ህዳር ፳፫ ቀን ፪፲፫. ዓ.ም.
በሰሞነኛዉ አገራችንና እና ህዝቧን የገጠማቸዉ ፈተና ልክ እንደ ብዙ ኢትዮጵያዉያን ለዓመታት የነበረባቸዉን የሠላም እና ደህንነት ዕጦት ለሳምንታት የትግራይ እና አካባቢ ህዝብ የደረሰበት አሳኝ እና አስደንጋጭ የነበር እና በአሁኑ ጊዜ አንጻራዊ መረጋጋት መኖሩ ፤ይህም በቁርጥ ቀን ልጆች የህይወት እና ደም ዋጋ የተገኘ የመጀመሪያ ብሄራዊ ድል ጉዞ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ሆኖም የተለኮሰዉን አገርን እና ህዝብን አደጋ ላይ የሚጥል የጥፋት እሳት ከአካባቢዉ መዲና“ መቋለ/ መቀሌ ” መግፋት እሳት ማጥፋት ስላልሆነ እንደ መጨረሻ እና ሁነኛ ድል አድርጎ የማይመጥን አድናቆትም ሆነ ቸልተኝነት(ንቀት) የተዳፈነ እሳት መኖሩን መርሳት እንዳይሆን ሊሰመርበት ፤ሊታሰብበት ይገባል፡፡
አድናቆት እና ንቀት በእኛ አገር ልማድ ከሠዉነት እና ከዕዉነት የሚያራርቁ እና የማይታረቁ በስሜት እና በአስመሳይ አገልጋይነት የሚጋረዱ አዘናጊ እና አስጊ መሆናቸዉ ለአፍታም ችላ ሊባሉ አይገባም ፡፡
ዛሬ ህዝብ እና ከህዝብ አጋም እና ቁልቋል የሚያደርግ እና የሚያስለቅስ አሜኬላ ሳይነቀል እና እንክርዳድ ከስንዴዉ ባልተለየበት በአድናቆትም ሆነ በቸልተኝነት መዘናጋት እና ጊዜ ማጥፋት ወቅቱ የሚጠይቀዉን ዝግጅት እና ጥረት የማስተጓጎል ዕንቅፋት እንዳይሆን እየተስተዋለ መሆን አለበት ፡፡
ህዝብ እና መንግስት ከልክ ባለፈ ግፊት እና መገደድ የገባበት አገርን ከፍርሰት ህዝብን ከፍልሰት ፣ስደት እና ሞት ለመታደግ የተደረገዉ እና በሂደት የሚኖረዉ ትንቅንቅ ትንፋሽ ለማግኘት እና ህብረትን ለማጠንከር ካልሆነ በቀር በአዉሎ ነፋስ የተረጨ የጥፋት እሳት ከተነሳበት አስከ አስከሚገኝበት ሳይጠፋ በተገኘዉ የሁለተኛ ክፍል/ምዕራፍ ድል መደነቅ /መደመም አገራዊ ጉዳዩን ቸል የማለት እና አሁንም ይህ“ ቁጭ ብሎ የሰቀሉት ቆሞ ለማዉረድ ” ወይም በሌላ አገላለጽ “ሰዶ ማሳደድ ካማረህ ዶሮህን በቆቅ ” እንዳይሆን በረጅም እና በስፋት ሊታሰብበት ይገባል፡፡
እዚህ ጋ ሁላችን ልብ የምንለዉ የአካባቢዉን መዲና ከጦርነት ቀጠና ማላቀቅ የብሄራዊ አንድነት እና ደህንነት የማረጋገጥ ሂደት እንጅ የህዝብ እና መንግስት የመነሻ ዕቅድም ሆነ መዳረሻ ግብ ይህም ሶስተኛዉ ምዕራፍ የጥፋት ዕሳት እጅን መያዝ ፣ማምከን ወይም ማጥፋት ካልሆነ አስካሁን ዕለት ከተከፈለ ዋጋ በላይ የተራዘመ ተጨማሪ መስዋዕት የሚጠይቅ እንዳይሆን ሁሉም ወገን ሊያስብበት ይገባል፡፡
የትኛዉም ወገን ለራሱ የሚያስብ ከሆነ ለሌላዉ አለማሰብ የሚነደዉ እሳት ከርሱ አልፎ ለሌላዉ መትረፉን ለሀጥያን የተባለ ለጻድቃን ይደርሳል ነዉና ሊያስብ ሊያገናዝብ ይገባል፡፡
ይህ በሚያልፍ ጊዜ እና ሁኔታ ጥፋተኞች ጥፋታቸዉን ተቀብለዉ ለዚህም ኃላፊነት ወስደዉ ህዝብ እና አገር አሳርፈዉ ቢያልፉ ለሚወዱት ወገን እና ህዝብ ታሪክ ሰርቶ የማዉረስ እንዲሁም ለመጭዉ ትዉልድ አስተማሪ እና መካሪ በመሆን የጎዱትን መካስ ስለሚሆን ይህን አሁንም ሳይዘገዩ ሊገነዘቡት ቢችሉ ምንኛ መልካም በሆነ ነበር ፡፡
“ማላጅ ”
እናት አገር ለምንጊዜም ትኑር !!!