የካቲት 16፣ 2014
እኛ፣ ስማችን ከታች የተዘረዘረው በውጭ የምንኖር ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ድርጅቶች እና ተቋማት፣ በኢትዮጵያ መንግሥት ወይም በአንዳንድ ምዕራባውያን አገራት ግፊት፣ አሸባሪዉ ትሕነግ በጉልበት ይዟቸው የነበሩትን የአማራ ቅርስ የሆኑትን ቦታዎች በድርድር ስም አሳልፎ ለመስጠት የሚደረገውን ጥረት ሁሉ አጥብቀን ለመቃወም ያለንን የማያወላውል አቋም ስናሳውቅ በማያሻማ ቆራጥነትና ፅናት ነው።
በስልጣን ላይ ባለው መንግሥት ዘንድ፣ በግልፅም ሆነ በሕቡዕ፣ እነዚህን ቦታዎች አሳልፎ ለትሕነግ ለመስጠት የሚደረግ ሙከራ፣ የኢትዮዽያን ልዕልና ለመጻረር፣ ብሎም የአማራውን ወገን ለማዳከም፣ በአገር ውስጥ ባሉ ፅንፈኞች እና በባዕዳን አካላት ከሚካሄድ አደገኛ ሴራ ተለይቶ ሊታይ እንደማይቻል ልናስገነዝብ እንወዳለን።
የአማራ ሕዝብ ቅርስ የሆኑት፣ በተለይም ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞንን እና ራያን የመሳሰሉት ቦታዎችን ለመደራደሪያ አቅርቦ ለመስጠት የሚቀርበውን ትርክት የሚደግፍ ታሪካዊም ሆነ ሕጋዊ መሠረት የሌለ መሆኑን በማያጠራጥር ሁኔታ አጥብቀን እናምናለን::
በዋናነትና በቅድሚያ፣ በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚኖረው አብዛኛው ሕዝብ፣ በማንነቱ ከአማራነት በስተቀር በሌላ ታውቆም ሆነ፣ በሌላ ወገን አስተዳደር ሥር ስለመኖሩ የሚያሳይ፣ መሠረት የያዘ ምንም አይነት የታሪክ ማስረጃ ኖሮ አያውቅም::
በአንፃሩ፣ ትሕነግ ለሠላሳ አመታት ያህል በጉልበት ይዟቸው የነበሩት ቦታዎች፣ ወደትግራይ ክልል እንዲጠቀለሉ የተደረገው፣ ኢትዮጵያን ቋንቋን መሠረት ባደረገ ፍረጃ የከፋፈለዉና የችግሮች ሁሉ መንስኤ የሆነው ሕገ መንግሥት ከመታወጁ በፊት ከመሆኑም በላይ፣ በጊዜው የነበረውን የራሱን የትሕነግን የሽግግር ቻርተር ሳይቀር የሚፃረር እርምጃ መሆኑ የተርጋገጠ ሃቅ ነው::
በአለፉት ሁለት አመታት፣ የኢትዮዽያ መንግሥት ለትግራይ ክልል ከመቶ ቢሊዮን ብር በላይ ሲያወጣ፣ ከትሕነግ ጭቆና አገዛዝ ለተላቀቁት ቦታዎች ግን የበጀት ድጋፍ መነሳቱ፣ ሁኔታዉን በከፍተኛት ዝብት፣ ቅሬታና ንዴት ስንመለከተው እንድንቆይ አድርጎናል።
የምዕራባውያን አገሮችም፣ የአማራው ሕዝብ ለደረሰበት ጉዳት ትኩረት ሳይሰጡ፣ የዚህ ሕዝብ ታሪካዊ ቅርስ የሆኑትነ ቦታዎች ለአሸባሪው ትሕነግ ተላልፎ እንዲሰጥ ከባድ ተፅእኖ ሲያደርጉ ይታያሉ:: በአጠቃላይ፣ ትሕነግ በኃይል እና በዕብሪት አስፋፍቶት ለነበረው ወሰን እውቅና መስጠት፣ የአካባቢዉን ነዋሪዎች ሰብአዊ መብት ከመጣስ አልፎ፣ ትሕነግ \ 2 ከሠላሳ ዓመታት በላይ ሲፈጽም የነበረዉን ግፍ እና በደል እንዲቀጥል ድጋፍ ተለይቶ ሊታይ አይችልም የሚል እምነት
አለን። ይህንን በተመለከተም፣ የአሁኑ የአሜሪካ አስተዳደር፣ ለትሕነግ ተስፋፊነት ጥያቄ የሚያደርገው ጥብቅና አድሎአዊና ኢፍትሃዊ በመሆኑ አበክረን እናወግዛለን።
ስለዚህ፣ ከዚህ በታች ስማችን የተዘረዘረው ድርጅቶች፣ የሚቀጥሉትን ጥሪዎች በአስቸኳይ ለማቅረብ እንወዳለን፤
1.ለፍትሕ እና እኩልነት የቆሙ ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ፣ ነጻ የወጡትን የአማራ ቦታዎች ለትሕነግ የግፍ አገዛዝ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፣ አሳልፎ ለመስጠት የሚኖረውን ማንኛውንም ጥረት አጥብቀው እንዲቃወሙ፤
2.በስልጣን ላይ ያለው ክልላዊም ሆነ ፌደራላዊ መንግሥት፣ ነጻ የወጡትን የአማራ ቦታዎች፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፣ ለትሕነግ የግፍ አገዛዝ አሳልፎ ለመስጠት ከሚደርገ ግፊት በአስቸኳይ እንዲቆጠብ፤
3.በመጨረሻም፣ አሜሪካና ሌሎች ምዕራብውያን አገሮች በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት፣ የተጠቀሱት አካባቢዎች፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፣ በትሕነግ አረመኔያዊ አገዛዝ ሥር እንደገና እንዲወድቁ የሚያደርጉትን ጥረት እንዲያቆሙ።
ፈራሚ ድርጅቶች
1. Adwa Great African Victory Association (AGAVA)
2. All Shewa Ethiopian People Multipurpose International Association
3. Amhara Dimtse Serechit
4. Amhara Wellbeing and Development Organization
5. Communities of Ethiopians in Finland
6. Ethio-Canadian Human Rights Association
7. Ethiopian-American Development Council (EADC)
8. Ethiopian Dialogue Forum (EDF)
9. International Ethiopian Women’s Organization (IEWO)
10. Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause
11. Global Alliance for the Rights of Ethiopians (GARE)
12. Global Amhara Coalition
13. Global Ethiopian Scholars Initiative (GESI)
14. Gonder Hibret for Ethiopian Unity
15. New York/New Jersey Tri-State Hope for Ethiopia, Inc. (H4E)
16. Major Lemma Woldetsadik Memorial Foundation
17. Menelik Hall Foundation
18. Network of Ethiopian Scholars (NES)
19. People To People, Inc. (P2P)
20. Radio Yenesew Ethiopia
21. Selassie Stand Up, Inc.
22. The Ethiopian Broadcast Group \ 2
23. Vision Ethiopia (VE)
24. Worldwide Ethiopian Civic Associations Network (WE-CAN