛውም አጋጣሚ ጎላ ብላ እንድትታይ መባተሉ፤ ክብሯ ሲነካ እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ በቁጣ ከጥንፍ አስከ ጥንፍ መነሳቱ – ከሌሎች ሀገሮች ጋር ሲነጻጻር ሚዛን ላይ ልታስቀምጠው የማትችል የበቃ – ብቃትን ታያለህ። እርግጥ ስደትና ትግል ሰፊ ፈተና በመሆኑ የሚታገሉን በተርካታ ነገሮች በመኖራቸው፤ በተጨማሪም ከድሉ መዘግዬት ከሚመጡ ጭብጦች ጋር ያሉ ወጣ ገብ ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው ማለቴ ግን ብርቱዎች ነን የእውነት።

ለዛውም አንተም እንደምታውቀው የፖለቲካ ትግል በትርፍ ሰዐታት ሰርተህ አይደለም ትርፍ የምታስገኘው። በመደበኛና በቋሚነት ተቀጥረህ የምትሰራው ሆኖ፤ ግን ነገር ግን ተስፋ የሚሰጡ ነገሮች ታያለህ። አንተ የምትደክምለት ሚዲያ ኢሳትም የዚህ ውጤት ነው።  በአጋጣሚ ስለሚዲያው ስለ ኢሳት ካነሳሁ በንጉሦች ንጉሥ ዐፄ ሚኒሊክ የልደት በዐል አስመልክቶ በተነሳው የሃሳብ በለው ድንበር ዘለል ጦርነት በነበራችሁ ውይይት በተጻራሪው ወገን የነበረውን ኮበሌ የሚመጥን ሰው አላቀረባችሁም ነበር። እባካችሁ የሚመክት ብቃትን በሃሳብ ማታገል አድማጭን ወደ በሰለ የሃሳብ መቀራርብ ያመጣልና ጥንቃቄ አድርጉበት። አቅም ማለት እኮ ሃሳብህን የሚሸምት ሰራዊት ማግኘት ማለት ነው።

 

እንድ መቋጫ ወንድሜ ጋዜጠኛ ፋሲል ሙሁራኖቹ ጭብጥን በጭብጥ ማህሏን እያስቀመጡ ይሟገቱህ።  እኔ ማሃይሟ ደግሞ በሀገር ወዳድነት ህልምና ናፍቆቴን ብቻ ስሜቴን አቅርቤ ሃሳቤን ገለጽኩኝ። ለነበረን ጊዜ ምስጋናዬ ከፍቅራዊ እክብሮት ጋር ላኩኝ። በተረፈ ክብረቶቼ ይሄውላችሁ ልጅ ፋሲል የማትመቸኝን ነገር ኮልኩሎ ለዛሬ ያቀድኳትን ጊዜ ተሻማኝ – እናንተንም አደከምኩ ከሳምንት በፊት ብቅ ላል ወስኜ ነበር — ለሰጣችሁኝ ጊዜ ውስጤን ፈቅጄ ሰጠኋችሁ። መልካም ጊዜ።

 

ከ አሲድ የሚገኝ ዘርም ፍሬም የለም!

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጥር!

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ!

 

 

 

Latest from Blog

ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop