በየቀኑ ከመሞት አንዴ መሞት አይሻልም ? ? (ከሎሚ ተራ፤)

(ከሎሚ ተራ፤)     Friday, September-06-13

ከጥቂት አመታት በፊት አንድ የልብ ወዳጄ የሆነ ፤በድንገት በመታመሙ ምክነያት በዚህ በምኖርበት አገር በሆሰፒታል ተኝቶ ሀኪሞች በሚቻለው ሁሉ ሊያድኑት ሞክረው ሰላልቻሉ፤ በመጨረሻ ግን በመዳህኒት እድሜውን ማሰረዘም እንጂ ማዳን እንደማይችሉ ለቤተሰቦቹ ገልጸው መድሀኒት መሰጠቱን ቀጠሉ። በሸተኛው ግን፤ ምን የሚናፈቅ ነገር አለና በመዳኸኒት እድሜዬን አራዝማለሁ ? እባካችሁ ተዉኝ ልሙት መዳህኒቱን ሌላ ሰው እርዱበት ቢል ሰሜ አጣ። ልሙት ተዉኝ ቢል አትሞትም፤ አንትን ማዳን ባንችል ማቆየት የኛ የሞያ ግዴታ ነው። እንድትሞት ለመተባበር ሕጉ አይፈቅድልንም (Assisted suicide)በህግ የተከለከለ ነው። በሚል ለመሞት ፈልጎ የቆረጠውን ወዳጄን ሳይወድ በግዱ እያቃሰተ ህይውቱ እንዲቆይ አደረጉት። ከብዙ ሰቃይ በሆላ ግን መሞቱ አልቀረምና ሞተ። ታዲያ ሁልጊዜ ይህን ወዳጄን ባሰብኩ ቁጥር መሞት ላይቀር መሰቃየት ለምን ይመረጣል ? እየተሰቃዩ በህይወት መቆየትሰ ትርፉ ምንድነው ? የሚለውን ባሰብኩ ቁጥር የ ወቅቱ ያገራችንም የፖሎቲካና ፖሎቲከኞች ጉዳይ ከዚሁ እውነታ ጋራ ይያያዝብኛል።

በየቅኑ ከመሞት አንዴ መሞት አይሻልም ? ?

ይሄን ያኸሉ የዚህ ከልል ነዋሪዎች ታሰሩ። ይሄን ያኸሉ፤ ተገደሉ። የዚህ ፖሎቲካ መሪ ታሰረ፤ እነከሌ የደረሱበት አልታወቀም። ይሄን ያኸል ሺዎች ተሰደዱ። በሺ የሚቆጠሩ ተፈናቀሉ።  እነከሌ እደሜ ልክ ተፈረደባቸው። በዚህ ቀን ፤ የዚኸኛው የፖሎቲካ ድርጅት ሰልፍ ጠርቷል። በዚኸ ቀን ደግሞ የዚኸኛው ድርጅት በቀጠሮ ላይ ነው፤  10 ሩ ተዋሀዱ 33ቱ ህብረት አደረጉ። ሰልፉ ተፈቀደ። ፍቃድ ተከለከለ። ሰልፈኞች ተደበደቡ። ደማቸውን እያዘሩ በሩጫ አመለጡ.።. ወዘተርፈ፤ የዚህ…..የዚያ…. የሚለው የትግል ሂደት ብዙዎችችንን  ልባችንን እያማለለ ከዛሬ ነግ አንድ ውጤት ላይ ይደረሳል በሚል ተሰፋ ፤በእጅ ጨብጠው የማይገምጡት ዳቦ ሆኖብናል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ትንሽ ስለ ጀዋር መሓመድ - በአብርሃ ደስታ

በየቀኑ ከመሞት አንዴ መሞት አይሻልም ? ?

ሁልጊዜ የወቅቱን ያገራችንን ሰቃይ አጀንዳ እያደረግን ሰንወያይ ከመዋል ? ተንታኞችም በቸግሩ ሳቢያ ሊደረሰ ሰለሚችለው የ ኢኮኖሚ ውደቀትና የሕዘብ እልቂት ሲተነትኑ ከመዋልና በየቀኑ ለሚታሰረውና ለሚሞተው ከማዘንና ከማንባት፤  ጋዜጠኞችም ሁልጊዜ መከራውንና ሰቃዩን ሰንት ሰው እንደታሰረና እንደተገደለ ሰንቶችም እንደተፈናቀሉ፤  የተጨበጠውን ዜና ለሕዘብ ለማድረሰ ከመውጣት ከመውረድ ሰለ ሰላም፤ ሰለ ዲሞክራሲ መሰፈን፤ ሰለ ኢኮኖሚ እደገት ሰለ መሀበራዊ ኑሮ መሻሻል መዘገብ አልናፈቃችሁም ? ?

በየቀኑ ከመሞት አንዴ መሞት አይሻልም ? ?

ከሚጻፉ ተጨባጭ የሀገር ወቅታዊ እዉነታዎች እንኳን ሳይቀር  መጣጥፎቹ ገና ለገና የአንዱን የፖሎቲካ ፓርቲ ህልውና ይነካል በሚል ሳቢያ ለንባብ እንዳይበቁ፤ የሚደረገው ጥረትና ሴራ፤ ቁጥር ሰፍር የላቸውም ፤ሃቅ የሚናገር ምሁር ሳይቅር ልዩ ታፔላ እየተለጠፈለት  ቁልቁል እንዲወረድና እንጦርጦሮሰ እንዲወረድ ሲደረግ ማየትና መሰማት  ልብ ያደማል። ሰንቶች ባገራቸው ጉዳይ ጨሰውና ነደው በደረሰባቸው መገፋትም አዝነው እና ቆዝመው በጓዳቸው በሸተኛ ሆነው የተቀመጡ እንዳሉ እኔም አውቃለሁ እናንተም ታውቃላችሁ።  ሰንቱ ይነገራል። ለዚህ ሁሉ ያበቃን ግን የወያኔ የግፍ አገዛዝ እንደሆነ ማንም አይዘነጋም።

በየቀኑ ከመሞት አንዴ መሞት አይሻልም ? ?

ዛሬ ደግሞ በድንገት በዜና ማሰራጫ “ምሁራን ጫካ ገቡ “? የሚል ዜና ተሰማ። ደሰ የሚል ዜና ነው።

እንደ እውነቱማ ቢሆን አገርን ነጻ ለማውጣት፤ ማርክሰ እና ኤንግልሰ ሌኒን ቼኩቬራ.. ምሁር ነበሩ.። .እየተባለ መተንተን አለበት በዬ አላምንም።   በየቀኑ ከመሞት፤ ኢትዬፒያን እወዳለሁ፤ እየደረሰ ያለው ግፍና መከራ እንቅልፍ የሚያሰተኛ አይደለም፤ የሚል ሁሉ የተማረ ያለተማረ አሮጊት፤ወጣት ሸማግሌ ሳይል ሁሉም በአንድ ልብ ቢሰለፍና ቆርጦ በየቀኑ ከምሞት አንዴ ልሙት።፤ ( እኔ ሞቼ) መጪው ትውልድ ነጻነቱን ያግኝ ብሎ የቆረጠ ሕዘብና የፖሎቲካ መሪ ቢወጣና የቆረጠ አቋም ቢኖር ጫካ መግባትም አያሰፈልግም ነበር ብዬ አምናለሁ በግሌ። እኔን ያልገባኝ ነገር እና ጫካ የገቡትንም ምሁራንን እንዲያሰረዱኝና ሊገቡ የተዘጋጁትንም ምሁራኖች የምጠይቀው? ከ ኤርትራ መሬት ተነሰቶ ወያኔን መጣል እንዴት እንደሚቻል ብቻ ነው። ከተቻለ እሰየው። መታሰር ላይቀር፤ መሞትም ላይቀር፤ መሰደዱም ላይቀር፤ ጨረቄን ማቄን ሳንል ቆርጠን፤ ዛሬ እኔ ሞቼ ነገ ትውልዱ ነጻ ይውጣ ማለት ካልቻልን መቼውንም ቢሆን ነጻነት የለም። በየትኛውም አይነት የትግል ታሪክም መሰዋትነት ሳይከፈል ነጻነት ተቀዳጁ የሚል ታሪክ አናነብምና፤ በየቀኑ ከመሞት አንዴ መሞት ይሻላል በሚል ልሰናበት። በቸር ይግጠመን። ለመሞት የቆረጥንም ያርገን። አሜን! !

ተጨማሪ ያንብቡ:  ‹ልጅ ያቦካው ---- › እንዲሉ! (ልጅ ተክሌ 'የኢሳት 3ኛ አመት ክብረ-በዓል የሙስሊሞች ብቻ ነው እንዴ?' በሚል ላቀረበው ጽሁፍ የተሰጠ ምላሽ)

በየቀኑ ከመሞት አንዴ መሞት አይሻልም? ? አሰተያየትም ሆነ ወቀሳ በዚህ ኢሜል ያድርሱን አደራ mwl200825@yahoo.com

Share