ሰሞኑን የታላቋ አሜሪካ መሪ ፕ/ት ትራምፕ ስለ ዓባይ ግድብ(ኢት-ዓባይ) ለግብፅ አፍራሽ ግብረ ኃይል መልዕክት አስተላለፉ በተባለዉ ጉዳይ ብዙ በብዙ ከዘመኑ ገዳይ ጉንፋን ፈጥኖ ሳር ቅጠሉን ከብርሃን ፍጥነት የሚስተካከል አስኪመስል ነገሩ ጉኗል፡፡
በርግጥ ይህ ዓይነት ኢትዮጵያን ቋሚ ጥገኛ እና ተስፈኛ ለማድረግ የሚሸረብ የሴራ ገመድ አዲስም ብርቅም እንዳልሆነ ኢትዮጵያዊዉ አይደለም ዓለም የሚያዉቀዉ ነዉ ፡፡ ከ18ኛዉ መቶ ክፍለ ዘመን አንስቶ አስከ ቅርብ እና ሁለተኛ የወራሪ ኢጣሊ ግፈኛ መንግስት ለ2ኛ ጊዜ ከ1928 አስከ 1933 .ዓ.ም. በነበረዉ የኢትዮጵያዉያን የነጻነት ተጋድሎ እና የንጉሰ ነገስቱ ለዓለም አቀፉ ህብረት/ ሊግ ኦፍ ኔሽን/ ያሰሙት የቅኝ ግዛት እና ወረራ የሉዓላዊነት እና የሠባዊነት መብት ጥሰት ድርጊት በፍረደ ገምድል እና ሰስስታም ተስፋፊዎች ለንጉሰ ነግስቱ ጥያቄ የነበራቸዉ ዕይታ እና ምላሽ ሊረሳ አይገባም፡፡
ከዚህም ሌላ በኤርትራ በ1937 አካባቢ አስከ 1953 ዓ.ም. ድረስ ወደ እናት አገር ኢትዮጵያ በፌደሬሽን ሆነ በኮንፌድርሽን መልስ የመቀለቀል ሂደት ወቅቱ የኢትዮጵያን እና ኤርትራዉያን ተፈጥሯዊ ትስስር እና አንድነት የሚያዉቁ ግን የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የተጫወቱት አፍራሽ ሚና ዛሬ አንድ እና አንድ ህዝቦች እንደ ሁለት እንዲቆጠሩ አድርገዋል፡፡
ለዚህም ግብፅ(የአረብ ሊግ የበላይ ዘዋሪ)፣ ሶሪያ፣ እነ ፓኪስታን፣አፍጋኒስታን ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ጋር ሁነዉ በወቅቱ የኤርትራን ጉዳይ ለተባበሩት መንግስታት ተመልክተዉ የድምዳሜ ስምምነት እንዲያቀርቡ ሲደረግ የፈፀሙት ታሪካዊ ስህተት መሆኑን በራሳቸዉ በነዚህ የኢትዮጵያ ጠላቶች ለእኛ ያጠመዱት የመለያየት ወጥመድ እነርሱን እና ጉዳይ አስፈጻሚ ጎረቢት አገሮችን ሲጠልፋቸዉ አይተናል ፤እናያለን ፡፡
ይህ በዝዉርዉር በዕብሪት እና ራስ ወዳድነት ሽፍንፍን ስሜት በቀለም ልዩነት ልክፍት የአገርን ልዑዋላዊነት የሚዳፈር ፣የሠዉ ልጅን ሠባዊ መብት የሚጥስ ዕይታ ንቀት ከባዶነት የሚመጣ ማንነት እንጅ እዉቀት ሊባል አይችልም፡፡
ዛቻ በሌለበት እንደ ኢትዮጵያ አይነት አገሮችን መጉዳት ቀላል ሊመስል እና ሊሆንም ይችላል ፡፡ ሊታወቅ የሚገባ ሀቅ ግን የተገፋ እና የሚንቁት ወዳጅ እንዴት እንደሚያሸንፍ አለማወቅ ነዉ፡፡
የትኛዉም የምዕራባዉያን መንግስታት የሚያዉቁን በድህነት እና ርስ በርስ በመጠላለፍ መሆኑን እንጅ እነርሱ የሌላዉን ለራሳቸዉ ለማድረግ እንደሚቃትቱት ኢትዮጵያዊ የእኔ የሚለዉን ለመጠበቅም ሆነ ለመከላከል ብቁ እና ቀነኢ መሆኑን በተለያዩ ጊዜ እና የታሪክ ዑደት ያሳያቸዉን መርሳት አልነበረባቸዉም፡፡
የቅርብ ዘመናት የዚ አድባሪ (ሶማሊያ) እና ከጀርባዋ የነበረዉ የኃይል አሰላለፍ እና ዛሬ ሰማሊያም ሆነ የቅርብ እና ሩቅ የግፍ ደቦ ተገባበሪዎች ያስተናገዱት ዉድቀት እና የማይረሳ ታሪካዊ ፀፀት ከብዙ የሚጠቀስ ነዉ፡፡
የአረብ አገራት ሴራ እና ግፍ በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ባሉ ቱባ ታሪካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኃይማኖታዊ እና ሁለንተናዊ አኩሪ ማንነት ላይ የሚመነጭ የምቀኝነት አባዜ እንዲሁ አይለቀቸዉም ፡፡
ለአብነትም ግብጾች በእየሩሳሌም የሚገኘዉን እነዚያ ሩቅ አዳሪ ፣በጎ መካሪ እና አስተማሪ አርቆ አስተዋይ ጀግኖች እና ደጎች ኢትዮጵያዉያን አባቶች የመሰረቱትን እና ያቆዩትን ገዳም “ ዴር ሱልጣን ” በማን አለብኝነት ለመንጠቅ ብዙ የደከሙት እና እየደከሙ ያሉት በቅርብ እና በሩቅ ባሉ ብሄራዊ እና ዓለማቀፋዊ ጠላቶቻችን ድጋፍ እና አይዞህ ባይነት እንጅ የእነርሱ ፍላጎትም አቅም እንዳልሆነ እነርሱም ሆነ በትር አቀባይ የዕብድ ገላጋይ አጋሮቻቸዉ ያዉቁታል፡፡
ይህ ሁሉ የዘመናት ድርብርብ ሴራ ከራሳችን የሚጠበቅብንን በአገራችን የጋራ ጉዳይ ላይ በጋራ የመምከር እና መመካከር ባህል እና ዉል ከማሳደግ ይልቅ በግለኝነት እና የጥፋት ህብረት ላይ ማተኮር ለጠላቶቻችን የጥፋት ሜዳዉን እንደማመቻቸት መስራት ነዉ ፡፡
በአገራችን የሰራ የሚከበርባት ፣ እዉነት ተናጋሪ የሚሰማባት እና ጥፋተኛ የሚጠየቅበት አሰራር ኑሮ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያዉን የምትሆነበት ጊዜ ላይ ለመድረስ እና ዛሬ ቀደምት ኢትዮጵያዉያን አባቶች በደም እና አጥንት መስርተዉ ፤የህይወት ዋጋ ከፍለዉ ያቀዩንን አገር በህብረት እና በአንድነት ብንቆም እንኳንስ ከማስፈራሪያ ዛቻ ከተወረወረ ጦር መዳን እንደምንችል የኋላ ታሪካችን ቋሚ ማስረጃ ነዉ ፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳንስ በተልዕኮ በቀጥታ ለሚመጣ እና ለሚሰነዘር ጥቃት አይታሰብነት እና አልበገር ባይነት ከእኛ ይልቅ ዓለም እና ቋሚ የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያዊነት ሰለሊቶች አሳምረዉ ያወቁታል ፡፡
አሁንም የእኛ ችግር ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት አይነጠሌነት የአንድ ጅረት ወይም ምንጭ ዉሃ እርሱም አባይነት መሆኑን አስረግጦ የመነጋገር እና የመተማመን ጉዳይ ነዉ ፡፡
ይህን ከቅርብ እና ሩቅ ታረካችን ወንዝ በጥቂቱ መጭለፍ ይቻላል በምሳሌ ማሳየት ይቻላል ፡፡ በቀደመዉ ጨካኝ እና ወራሪ(ፋሽስት) ኢጣሊ በዱር በገደል በዱር አዉሬ በማደር የዱር ፍሬ እየበሉ ለአገራቸዉ እና ህዝባቸዉ የማይተካ ጠጋድሎ ያደረጉት ብርቶዎች መረሳታቸዉ ብቻ ሳይሆን በህይዎት የመኖር ተፈጥሯዊ መብታቸዉ በታሪካዊ ጠላት ሴራ እና ትግበራ እንዲያጡ መሆኑ ይኸዉም ከሩቅ ጊዜ ፡ ደጃች ባልቻ አባነፍሶ፣ ደጃች በላይ ዘለቀ በቅርብ ሩቅ እነ አክሊሉ ሀብተ ወልድ፣ ጀ/ል ዓብይ አበበ፣ እነ መኮንን እናዳልካቸዉ፣ እነ ከሎኔል አጥናፉ ኣባተ ወ.ዘ.ተ) ከቅርብ እነ ሙሉዓለም አበበ፣ እነ ዶ/ር አምባቸዉ መኮንን፣ ፕ/ር አስራት፣ እነ ዓለማየሁ አቶ ምሳ……) ቢያንስ ብናጣቸዉ እንኳን ስራቸዉን እና ተጋድሏቸዉን መርሳት የለብንም፡፡
ይህን እዉነጠኛ እና ሠባዊነት ያላቸዉ ሠዎች የሚክዱት አይደለም ሊነግሩን ሊያስምሩን ይገባል ፡፡
እዚህ ጋ ማናችንንም ልበ ልንል የሚገባዉ ጥቂቶችን እንጅ ብቻ ናቸዉ እያልኩ አይደለም፡፡ ማንም ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ሠባዊነት ያለዉ ሁሉ ጥፋቱን ባያምን ወይም ይቅር ባይል ዕዳዉ የራሱ ነዉ ነገር ግን እንደ ሠዉ አገሩን የሚወድ ሁሉ እዉነቱን ነግሮን እና አስተምሮን ቢያልፍ ይህችን አገር ከዓለም ቁጣ እና ዣቻ ብቻ ሳይሆን ከሁሉ ባለቤት ዓምላክ ጋር ህብረት እና ቅቡልነት እንፈጥራለን ፡፡
ፍቅር ፣ ህብረት እና አንድነት ባለበት ሁሉ የዓምላክ ዕገዛ እናዳለ እናምናለን እና “ይኸዉም በከርስቶስ ነጻ ወጥታችኋል እና ዳግም ወደ ባርነት አትመለሱ ”ይላል እና ቃሉ ፡፡
ዛሬም ነጻ እናወጣችሁ የሚሉን ከቅርብ አስከ ሩቅ (ምዕራባዊያን) ወዳጆቻችን ያላወቁልን ችግር እነርሱ ከጥላቻ እና ዕብሪት ሰንሰለት ራሳቸዉን ሳያላቅቁ እና ያረጀ ያፈጀ አመለካከታቸዉን ሳይቀይሩ የህልም ዓለም ባርነት የሚፈጥሩት ከተጣባቸዉ የጥላቻ ስሜት እና ዉድቀት ሳይነሱ መልክም ሆነ ልክ የማይገኝለት ነጻነት በራሳቸዉ ወርድ እና ቁመት ለክተዉ ህዝብን እና አገርን ለሚያስጨንቁት በቅድሚያ ራሳቸዉ ከራሳቸዉ ምቀኝነት ከወለደዉ የበታችነት ስሜት ባርነት ቀንበር ተላቀዉ ነጻዳ ነበረ ኅዝብ እና አገር እንዲቀላቀሉ ሊታገዙ ይገባል፡፡
ከዚህ በተቃራኒ ለነጻ አገር እና ህዝብ የነጻነት ጭንብል አጥልቆ ለማይበጅ እና ጫፍ ለሌለዉ መዳረሻ ከጠላት ጋር መኳተን በነጻነት ስም ለህዝብ የድህነት ባርነት እና የጥላቻ አረም ማስፋፋት ነዉ ፡፡
እዚህ ጋ በአሜሪካ የሚኖሩ እዉነተኛ ኢትዮጵያዉያን የአሜሪካዉ ፕሬዚደንት የኢትዮጵያዉያንን በአገራቸዉ ምድር እና ዳር ድንበር ያለ ሀብት የማልማት እና የመጠቀም የባለቤትነት መብት በሚጻረር መንገድ አስተላለፉት በተባለዉ መልዕክት የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ እንዲጠይቁ ፣ ማስተባበያ እንዲያደርጉ መጠየቃቸዉን ሰምተናል፡፡
የዚሁ ኢትዮጵያዉያን ምክር ቤት አስተባባሪ እና ተባባሪ የሆኑት ድንቅ ኢትዮጵያዉያን ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ እና ደ/ር ልዑል ሰገድ አበባ በዚህ ረገድ ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ጋር ሆነዉ እየሰሩ ያሉት በጎ ስራ በሌላዉ ዓለም ቢሆን የዓለም አቀፍ የሰላም ሽልማት(ኖቤል) የሚያሰጣቸዉ በሆነ ነበር ፡፡
ዳሩ ኢትዮጵያዊ መሆናቸዉ ነብይ በአገሩ አይከበርም እና እዚህም እዚያም ኢትዮጵያዊ መሆናቸዉ ክብር እና መስጋና ከኢትዮጵያዉያን ብቻ ይሆናል፡፡
ለምን ቢባል የታላቋ አሜሪካ ፕ/ቱ ኢት-አባይን ለማክሰም ዱላ ሲያቀብሉ ሃሳቡም ሆነ ድርጊቱ የጥፋት መልዕክት እና ይዘት ስላለዉ የእኛ አምባሳደሮች የሰላም ጥሪ ማቅረብ እና ይህን የጥፋት መስመር ማስቀየር ትሩፋቱ የኢትዮጵያ እና ግብፅ ብቻ ሳይሆን ለመላለዉ ሠባዊ ፍጡር መሆኑን በማገናዘብ ነዉ ፡፡
እናም ይህ ጠብ ያለሽ በዳቦ ዛቻ ለደካማ መንግስታት ብቻ ሳይሆን ለባለጉልበተኞች የዉድቀት መንገድ ጅምር ስለሚሆን የእኛ አንድነት እና ህብረት እንጅ የክፉዎች ድንፋታ በእኛ ላይ የሚያሳድረዉ ተፅዕኖ አይኖርም ፡፡
የብድር ገንዘብ ህዝቡን እና አገሪቷን ተስፈኛ ከማድረግ ያለፈ ራስ የመቻል ነገር ስለማይታይ ብድሩም ከአገር እና ህዝብ በላይ የሚታይ አይሆንም ፡፡
እዚህ ጋ እኛ ኢትዮጵያዉያን በአሜሪካ ካሉት የምንማረዉ እነርሱ በሠዉ አገር ሆነዉ የታላቋን አሜሪካ ፕ/ት ዶናልድ ትራምፕ ከአንደበታቸዉ ያወጡትን ድፈርት አይሉት ዕፍረት ዛቻ አዘል ቃል እንዲያስተባብሉ እና የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ እንዲጠይቁ ሲያሳስቡ ምን ያህል የግለሰብ ነጻነት እና መብት በምድረ አሜሪካ እንዳለ እኛም መንግስትም ሊማርበት ይገባል፡፡
እኛ አገር የራሱን እና እንዲጠበቅ ኃላፊነት ያለበትን ወገን ፣ዜጋ እየገደሉ እና እያፈናቀሉ በኃላፊነት አለመጠየቅም ሆነ ህዝብን ይቅርታ ለመጠየቅ ክብርን እንደማጣት በሚቆጠርባት አገር ላይ የልዩነት መስመር መስፋት ባያሰገርምም እነዚህ ብርቱ ኢትዮጵያዉያን ግን እዉነተኛ ሠባዊነት እና ኢትዮጵያዊነት በተለይም በህዝብ እና አገር ስም በንግግር እንጅ በተግባር ለሌሉት እና መማር ለሚሹት አስተማሪነቱን ሁላችንም ልናጤን ይገባል፡፡
ዶናልድ ይቅርታ ባይሉም ቢሉም እናንተ የመከራ ቀን ፈጥኖ ደራሽ የቁርጥ ቀናት ልጆች አደራችሁንም ፤ተልዕኮአችሁንም ተወጥታችኋል ፡፡ ሠዉነትም ሠባዊነትም እንደዚህ በተግባር ሲታይ በአገር እና ህዝብ ላይ የሚመጣ ሠዉ ሠራሽ እና ተፈጥሯዊ ስጋት በተባበረ አንድነት ለመቋቋም ይቻላል (ድር ቢያብር አንበሳ ያስር)፡፡ ድሮም ዓለምን ለማልማት ሆነ ለመለወጥ በግንባር ቀደምትነት የሚገኙት ፣የሚታወቁት ጥቂቶች ሲሆኑ አዕላፍ ይከተሏቸዋል እዉነተኛ መሪዎች ናቸዋ ፤ መሪዎችም አገር እና ህዝብ/ወገን አላቸዉ እንጅ የእኔ የሚሉት የላቸዉም ፡፡
መፅኃፍ ቅዱስ “አስታራቂዎች ብፁዓን ናቸዉ፤ ክርስቶስ ይመስላሉ ” እንዲል እነኝህ ትጉሃን ኢትዮጵያዊያን ቋንቋ እና የግል ልዩነት ሳይገድባቸዉ የሚኖሩለት አገር እና ወገን እንዳላቸዉ እንዲያዉም የግል ጥቅም ፣ምቾት ማንነት ከአገር እና ህዝብ /ደህንነት በታች መሆኑን በግላጭ አሳይተዉናል እና ልናከብራቸዉ ፤ልናመሰግናቸዉ፤ ዕዉቅና ልንሰጣቸዉ የሚገቡ የህዝበ አበሻ እና አገረ ኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ልሳን እና አምባሳደሮች ናቸዉ !!!፡፡
ማላጂ
እናት አገር ምንጊዜም ትኑር !!!