August 12, 2013
4 mins read

ሙስሊም ወገኖቻችንን የሚያዋከወበውንና የሚያሸብረውን የወያኔ/ኢህአዴግ ተግባር እናውግዝ፣

 

ከሙስሊም ወገኖቻችን ጎን እንቁም። እናውግዝ፣ ከሙስሊም ወገኖቻችን ጎን እንቁም።

የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች፣ በየትኛውም አለም ክፍል፣ የኢድ አል ፈጢር በአል በደስታ አክብረው ሲውሉ፤  የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ብቻ በአገራቸው መንግስት ተብዬ ሲዋከቡና ሲሸበሩ ውለዋል። በብዙ የኢትዮጵያ ከተሞች፣
በተለይ ባዲስ አበባ፣ የኢድ አል ፈጢር በአሉን ለማከበር የተሰበሰበውን ሕዝበ-ሙስሊም፣ ፖሊስ በዱላና በጠመንጃ  ባካሄደው ሺብር፣ ህፃንና ነፍሰጡር ጨምሮ ህይወት ማለፉ፣ ብዙ ሰው መቁሰሉና ቁጥሩ ከግምት በላይ የሆነ ሕዝብ  መታሰሩ በሰፊው ተነግሯል።
ይህ በኢድ አል ፈጢር ክብረ-በአል ወቅት የተካሄደው ሺብር፤ ወያኔ/ኢህአዴግ ከአንደ አመት ተኩል በላይ የቀጠለውን፣  ”ድምፃችን ይሰማ፣ መብታችን ይከበር”oበማለት ሙስሊሙ ህብረተሰብ የሚያካሂደውን ሰላማዊ ትግል ለማፈን በተለያዩ  ወቅቶችና በተለያዩ ቦታዎች ሲያካሂደው የኖረው ሺብር አነዱ አካል ነው። ከኢድ አል ፈጢር ክብረ-በአል ሁለት ቀን  ቀድሞ፣ በኮፈሌ ወረዳ (አርሲ) የተካሄደው ጪፍጨፋ የቅርብ ምሳሌ ነው።
ወያኔ/ኢህአዴግ የኢትዮጵያን ሕዝብ በቁጥጥሩ ዉስጥ አስገብቶ እንደፈለገው ሲያመሳቅል ከ20አመት በላይ ያለምንም  ተጋፊ ሃይል ቢቆይም፤ ለቀጣዩ እድሜው ተፃራሪ ሃይል እንዳይነሳበት፣ ለማንኛውም ድርጅት፣ የፖለቲካ፣ የማህበራዊ፣  የሙያ፣ የሃይማኖት ወዘተ፣ ”ምስል-ጥጃ”oበማበጀት ሃቀኛ ድርጅቶችን ሲያኮላሺ ኖሯል። እስካሁን ድረስ ቀጣይና  ጠንካራ ተቃዉሞ ያጋጠመው ከሙስሊም ኢይዮጵያዊያን ብቻ በመሆኑ፣ በህዝበ-ሙስሊሙ ላይ እዬከፋ የመጣ ሺብር  ቀጥሏል።
በዚህ የሺብር ዘመን፣ ሆዳቸውን ወድደው ነፍስ የማትፋት ትዛዝ የሚፈጽሙትንና በተሰጣቸው ስልጣን በመመካት  ህዝብ የሚያሸብሩ ግለሰቦችን በወቅቱ ፍርድ ላይ ማቅረብ አይቻልም። ዘመኑ ”አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ”oእንደሚባለው
ነውና። ነፍስ አስገዳዩ የወያኔ/ኢህአዴግ ሥርዓት፣ ፍርድ ሰጪም የወያኔ/ኢህአዴግ ሥርዓት በመሆኑ ነፍሰ-ገዳዮች በነፃ  ይኖራሉ። ይሁንና የአገራቸው ጉዳይ የሚያስጨንቃቸው ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ሁሉ በነፍስ ግዳይ መጠየቅ ያለባቸውን  ግለሰቦች፤ ቀን የወጣ እለት ለፍርድ የሚቀርቡበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይኖርባቸዎል።
የህዝበ-ሙስሊሙ ’’ድምፃጭን ይሰማ፣ መብታችን ይከበር”oጥያቄ ህዝባዊ ጥያቄ እንደ መሆኑ መጠን የሁላችንም ጥያቄ  ነው። ስለሆነም የወያኔኢህአዴግን የሺብር ተግባር ከማውገዝ ባሻገር ከሙስሊም ወገኖቻችን ጎን መሰለፍ ግዴታችን
መሆን አለበት።
ህዝባዊ ትግል ይፋፋም፣
ዴሞክራሲ ይስፋፋ፣ አንድነት ይጠንክር፣
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።
መኢሶን
ነሃሴ 3 ቀን 2005 ዓ ም

 

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop