በተፈጥሮአዊና በሰዉ ሰራሽ ተግዳሮቶችና ፈተናዎች እየተናጠች ያለችዉ ዓለማችን ከአንደኛዉ አዙሪት ወደሌላኛዉ ክብ እሽክርክሪት ተዘፍቃለች ፡፡ በሰዉ ዘር አብሮነት ላይ ዘምቶ በርካቶችን ጭዳ እያደረገ ያለዉ ሳንባ ቆልፍ (ኮሬና ቫይረስ) ፤ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት (በቀለም፤በብሄር፤በቋንቋ፤ በመልክዓ-ምድር አቀማመጥ ፤ በእምነት ) አካታች ፤ አሳታፊ እዉቀትንና ክህሎትን ሙያዊ ምግባርን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ብቻ ስርአተ-መንግስት አዋቅሬአለሁ የምትለዉ አሜሪካ ጆርጅ ፍሮይድ የፍትህ ስርአቱን እርቃኑን አስቀርቶ በርካቶችን አስቆጥቶ የፍትህ ሰርአቱ በአዲስ መልክ አንዲቃኝ መንገድ ጠርጓል ፡፡ የእርስ-በእርስ ጦርነቱ ፤ ወረርሽኙ ፤ ስደት ፤ መፈናቀል ፤ ርሃብ ፤ የስራ-አጥነት ፤ የኢኮኖሚ ድቅት ፤…ወ.ዘ.ተ የሰዎችን የአኗኗር ዘይቤን እየፈተነ ለበርካታ ማህበራዊ ምስቅልቅሎች ዳርጓል ፡፡ ሃያሉ ሀገራት በተለያየ የጥቅል አግልግሎት በዲፕማሲ ፤ በብድር አቅርቦት ፤ በእዳ ስረዛ ፤ በወታደራዊ ቁሳቁሶችና የስልጠና አቅርቦት ፤ በዲሞክራሲ ሰርአት ግንባታ ፤ ይሄ ካልተሳካ አስተዳደራዊ ቅራኔዎችን ወደግጭት አንዲያድጉ በተለያዩ የመገናኛ ብዘሁኋን ሀሰተኛ ትርክቶችን በመፈብረክ መርዘኛ ቅስቀሳ መርጨት ፤ በተለያየ መክንያት ያኮረፉ ሃይሎችን አስታጥቆ ጥርስ የነከሱበት ሰርአተ-መንገስት ላይ ማዝመት ….ወ.ዘ.ተ መለያቸዉ ሲሆን ማጠንጠኛዉ ግን በየትኛዉም ሁኔታና አግባብ ብሄራዊ ጥቅምን ማስከበር ነዉ ፡፡ የሶርያ ፤ የሊቢያ ፤ የመን ሊሂቃኖቻቸዉና ፖለቲከኞቻቸዉ በመነጋገር ፤ በመወያየት ፤ በመደራደር ፤ በመቻቻል ፤ የበቀሉባቸዉን ማህረሰብ ባህላዊ የግጭት አፈታት ልምዶቻቸዉን በመጠቀም በጋራ ሀገራቸዉን መገንባት የሚችሉበት እድል እያለ ሃያላኑን ተማነዉ ላታቸዉን ደጅ በማሳደራቸዉ መጨረሻ ያመኑት ፈረስ በደንደስ ጥሎዋቸዉ ዛሬ የዓለም መሳቂያ ሆነዋል ፡፡ ዛሬ በሀገራቸዉን ጉዳይ የመወሰን አቅማቸዉን ተነጥቀዉ የሃያላኖቹ የዘመናዊ ጦር መሳርያ የደራ ገብያና የሙከራ ፍተሸ ጣብያ ሆነዋል ፡፡ ዛሬ የዉክልና ጦርነት የሚካሄድባቸዉ አዉድማ ሆነዋል ሊቢያ (አሜሪካ ፤ ጣሊያን ፤ ፈረንሳይ ፤ የተባበሩት መንገስታት ቱርክ ፤ ግብጽ ..እስራኤል ) የሚፈታተሸባት ፤ ሶርያ (ሩስያ ፤ እስራኤል ፤ አሜሪካ ) የሚቀልዱባት የመን ( የሳዉዲ ጥምረት እና ኢራን ዳማ የሚጫወቱባት መድረክ ሆናለች ) የአበራሽን ጠባሳ ያየ በእሳት አይጫወትም የሚል ብሂል ቢኖረንም ነገረ-ስራችን ፤ አካሄዳችን ፤ድርጊታችን ፤ የአመለካከት ቅኝታችን ዓለም-አቀፍ ማህረሰብ ምን አንደ ደገሰ ጠጋ ብለን በማይመች የአኗኗር ዘይቤ ዉስጥ እየተፈተኑ በቂ የመሰረተ-ልማት አቅርቦት ፤ የመገናኛ አዉታሮች ባልዳበሩበት አኗኗር ዉስጥ እየተሰቃዩ በዘመናቸዉ ፤ በትዉልዳቸዉ ያጋጠማቸዉን ተግዳሮት በጋራ እየተወጡ ሀገርን ለሚቀጥለዉ ትዉልድ ያስረከቡን ዘንግተን ቀኝ -ገዢዎች የጋቱንን ሀሰተኛ ትርክት መሰረት አድረገን ለዘመናት በአብሮነት ተጋምዶ የነሮዉን ማህበረሰብ እሴቶች በመናድ ፤ በማፍረስ ፤ በመዘባበት በለየለት የጥላቻ ፤ የድንቁርና ፤ የጠባብነት ፤ የጽንፈኝነት ፤ የአክራሪነት ምህዋር ዉስጥ ተዘፍቀናል ፡፡ በሀገር ጉዳይ ላይ የፖለቲካ አመለካከታችንን ፤ የወንበር ጥማታችንን ገታ አድረገን በስሙ ምለን በመንገዘተዉ ህዘብ ጥቅሞች ላይ በማህረሰብ ልማት ንቅናቄዎች ፤ የግንዛቤ ማስጨባጫ ፕሮግራሞች ላይ አንኳን በጋራ ለመስራት አልታደልንም ፡፡ ወቅቱ የሚጠይቀዉ ትግል ከፖለቲካ ሰልጣን ፤ ከግል ዝና ግንባታ ፤ የቡድንና የግል ጥቅምን በሚፈጠሩ ክፍተቶችን ተጠቅሞ ሀብት ከማካበት በላይ ህዘብና ሀገር በሰዉ ሰራሽን በተፈጥሮአዊ ተግዳሮቶች ሲፈተን በተናጠል ያለንን አቅም አሟጠን ለጋራ ግብ ማዋል ይጠበቅብናል ፡፡
- የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
በጥናትና ምርምር የታገዙ ቸግር-ፈቺ ዉጤቶችን በማፍለቅ የማህበረሰቡን ወገብ የጎበጡ ሸክሞችን ማቅለል ዋነኛዉ ስራቸዉ መሆን አለበት ፡፡ ህዘብ ከእለት ጉርሱ እየነጠቀ አንዚህን ተቋማት የገነባዉ በፈተና ወቅት ያሻግሩኛል የአኗኗር ዘይቤን ይቀይሩልኛል በሚል ነበር ትላንት የሰላ ሃሳብ ሳይ የተሳለ ካራ ሲወነጨፍበት ዛሬ ድርቆሽ ማከፋፈል የማህበረሰቡን ወገብ በጩቤ አንደመዘልዘል ነዉ የሚታየዉ ፡፡ የሀገር በቀል የህክምና ምርቶቻችንን ላይ ምርምር በማድረግ በማዘመን ለሳንባ ቆልፍ ( ኮረና በሽታ ) መከላከል የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ ለማድረግ በአመለካከት ፤ በስነ-ልቦና ዝግጁነት ቀድመዉ አርእያ ሊሆኑ ይገባል ፡፡
- የብሄራዊ ደህንነትና መረጃ ማእከል
ሰረገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ ዘመቻ ተላቆ የስጋት ቀጠናዎችን በመለየት የቅደመ-መከላል ስልቶችን በመቀየስ ሀገርና ህዝብን ከተገማች አደጋ መታደግ አለበት ፡፡ የግብጽ ቀረርቶን በሚገባ ተረድቶ በዲፕሎማሲ ፤ በመረጃ የበላይነት ፤ የመጨረሻዉ አማራጭ ያሉት ጥቃት ከተሰነዘረም ተከላክሎ ፈጣን ገቢራዊ -ምላሽ መስጠት በሚያስችል ቁመና መረጃ አደራጅቶ ፤ ተንትኖ ለሚመለከተዉ አካል መስጠት መቻል አለበት ፡፡ ለመሆኑ ግብጽ ዉስጥ ሙያዉ በሚጠይቀዉ ክህሎት ፤ እውቀት ፤ ልምድ ፤ ህዝባዊ ዉግንና መሰረተ ባደረገ መልኩ ካይሮ ዉስጥ መዋቅር አለዉ?? ከዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ጋር ተናቦ የሚሰራበት የመረጃ ፍሰት አለ ? በአባይ ጉዳይ ላይ ድርሻ ያለቸዉ ሀገራት የሚያደርጉትን ተለዋዋጭ አቋም እና ገፊ መክንያታቸዉን ተንትኖ የአማራጭ ሃሰብ ለተደራደራዎች የሚያቀብልበት ስረአት አለ? የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነዉ ለመሆኑ ግብጽ በሊቢያ ከቱርክ ጋር የገባችዉን ሰጣ ገባ በምን መልኩ መዝኖ እየተጠቀመበት ነዉ ??? በሀገራችን ዉስጥ ጽንፈኞችና አክራሪዎች ተጋብተዉ የመንገስት አስተዳደራዊና የፀጥታ መዋቅሮች ዉስጥ አንዳሻቸዉ እየፈነጩ በዜጎች ላይ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ሲገድሉ፤የሃይማኖት ተቋማት ሲያቃጥሉ ፤ ሲያፈናቅሉ መረጃዉ ቀድሞ ኖሮት የሚያከሽፍበት አሰራር ዘርግቷል ወይ ??? `በየክልሉ ያሉ የመገናኛ ብዙሃን የጥላቻ ቅስቀሳ ሲዘሩ ዉጤቱን ገምቶ ሳይቃጠል በቅጠል አይልም ወይ ??
- የሃይማኖት ተቋማት / የሀገር ሽማግሌዎች
የቆሰሉ አንጀቶችን ፤ የሸፈቱ ልቦችን በሀገር በቀል የግጭት አፈታት መሰረት በአፋጣኝ አርቀዉ ፤ ፈዉሰዉ ሀገር አንደ ሀገር አንድትቀጥል የበኩላቸዉን ሚና እየተወጡ ነዉ ? በተለያዩ የመገናኛ ብዙኋን የሚረጩትን የጥላቻ ድግሶች ለማምከን ምን እየሰሩ ነዉ በፌደራል መንገስተና በክልል መንገስታት ያለዉ አለመናበብ ፤ በየክልል ሚዲያዎች አንዱ ስለአንዱ የሚነዛዉ የፕሮፖጋንዳ ዶክመንተሪ ጉዳይ አንዴት እየታየ ነዉ? የክልል ፤ የወረዳ ፤ ራስ-ገዝ አስተዳደር ጥያቄዎች የሚመለሱበት አግባብ ወደ ግጭት አንዳያመሩ ምን አይነት የቅደመ-ጥንቃቄ ሰልት ቀይሰዋል ?
- ሰፊዉ-ህዘብ
የግልና የቡድን ፍላጎታቸዉን ለማስከበር ስስ ብልትህን (ብሄር ፤ቋንቋ፤ እምነት ) እየኮረኮሩ ሀሰተኛ ትርክት እየጋቱህ ለዘመናት አብሮ በመኖር በሀዘን በደስታ በመደራረስ ፤ በጋብቻ በመዋለድ ፤ ተስፋዎችህንና ስጋቶችህን እየተጋራህ ባዳበርካቸዉ እሴቶች ላይ አንድትዘምት የሚቀሰቅሱን የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች ጆሮ ዳባ ብለህ በጎ ሚናህን ተወጣ ፡፡ የተቀርቋሪነት ካባ ደርበዉ በስምህ (በብሄር፤በቋንቋህ ፤ በእምነትህ ) ተጣብቀዉ ሳትወክላቸዉ በየመድረኩ ሲሽቀረቀሩብህ አይተህ አንዳለየህ ማለፍ ሳይሆን አንቀረህ ትፋቸዉ አብሮነትህን በማጠበቅ ቅዠታቸዉን አፍረሰዉ ፡፡
መዉጫ ፡- የአበራሽን(ሶርያ ፤ የመን ፤ ሊቢያ….) ጠባሳ ያየ በእሳት አይጫወትም ፡፡ ቁርሾዎቻችንን በሀገር በቀል የግጭት አፈታት ፈተን አንደ ሀገር በዓለም-አቀፍ መድርክ ለሚያጋጥመን ተግዳሮት በጋራ አንቁም ፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ የሁላችንንም ፍላጎት የምታንጸባርቅ የጋራ ጥቅሞቻችንን የምታስከብር አካታች ፤ አሳታፊ ፤ ከፖለቲካ ዉግንና ተፋቶ በገለልተኝነት ህዘብን የሚያገለግሉ ተቋማት ምስረታ ላይ እንረባረብ ፡፡
ኢዮብ ሳለሞት
ያልታወቁ ታጣቂዎች እነማን ናቸዉ ?
ከቅርብ ግዜ አንስቶ በከፍተኛ ፍጥነት በአራቱም ማእዘናት ማንነትን መሰረት ያደረገ ግጭት ፤መፈናቀል ፤ ግድያ ፤ዘረፋ በአስፈሪ ሁኔታ ከአንዱ ክልል ወደሌላኛዉ እየተዛመተ የሀገርና የህዘብ ህልዉና አደጋ ዉስጥ የገባበት ሁኔታ እየተስተዋለ ነዉ ፡፡ የግለሰቦች ግጭት ወደብሄር እያደገ የእምነት ተቋማት እየተቃጠሉ በሰዉ ሰራሽ ችግርና ተፈጥሮአዊ ተግዳሮቶች ማህበረሰባችን ወዲህና ወዲህ እየተገላታ ሃላፊነት የሚሰማቸዉ ዜጎች ፤ ከእጅ ወደአፍ ከሆነ ኑሮዉ ሰላምና ደህንነቴን ያስጠብቅልኛል ብሎ ህዘብ ቀለብ የሚሰፍርላቸዉ የፍትህ ፤የጸጥታ አካላት ያጎረሳቸዉን እጅ የሚነክሱበት ወቅት ላይ ደርሰናል ፡፡ አንደተቋም የህዘብን የጸጥታ ስጋት በመቅረፍ አስተማማኝ ሰላም ማረጋገጥ ሲገባቸዉ ዋነኛ የግጭት ፤የቀዉስ መሃንዲስ የሰላም ጸር እየሆኑ ለመምጣታቸዉ በርካታ ማሳያዎች አሉ የእርስ-በእርስ ግጭት ጠንሳሾችን በሽፋን በማስመለጥ ፤ ህጻናትና አዛዉንቶች በስረአተ-አለበኞች ሲመተሩ ተልከሻ የቢሮክራሲ ምክንያት በመደርድር ታዛቢ ሆነዋል ፡፡ ዜጎች የእለት ተእለት አንቅስቃሴ በሚያከናዉነባቸዉ ቦታዎች ድንገት ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ሰለባ የሚሆኑበትም ምክንያት ምንድነዉ