March 4, 2021
20 mins read

ባለቤቱን ካልናቁ ፤አጥሩን አይነቀንቁም !! – ማላጂ  

የሰሞኑ የአሜንስት ኢንተርናሽናል እና የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ መግለጫ መደጋገፉ የሚያሳየን ከተሰጣቸዉ መብት እና ድንበር ዉጭ ለመንቀሳቀስ የማይገዳቸዉ መሆኑን ከማሳየት በላይ ለራሳቸዉ እና ለአገራቸዉ የማይመኙትን በሌላዉ ዓለም ለመጫን ያላቸዉን ከንቱ ቅዠት ነዉ ፡፡

የዓለም ሠባዊ መብት ጠበቃ ነኝ ባይ እና ስሙኝ ባይ ጩኸቱ ለምን ዕድሜ ልክ ሰሚ ያጣ ቁራ መሆኑን እንኳን ቆም ብሎ ጠይቆ አያዉቅም ፡፡

አሳዳሪዉን የሚከተል አሳዳሪዉን ያመልካል እንጅ ምግባር እና ተግባር በሌለበት ስም ይዞ ጩኸቴን ቀሙኝ ማስተጋባት ልፋት ነዉ ፡፡

ለመሆኑ አሳዳሪዋ (አሜሪካ) ሆነ አገልጋይ አሜንስቲ ( አስቲ ስማ  ዓለም ) ዓለም ላይ ለሚደረገዉ ዕጅግ ለሚዘገንን የሰዉ ልጆች ስቃይ. መከራ ፣ ስደት እና ሞት መንስኤ ለሆኑት አምባገነን ታማኞቻቸዉ አይዞህ ባይ በመሆን የራሳቸዉን ጥቀም እና ስም ለማስከበር ከመተባበር እና ከማስተባበር ዉጭ ምን ሰርተዉ ይሆን ዛሬ በኢትዮጵያ የዉስጥ እና ሉዓላዊነት ጉዳይ  ላይ ፈራጅ እና ማላጅ ለመሆን የሚቃጣቸዉ ፡፡

አስከ ሁለቱንም ከንጉሰ ነግስት ኃ/ስላሴ አስከ አሁን የዕኛ ዘመን የነበራቸዉን እና ያላቸዉን አቋም እንይ( ዘመን እ.ኤ.አ ነዉ) ፡-

  • በቅኝ ግዛት ዋዜማም ሆነ ማግስት በሠዉ ልጆች ላይ በቀለም እና በድህነት ምክነያት ለደረሰ ግፍ እና በደል ሁለቱም አካላት ያሉትም ሆነ ያደረጉት ነገር የለም ፣
  • ኢትዮጵያ በኢጣሊ ወረራ ዓለም አቀፍ ጥሰት እና ወንጀል በሉዓላዊ ህዝብ እና አገር ይቁም በማለት ያቀረበችዉን አቤት ከምንም ባለመቁጠር  ይባስ ብለዉ ለወራሪዉ ድጋፍ እና ይሁንታ ሰጥተዋል፣
  • በዘመነ የአልገዛም ባይነት እና የነጻነት ትግል በግፍ ለሞቱት አዕላፍ ኢትዮጵያዉያን በአገራቸዉ ላይ ለደረሰባቸዉ በደል ይቅርታም ሆነ ከሳ ክፍያ የጠየቀ አካል አልነበረም ፤የለም ፣
  • ከድህረ ኢጣሊ ወረራ እና ማፈግፈግ በኋላ በእንግሊዝ ስዉር እጅ ለአገራቸዉ ነጻነት የተዋደቁትን ብሄራዊ አርበኞች የማዳከም እና የቅኝ ተገዥነትን እና አድር ባይነት አስተሳሰብ የማስረፅ ሴራ ተደግሷል ፤ ተከናዉኗል፣ብዙ የቁርጥ ቀን ልጆቿን ኢትዮጵያ በጥቅመኞች እና በአድር ባዮች ሴራ በግፍ በሞት እና በግዞት ተኘጥቃለች ፣
  • በግንቦት 1943 ከጣሊያን ሽንፈት ማግስት የትግራይ ህዝብ ነጻ አዉጭ አመፅ መስራች እና መሪ ኃ/ማርያም ረዳ በንጉሱ ላይ ሲያሳምፁ የነበረዉን ስርዓት ለማስቀጠል አሜሪካ ደግፋለች በወቅቱ መጠነኛ የሚባል ሠባዊ ቀዉስ ተከስቷል ነገር ግን አስቲ ስማ ዓለም ያለዉ የለም፤ቢልም አይሰማም፣
  • እ.ኤ.አ.ከ 161 አስከ 1974 በነበረ የተለያየ የህዝብ የመብት ጥያቄ በተለይም በጎጃም አርሶ አደር የተነሳዉን አመፅ ለማዳፈን ከፍተኛ ዕገዛ በማድረግ አሜሪካ ግንባር ቀደም ናት፣
  • እ.ኤ.አ. በ1974 መስከረም 12(2/1967 ዓ.ም) በፊት እና በኋላ የኢትዮጵያን አንድነት እና ሉዓላዊነት አደጋ ዉስጥ ለመጣል ከሚሰሩት የዉስጥ እና የዉጭ ኃይሎች ጋር በተለያየ ዘዴ የማበረታታት ድጋፍ ሲሰጥ የነበረዉ በነዚሁ አካላት እንደነበር ታሪክ እና ዕዉነት ይናገራሉ፣
  • የሶማሊ (መቃዲሾ) በዕብሪተኛዉ ዚያድባሪ ቅዠት እና ቀቢፀ ተስፋ ምኞት የነበረዉን አጋጣሚ ለመጠቀም ለወረራ ሲነሳ እንደዛሬዋ ሱዳን በማን አለብኝነት እና በታሪካዊ የዉስጥ ጥገኞች እና በዉጭ እና ሩቅ አሳዳሪዎች አይዞህ ባይነት ከፍተኛ እና ምን አልባትም በአፍሪካ ሉዓላዊ አገራት መካከል የተደረገ ከፍተኛ ዋጋ ያስከፈለ ጦርነት ሲደገስ እና ሲቀደስ የዛሬ አዞ አንቢዎችያንጊዜ ነበሩ ፤ነገር ግን ትብብራቸዉ ከአምባገነኖች እና ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ነበር ፣
  • የኢትዮጵያ መንግስት አስቀድሞ ለአገር መከላከያ መሳሪያ ግዥ የከፈለዉን ገንዘብ ሆነ መሳሪያ በሶማሊያ ወረራ ጊዜ እንዳያገኝ እና ባዶ እጅ በመነበር አሜን ብሎ ጥቃት እና ሞት እንዲቀበል የተወሰነበት በዛሬ አዞ ዕንባ በሚተናነቃቸዉ ነዉ፣
  • በዚህ ክህደት የተነሳም በወቅቱ የነበረዉ መንግስት ወደ ህብረተሰባዊ አስተዳደር ፊቱን በማዞር ቀድሞዉን ለሶማሊያ ድጋፍ ታደርግ ለነበር ራሽያ የመሳሪያ ጥያቄ እና የኃይል አሰላፍ ስልት መዛወር ግድ የሚል የወቅቱ አሳሳቢ በመሆኑ በዕንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ቀጥታ ብቀላ በአዲስ መልክ መጀመሯን ከተለያዩ ድርሳናት ይማሯል፣
  • እ.ኤ.አ. 1991 ዓ.ም. የኢህዴግ /ትህነግ ኃይል በጓዳ በር እንደ በጎ ዕንግዳ ሰተጥ ብሎ በሚያቀለሸልሸዉ ብሄዊ የሚኒሊክ ቤተ መንግስት ተጎትቶ የገባዉ በእነዚህ ባለአደራዎች መሆኑን በጊዜዉ የነበረ መሪር ዕዉነት ነበር ፣
  • ያ ሳይበቃ ያለምንም የኢትዮጵያ ህዝብ ተሳትፎ እና ይሁንታ አገር ያለድንበር፣ ባህር በር እና ያለክብር ዕንድትዋረድ ህዝብ ለዓመታት በራሱ አገር ባይተዋር እንዲሆን የሚያደርጉ የክፉ አስተዳደር አሚኬላ እንዲተከል ሲሆን ሠባዊ ክብር ያሳስበናል የሚለዉ አካል ያደረገዉ የለም ፣
  • ቀጥሎም በህዝብ ላይ ሊነገር ቀርቶ ሊታሰብ የማይችል በደል ከመብት አስከ ሞት የደረሰ (ይህም ከግንቦት 20/1983 ዓ.ም አስከ አሁን ዕለት ያለዉ) ያላሳሰባቸዉ ዛሬ ምን አይተዉ ፤ምን ሰምተዉ ስለሰባዊ እና ግዛት አስተዳደር እንዳሳሰባቸዉ ባናዉቅም ድሮም ዕዉነት እና ሠባዊነት ሳይሆን ስሙን አለን ለማለት እንደሆነ አመላካች ነዉ ፡፡

የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ከሱዳን ከሳ ሲያገኝ ፣ መካከለኛዉ ምስራቅ አንድ ዜጋ ሲሞትበት ዕሳት የሚወረወር፣ የመን ላይ ያለዉ የዕሳት ወላፈን አገሪቷን ምደረ በዳ ሲያደርግ፣ የሶሪያ ዕሳት ሲቀጣጠል፣ እነ ፓኪስታን በታሊባን ሲናጡ ፣ ሊቢያ የጦርነት አዉድማ ስትሆን ለሚያይ ዓለም …… ይህ ሁሉ ማን የረገጠዉ ምድር ነዉ ከህይዎት ወደ ዓመድ ያደረሰዉ ስንል መልሱን ለዓለም እና ዕዉነተኛ ዳኛ ይተዉ ፡፡

ነገር ግን ይህ ሁሉ ባለበት ሠባዊነት የሌለዉ አካል በሠባዊ መብት ተቋም ስም በኢትዮጵያ እና ህዝቧ የዉስጥ ጉዳይ በመፈትፈት ተጠሪ፣ አጣሪ፣ መርማሪ እና አስተማሪ የሚሆነዉ ፡፡

እኛን የሚያሳዝን እንበለዉ የሚያሳፍር አስኪ መቸም ከአነጋገር ይፈረዳል ፤ ከአለባበስ ይቀደዳል እንዲሉ አበዉ  ከመሰረታዊ ነገሩ ይጀመር ፡፡

፩) ሁለቱ  የዓለም ሰባዊ መብት አለኝታ ነኝ ባይ / አሜንስቲ ( ስሙኝ አስቲ ) እና አሜሪካ የኢትጵያ ልዩ ኃይል ወይም አጎራባች ክልል ኃይል እና የኤርትራ ጦር ከትግራይ ይዉጣ ነዉ ያሉት ለምን እና እንዴት ይህን እናዳሉት ግን አላስረዱም /አላብራሩም ፣

) ኢትዮጵያን ለመርዳት  ኢትዮጵያን መግፋት እንዳያማህ ጥራዉ ፤እንዳይበላ ግፈዉ ካልሆነ ይህ ሠባዊነትም ዓለማቀፋዊነትም ሳይሆን ተጨፈኑ ላሞኛችሁ ዳግም ደባ ነዉ ፣

) የዉስጥ ምንዱባኖች እና የኢትዮጵያን አንድነት ፣ ዕድገት ፣ብልጽግና እና ገናናነት የሚያማቸዉ ኢትዮጵያዉያን ዳር ድንበራቸዉን ፣ ማንነታቸዉን እና ህይዋታቸዉን በግፍ ለዓመታት ሲነጠቁ  የሚደሰቱ የነበሩ ዛሬ በሞት ዋጋ ህልናቸዉን ሲያረጋግጡ የሚያማቸዉ ለአፍታ እንኳን ዕዉነትን አይደፍሯትም ፤አይሞክሯትም ፡፡

ርግጥ ነዉ የህዝብ ፣ የማዕከላዊ መንገስትም ሆነ የክልል አስተዳደር የሰጠዉ ምላሽ ህዝብ የሚያስደስት ጠላትን እና የኢትዮጵያዉያንን ህብረት እና አንድነት ለማይዱት አሁንንም የእግር እሳት ግብረ መልስ ነዉ ፡፡

ግን በእኛ በኢትዮጵያዉያን ጨዋነት በአሜሪካም ሆነ በዓለም አቀፍ ሠባዊ መብት ተቋም ስም የተለየ ተልዕኮ ባላቸዉ ቡድኖች እና ግለሰቦች በአገሪቷ፣ በህዝቧ እና የአገሪቷን ሉዓላዊነት ለማስቀጠል የህይወት እና የደም ዋጋ በከፈሉት ኢትዮጵያዉያን እና ወዳጆች ላይ ከፍተኛ የጥላቻ እና ንቀት መልዕክት ማስተላለፋቸዉ ሳይበቃ ጣልቃ ገብነቱን ሳንዘነጋ በህግም ሆነ በግብረገብነት/ሞራል ረገድ ለጥፋተኛ እና ህገ ወጥነት ሽፋን፣ ከለላ እና ዕዉቅና የመስጠት ያህል መተላለፍ ስተዉሏል ፡፡ ይህም ፡-

፩ኛ) የኤርትራ መንግስት ሠራዊት በኢትዮጵያ ምድር/ጋዛት ይኑር አይኑር ማረጋገጫ መስጠት ያለበት የኢትዮጵያ ማዕከላዊ መነግስ ሲሆን ከየት እናዳመጡት እና ይህም ቀጥታ የፖለቲካ ጉዳይ እንጅ ሠባዊነት አገልግሎት ባለመሆኑ፣

ኛ) የኤርትራ ጦር /ኃይል ከትግራይ ግዛት /ክልል ይዉጣ ማለት አገላለፁ አደገኛ እና መርዘኛ  ይዘት ያለበት መሆኑ፣

ኛ) በተራ ቁጥር የኤርትራ የጦር ኃይል  ከኢትዮጵያ ይዉጣ ሳይሆን ከትግራይ ይዉጣ ማለት የኢትዮጵያንም ሆነ የኤርትራን ዓለመቃፋዊ ፣ አህጉራዊ እና ብሄራዊ ክብር እና ዳር ድንበር  የሚጻረር መልዕክት ስለሚያስተጋባ ፣

ኛ) የሌላ ሉዓላዊት አገር ኃይል ወደ አንዲት ሉዓላዊት አገር- ኢትዮጵያ- የገባ እንደሆን ማንኛዉም አካል እና ያገባኛል ባይ ማሳወቅ ያለበት ለኢትዮጵያ እና ለሚመለከተዉ ሌላ ሉዓላዊ አገር እንጅ ለሶስተኛ እና ለማይመለከተዉ አገር ማሳወቅ ይህ አስተሳሰቡም መሰረቱም፣ ምንነቱም በማር የተለወሰ መርዝ ነዉ፣

ኛ) የአንዲት ሉዓላዊት አገር ዳር ድንበር ተጥሷል፣ ህዝብ በባዕድ አገር ተይዟል የሚል አካል የአስተዳደር እና የዉስጥ ጉዳይ እንደመሆኑ ጠያቂነት የሠባዊ ጉዳይ፣ ተጠያቂነት የመንግስት ጉዳይ፣ዳኝነት የሌላ እና የማይመለከተዉ አገር ማድረግ  ትክክልም እዉነትም ስለማይሆን ፣

ኛ) ሱዳን ልክ ሱማሊ በ1960/1970 ዎች ዓ.ም. እንዳደረገችዉ እና የዛሬወች የአዞ ዕንባ የሚያሰቃያቸዉ ዕንደሚያዉቁት የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ድሆች እና በሞት እና ህይዎት መካከል የሚያጣጥሩ ደካሞች ናቸዉ ብለዉ ከዳር ሆነዉ ብትር የሚያብሉት ሱዳን የገደለችዉን ገድላ ፣ የቻለችዉን ዘርፋ ፣ ያወደመችዉን አዉድማ የኢትዮጵያን ግዛት ተቆጣጥራ አስፍታ እና ተነሰራፍት ጦር አምጣ እያለች መሬት ትደበድባለች

ኛ) ዚያ ድባሪ እና የመቋዲሾ መንግስት ያደረገዉ ይህን ነበር (ታሪክን ማወቅም ሆነ አለማወቅ እንዲህ ነወ…….)፣

ኛ) ይህ ሁሉ ግፍ እና በደል በኢትዮጵያዉያን የሆነዉ እና ዕየሆነ ያለዉ በታሪካዊ ጠላቶች ደባ መሆኑን የሚያዉቅ ያዉቀዋል ግን የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም ዚያድባሪም ሆኑ አልበሽር ኢትዮጵያን ከሩቅ አሳዳሪዎቻቸዉ  የጥፋት ዕሳት እየተቀበሉ ወደ ኢትዮጵያ ቢወረዉሩም  የጥፋት ዕሳት መልሶ ሲያጠፋ እንጅ ዕዉነኛ ማንነትን ለሚይዝ ብስለት እና ጉልበት ይሆናል፣

ኛ) የ…. ክልል ኃይል ጋር ሠባዊ ዕርዳታ እና አዛኝ ቅቤ አንጓች ዓለም ነን ባዮች ምን አገናኛቸዉ ፡ እንዴትስ አንድ ሉዓላዊት አገር(አሜሪካ) የምስራቅ አፍሪካ የዶላር ድሃ የማንነት እና ታሪካዊ ሀብት አገር ባለፀጋ አገር የአካባቢ ህዝባዊ ኃይል ምን አሳስቧትይሆን  በመንግስት እና ህዝብ መኃል  ሸምጋይ መሆን……መምጣቱንስ እሽ ….ግን ምን አስበዉ ይሆን አባ ጅቦ …አለች …….

ኛ) የዓለም ሠባዊ…… እና አሜሪካ የሱዳንን ወረራ እና ሠባዊ ጥሰት እኛ የጦር ወንጀል……. አይተዉ እንዳላዩ ማለፍ የሚታወቅ እና የሚጠበቅ ስለሆነ ለእኛ ለኢትዮጵያዉያን ራስን፣ አገርን እና ዳር ድንበርን በአብሮነት እና በአንድነት በተጠንቀቅ ከመጠበቅ ዉጭ ከዚህ ዓለም ምንም ዕዉነተኛ ነገር መጠበቅ የትናንቱን ስህተት መድገም እና ራስን ለባርነት አሳልፎ መስጠት ስለሚሆን በንቃት እንታጠቅ ፡፡

በመጨረሻም በአንዲት ልዑላዊት አገር እና ህዝብ የዉስጥ ጉዳይ አንድን አካባቢ ልላዊ ግዛት በማድረግ ዕዉቅና የመስጠት እና የህዝብ እና የመንግስት ብሄራዊ ጥቅም ፣ መብት  እና ኃላፊነት  በመጋፋት በኢትዮጵያዉያን የደም፣ አጥንት እና የህይዎት መስዋዕትነት የተገነባች አንዲት አገር ለማዳከም እና የራሳቸዉን ፍላጎት ለመጫን ለሚጥሩት አካላት በመንግስት እና ህዝብ  ላይ ለዳረሱት ጥፋት እና በደል ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል ፡፡

ለዓመታት የደረሰዉን የዜጎች ሰቆቃ ለማስቀጠል ፣ ብሄራዊ ዳር ድንበርን ለማፍረስ ፣ እንዲሁም ትናንት የባህር በር ያሳጡንን ዛሬ ደግሞ ቀሪዋን ኢትዮጵያ ለማፍረስ ድንጊያ ለሚፈነቅሉት እና ቅጠል ለሚበጥሱት ከትናንት ስህተታችን ተምረን ትናንት ዛሬ አለመሆኑን በተባበረ ክንድ እና ዉህድ ዓላማ ልናረዳቸዉ ይገባል ፡፡

                     ማላጂ    “ ኢትዮጵያ ባለታሪክ ብቻ ሳትሆን ዳግም ታሪክ መስራት የሚችል ትዉልድ ምድር ናት   !!

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop