እናት ሀገራቸን ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት ከሩቅ የመጡ ባዕዳንና ከጎረቤቶቿ ጭምር ትንኮሳ ቤካሄድባትም ፡ በቆራጥ ጀግኖች ልጆቿ ይህ ቀረው የማይባል የደምና በጥሬታቸው የመሰዋዕትነት ዋጋ በመክፈል ሀገሬቱን ለዘመኑ ትውልድ አብቅተዋታል ። በታሪካዊው የአድዋ ጦርነት በአፄ ሚኒሊክ መሪነት ድል የተነሳው ፋሽሽዝት ጣሊያን ፡ የዛሬ 70 ዓመት እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1928 ዓ.ም የደርሰበትን ሽንፈት ለመበቀል ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎችን ታጥቆ በዓለም የተከለከለ የመርዝ ጢስ በመጠቀም አዲስ አበባ ድረስ በመዝለቅ ለአምስት ዓመታት ያህል በከተሞችና በካምፖች ተወስኖ ከቆየ በኃላ ጀግኖች አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ዳግመኞ በከፈሉት መሰዋትነት ድል ተመትቶ ከሀገራችን ተጠራርጎ ለመውጣት ተገዷል ። ይሁን እንጂ ከ70 ዓመት በኋላ የጣሊያን ወራሪ ግፈኞ ጦር መሪ ለነበረው ሩዶልፎ ግራዚያኒ እነሆ እንደ ብሄራዊ ጀግና በመቁጠር በቅርቡ ሐውልት ተሠርቶለት ተመርቋል ። በወቅቱ የፋሽሽዝቱ ሥርዓት ቁንጮ ለነበረው ቤኒቶ ሞሶሎኒ ደግሞ ድርጊቱን በማወደስ ግፈኛና ወንጀለኛ ታሪኩን ለማደስ የፋሽሽዝም አቀንቃኞች
አንገታቸውን ቀና ቀና ማድረግ ተያይዘውታል ። በዚህ ሂደት ባለፉት ዓመታት በቅሌት ከስልጣን የተባረርው ቫሊስኮኒ ግንባር ቀደሙ ነው ። በሳንሆዜ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መል ዕክትን ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ