ክንፉ አሰፋ
በተንጣለለ ቪላ ውስጥ ከበድ ያሉ እንግዶች “ጸዳ” ባሉ ምግብና መጠጦች እየተስተናገዱ ነው። ታዋቂ ግለሰቦች፤ ባለስልጣናት እና አርቲስቶች የቀረበላቸውን ብፌ በልማታዊ ወጋቸው እያወራረዱ ሳሉ አንድ እንግዳ ነገር በመሃላቸው ተከሰተ። ሞቅ ባለው የአይቴ ነጋ ገብረእግዚአብሄር ድግስ ላይ ያልተጋበዙ ሁለት ሰዎች ዘው ብለው ከግብዣው ክፍል ገቡ። የፌዴራል ፖሊስ አባላት ነበሩ።
በዚህ ያልተለመደ ክስተት የአቶ ነጋ እንግዶች አልተደናገጡም ነበር። ይልቁንም የፌዴራል ፖሊሶቹ ለተጨማሪ ጥበቃ የመጡ ነበር የመሰላቸው። አንድ ብርጌድ ያህል ጦር አስከትለው የመጡት ፖሊሶች ግን አቶ ነጋ ገብረእግዚአብሄርን አስጠሯቸው። አቶ ነጋም ለጥሪው እንደወትሮው በመወጣጠርና ፍጹም ትእቢት በተሞላበት አነጋገር ምላሽ ሰጡ። በፖሊስ አባላቱ እና በአቶ ነጋ መካከል የሃይለ-ቃል ልውውጥ ተጀመረ። እሰጥ እገባው አንድ፣ ሁለት እያለ ሄደና በመጨረሻ ተካረረ። በዚህ ሰዓት አቶ ነጋ ስልክ መደዋወል ያዙ። ከፍተኛ የሚባሉ ባለስልጣናትና ምኒስትሮች ጋ ደወሉ። ከዚያም በመቀጠል፣ ጀነራሎች ጋ ደወሉ… የጦር መኮንኖች፣ የፓርቲ ባለስልጣናት… ሁሉም ጋ ተደወለ። የባለስልጣናቱ ምላሽ ግን ጥሩ እንዳልነበር ከአቶ ነጋ ፊት ላይ ይነበብ ነበር። ወዳጆቻቸው ሁሉ እንደ ቱኒዚያው ቤን አሊ በአንድ ጊዜ ከዷቸው።
“በል – ና – ውጣ!” አለ አንደኛው የፖሊስ አባል፣ የስልኩን ሽርጉድ በጥሞና ከተከታተለ በኋላ።
“ምን ማለትህ ነው? እኔኮ ነጋ ነኝ። ነጋ ታሪኩ!” አሉ። አነጋገራቸው የጀምስ ቦንድን ይመስል ነበር። በዚህ ጊዜ ታዲያ እጃቸውም አላረፈም። ከጎን ያሸጎጡትን መሳርያ ለማውጣትም ዳዳቸው።
በቅጽበት ግን ፌዴራል ፖሊሱ ቀደማቸው። በድንገት “ጯ!” የሚል ድምጽ አዳራሹን አናጋው። የፖሊሱ አይበሉባ የግራ መንጋጭላቸው ላይ ሲያርፍባቸው ጊዜ፤ አይቴ ነጋ ነገር አለሙ ተደበላለቀባቸውና እጅ መስጠትን መረጡ። ግብር ሊያበሉ በጠሯቸው የክብር እንግዶቻቸው ፊት፣ ከዚህ በላይ መዋረድ አልፈቀዱም። ሁለት እጃቸውንም ወደ ፖሊሱ በመዘርጋት ለብረት ማሰርያው ራሳቸውን አመቻቹ። እጃቸው የኋሊት ከተጠፈረ በኋላም አቶ ነጋ እንዲህ አሉ። “በቃ! ህወሃት አበቃለት!”
“ባለሃብቱ” በዚህ ሁኔታ በፖሊስ መኪና ተጭነው ወደ እስር ቤት ሲሄዱ፣ ተጋባዥ እንግዶቹም እግሬ-አውጭኝ እያሉ ከስፍራው አፈተለኩ። ይህ ታሪክ ድራማ ሊመስል ይችላል። ግን በእውን የተፈጸመ ሃቅ ነው። ታሪኩን ያጫወተኝ ሰውም እዚያ ግብዣ ላይ ግብር ሊበላ ተገኝቶ ነበር። እንደ አግራሞቱም “ይህ መቼም የፈጣሪ ስራ ነው።” ከማለት ውጪ ስለ ጉዳዩ እንድምታ የሰጠው ማብራሪያ የለም።
ነጋ ገብረእግዚአብሄር የነፃ ትሬዲግ ኃላፊነቱ የተወሰነ (ሰዎች ያልተወሰነ ይሉታል) የግል ማህበር ባለቤት ነበሩ። ድርጅታቸውም እንደስሙ ከሁሉም ነገር ነጻ ነበር። ከግብር ነጻ፤ ከቁጥጥጥር ነጻ፤ ከፍተሻም ነጻ። በመቶዎች የሚቆጠሩ የጭነት መኪናዎች እቃ ጭነው በየኬላው ሳይፈተሹ እንዲያልፉ የተሰጠ ልዩ መብት ሁሉ እንደነበራቸው ይነገራል። ዛሬ ፈጣሪ ሲፈርድባቸው በኢፍትሃዊ መንገድ ቢልየነር ያደረጋቸው ስርዓት፤ ያው ስርዓት ሰለባ አደረጋቸው… ነጋ ገብረእግዚአብሄር ለአቶ መለስ ዜናዊ እና ለባለቤታቸው ለወ/ሮ አዜብ መስፍን ቅርብ – በጣም ቅርብ ነበሩ። ለጉምቱ ባለስልጣናት ይሰጡት የነበረው እጅ መንሻ ከዚህ አይነት ውርደት እና እስራት ሊያድናቸው አልቻለም። በትግራይ ውስጥ ከ40 ሚሊየን ብር በላይ አውጥተው በስማቸው ያሰሩት የቴክኒክ ኮሌጅም እንደ ውለታ አልተቆጠረላቸውም።…
ይህችን አጭር መጣጥፍ ለመጫር እንደተቀመጥኩ አንድ ዜና በኢሜይል ደረሰኝ። የዜናው ርእስ “ጀነራል ባጫ ደበሌ የአዋሽ ባንክ ሰራተኞችን ከሥራ እንዲባረሩ አደረጉ!” ይላል። ባጫ ደበሌ የባንክ ሰራተኞቹን ያባረሩዋቸው ‘’እኔ ጀነራል ባጫ ደበሌን እንዴት አታውቁኝም?’’ በሚል በሰራተኞቹ አለመታወቃቸው አበሳጭቷቸው ነበር። ወደ ፌስ ቡክ ጎራ ስልም አንዳንዶች በዜናው ላይ ሲወያዩ አስተዋልኩ። ይህ እኮ አዲስ ክስተት አይደለም። ለብዙ ጊዜ የሚደጋገም እና የተለመድ ነገር ዜና ሊሆን አይችልም። ውሻ ሰውን ሲነክስ ዜና አይሆንም። በተቃራኒው ግን ሰው ውሻን ከነከሰ ዜና ይሆናል። እንዲህ አይነቱ ክስተት ስር የሰደደ የስርዓቱ ባህርይ ነው። ባጫ ደበሌ እነዚያን ሰዎች ማስገደል የሚያስችልም ስልጣን እና መብት ያላቸው የአዜብ ሰው መሆናቸውን አንዘንጋ። ጀነራል ባጫ በተልእኮ ትምህርት ከአንድም ሁለተኛ ዲግሪ እንዲገዛላቸው ካደረጉ በኋላ፣ ለምርቃታቸው ስነ-ስርዓት፣ ሰንጋዎች ጥለው፣ የሙዚቃ ባንድም አስመጥተው፣ መንገድ ሁሉ እንዲዘጋ አድርገው ሲያበቁ፤ በተለመደው ብሬክ ዳንሳቸው መንደሩን የቀወጡ ሰው ናቸው። በብርሃን ፍጥነት ከኪነት ጓድነት ወደ ጀነራል የተሸጋገሩት ባጫ ደበሌ በመደበኛ የስራ ጊዜያቸው ጫት ይነግዳሉ። በትርፍ ጊዜያቸው ደግሞ በዜጋው ላይ እንዲሁ እንደዋዛ እየቀለዱ እስካሁን አሉ። የነገውን አንድዬ ብቻ ነው የሚያውቀው። የፍትህ ሳይሆን የግለሰቦች የበላይነት የሰፈነበት ሃገር ስልጣንን ያላግባብ መጠቀም ሙስና ሊደንቀን አይገባም። የፍትሃዊ ስርዓት መጥፋት ነው ሙስና።
ፕሮፌሰር አል ማርያም ባለፈው መጣጥፉ ስለሙስና ሲጽፍ ከሙስና ሁሉ በላይ ሙስና የሚሆነው የፍትህ መጓደል እንደሆነ አስነብቦናል። የፍትህ መጥፋት ስብእናን፣ ነጻነትንና ንብረት ማጣትን ያስከትላልና። In my view, denial of due process (fair trial) is the highest form of corruption imaginable in the “justice sector” because it results in the arbitrary deprivation of a person’s life, liberty and property. (Al Mariam)
ከሰሞኑ ደግሞ ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም ምንጩ ያልታወቀ ሃብት አፍርተሃል በመባል ተወንጅሎ ወህኒ የወረደው የወልደስላሴ ወልደሚካኤልም ዜና በስፋት እየተሰራጨ ነው። ወልደስላሴ ሌላኛው የአዜብ መስፍን የቅርብ ሰው ነበር። በዚህ ጉዳይ ላይ ዳዊት ከበደ በስፋት ትንታኔ ስለሰጠበት እዚህ ላይ አልደግመውም። ወልደስላሴ ግን ከህወሃት የጫካ ትግል ጀምሮ ቀልፍ ቦታዎች ላይ ተመድቦ የሰራና – የመለስ ቀኝ እጅ የነበረ ሰው ነው። ታማኝ አገልጋይም ስለነበረ በህወሃት ውስጥ ወሳኝ ቦታ ነበረው።
ከወልደስላሴ እስር በኋላ ብዙዎች በህወሃት ውስጥ ውጥረት እንዳለ መናገር ጀምረዋል። ውስጥ ለውስ እየተንከባለለ ያለው ውጥረትማ ከከረረ ትንሽ ዘግየት ያለ ይመስላል። በውጥረቱ የተነሳም በባለስልጣናቱ መካከል እርስ በርስ መተማመን ከጠፋ ቆየ። አንድ ውስጥ አዋቂ ስለዚህ ሁኔታ ሲያጫውተኝ አባላቱ በምሽት ሲወጡ እንደ ጅብ ጎን ለጎን ነው የሚሄዱት። ጅብ ስለሚፈራ ብቻውን አይሄድም። ሁሌም ተጠራርቶ በቡድን ይሄዳል። ከባልንጀራው ጋር አብሮ ሲሄድ ደግሞ ጎን ለጎን መሆን አለበት። ፊትና ኋላ ከሆኑ እርስበርስ ይበላላሉ።
በአሁኑ የህወሃት አሰላለፍ ግን አንደኛው ወገን ከኋሊት መጥቶ የቀደመ ይመስላል። ከፊት ያለው የኋላውን መብላት ጀምሯል። ተገላቢጦሽ የሆነው ይህ አስገራሚ ክስተት ነው ውጥረቱን ይበልጥ ያከረረው። የአዜብን ቡድን የማጥፋቱ ሂደት ላይ ግን ከፍተኛ ጥናት ሳይደረግ አልቀረም። የፖለቲካ ሃይል አሰላለፉ ላይ ሚዛን የደፋው አንደኛው ቡድን ከደሙ ንጹ ባይሆንም የሙስናውን ወንጀል ለብቀላ መጠቀምያ ማድረጉ የአደባባይ ምስጢር ነው።
አንዳንድ የዋሆች ታዲያ ይህ የጸረ-ሙስና ዘመቻ አቶ መለስን ለማሳጣት እየተደረገ ያለ ድራማ እንደሆነ ይናገራሉ። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝንም የሚያመሰግኑም አልጠፉም። አቶ ሃይለማርያም ብዙውን ክስተት እንደ ተራው ሰው በዜና እንደሚሰሙ የሚያውቁት በቅርብ ያሉት ሰዎች ብቻ ናቸው። ለነገሩ እሳቸውም አስቀድመው “የእኔ ስራ ከፊትም ሆነ ከኋላ የሚሰጠኝን ትእዛዝ እየተቀበሉ ማስፈጸም ብቻ ነው።” ብለዋል። ከፊትና ከኋላ ብቻ ሳይሆን ከላይና ከታችም መመርያ እየተቀበሉ ያስፈጽማሉ። በሙስናው ስም የሚካሄደው ጨዋታ ከሳቸው ራዳር ውጭ ያለ መሆኑን ለመረዳት የፖለቲካ ጥበብን አይጠይቅም።
አቦይ ስብሃት በአንድ ቃለ-መጠይቅ ላይ ስለዚህ ጨዋታ ሲናገሩ የ10 ሚሊዮኑ ዘራፊ ቁጭ ብሎ የ10 ሺው መታሰር የለበትም ብለው ነበር። አቦይ ስብሃት እውነት ብለዋል። ከሌላው ጋር ሲነጻጸር ከአቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ ቤት ተገኘች ተብላ በኢቲቪ ጭምር ስትታይ የነበረችው 26 ሺ ኢሮ ኢምንት ናት። Global Financial Integrity (GFI) በመባል የሚታወቀው አለማቀፍ የገንዘብ ግልጸኝነት ተቋም ከ 2001 እስከ 2010 ብቻ ከኢትዮጵያ ተዘርፎ ወደውጭ የወጣው ገንዘብ 16.5 (አስራ ስድስት ነጥብ አምስት) ቢሊየን ዶላር ነው ሲል መረጃውን ከነማስረጃው ይፋ አድርጓል። ይህ ድርጊት ደግሞ በሙስና ከዘቀጡ ሃገራት ኢትዮጵያን በመጀመሪያው ደረጃ ላይ አስቀምጧታል። ልብ በሉ! 16.5 ቢሊየን ዶላር ከአራት በላይ የ”ህዳሴ” ግድቦችን ያሰራል። ከሁለተኛው አለም ጦርነት በኋላ መላው አውሮፓን ከውድቀት ያስነሳው የማርሻል ፕላን በጀት 20 ቢሊየን ዶላር ነበር። ከኢትዮጵያ በስምንት አመታት ጊዜ ውስጥ ብቻ የወጣው 16 ቢሊየን ዶላር ደግሞ አፍሪካ ካለችበት ውድቀት ሊያስነሳት የሚችል ገንዘብ እንደሆነ የኢኮኖሚ ጠበብት ይናገራሉ።
ኤ.ቢ.ሲ ኢንተርናሽናል የተባለው የማድሪድ ጋዜጣ ወ/ሮ አዜብ መስፍን በአንድ ቀን ግብይት ብቻ ለልብሷ 1.5 ሚሊዮን ዶላር እንዳወጣች ዘግቧል። አዜብ መስፍን ባለፈው የህወሃት ስብሰባ ላይ ተገኝታ ስትናገር ግን የአቶ መለስ የወር ደሞዝ 250 ዶላር እንደሆነ ነበር የተናገረችው። አዜብ የ1.5 ሚሊዮን ዶላር ልብስ በአንዲት ምሽት ስትሸምት መንግስት ድጎማ አድርጎላት ከሆነ ይኸው በይፋ ይነገር። በ250 ዶላር የወር ገቢ በሚሊዮን ዶላር ወጪ ማድረግ የሚቻልበት ሚስጥር የአባባ ታምራት ገለቴ ምትሃት ካልሆነ ታዲያ ምን ሊሆን ይችላል? ይህንን መራራ ሃቅ የጸረ-ሙስናው ኮሚሽንን የሚነዳው ቡድን እንዴት ችላ ሊለው ቻለ? በዚህ ጉዳይ ላይ በርካታ ታዛቢዎች የሚሰጡት አስተያየት የሚያስኬድ ይመስላል። ቡድኑ በቅድሚያ ወደ እነ አዜብ ሰፈር የሚወስደው መንገድ ላይ ያሉ ከእንቅፋቶችን ሁሉ ማጥራት አለበት።
በዛሬይቱ ኢትዮጵያ እንደ ቀልድ የሚነገሩ አንዳንድ እውነታዎች ለማመን የሚከብዱ ናቸው። አንዱ ‘ልማታዊ ባለሃብት’ በሪል ስቴት ስም የተመራው ቦታ ሲሰላ ከጅቡቲ የቆዳ ስፋት በልጦ ተገኘ። ይህ ሰው ትንሽ ቆይቶ ህገ-መንግስታዊ መብቱን በመጠቀም የመገንጠል ጥያቄም ሊያነሳ ይችላል እያሉ ያወሩ ነበር – በዚያ የቀኑት ባልንጀራዎቹ። በመጨረሻ ግን “ባለሃብቱ” በሙስና ታሰረና ይዞት የነበረው መሬት ለነ ቱሬ ዘመዶች በሄክታር ሁለት ብር ሂሳብ ተቸበቸበ። ለነገሩ 3.5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ከዜጋው እየተቀማ ለውጭ ዜጎች በተቸበቸባት ሃገር ይህ ምንም ላይደንቀን ይችላል።
የሙስና ሰለባ የሆነው የሌላኛው ባለስልጣን ቤት ሲበረበር ደግሞ ብሄራዊ ባንክ ይመስል ነበር። እዚያ ቤት ውስጥም የአለም መገበያያ ገንዘብ ተገኘ። ዶላር፣ ኢሮ፣ ድራም፣ የን፣ ፓውንድ፤ ክሮን፤ ፍራንክ፣ ዲናር፣ ረንቢኒ … እንዲያውም የኤርትራ ናቅፋ በገፍ ነበር። ከአቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ 26 ሺ ዶላር ተጋንና በቲቪ ስትቀርብ የዚህኛው ንግድ ፈቃድ የሌለው ባንክ በግል እጅ ሲገኝ ሜዲያም ዝም ማለትን መረጠ። በዚህ ጊዜ ነበር የአሳሪው ቡደን ሃላፊ የኮሎኔል መንግስቱን ንግግር የተጠቀመው። “ደፍረውናል፣ ንቀውናል።.. ብታምኑም ባታምኑም በቁም ሞተናል።”
አነጋገሩ ለምን ሃገር ተዘረፈ ሳይሆን እኛ ታግለን ለዚህ የደረስን የቁርጥ ቀን ታጋዮች ቁጭ ብለን እንዴት ከኋላ የመጣው ሊበልጠን ቻለ ለማለት ነበር። የሙስናው ዘመቻ ድራማ ቁልፍ እዚህ ላይ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ወደፊት በሰፊው እሄድበታለሁ። ለአሁን ግን በአቶ ኤርምያስ አመልጋ የሚደነቅ ታሪክ ጽሁፌን ልቋጭ።
በዚያ ሰሞን የአክሰስ ሪል ስቴት ሥራ አስኪያጅና የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት አቶ ኤርምያስ ጠቅል አመልጋ፣ በተለይ በውጪ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለመኖሪያ ቤት ግንባታ ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ከሰበሰቡ በኋላ፣ ከሃገር መጥፋታቸው ተዘግቦ ነበር። ታዲያ አቶ ኤርምያስን የሚረግሙ ጌጃ ዲያስፖራዎች እንዳሉ ሁሉ እሳቸውን የሚያደንቁም አልጠፉም። ስለአቶ ኤርምያስ በቀልድ እየተመሰለ ብዙ ነገር ይወራል። የተከበሩ ሎሬት አፈወርቅ ተክሌን እና አቶ ኤርምያስን የሚያመሳስላቸው ነገር ቢኖር ሁለቱም የተዋጣላቸው ሰአሊያን መሆናቸው ነው ተብሏል። ለላሜ ቦራው ዲያስፖራ እንዲሰሩ ገንዘብ የተከፈለባቸው ቤቶች ሁሉ ባማሩ ስዕሎች በወረቀት ላይ ዱቅ ብለዋል። በንዴት ገንዘቡን ሊያስመልስ የሚሄደው ሁሉ በስእሎቹ እና በአቶ ኤርምያስ ምትሃታዊ ንግግር እየተማረከ እንዲያውም ለሁለተኛና ሶስተኛ ቤት የከፈለው ዲያስፖራ ቁጥር ትንሽ አይደለም። አቶ ኤርምያስ በአንድ በኩል በሙስና ክስ እየተፈለጉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከሃገር በቦሌ አድርገው እንዲወጡ የተደረጉ “ጀግና” ባለሃብት ናቸው።
ለፖለቲካው እንግዳ ለሆኑ ሰዎች፤ እነዚህ ሁሉ ፈጠራ ሊመስሉ ይችላሉ። ግን የኢትዮጵያ ህዝብ የእለት ተለት ገጠመኞች ውስጥ አንድ እጅ እንኳን የማይሞሉ እውነታዎች ናቸው።
የሙስናው ጉዳይ – ከክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ)
Latest from Blog
ከሃይለገብርኤል አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ
የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’
ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም January 10, 2025 በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና
በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡
ሀገሪቱ እኮ የለችም…. የጄነራሎቹ ጉድ…. የአብይ አህመድ ነገር…
ሀገሪቱ እኮ የለችም…. የጄነራሎቹ ጉድ…. የአብይ አህመድ ነገር…
ዓለም ሁሉ ያስደነቀው ሚልዮኖች የተመለከቱት አስደናቂው ቪድዮ| Ethiopian Orthodox Mezmur
ዓለም ሁሉ ያስደነቀው ሚልዮኖች የተመለከቱት አስደናቂው ቪድዮ| Ethiopian Orthodox Mezmur
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤ 15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን
ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር
የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!” አቶ ቡልቻ ደመቅሳ
ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
ሀገሪቱ እኮ የለችም…. የጄነራሎቹ ጉድ…. የአብይ አህመድ ነገር…ሀገሪቱ እኮ የለችም…. የጄነራሎቹ ጉድ…. የአብይ አህመድ ነገር…ሀገሪቱ እኮ የለችም…. የጄነራሎቹ ጉድ…. የአብይ አህመድ ነገር…
ሀገሪቱ እኮ የለችም…. የጄነራሎቹ ጉድ…. የአብይ አህመድ ነገር…
ቴዲ አፍሮና ጃዋር መሐመድ፤ ”ንጉሥ አንጋሹ ፖለቲከኛ” የዘመኑ ፖለቲከኞች መካከል አንዱ የሆነው ጃዋር መሐመድ ‘አልፀፀትም’ በሚል ርዕስ ያዘጋጀውን መጽሐፍ 🔴What separates Jawar and Abiy is their measure of how much non-Oromos
ቴዲ አፍሮና ጃዋር መሐመድ፤ ”ንጉሥ አንጋሹ ፖለቲከኛ”
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ