November 3, 2020
8 mins read

ከሞትንማ ቆይተናል!!! –    ማላጂ

እኛ ድህነትን ለመቀነስ ሳይሆን ድህነትን ማባባስ ስለመሰራቱ ብዙ ብዙ ሊጠቀስ ይችላል ፡፡

እንዲያዉም ድህነት ቅነሳ ማለት ድሃን(ለፍቶ/ሰርቶ  አዳሪን)  ማሳደድ ከሆነ ዓመታት አስቆጥረናል፡፡

ለዚህም መነሻየ በ ምዕራብ  ወለጋ ታይቶ በማይታወቅ ምን አልባት በአረሲ አርባጉጉ ከተደረገዉ የአንድ ጊዜ ጅምላ ግድያ የ1980ዎች የሚመሳሰል ግድያ በዜጎች መፈፀሙ መስማት ነዉ ፡፡

ነገሩን አዲስ የሚያደርገዉ  የህዝብ ሞት ሳይሆን የአገር ሞት እንዴት አገርን አያሳስበዉም የሚለዉ ነዉ ፡፡

አገር ሲሞት አገር እና መንግስት ከትናንቱ ሞት እና ጥፋት አለመማር ምን ሊባል ነዉ ፡፡

ይህ የሰባዊነት ጉዳይ ሳይሆን የተጠያቂነት ጉዳይ መሆን አለበት ፡፡ አስከ መቸ መርዶ እና ወሬ ነጋሪ ሆኖ መንግስት ይቀጥላል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ጎረቢትም መንግስትም አይጣለትም የሚባለዉ አስከ መቸ ነዉ ፡፡ ይህ ህዝብ በሰለጠነዉ ዓለም ሀዲድ ጋር መሳፈር እና መኖር ሲገባዉ የራሱ ተወካዮች ጠላት እና ወዳጅ አድርገዉ ከማገልገል መገልገልን የመንግስት መብት ማድረጋቸዉ አስከመቸ ይቀጥላል ፡፡ ለዚህ ክምሩ በአጭሩ የኢህዴግ ህለዉና እንደሚከተለዉ መጭለፍ/መጥቀስ  ይቻላል ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ሰሜን ምዕራብ ክፍለ ሀገራት ህዝቦች ከየትኛዉም የአገራችን ህዝቦች በላቀ ሁኔታ ፊዉታራሪነት ቀድሞ የነበረዉን የኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም አስተዳደር በወቅቱ ከነበረዉ ሁኔታ አኳያ አምርሮ ይታገለዉ ነበር ፡፡ በዚህ መራር ትግል ስርዓቱን ገርስሷል መንበረ ስልጣኑን ለኢሀዴግ አስረክቧል፡፡

ይህን እርሳቸዉ የቀድሟዋ ታላቋ ኢትዮጵያ መሪ / ሊቀመንበር መንግስቱ ኃይለማርያም እና ነባር ጓዶቻቸዉ የሚመሰክሩት እዉነታ ነዉ ፡፡  ነገር ግን ኅዝቡ በስርዓቱ ጉያ በተወሸቁ አድር ባይ የዉስጥ ቅጥረኞች እና የዛሬ የይስሙላ ተራማጆች በህዝብ ላይ ያደርሱ የነበሩት እነኝህ ተቀጽላዎች አማካኝነት ይደርስበት በነበር የአስተዳደር በደል የተነሳ ስርዓቱን ለማዳካም እና የዛሬ ጠላቱን የጠላቴ ጠላት ወዳጀ ነዉ በሚል አጉል ብሂል ጎትቶ እና መርቶ አስገብቷል ፡፡

ሆኖም ዉለታ ቢሱ ኢሀዴግ /ህዋሀት የዚህን ህዝብ ዉለታ ሳይዘገይ አዲስ አበባ ከገባበት ግንቦት 20 1983 ዓ.ም.ጀምሮ በግላጭ መንገድ የተመራበትን እና  የጎረሰበትን እጅ ለመነከስ ጊዜ አላጠፋም፡፡

እንግዲህ ይህን ህዝብ ነዉ ለመንግስት እና ክልል ምስረታ ባለማሳተፍ የተጀመረዉ ማግለል እና በደል እያደገ መጥቶ በመላዉ አገሪቷ ክፍል  የሚገኘዉን ቅሪት ህዝብ የማሳደድ ተግባር አጠናክሮ ከመሰል ግብር አበሮች ጋር እያካሄደ ያለዉ ፡፡

ይህ ከሽግግር መንግስት፣ ከህገ መንግስት እና ክልል አደረጃጀት ወቅት የጀመረዉ የማግለል እና በደል ድርጊት ዛሬ ላይ ቀጥሎ ማየት አዲስ ባይሆንም ከ 2010 ዓ.ም የለዉጥ ጊዜ አንስቶ እንደ ገና ማገርሸት ግን በለዉጥ ስም ያልተለወጡ እና በህዝብ የሚያላግጡ መኖራቸዉ ነዉ ፡፡

ብሄራዊ የችግር ምንጭ እና አካል የችግር ፈች አካል ማድረግ በተግባርም ሆነ በተግባር ከለዉጥ ይልቅ የመገላበጥ ዕድል ፈጥሯል፡፡

ይህም ተደጋጋሚ ብሄራዊ ጥፋት እንደ ብሄረሰባዊ ጀግንነት እና ልማት እየተቆጠረ በዳይ በማይጠቅባት ምድር ኢትዮጵያ ዳግም ነጻ አዉጭ በመሆን ኢትዮጵያዉያን ፍዳ እየከፈሉ ነዉ ፡፡

ጅምላ እና ለይቶ መግደል የቆየ እና የሚደጋገም ግን ጠያቂም ተጠያቂም ባለመኖሩ እንደ አገር እና ህዝብ ከሞትን  ቆይተናል የምንለዉ ፡፡

በዚህች አገር አንደኛዉን ጠላት ሌላዉን ወዳጅ አድርጎ ከፋፍሎ በአድለዋዊ የመንግስት አስተዳደር መዳፍ ስር ህዝብን የመምራት ልማድም እንዲሁ ለይቶ የማሳደድ እና የፖለቲካ ንግድ አካል እና በራሱ ህዝብ እና አገር ጥላቻ እና ምቀኝነት የዘራ መንግስት ነበር ለማለት የሚያስችለዉ  ፡፡

ይህም  በዓለም ታሪክ በራሱ ህዝብ እና አገር ላይ ተወዳዳሪ የሌለዉ  በደል የፈፀመ ግለሰብ፣ ቡድን ሆነ የፖለቲካ ድርጅት ተጠያቂ የማይደረግባት አገር ላይ ለዘመናት ደጋግመዉ የገደሉትን ህዝብ እንደገና ከወደቀበት መቀስቀስ በጥፋተኞች አይን ህጋዊ እና ባህል ሆኗል ፡፡

የአገራችን ህገ መንግስት እና የክልል አደረጃጀት ከህገ መንግስት ወደ ህገ -አገር/ህዝብ እና ፌደራሊዝም / ፊዉዳሊዝም(የመሬት ሽሚያነት) ወደ ህብረተሰባዊት እና ህዝባዊ ኢትዮጵያ አስካልተሸጋገረ ድረስ ብሄራዊ እና ህዝባዊ መብትን አሳልፎ እንደመስጠት የሚቆጠር ይሆናል፡፡

ሁሉ ነገር በጥቂቶች እጅ በሆነባት አገር የፌደራል ስርዓቱ ፍትሃዊ የአስተዳር ስርዓት አለዉ ማለት የጉልተኞችን ጥቅም ማስጠበቅ በመሆኑ ይህ አሁንም ሊስተካከል ፤ሊታረም ይገባል፡፡

ለእኛ ኢትዮጵያዉያን በዚህች አገር ዕጣ ፋንታ ላይ ገለልለተኛ መሆን የማይቻለን ሲሆን ከሞትን መቆየታችንን ተቀብለን ለትንሳኤ  እንነሳ ፡፡ ላዳግም ለሚደግሱልን ለዘመናት እና አሁንም ላደረሱት አገራዊ እና ህዝባዊ በደል በህዝብ ፊት ተጠያቂ መሆን እንዳለባቸዉ በህብረት እና በአንድነት ካለቆምን በቀር የትንሳኤ ትግላችን ለዳግም ሞት መንስኤ ይሆናል ይህም በየዕለቱ የምናየዉ እና የምንሰማዉ ሆኖ ይቀጥላል  ፡፡

 

እናት አገር ምንጊዜም ትኑር !!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop