ትናንት በህዝብ ተወካዮች 6ኛ ዓመት 5ኛ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዙር አስቸኳይ ስብሰባ መልካም እና በኢትዮጵያ አቋም ላይ ጠንከር ያለ እና ህዝባዊ ንቅናቄ የሚፈጥር ሃሳብ እና አስተያየት በጠቅላይ ሚ /ር ዓብይ አህመድ መገለጥ እና ይህን መስማት የሚያስደስት ነበር ፤የሚመረዉ ባይታጣም ፡፡
በበዓለ ሲመታቸዉ የተናገሩትን አሁንም የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ላይ የሰነዘሩትን ቃል ዳግም አረጋግጠዋል ይህም ብዙዎችን አስደንግጥ ፤ አንቀጥቅጥ እንደነበር አይጠረጠርም ፡፡ እዚህ ጋ ብዙ ስንል ጠላት ብዙ መልክ እና ጠባይ ስላለዉ በመጠን ጥቂት አይባልም፤በዉጤቱም አይናቅም ፤እንዲሁ አይታወቅም ፡፡
ነገር ግን መንግስት የሚነግረን የኢትዮጵያ ህዝብ ለረጅም ዓመታት የሚያዉቀዉን እና ሳይቃጠል በቅጠል እርምጃ ይወሰድ ያለበትን እያስታወስን ያልተገፀዉን እና ድብቅ የሆነዉን መግለፅ ለላቀ ብሄራዊ አንድነት እና ተግባቦት ወሳኝ ፋይዳ ያስገኛል የሚል ምልከታ አለን ፡፡
በትህነግ የበላይነት እና መልካም ፈቃድ ብቻ ሁሉ ነገር እንዲሆን የነበረዉ ፍላጎት የረጅም ዓመት ልምድ እና ሴራ እንደነበር ህዝብ አንገሽግሾት ነጻነት ወይ ሞት ብሎ የተነሳዉ ከ1966 ዓ.ም በኋላ በ1980ዎች አጋማሽ አካባቢ በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች የነበረዉን ትግል አስከ 2008 ዓ.ም ቀጥሎ ያየንዉ እዉነት ነዉ ፡፡
ይህን አለመዘከር የአዋጁን በጆሮ (ሚስጢር) ማድረግ እንደመሞከርም እንዳይሆን ለፅኑ ብሄራዊ ህብረት እና አንድነት እዉነት እየተነቀሰ መዉጣት እና በየስፍራዉ እንደአረም የተንሰራፋዉ ዉሸት እና ክህደት እየተነቀለ መድረቅ እና መሞት አለበት ፡፡
ለዚህም የትህነግ እና ግብረ አበሮች የሽብር ድርጊት ፣ አገር ክህደት እና ዘር ፍጅት የመሳሰሉት የጥፋት ድርጊቶች ድምር የሁለት ዓመት 114 ሲሆን የ27 ዓመታት ስንት እንደነበር ስሌት ሳይገባ በምድር ላይ የነበረዉ ሀቅ ግን ምን እንደነበር ሊታለፍ የሚገባ አይሆንም ፡፡
የጥቅምት 24፣2013 ዓ.ም. በትህነግ በእሳት እንጫወት የጥፋት ጥሪ ጅምር አገርን ከመበታተን ህዝብን ከመባዘን ለመታደግ የተደረገዉ ትንቅንቅ በመንግስት እና ህዝብ የጋራ ጥረት ቢረግብም ዓይነቱን እና ስልቱን ቀይሮ እንዳያገረሽ ጥብቅ ትኩረት እንደሚጠይቅ ለአፍታ መዘናጋት እንዳይኖር በሁሉም ረገድ ሊታሰብበት ይገባል ፡፡
ሌላዉ ለነበረዉ አገርን ከጥፋት ለመታደግ የመንግስትን እና የህዝብን የመከላከል ህብረት ያስተሳሰረዉ የመጨረሻዎች ትንኮሳ መከላከያን እና የዓማራ ክልል ወረራራ ሙከራ እንደሆነ በመንግስት ተገልጧል ፡፡
እዚህ ጋ ሁሉም ኢትዮጵዉያን በግልፅ እና በማያሻማ ቋንቋ ነገሮችን እንድናዉቅ ይጠበቅብናል፡፡
ለሠዉ ልጅ ደህነት እና ለአገር ሉዓላዊነት ግድ የማይላቸዉ ግለሰቦች ሆኑ ቡድኖች ሠራዊቱን መተንኮስ አገር እና ህዝብ ወደ ማያባራ የርስ በርስ መታመስ እና መተራመስ ሲገቡ የራስን ግዛት እና አጥር የመመስረት የዘመናት ቀቢፀ ተስፋ የጠላትነት ምኞት እንደነበር ህዝብ እና አገር የሚያዉቀዉ ቢሆንም በዘመናችን ላለዉ ትዉልድ ዳግም ሊረጋገጥለት ይገባል፡፡
ከዚህ ሌላ የዓማራ ክልል ወረራ የሚባለዉ ለ27 ዓመት የነበረዉ አገላለፅ ቀርቶ“ አገረ ኢትዮጵያን ሽርሸራ ፣ቡርቦራ እና ወረራ ሴራ ”በሚል ቢገለፅ ኑሮ ምንኛ የጠላትን ክፉ ሞኞት እና ስሜት ሊያረክስ እና ሊያከስም በቻለ ነበር ፡፡
በማንኛዉም ህዝብ ከመንግስት ወቅታዊ እና አሁናዊ የነበሩ እና ያሉ ድብቅ እዉነታወችን ሲጠብቅ መንግስትም ለአገር እና ህዝብ ወሳኝ በሚባሉ ነገሮች ላይ ጆሮዉን ለመስማት፣ ያለዉን አቅም ለህዝብ ለማገልገል መዘጋጀት እና የሚገጥሙትን ክስተቶች የማሳወቅ ኃላፊነት እንዳለበት በመገንዘብ ለብሄራዊ ችግሮች ብሄራዊ መፍትሄ ማግኘት በማስቻል በአገርኛዉ “ሳይቃጠል በቅጠል ” ከብዙ ድካም ያድናል ለምንጊዜም ፤ለሁሉም ይበጃል እንላለን ፡፡
ማላጂ
እናት አገር ለምንጊዜም ትኑር !!!