April 17, 2020
34 mins read

ሰው የዳቢሎስ ጠበቃ ከሆነ ነገር ዓለሙ ሁሉ መበላሸቱ አይቀርም – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ 

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ
(Revelation 13 )
 ————
 1. አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፥ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።
 2 .ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፥ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፥ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኃይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው።
 3. ከራሶቹም ለሞት እንደ ታረደ ሆኖ አንዱን አየሁ፥ ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰ። ምድርም ሁሉ አውሬውን እየተከተለ ተደነቀ፥
 4 .ለዘንዶውም ሰገዱለት፥ ለአውሬው ሥልጣንን ሰጥቶታልና፤ ለአውሬውም፦ አውሬውን ማን ይመስለዋል፥ እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል? እያሉ ሰገዱለት።
 5. ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።
 6 .እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ።
 7. ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው፥ በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው።
 8 .ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ ሕይወት መጽሐፍ ስሞቻቸው ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ ሁሉ ይሰግዱለታል።
 9. ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ።
 10 .ይማረክ ዘንድ ያለው ማንም ቢኖር ወደ ምርኮነት ይሄዳል፤ በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል። የቅዱሳን ትዕግሥትና እምነት በዚህ ነው።
11 . ሌላም አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ፥ የበግ ቀንዶችን የሚመስሉ ሁለት ቀንዶችም ነበሩት እንደ ዘንዶም ይናገር ነበር።
 12 .በፊተኛውም አውሬ ሥልጣን በእርሱ ፊት ሁሉን ያደርጋል። ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰለት ለፊተኛው አውሬ ምድርና በእርሱ የሚኖሩት እንዲሰግዱለት ያደርጋል።
 13 .እሳትንም እንኳ ከሰማይ ወደ ምድር በሰው ፊት እስኪያወርድ ድረስ ታላላቆችን ምልክቶች ያደርጋል።
 14 .በአውሬውም ፊት ያደርግ ዘንድ ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታል፤ የሰይፍም ቍስል ለነበረውና በሕይወት ለኖረው ለአውሬው ምስልን እንዲያደርጉ በምድር የሚኖሩትን ይናገራል።
 15. የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው።
 16. ታናናሾችና ታላላቆችም ባለ ጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ፥
 17. የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል። ጥበብ በዚህ አለ።
 18. አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ይቍጠረው፤ ቍጥሩ የሰው ቍጥር ነውና፥ ቍጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው።
   የእግዜር ፍጥረታት ሁላ በዓለማዊ ድንዛዜ ውስጥ ሥለሆንን  ” የዳቢሎስ ጠበቃ” የሆኑ ሰዎች ዓለምን ሲያሾሮት ከቶም አላሥተዋልንም።”
  በዓለም ላይ የቴክኖሎጂ ምጥቀት እየታየ ነው።የዓለም ሰው በሙሉ  በማሽን ቁጥጥር ሥር እንዲውል ሰባቱ በሚሥጥራዊው ማህበረሰብ ውስጥ ያሉት የቱጃር ማህበር ተጠሪዎች ያላሰለሰ ጥረት እያደረጉ ነው።እናም በቴክኖሎጂ ሰበብ የእያንዳንዳችንን ጓዳ ሊቆጣጠሩ አንድ ሃሙሥ ቀርቷቸዋል።እናም ከትንሽ ዘመን  በኋላ ምናልባትም፣ ከሦሥት ና አራት ትውልድ በኋላ፣ በእያንዳንዳችን ክንድ ፣666 ካልተቀበረ ልንገዛ እና ልንሸጥ ከቶም እንደማይቻል ይታሰባል።
 ይህ አይቀሬ ክስተት እንደሚሆንም ጅማሬዎች እየታዩ ነው።  ምልክቶቹንም በገንዘብ አልቦ ንግድ ጅማሮ እያየን ነው። ዛሬ የአዳም  ዘር  ምንም ሣይነቃ፣ የሰውን ጭንቅላት በመበረዝ ፣ሳያውቀው የሰውን ፈጠራ  ሴጣን ለራሱ ጥቅም እየተገለገለበት ነው። ሴጣን ለሰው ልጅ መልካም ነገር ለማሥገኘት  በሰው የተፈለሠፉትን አሥደናቂ ፈጠራዎች በራሳቸው በሰዎች አማካኝነት ለጥፋት እንዲውሉ በረቀቀ ዘዴ እየቀየራቸው ነው።
 ይህንን እውነት ለማረጋገጥ በምሳሌነት የአልበርት አንሥታይን እና የአልፍረድ ኖብልን ፈጠራዎች እና ያልተገባ የጥፋት መሣሪያነት ይጠቅሷል።
   አልበርት አንስታይንም ሆነ አልፍረድ ኖብል ፣ለሰው ልጅ የሚጠቅም ሥራ ሊሰራ የሚችል ልዩ  ፈጠራ ቢፈጥሩም ፣ፈጠራዎቻቸውን ሴጣን ሰውን በዓለም ኃላፊ ምቾት እና ድሎት በማጥመድ ፣ፈጠራዎቹ ለጥፋት እንዲውሉ በማድረግ ሰው በራሱ ላይ እንዲጨክን አድርጓል።
   ሰው ልጅ፣የእነሱን ፈጠራዎችን በመጠቀም፣  የጥፋት መሣሪያ ሆነው ፣አንዱ ሌላውን እንዳያጠፋው በመፍራት በፍቃደኝነት ባሪያ እንዲሆን ከማሥቻላቸውም በለይ፣ያለመጠን ሀብት በማጋበስ  ከምቾታቸው ጫፍ የተነሳ ሰማይን በእርግጫ የሚመቱ ቱጃሮች ፈጥሯል።እነዚህ ቱጃሮችም ከሰው ለጅ መገዳደል አትራፊዎች ሆነዋል።
    የኃያላኑ ሀገራት መንግሥታትም በነዚህ ሣይንቲሥቶችች ድንቅ ፈጠራ በመጠቀም አውዳሚ የጦር መሣሪያ እና ሀገር አቋራጭ መተኮሻ ሰርተዋል።
 ትላንት በቀርፋፋ አውሮፕላን ነበር፣ሄሮሽማን እና ናጋሳኪን በአውቶሚክ ቦንብ ያወደሙት።ዛሬ ግን አሜሪካ ቂጭ ብለው ሩሲያ ላይ ለመተኮስ የሚያሥችል ቴክኖሎጂን እሥከመሥራት ደርሰዋል።ሩሲያም እንደዛው።…
   በነገራችን ላይ ዛሬ ቴክኖሎጂ እጅግ በመራቀቁ ፣በቴክኖሎጂ ተጠቅመውግለሰብን እና መንግሥትን የሚዘርፉ ሌቦች መብዛታቸውይታወቃል።
  ዛሬ   ገንዘባችሁን የቴክኖሎጂ ሌባ ቢዘርፋ
ኳን ግለሰብ ባንክ ሊዘረፍ ይችላል።የሥልካችሁን ሁሉ ነገር ተቆጣጥሮ ሣንቲማችሁን በቴክኖሎጂ  በተራቀቀው መሣሪያ የመንግሥት ሌባና የግል ሌባ ቢወሥድባችሁ ለማንም አቤት ማለት አትችሉም።ያላችሁ አማራጭ ሥልክ ለመደዋወል ብቻ ሞባይላችሁን መጠቀም እና ዳታችሁን መዝጋት ነው።ወይም የተወሰኑ መተግበሪያዎችን እንዳይሰሩ ማድረግ ነው።በተለይም ጓግል ፕለይን እና ዩቲዩብን።አለበለዚያ በሥማርት ፎናችሁ ያለትዕዛዝ ዳውን ሎድ ማድረግ ዘወትር ማልቀሳችሁን ትቀጥላላችሁ።
    ከዚህም በላይ ጎግል በየጊዜው በሚያዘምነው ቴክኖሎጂ፣ሥልካችሁ እንዳይጠለፍ ካላደረገ ሥልካችሁ የባቄላ ወፍጮ መሆኑን ተገንዘቡት።እንኳን የናንተ ይቅርና የመሪዎችም ሥልክ ይጠለፋል።መፍትሄው ፋይላችሁን በፍለሻችሁ ማኖር ነው።ሰነዳችሁ የባቄላ ወፍጮ እንዳይሆን ከፈለጋችሁ።
    የተለያዩ የሶፍት ዌር ፕሮግራሞችን በመፈልሰፍ ና በሌሎች ሰዎች ኔት ወርኮች ውስጥ በመግባት ፣ ያሻቸውን ከማድረግ የማይመለሱ የፈጠራ ሰዎች ወደፊት በብዛት መከሰታቸውም አይቀሬ ነው።መንግሥታትም በማሽኖች ቁጥጥር ውስጥ በማዋል፣ሥራቸውን በሙሉ በነሱ ሊያካሂዱ ይችላሉ። መጥፎ ጎናቸውን ግን በተለያዩ ፊልሞች  ተመልክተናል።ለምሳሌ “The matrix 1 እና 2” ይጠቀሳሉ።
   ሰው እጅግ በመራቀቁ እና እጅግ በመጠበቡ ምክንያት አመዛዛኝ ህሊናውን በማጣት ወደ እብደት ውስጥ እየገባ መሆኑን ፊልሞች አሥቀድመው እየመሠከሩ ነው። የበለፀጉ እና በሥልጣኔ ጎዳና እጅግ የተራመዱ ሀገራት መሪዎችም እሥከሚሞቱ ድረስ  “የሤጣን ፈጠራ ጠበቃ” ሆነው እያገለገሉ ነው።
    ለምሳሌ የኃያሏ አሜሪካ ንጉሥ  ፣ “ከዓለም ድሆች ጋር ትብብር የለኝም።” እያሉ፣በሌላ በኩል ” እግዛብሔር አሜሪካንን ይባርክ ።”ይላሉ። ይህ ማለት ደግሞ “እየሱስም መልካም ነው።ሤጣንም እንዲሁ።” ማለት እንደሆነ አልተገነዘቡም።
    እኝህ የታላቅ ሀገር መሪ  በየቀኑ  ይቀባጥራሉ። ዛሬ የተናገሩትን ሥህተት ነገ ለማረም ሣይሆን ተጨማሪ ሥህተት ለመፈፀም ድፍረቱ አላቸው።እናም አሜሪካ እንደ ዛሬው ዓይነት እጅግ ፍሬን የለቀቀ አምባገነን መሪ አጋጥሞት አያውቅም።
   እኝህ ሰው የጋዜጠኞችን ጥያቄ እንኳን በአግባቡ የማይመልሱ ከመሆናቸውም በላይ። “ውይ! ጥያቄ ጥይቀህ ሞተሃል ?” ብለው ጋዜጠኛን የሚያንጓጥጡ ሆነው ተገኝተዋል። ይልቁንም የዓለም የጤና ደርጅት በአንድ ሰው እንደሚመራ በመቁጠር እና ፕሬዝዳንቱ፣ አፍሪካዊ በመሆኑ ፣አፍሪካዊያንን እንደፍረጃቸው በጣም ዝቅ አድርጎ በመመልከት ፣የራሳቸውን የደህንነት ክፍል መረጃ በመናቃቸው የተነሳ ለዚህ ውድቀት አገራቸውን እንዳበቋት እንዳይነቃባቸው፣በዚህ ክስ ለመሸፋፈን “ያሣሣተኝ የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ ነው።ለቻይና ያደላል።ቅብርጥስዮ። ” በማለት የአብዬን ወደእምዬ ሲያላክኩ ማሰብና ማሥተዋል የሚችል የእግዜር ፍጥረት ሁሉ ታዝቧቸዋል።
  “ሰውየውን ምን ነካቸው? አሜሪካ እንኳን በሌላው ሀገር ተራ ዜጋ ላይ  በጅምላ የሚከሰት ወይም የሚፈፀም ደባን እና የሥነ ህይወት ጦር መሥሪያን ወይም የተፈጥሮ አሉታ ዊ ክስተትን ይቅርና ፣በየሀገሩ ቤተመንግሥት በምሥጢር የሚሾካሾከውን እንኳን ለማወቅ እንደማያዳግታት ዓለም ሁሉ ያውቃል።”  በሚባልበት ፣በዚህ በቴክኖሎጂ በተራቀቀ ዘመን ሥለ “ኮቪድ 19 በቂ ማረጃ ባለመሥጠት  የተባበሩት መንግሥታት አሳስቶኛልና ለዓለም ጤና መጨነቄን አቆማለሁ።” ማለታቸው   ቢያንስ ለጥቂቶቻችን የ21ኛው ክ/ዘ ቀልድ ነው።
  ኃያሏ አሜሪካ እኮ  በይፋ የሚታየውን  ይቅርና በጓዳ የሚዶለተውን ለማወቅ የሚችል ኤፍ ቢ አይን የመሠለ የደህንነት መዋቅር ያላት ትልቅ ሀገር ናት። “ይህ የቫይረስ ወረርሺኝ በፍጥነት ተዛማች እንደሆነ ቀድሜ አላወቅሁም። ” ለማለትም ከቶም  አትችልም።ይህ ለአሜሪካ የምክርቤት አባላት እንደሥድብ ይቆጠራል።በእርግጠኝነት  ኤፍ ቢ አይ ጮክ ብሎ ለፕሬዝዳንት ዶናልድ  ትራምፕ በቻይና ሥለተከሰተው ወረርሺኝ የዳቦ ሥም ሳይወጣለት በፊት ነግሯቸው ነበር።እሳቸው ግን ከሀገራቸው ሣይንቲሥቶች ጋር በመነጋገር አሥቀድመው በራቸውን እንደመዝጋት በራሳቸው የተሳሳተ መንገድ ብቻ ተጉዘዋል።…
   ዘገየም ፈጠንም  እሳቸው ብቻ ሣይሆኑ በተሳሳተ መንገድ የአለም ጤና ድርጅትን ማሥጠንቀቂያ ችላ ያሉት፣አንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት እብዛም አልተጨነቁበትም ነበር።    እነዚህ ታላላቅ ሀገራት ከዚህ በፊት የተከሰቱትን በባክቴሪያ፣በቫይረስ እና በነፍሳት አማካኝነት በዓለማችን ተከሥተው አያሌ ሰዎች የጨረሱትን  ሃያ (20) ዋና፣ዋና ገዳይ ወረርሺኞችን  አሣምረው የሚያውቁ መሆናቸው ደግሞ ከታሪክ የሚማር መሪ እንዳጡ ጠቋሚ ነው።
    እሥቲ እነዚህን 20 በዓለም የታሪክ የወርሺኝ መዝገብ የሰፈሩ የሰው ልጅን ህልውና የፈተኑ ክፉ በሽታዎች እናሥታውሳቸው።
1ኛ/ቅድመ ታሪክ ወረርሺኝ ነው። (prehistoric epidemic)  በ 3000 ዓ/ዓ (ከክርስቶስ ልደት በፊት)
በቻይና የተከሰተ እና በቁፋሮ በጅምላ የተቃጠሉ አሥከሬኖች ተግኝተው በወረርሺኝ ሰበብ የሞቱ ሰዎች እንደሆኑ ተረጋግጧል።
2ኛ/የአቴንስ ገዳይ መቅሰፍት ወይም ወረርሺኝ(plague of Athens )የሚባለው ነው።ይህ ጅምላ ጨራሽ ደዌ በ430 ዓ/ዓ የተከሰተ ነው። 100ሺ ሰውን እንደገደለም ይታመናል።
3ኛ/ የአንቶኒያን ደዌ ወረርሺኝ (Antonine plague ) ከ165—180 ዓ/ም እኤአ የተከሰተ
ሲሆን ከክርስቶስ ልደት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተ ወረርሺኝ ነው።ይህ ከሮም ወታደሮች በኋላ በወታደሮቹ አማካኝነት ወደሮም የገባ ገዳይ በሽታ እንደሆነ ይታመናል።
  የህ ደዌ ፈንጣጣ እንደሆነ ይታመናል። በግምት 5 ሚሊዮን የሮማን ግዛት ህዝብ እንደጨረሰ ተገምቷል።
4ኛ/የሲፕሪያን ወረርሺኝ “plague of cyprian ” ነው።250—271 የተከሰተ ነው።ይህንንም ወረርሽኝ በ2014 የተገኘው መረጃ በተጨባጭ 5000 ሮማዊያን እንደሞቱ በተገኘው ጅምላ ቀብር አረጋግጧል።
5ኛ/የጀሥቲኒያን ወረርሺኝ፣(plague of justinian) ከ541—542 ዓ/ም ቤንዛንታይን የአገዛዝ ዘመን የተከሰተ እና ከዓለም ህዝብ 10% የጨረሰ ነበር።
6ኛ/ ጥቁሩ ሞት(The black death ) ከ1346—1353 ከኢሲያ ወደ አውሮፓ የተሠራጨ ነው።ግማሹን የአውሮፓ የዘመኑን ሰው መጨረሱ ይታመናል።
7ኛ/ ኮኮሊዝትሊ ውሱን  ወረርሺኝ(Cocoliztli  Epidemic ) ከ1545—-1548 ዓ/ም
ደም እያነሠረ 15 ሚሊዮን ፍጡራንን፣ ሰውን ጨምሮ  ቀጥፏል።
8ኛ/የአሜሪካው ወረርሺኝ ።American plague ) በ16 ኛው ክ/ዘ የተከሰተ  ሲሆን፣ከኢሲያ በአውሮፓውያን ሀገር አሳሾች ወደ አሜሪካ ገብቶ 90% በምእራብ ጫፍ ያሉ በለሀገሮቹን የጨረሰ ነው።
9ኛ/ታላቁ ገዳይ የለንደን ወረርሺኝ ከ1965—1666 ዓ/ም እአኤ የተከሰተ ሲሆን፣ቢቢሲ ዘጋቢ ፊልም (Documentary film ) ሰርቶበታል። ይህ በአዮጦች ና በሌሎች በቤት ውስጥ ነፍሳት ወደሰው የሚተላለፈ በሽታ ነው።ይህ  ገዳይ በሽታ በ1346 ከከሰተው የኢሲያው ጥቁር ሞት በኋላ የተከሰተ ዘግናኝ “ጥቁር ሞት “ነበር። ይህ በቅድሚያ ብብት ውስጥ እባጭ ፈጥሮ በትኩሳት እና በሳል የሚያጣድፍ ፣እጅግ አሰቃይ በሽታ ሲሆን ፣ በሽታውን እንዳያሥተላልፉ ታሥቦ  ቤት ተቆልፎባቸው ከእነ ቤተሰባቸው እንዲቀመጡ በመገደዳቸው አያሌዎች በርሃብ ጭምር  ለሞት እንደተዳረጉ ጥናቶች ያመለክታሉ። 100 ሺ  እንግሊዛውያንን የሞት ሰለባ ሲያደርግ 15% የለንደን ነዋሪዎች ናቸው።
10ኛ/ የማርሴሉ ዘግናኙ ታላቅ ወረርሽኝ (Great plage of marseille ) 1720–1723 መቶሺ የፈረንሳይ ህዝብን ለሞት ዳርጓል።30% የማርሴል ነዋሪ ነው።
11ኛ/የሩሲያ ወረርሽኝ (Russian plagu ) 1770–1772
  ተከስቶ 100,000 ሰው ገድሏል።
12ኛ/የፊላዴልፊያው የቢጫ ወባ ወረርሽኝ(Philadelphia  yellow fever epidemic ) ይህ ገዳይ ህመም በ1793 ተከሰቶ 5000  ሰው፣  በዛው አካባቢ ገድሏል።
13ኛ/ ዓለም አቀፉ የኢንፍሎዌንዛ ህመም ። 1889–1890
የተከሰተ ነው።በመላው አውሮፓና እና በዓለም 1,000,000 ሰዎችን ለድንገተኛ ሞት ዳርጓል።
14ኛ/የአሜሪካ የፖሊዮ በሽታ ወረርሺኝ።American polio epidemic 1916 ዓ/ም ፣በሽታው የጀመረው ኒዎርክ ነው። 27,000 ሰዎችን አጥቅቶ 6,000 ዎችን ሲገድል፣ብዙዎቹን ለአካለ ጎዶሎነት ዳርጓል።
15ኛ/ የእሥፓንሽ  ኢንፍሉዌንዛ ።(Spanish flu ) 1918–1920 ዓ/ም ።ይህ ወረርሽኝ ከደቡብ ባህር አንስቶ እስከሰሜን ዋልታ አዳርሷል።ይህ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ  በአውሮፓውያኑ ቅኝ ገዢ ወታደሮች የተሥፋፋ ነው።ስፔን በዛን ወቅት በእዚህ ወታደራዊ እንቅሥቃሴ ውስጥ ተሳትፎ የላትም ይሁን እንጂ ሥለበሽታው በጋዜጣዋ ለመጀመሪያ በመዘገቧ እና አለም በማወቁ  በሽታውን ” የእስፔን ጉንፋን” ብሎ ሰይሞታል።ይህ ገዳይ  ወረርሺኝ 500 ሚሊዮን የዓለምን ህዝብ አጥቅቶ አንድ አምስተኛውን ህዝብ እንደጨረሰ ይገመታል።
16ኛ/ የኢሲያን ኢንፍሉዌንዛ   ።( Asian Flu ) ከ1957–1958 ዓ/ም በመጀመሪያ በቻይና የተከሰተ ነው። በአሜሪካ ከተከሰተው አቭየን ኢንፍሉዌንዛ (Avian  flu )  ጋር ተቀይጦ ወደ አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ህዝብ በዓለም ላይ ጨርሶል።
17ኛ/ኤች አይ ቪ ኤድስ ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ወረርሺኝ (AIDS pandemic and epidemic ) የጀመረው፣ በ1981 ዓ/ም እኤአ ነው ይፋ የሆነው። ማን ሀገር እንደተፈጠረ አከራካሪ ነው።በይበልጥ ግን ወደዝሙት የተጠጋ በቫይረስ አማካኝነት የሚከሰት በሽታ መሆኑ አይካድም።ኤድስ  በዓለም ተንሰራፍቶ 35 ሚሊዮን ሰው ገድሏል። ዛሬም ከሣህራ በታች ባሉ ሀገሮችና በአፍሪካ 40,000,000 ሰዎች ከቫይረሱ ጋር እንደሚኖሩ ይታወቃል።
18ኛ/  ኤች1ኤን1 ሥዊን ኢንፍሉዌንዛ (H1N1 swine flu) .2009–2010 ዓ/ም እኤአ  ፍጥረቱን ሜክሲኮ አድርጎ 1.4 ቢሊዮን የዓለምን ህዝብ ሲያጠቃ ፣የገደለው ከ151,700—575,400 ነው ይባላል።
19ኛ/ የምእራብ አፍሪካው ኢቦላ ወረርሺኝ( West africsn Ebola ) 2014 -2018 ተከሥቶ በ2016 ዓ/ም ብቻ 28,600 ሰዎች በዚህ ገዳይ ቫይረስ በምእራብ አፍሪካ ተይዘው 11,325 ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ሞተዋል።
በሽታው መጀመሪያ በጊኒ በ2013 እኤአ ነው የታወቀው።ከ2014 ጀምሮ በመሥፋፋት ወደ ላይቤሪያና ሴራሊዮን ተዛምቷል።ይህ በሽታ በጥቂት ሰዎች ላይ፣በናይጄሪያ፣በማሊ፣በሴኔጋል፣እንዲሁም በአሜሪካና አውሮፓ ተከስቷል።እሥከዛሬም ፈዋሽ  መድሃኒት አልተገኘለትም።
  20ኛ/የዚካ ቫይረስ ወረርሽኝ (Zica virus epidemic ) በ2015 እኤአ በደቡብና በመካከለኛው አሜሪካ ቢከሰትም በቅጡ አልታወቀም ነበር።  በወባ ትንኝ እና በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፍ መሆኑ በጥናት ተረጋግጧል።የከፋ ገዳት በአዋቂም ሆነ በህፃናት ላይ ባያሥከትልም ፣ገና ያልተወለዱ ልጆች አካለ ጎደሎ  ሆነው እንዲወለዱ በማድረግ ወላጅን እና ማህበረሰቡን ለከፋ የሥነ ልቡና ጉዳት ይዳርጋል።
   እና አንባብያን ምን ትላላችሁ ?ይህንን እውነት ሣይንቲሥቶች ፅፈው ያሥቀመጡት እና ማንም ሰው ከጉግል መረጃውን ጎልጉሎ መገንዘብ ይችላል።ታዲያ ፕሬዝዳንት ዶናልትራፕ ይህንን ኮቪድ 19 እንደ አዲሥ ክስተት ለምን መቁጠር አሥፈለጋቸው።ሀገራቸው ሥለበሽታው ቀድማ የማወቅ፣ህዝቧን ከሞት የመጠበቅ ችሎታው እያለት ለምን አውቆ የተኛ ሆኑ?ድብቁ ዓላማቸውስ ምንድነው? ለምንድነውስ ሰውየው፣ ሁሌም በአንድ ራሥ ሁለት ምላሥ ያላቸው ሆነው የሚታዩት?…
    ከዚህ ጥያቄ ተነሥተን ፣ሰውየው በአንድ ራሥ ሁለት ምላሥ እያሳዩን ፣በአንዱ ምላሳቸው ሥለ መልካም ነገር፣ሥለርህራሄ እያወሩልን፣በሌላው ምላሳቸው በችግር እና በችጋር እንድንሞት የእልቂት ነጋሪት በአፍሪካ እንዲመታ እየደገሱልን እንደሆነ መጠርጠር ይኖርብናል።ለእሳቸውና ለመሠሎቻቸው እኛ ሸቀጥ ነን ።…
     ይህ መግበስበስ መውደድ  እና ማን አለብኝነት  እኔ የዓለም አለቃ ነኝ ባይነትን ሢጨምር የሤጣን ጠበቃነትን ያመለክታል።በእንግሊዝኛው (The devil  advocacy .) እንደማለት ነው።
     በነገራችን ላይ እንዲህ ዓይነት ፊልም በወጣትነት ዘመኔ አይቻለሁ። ( ፊልም ማየት ከገነት ጦር ተምህርት ቤት አሥናቀ አዳራሽ ጀምሮ ማየቴን አላቋረጥኩም። እድሜ ፊልሞችን ለእጩ መኮንኖች እና ለካምፑ ወታደሮች ለሚያሳየው ለፕሮጀክተሩ ቴክኒሻን አባቴ ይሁንና ፣  ፊልም መጥቀሥ ሳበዛ እንዳትገረሙ።) “የሴጣን ጠበቃ ” የተሰኘው አሥፈሪ  ፊልም ጭብጥ አንድ ሰባኪ በመንገድ ሢሄድ ሤጣን እሱን ገድሎ ሰወነት ወሰጥ በመግባት ፣ክርስቴያንነትን ለማጥፋት እና ሤጣንን ለማንገሥ እንዴት እንደጣረ የሚያሳይና ሰባኪ ሆኖ በምእመናኑ ፊት ሤጣንን ወይም ራሡን ሢያወድስ የሚያሳይ ነው።የፊልሙም   ሠሪዎች አሜሪካኖች ናቸው።
  ትራምፕ ከዚህ ፊልም የባሠ ኢ-ሰብአዊ ምግባርን የሚያራምዱ ፀረ ክርስቶስ ናቸው።ይህንንም ያለ አንዳች የአፍ ወለምታ እላለሁ።ክርስቶስ የቀኝ ጉንጭህን ቢመታህ የግራህን ደግሞ ሠጠው እንደሚል አያውቁም ማለትም አንችልም።እናም በአቅመ ቢሱ አፍሪካዊ ላይ የበለጠ ጉዳት እንዲደርስ የታክስ ከፋዩን የአሜሪካ ህዝብን ችሮታ አልሰጥም ማለታቸው ፃድቅ አያሠኛቸውም።
   ትራምፕ በሰው ሥቃይ ወደር የሌለው እርካታ የሚያገኙ ይመሥላሉ። ለበጎ ዓላማ የትላንት የክርስቶስ ወዳጆች የለገሱትን ብር እንኳን እንደራሳቸው በመቁጠር ለዓለም አቀፉ የጤና ተቋም አልሰጥም ማለት ትርጉሙ ይሄው ነው። በዚህም አድራጎታቸው ከጥንት የሮማዊያን ጨካኝ ባህሪ ያልተላቀቁ መሆኑን ያሥመሠክራሉ እንጂ መልካም ሥም አያገኙም። የእኚ ሰውን ፣በራሥ ፍቅር መሥከር፣እና በሌሎች ፍቅርና መብገን  “ከግላድያተር ፊልም” ልትገነዘብ ትችላለህ። (Gladiator Movie )።…ታላቅ ሥትሆንባቸው እንዴት አድርገው አዳክመው እንደሚጥሉህ ነው ሌትና ቀን ሤያሤሩብህ የሚያድሩት።
     ሁል ጊዜ ባላቸው ትልቅ ዱላ ተመኪዎች ቢሆኑም ፣አንድ ቀን ግን የእግዜር ለምጭ እንደሚያጠፋቸው አያሥተውሉም።ምክንያቱም ማሥተዋላቸውን ሤጣን ከተፈጥሮ ውጪ እንዲጨማለቁ አድርጎ ለውጦታልና።
   “ምነው ይህን ያህል አመረርክባቸው?አንተንም በደቂቃዎች ውሥጥ ሊያጠፉህ ይችላሉ እኮ”ሊል ይችላል  አንድ ከጥብ የራቀ ሰው።ወንድሜ እኔ ከተወለድኩ ጀምሮ ሞትን ይዤ እንደምዞር አሳምሬ አውቃለሁና ሞቴ አይገርመኝም።ይሁን እንጂ የፅሑፊ ዓላማ አውሮፓና አሜሪካን እንዲሁም ኢሲያን ከፍቅር አልባነት ማላቀቅ እና የሰው ልጅን ታላቅነት በሚያሥከብሩ ፣ዜጎች መሪዎቻቸው እንዲተኩ የሚያሥችል የጥበብ ብርሃን በዜጎቻቸው ልብ እንዲበራ ማድረግ ነው ። ደርሶ እንደ አበደ ሰው የትራምፕን ፀጉር ላጭቼ ወደ ቂሊንጦ አሥገባቸዋለሁ በማለት የእብድ ፅሑፍ እንዳልፃፍኩም ተረዳ።እወቅ፣ እሳቸው የታላቋ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ናቸውና   አከብራቸዋለሁ።ሆኖም ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት አይመጥኑም ብለው ድምፅ ካልሰጧቸው ጎን ደሞ እሰለፋለሁ።
  እኔም እንደብዙዎቹ፣ተቃዎሚዎቻቸው፣እርሳቸው  ለራሳቸው እና ለጥቅም ሸሪኮቻቸው ድሎት እና ምቾት ሌት ተቀን ተጨናቂ እንጂ ለአሜሪካም ሆነ ለዓለም ህዝብ አይጨነቁም ባይ ነኝ። ምናልባትም በፍቅር አልባው ሤጣን አእምሯቸው የተሰለበ ከመሆኑ የተነሳ ፣ ሰው ለጅን በተለይም የአፍሪካን ህዝብ  እንደ ሰው ከማያዩት ጥቂቶች መካከል እሳቸው አንደኛው ሳይሆኑ አይቀርምም እላለሁ። “በዴቭል አድቮኬሲ” ውስጥ እንዳለው ሰባኪም ሆነው ይታዩኛል።እናም በጊዜ ተፀፅተው በንሥሐ ወደ ፈጣሪ ቢመለሱ እና “ሰውን በክርስቶስ እንጂ በሌላ አላውቀውም። ” ቢሉ ደስ ይለኛል። የምደሰተውም ለአሜሪካ ህዝብ ከክርስቶስ ኢየሱስ መድኃኒትን ቢያገኙ ነው።በቃ!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop