ለዛች አገር የሚገባት እውን ይሄ ነውን?

ከያሬድ ኤልያስ

ዘረኛው ወያኔ አገዛዝ መንግስት ስልጣን ከያዘበት ግዜ አንስቶ አሁን እስካለንበት ድረስ እየሰራ ያለው ነገር በውነት ከሌላ አገር ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛት ለመያዝ የመጡ ሰዎች እንጂ እውነት ኢትዮጵያኖች ናቸው ለማለት እያጠራጠረ መጥቷል።

ሃገራችን ኢትዮጵያ አውን በምትገኝበት ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ምስቅልቅል የፖለቲካው ነጸብራቅ መሆኑን ማንም ሊመሰክር ይችላል ለዚሁም አንዱ ማሳያ ከፍተኛ የሆነ የዜጎች ስደት ነው።ከሁለት ዓመት በፊት ጋሎፕ ኢንተርናሽናል ባደረገው ጥናት መሰረት የኢትዮጵያ ዜጎች ለኑሮ የማይመርጧት ሃገር እንደሆነች ተዘግቧል። ጥናቱ እንዳመለከተው ከሆነ እድሉን ካገኙ፣46 በመቶ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደውጭ የመውጣት ፍላጎት አላቸው ።ያው ይሄን ያደረገው ?

ይገርማል ግን! ኢትዮጵያዊያንን ከአገራቸው ያውም ወደ አረብ አገራት ያለምንም ማስተማመኛ በዓመት 500 000 ያውም ሳውዲ ዓረቢያ ብቻ ዲፖርት ያደርጋሉ ያው ዲፖርት ማለት አደለምን ። ከዛማ ስለነሱ ማን ይጠይቃል እንዲህ እያለ የወያኔ ጠባብ ብሄርተኛ ዘረኛው ፓርቲ ለተከታታይ ዓመታት ባለሁለት አሀዝ ኢኮኖሚዊ ዕድገት እንደተመዘገበ፣ ድህነት በገጠርና በከተማ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሸነፈ መምጣቱን እየነገረን ይገኛል፡፡ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የመጨረሻ የትግበራ ዓመት ከድህነት በታች የሚገኙ ዜጎች 22 በመቶ ብቻ እንደሚሆን ተነግሮናል። ሀገራችን ኢትዮጵያ ፈርጀ ብዙ በሆኑ ችግሮች ውስጥ ተተብትባ ትገኛለች፡፡ ገዥው ፓርቲ በሚያራምዳቸው ጠርዝ የያዙና ስልጣንን ከሀገር ጥቅም በፊት የሚያስቀድሙ አመለካከቶችና አሰራሮች ብዙ ዋጋ እያስከፈለን ይገኛል፡፡ አገዛዙ የሚከተላችው ጥራዝ ነጠቅና የዜጎችን ጥቅም ያላማከለ አካሄድ ሀገርን እየጎዳ ይገኛል፡፡ ከነዚህ ፖሊሲዎች አንዱ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ዘላቂ የሀገርን ጥቅም ባላገናዘበ መልኩ ለባዕዳን የመስጠት ጉዳይ ነው፡፡መንግስት ራሱ ባቀረበው መረጃ መሠረት ከ380 ሺ ሄክታር በላይ መሬት ለውጭ ባለሃብቶች መሰጠቱን ተገልጿዋል፡፡ የአዲስ አባባን 54 ሺ ሄክታር የቆዳ ስፋት በግምት ውስጥ ስናስገባ፣ ኢህአዴግ ለውጭ ባለሃብቶች የሰጠው መሬት የመዲናችንን ሰባት እጥፍ በላይ ነው፡፡ መንግስት የፊሊፒንስን ቆዳ ስፋት የሚያክል መሬት (3 ሚሊየን ሄክታር) ለውጭ ባለሃብቶች ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን እንደገለፀ ይታወቃል፡፡ በጋንቤላ ክልል ብቻ 1.2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለሰፋፊ እርሻ እንደተዘጋጀ መንግስት ገልጸዋል፡፡ ይህ ማለት ከጋንቤላ አጠቃላይ ስፋት 37 በመቶ በላይ መሬት በእርሻ ኢንቨስትመንት ስም ለውጭ ባለሃቶች ለመስጠት ኢህአዴግ እየሰራ ነው፡፡ ለዚሁ ማስፈጸሚያ ይረዳው ዘንድ ኢህአዴግ በጋንቤላ ሰፊ የሰፈራ ፕሮግራም እያካሄደ ይገኛል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሥውሩ (ገጽ አልባው) ሕወሐት - ኢኑሻ አየለ

ይቀጥልና ዘረኛው ወያኔ መንግስት ይሄ አስመሳይ በሃሪውን ቀየሮ ለስልጣን መቆያ ይሆነው ዘንድ በሃይማኖት በኩል ዞሮ መጥቶ በተለይ በመላው ኢትዮጵያ መስኪዶች ስፍር ቁጥር የሌለው ህዝብ በአይነቱ የተለየ እና ግዙፍ ተቃውሞ ያደረገ ሲሆን ሙስሊሙ ማህበረሰብም ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ መንግስት በሙስሊሙ ላይ እያደረሰ ያለውን ከፍተኛ እንግልት በሃይማኖቱ ላይ የሚያደርገውን ግልጽ ጣልቃ ገብነትና እንዲሁም የህዝብ ሙስሊሙ ተወካዮች ላይ መንግስት እያደረሰ ያለውን ንቀት የተሞላበት ከፍተኛ ስቃይ እና አምባገነናዊ ተግባር እረ እስከ መቼ ነው የሚጠበቀው ? ምንስ ነው ዝም ያስባለው ብዬ ሳስብ በአንድ ወቅት አንድ ተናጋሪ ባደረጉት ንግግር ላይ የተናገሩት ነገር ትዝ አለኝ ለካስ ትክክል ነበር ለማለት ወደድኩ ” አገር ቤት ውስጥ ያለው ህዝብ ሁሉንም ነገር ሰለለመደው ለሱ አዲስ ነገር አደለም የነጻነትን ትንፋሽ የሚባለውን አያውቅም ምክንያቱም አንድ ትልቅ ነገር ሲነሳ ለዛ ለተነሳው ነገር አንድ ሳምንት ሆይ ሆይ ይልና ወዲያው ይለምደዋል” ሌላም እንድህዚሁ አይነት ሲገጥም ለአንድ ወር ያህል ሰው ያለቅሳል ያዝናል ወዲያውም ይለምደዋል ስለዚህ ምንም አይነት ነገር ይፈጠር ነጻነት የምትባለዋን ነገር እንዳለችው ባለችው ነገር ላይ ተላምዶዋት ቍጭ ብሏል ነገር ግን የነጻነት ትንፋሽን የሚያውቀው ያው ወደውጭ አገር ወጥቶ የነጻነትን ትንፋሽ አጣጥሞ ወደ አገር ቤት የሚገባው ሰው ብቻ ነው እንደገባም የህዝቡ የነጻነት ትንፋሹ በትንሽና ጠባብ ብሄርተኛ ዘረኛ ወረኛ መንግስት ታግቶ ሲያይ ምንኛ እንደሚያሳዝን ያሳያል ።

ይህው እንዳየነው ሙስሊሙ ህብረተሰብ በቤታቸው እንኳን ቍጭ ማለት እንዳልቻሉ በሰላማዊ ሰልፍ እየገለጹ ይገኛሉ በአንድ ቴሌቪዠን ለ80_90 ሚልዮን ህዝብ ማስፈራሪያ ይነገረዋል አልፎ ተርፎ የ 1000 አመት ታሪክ ያላቸውን እነዛ ተከባብረው የሚኖሩ አጥር ብቻ የሚለያቸው ሁለቱ ወንድማማቾቹን ሙስሊምና ክርስትያኑን ሊያባሉ ስንት ይዘይዳሉ ። ለነገሩ ነው እንጂ ማን ይሰማቸዋል። ንጹህ የነጻነት ትንፋሽ እንዲተነፍስ እናድርገው ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጎሣ ፖለቲካ፣ የጎሣ ግጭቶች እና መዘዛቸው በኢትዮጵያ (በዘመነ ወያኔ)

እግዚሃብሄር ኢትዮጵያ ይባርክ!!

Share