March 21, 2013
13 mins read

ኦቲዝም (የአዕምሮ ዝግመት ችግር)

ኦቲዝም/የአዕምሮ ዝግመት ችግር/ ከሩቅ ሲያዩት የኛን ቤት የማያንኳኳ ችግር ሊመስል ይችላል፡፡ የችግሩ ተጠቂ ቤተሰቦችም ሆኑ የችግሩ ተጠቂ ህፃናት አንዳች ሰማያዊ ቁጣ /እርግማን/ ያለባቸው እንጂ ተራ የጤና እክል እንደገጠማቸው ላናስብም እንችል ይሆናል…፡፡ ይሁን እንጂ የኦቲዝም / የአዕምሮ ዝግመት/ ችግር ነገ በምንወልዳቸው ልጆች ላይ ላለመከሰቱ እርግጠኞች ልንሆን አይችልም፡፡ ችግሩ እንደሚባለው በእርግማን፣ በሐጢያት፣ ‹በቤት ጣጣ› የሚመጣ ሳይሆን ፅንስ በእርግዝና ወቅት በሚገጥመው ችግር የሚፈጠር ነውና፡፡

በአገራችን በርካታ ህፃናት፣ ወጣቶች፣ ጎልማሶች እና አዛውንቶች ከዚህ ከአዕምሮ ዝግመት ችግር ጋር አብረው ይኖራሉ፡፡ የዛሬን አያድርገውና እነዚህ ዜጎች ከቤት እንዳይወጡና ከሰው እንዳይገኛኙ ይደረጉ ነበር፡፡ ወላጆችም እንኳንስ ለልጆቻቸው መልካም ማህበራዊ ህይወት ማመቻቸት እራሳቸውም ቢሆኑ ከሰው መቀላቀል ሲያሸማቅቃቸው የታየበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡

ስለኦቲዝም በአደባባይ መወራት ከጀመረ ጥቂት ዓመታትን ቢያስቆጥርም አሁንም ቢሆን ግን ለጉዳዩ የተሰጠው ትኩረት አናሳ ከመሆኑም በላይ ህብረተሰቡም ስለ ችግሩ ያለው ግንዛቤ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡ ፡ ለዚህም ይመስላል በጉዳዩ ዙሪያ ከሚሰሩ ጥቂት ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው ነህምያ የኦቲዝም ማዕከል ጥር 20 ቀን 2005 ዓ.ም በችግሩ ዙሪያ የፓናል ውይይት ለማዘጋጀት የተነሳው፡፡

ነህምያ የኦቲዝም ማዕከል

ወ/ሮ ራሄል አባይነህና ባለቤታቸው ካፈሯቸው 3 ልጆች መካከል ሁለተኛው ህፃን በባህሪው ከሌሎች የተለየ ነበር፡፡ አካላዊ አቋሙ ፍፁም ጤናማ የሆነው የ3 ዓመቱ ህፃን በተደጋጋሚ ያለቅስ እንዲሁም እንቅልፍ አይወስደው የነበረ ሲሆን ጉዳዩ ያሳሰባቸው ወላጆች የችግሩን ምክንያት ለማወቅ አሉ የተባሉ ክሊኒኮችና ሆስፒታሎችን አዳርሰዋል፡ ፡ ይሁን እንጂ በየሄዱበት የህክምና ተቋም ሁሉ ልጁ ጤናማ እንደሆነ ከመግለፅ ውጭ የፈየዱላቸው አንዳችም ነገር አልነበረም፡፡

እናት ወ/ሮ ራሄል በውይይት መድረኩ ላይ ልምዳቸውን ሲያካፍሉ እንደተናገሩት አንድ ቀን የውጭ ቴሌቪዥን ጣቢያ በመከታተል ላይ ሳሉ ስለ ኦቲዝም (የአዕምሮ ዝግመት) ይሰማሉ፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የተጠቀሱት ምልክቶች በእርግጥም በልጃቸው ላይ ይታይ ነበርና በቅርብ ልጃቸውን ወዳከመው የህክምና ባለሙያ በመደወል ‹‹የልጁ ችግር ኦቲዝም ይሆን ወይ?›› ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ ይሁን እንጂ የህክምና ባለሙያው ስለ ኦቲዝም ብዙም እውቀቱ እንደሌለው ገልፆ ሌላ ሐኪም ይጠቁማቸዋል፡፡ የልጃቸው ችግር ኦቲዝም እንደነበርም በዚህ አጋጣሚ ያረጋግጣሉ፡፡

ለወ/ሮ ራሄል ቤተሰብ ይህ ዜና እጅግ አስደንጋጭ የነበረ ቢሆንም ከሁሉ የከፋው ደግሞ ልጃቸውን በተገቢውና ለኦቲስቲክ ልጆች በተመጠነ መልኩ የሚያስተምር ት/ ቤት በከተማው ያለመገኘቱ ጉዳይ ነበር፡፡ ይሄኔ ነበር አቅም በፈቀደ መጠን ልጃቸውንም ሆነ ሌሎች በዚህ ችግር የተጠቁ ህፃናትን ለመርዳት በማሰብ ሰኔ 9 ቀን 2002 ዓ.ም ነህምያ የኦቲዝም ማዕከል ሊቋቋም የቻለው፡፡

ጥቂት ስለ ኦቲዝም

ኦቲዝም የአዕምሯችን ሴሎች / neuron/ ዕድገት መዛባት የሚያስከትለው የማህበራዊ ግንኙነትና የመግባባት እክል ሲሆን ይህ እክል ተደጋጋሚ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግንም ያካትታል፡፡ ይሁን እንጂ ለበሽታው መነሻ የሚሆነው ምክንያት እስካሁን ግልፅ አይደለም፡፡ በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ባለሙያዎች ለህመሙ ምክንያት ናቸው ያሏቸውን የተለያዩ መላምቶች ይሰነዝራሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል ጄኔቲካል /Genetic/ ይዘቶች፣ የአዕምሯችን ሴሎች ኔትወርክ መዛባት/አፈጣጠር፣ ምግብ፣ በእርግዝና ወቅት የሚፈጠሩ ኢንፌክሽኖች፣ ለፀረ ተባይና ፀረ አረም መድሃኒቶች መጋለጥ፣ የእናቶች በእርግዝና ወቅት ማጨስና መጠጣት፣ እንዲሁም ክትባት ይጠቀሳሉ፡፡

ኦቲዝም በዓለማችን ካሉ 1000 ሰዎች ከ1-2 ሰዎችን እያጠቃ የሚገኝ ሲሆን በአሜሪካ እ.ኤ.አ በተደረገ ጥናት ከ1000 ሰዎች 11 ያህሉ በዚሁ ችግር የተጠቁ እንደሆኑ ጠቁሟል፡፡ ወላጆች ልጆቻቸው በኦቲዝም መጠቃታቸውን የሚያውቁት ልጆቻቸው ከተወለዱ ከሁለት ዓመታትና ከዚያ ከፍ ባሉ ጊዜያት ሲሆን ችግሩ አስፈላጊው ክትትልና እንክብካቤ ካልተደረገለት እየተባባሰ የመምጣት ዕድሉም ሰፊ ነው፡፡

በተለይ በህብረተሰባችን ዘንድ በኦቲዝም ዙሪያ በርካታ የተሳሳቱ አመለካከቶች ሲኖሩ ከእነዚህም ጥቂቶቹ ኦቲስቲክ ልጆች አደገኞች ናቸው ብሎ ማሰብ፣ ፈፅሞ ሊሻሻሉ እንደማይችሉ ማሰብ ዋነኞቹ ሲሆኑ ኦቲስቲክ ሰዎች የሰው አይን እያዩ አያወሩም፣ ሁሉም በአዕምሯቸው ምጡቅ /ጂኒየስ/ ናቸው፣ ማውራት አይችሉምና የመሳሰሉት አስተሳሰቦች ለችግሩ ተጠቂዎች እንክብካቤና ፍቅርን እንዳንሰጥ መሰናከል የሆኑ ጉዳዮች ናቸው፡፡

ይሁን እንጂ ኦቲዝም በራሱ በሽታ ሳይሆን የተለያዩ ጥምር የህመም አይነቶች ከሰው ልጅ ተለምዷዊ የአኗኗር ፀባይ ወጣ ያለ ፀባይ እንዲኖረን ሲያደርጉ የሚከሰት ችግር ነው፡፡ በተጠቂዎቹ ላይ ከሚታዩት የተለያዩ ስሜቶች አንፃር ችግሩ ዝብርቅርቅ ያለ ቢመስልም ጊዜ ሰጥተን ካጠናነው መረዳቱ ብዙም አስቸጋሪ አይሆንም፡፡ ከኦቲስቲኮች 90 ከመቶ ያህሉ እንደ ጤናማ ሰዎች ህይወታቸው ወደ ውጭ ሳይሆን ወደ ውስጣቸው በመንፀባረቁ እንደሌሎቻችን ሙሉ ኑሮ የማይኖሩ ቢመስሉንም ይህ አስተሳሰብ ፈፅሞ ስህተት መሆኑን ጥናቶች ያመለክታሉ፡ ፡

አንድ በኦቲዝም የተጠቃ ልጅ ከሌላው ኦቲስቲክ ልጅ የተለየ ባህሪ ሊኖረው ስለሚችል በጠቅላላው ኦቲስቲክ የሆኑ ልጆች እንዲህ አይነት ናቸው ብሎ ለመደምደም አስቸጋሪ ነው፡፡

በመሆኑም እያንዳንዱ በኦቲስቲክ የተጠቃ ሰው ፀባይ በቅርበት ማጥናት ልጁን ለመንከባከብም ሆነ ትምህርት ለመስጠት ዋነኛ አስፈላጊ ጉዳይ መሆኑን ባለሙያዎቹ ይናገራሉ፡፡

ኦቲስቲክ የሆኑ ሰዎች አብዛኞቹ የመግባባት /ከሌሎች ጋር የመቀላቀል/ እና የመናገር ችግር ሊታይባቸው ሲችል ያላቸው ፍላጎትም ውስን ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ተደጋጋሚ የሆነ ነገር ማድረግ እንደሚወዱ፣ ድምፅና ብርሃን ሊጋነንባቸው እንደሚችል፣ እንቅልፍ ላይተኙ እንደሚችሉ እንዲሁም አልፎ አልፎም ቢሆን በሚጥል በሽታ ሊጠቁ እንደሚችሉ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

በኦቲዝም የተጠቁ ሰዎች በልጅነታቸው አስፈላጊው እንክብካቤና ተዛማጅ ህክምናን ካገኙ ከ3-25 ከመቶ የሚደርሱት የመዳን እድል ሲኖራቸው የበሽታው መነሻ በእርግጠኝነት ባለመታወቁ በህክምና ማዳን አዳጋች ነው፡፡ ይሁን እንጂ በኦቲዝም የተጠቁ ሰዎችን ፍቅርና እንክብካቤ በመስጠት እንቅልፍ እንዲተኙና ቢያንስ ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረግ ይቻላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ስነ ልቦናዊ ህክምናን እንዲያገኙ ማድረግና ለእንቅልፍና ሌሎች ችግሮች የሚሰጡ መድሃኒቶችን በአግባቡ እንዲከታተሉ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ስለ ኦቲዝም ተጠቂዎች ምን ታስቧል?

ነህምያ የኦቲዝም ማዕከል በሀርመኒ ሆቴል ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ስለ ችግሩ ከተነሱት በርካታ ሀሳቦች በተጨማሪ እነዚህን ዜጎች ለመታደግ ተጨማሪ ት/ ቤቶችን መክፈትና የኦቲዝም ማዕከል ማቋቋም ታስቧል፡፡ በተለይ በነህምያ የኦቲዝም ማዕከል በተደረገ ጥናት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በዚሁ ችግር የተጠቁ በርካታ ህፃናት በመገኘታቸውና ሊማሩበት ብሎም ፍቅርና እንክብካቤን ሊያገኙበት የሚችሉበት ስፍራ ባለመኖሩ በዚሁ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ት/ቤት ለማቋቋም ታቅዷል፡፡ ይህን እቅድ ከግብ ለማድረስም በፕሮግራሙ ላይ በርካታ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን 810 ሺህ ብር ገደማ ተሰብስቧል፡፡ በቀጣይም ህብረተሰቡ ችግሩ የሁላችንም መሆኑን አውቆ የተጀመሩ ሀሳቦች ከግብ እንዲደርሱ አስፈላጊው ትብብር ማድረግ እንደሚጠበቅበት በዚህ አጋጣሚ ማሳሰብ እንወዳለን፡፡

 

Source: tenaadam.com

 

 

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ

ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ

እግዚኣብሔር ግን ወዴት አለ?

Go toTop