ዳዊት አበበ
በዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በሀገራችን ዉስጥ የተጣለብን ከፋፍለህ ግዛ ዘመቻ ከቀድሞው በተለየ እጅግ ዘግናኝና አስከፊ በሆነ ሁኔታ ላይ መገኘት የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ወኔና ሞራል ሳይነካ አይቀርም ብዬ እገምታለሁ። ከዚህም ውስጥ ዋነኛውና የመጀመሪያው ሰሞኑን በአማራዉ ብሔረሰብ ላይ በመድረስ ላይ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል ህዝቡን ከአድማስ አድማስ እያነጋገረው መምጣቱ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለሀገሬ ምን ሠራሁ በማለት እራሱን እየጠየቀ ? ይህን ዘረኛ የሆነ የወያኔ መንግስት ከስር መሰረቱ ነቅሎ ለመጣል በቁርጠኝነት በመነሳት ሀገራዊ የዜግነት ግዴታውን መወጣት አለበት ፡፡ ለዚህም በዋንኛነት ትኩረት ተሰጥቶት ለነገ ይደር የማይባልበት ጉዳይ ፣ ማናቸውም የተቃዋሚ ፓርቲዎችና ፥ የድጋፍ ድርጅቶች ፣ አንድ በመሆንና እጅ ለእጅ በመያያዝ ቅድሚያ ለሀገር ሰጥቶ የመጣብንን የወያኔ ሰደድ እሳት ማጥፋት ግድ ይለናል ፡፡
ለዚሁም ለ- April 8 ቀን በኦስሎ ኖርዌይ የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያና ኢህአፖ የጠሩት ሀገርህን አድን ዘመቻ ጥሪ እንደ አንድ አብነት ሆኖ የሚጠቀስ ነው ፡፡ ዘረኛው የወያኔ መንግስት ከጥነሰሱ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ስልጣን ላይ ፊጥ ብሎ እስከቀጠለበት ድረስ ሰንቆ ያመጣውን የሀይማኖትና የዘር ማጥፋት ትልም በተግባር ላይ ማዋል ከጀመረ እነሆ ብዙ አመታትን አስቆጥሯል ፡፡ ይኸውም የመጀመሪያው በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ የተጀመረው የሀይማኖት ብጥብጥ በአይበገሬው የሙስሊም ወንድሞቻችን ትግል ዕለት በዕለት እየተፋፋመ ወያኔን እንቅልፍ ቢነሳውም ፣ ህወሃት-ኢሃዴግ ተስፋ ባለመቁረጥ እንደገና ፊቱን ወደ ኦርቶዶክስ ኃይማኖት በማዞር የተለመደውን የስልጣን ማራዘም ዘመቻና ህዝብን ከህዝብ የማፋጀት አባዜን በማፋፋም እነሆ አሁን ደግሞ የአማራውን ህዝብ ከእናት ምድሩና ሀገሩ የማባረርና ዘር የማጽዳት ዘመቻውን በሰፊው ተያይዞታል።
ይህም ከማናለብኝነትና ለህዝቡ ካለው ከፍተኛ ጥላቻና ንቀት የመነጨ በመሆኑና በአንድ ዘር የበላይነት ብቻ የማመን ጠባብነት ጭምር የተጸናወተው በመሆኑ ነው ። ወያኔ ከመጀመሪያው ጀምሮ በኢትዮጵያ አንድነት የማያምንና ጭራሽ ኢትዮጵያ የምትባል አገር እንደሌለችና ኢትዮጵያ የሚለውንም ስም ያገኘችው በሚኒሊክ ዘመነ መንግሥት መሆኑን ለማሳመን የሚያደርጉትን ባዶ ጥረት በመረጃ አንድ ግለሰብ በኢሳት ቲቪ ላይ ከጋዜጠኛ ሲሳይ አገኔ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ከነ መረጃቸው አስደምጦናል ። ይህም ማለት አማራው ለትግራይ ህዝብ ጠላቱ መሆኑን አስምረው አረጋግጠውልናል ማለት ነው ። እንደውም ለአማራ ያላቸውን ጥላቻና ዘረኝነት ለመግለጽ ሲሉ ! ሆስፒታል ውስጥ አንድ በሽተኛ ከፈረንጅ ሀኪምና ከአማራ ሀኪም ማን እንዲያክምህ ትፈልጋለህ ተብሎ ምርጫ ሲቀርብለት የመለሰው መልስ አማራ ከሚያክመኝ ፈረንጁ የፈለገውን ቢያደርገኝ ይሻለኛል ብሎ በሽተኛው እስከመመለስ መድረሱን አድምጠናል።
ጎበዝ ! ወያኔዎች እኮ ዛሬ አማራውን ነገ ደግሞ ጉራጌውን ከዛም ኦሮሞውን ከሀገር በማፈናቀል እንደተባለውም ኢትዮጵያ የተባለችውንና ለዘመናት ተከብራና ታፍራ የኖረችውን፤ ጀግኖች አባቶቻችን አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍስሰው ያስረከቡንን ሀገር ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ሆን ብለው የተነሱ አረሞች ናቸው። እምነበረድ ይክበዳቸውና ! አሁን በአካለ ህይወት የሌሉት ፣ የቀድሞው ጠ.ሚኒስተር የነበሩት በራዕያቸው ግን አገሪቱን የሚያስተዳድሩት ሰው ባለቤት የሆንችው ወ\ሮ አዜብ መስፍን(ጎላ) ሰሞኑን በኢቲቪ ማቅ (ጥቁር ለብሳ) እኛን ግን ሳቅ አላብሳናለች ፣ ስለ ባለቤትዋ የወር ደሞዝ ማለት ነው ለኢህአዲግ መዋጮ ከፍሎ የሚደርሰው 4,000ብር ብቻ ነው ብላናለች ፡፡ አንድም ቀን ልጆቼን ፣ ቤቴን ሳይል ለሀገሩ 24 ሰአት ያገለገለ መሪ ነው ፥ ወደዚህ ሀገር ሲመጣም ጭንቅላቱን ብቻ ነው ይዞ የመጣው ብላናለች ። ሌላው ሰው ወደዚህ ዓለም ሲመጣ ምን ጨብጦ እነደመጣ ፣ ኧህ ! ካሏት አዜብ መስፈን ብዙ ቀልዶችን ሳትነግረን አትቀርም ፡፡
ወይዘሮዋን አንድ ያልገባት ነገር ቢኖር ፣ መለስ ጭንቅላቱን አሟጦ የተጠቀመበት ፣ የባንዳ ልጅ እየተባለ ያደገበትን በቀል ፣ህዝቡ ላይ በመበቀል ሙሉ ኃይሉን የተጠቀመ አረመኔ ፥ ጨካኝና ዘረኛ መሪ መሆኑን ያለመረዳቷ ጉዳይ ነው ። ከዚህ በፊት የመለስ ራእይ ሳይደለዝና ሳይበረዝ ትግሉ ወደ ፊት ይቀጥላል ያልሽው እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ ዛሬ ደሞ በትንሽ ደሞዝ እየተከፈለው ሌት ተቀን እየሰራ ሀገራችንን ትልቅ ደረጃ ላይ እንድትደርስ ያደረገ የመጀመሪያው መሪ መሆኑ ተሰምሮበት (Guinness book of records) ላይ ተመዝግቦ መቀመጥ አለበት አይነት ትእዛዛዊ የማስጠንቀቂያ መልክት በማስተላለፍ “የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያድርቅ” አይነት ጨዋታሽን በጥሩ ተውኔታዊ ገቢር ! የሃዘን ልብስሽን እንደ ጉሬዛ ግንባርሽ ድረስ ተከናንበሽ ትውነሽልናል ፡፡
ምናልባት መለስ ዜናዊ ትግራይን አልምቶ ይሆናል አላውቅም በእርግጠኝነት ግን መናገር የምችለው ቀሪዋን ኢትዮጵያን አድምቷል ። ህዝቡንም እርስ በእርሱ ደም እንዲቀባባና ፥ በዘርና በሀይማኖት በመከፋፈል የሀገሪቷንም መሬት ለባእዳን በመሸጥ ህዝቡን ለከፍተኛ ችግርና መከራ አጋፍጦ ፣ ዜጋ ሁሉ የሚወዳትን ሀገሩን እየጣለ በየአረብ ሀገሩና አውሮፓ ውስጥ እንዲሰደድ ያደረገ ትልቅ የማይረሳ ነቀርሳና ጠባሳ ህዝቡ ላይ ትቶ የሄደ መሪ ነው ። የእርሱን ራእይ በመከተል እነሆ አሁንም ያሉት መሪ ተብዬ ጃሌዎቹ ከሱ በባሰና አስከፊ በሆነ ሁኔታ ህዝቡን ከተወለደበትና እትብቱን ከቀበረበት ቀዬ በግፍና በጭቆና እያባረሩት ይገኛሉ ። ስለዚህ ጎበዝ ይህን ጉዳይ ዝም ብለን ማየት የማንችለውና ሁላችንም በአንድ ላይ ሆነን እጅ ለእጅ ተያይዘን ወያኔንና አንጃዎቹን “በቃ” ማለት የሚጠበቅብን ወቅቱ ከምንግዜውም በላይ አሁን ነው ።
በመጨረሻም ማለት የምፈልገው ነገር ቢኖር የኢህአፓ ወክንድ የሚያደርገው እንቅስቃሴ እጅግ የሚያኮራ በመሆኑ ሳይደነቅ መታለፍ የሌለበት ጉዳይ ነው። ለዚሁም ከዚህ በፊት በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ ወያኔ ያደረሰውን በደል አብሮ ከጎኑ በመሰለፍ ፣በኦርቶዶክስ ሀይማኖት ላይም እንዲሁ ችግሩን አብሮ በመጋፈጥና አሁን ደሞ በአማራው ህዝብ ላይ ወያኔ የሚያደርሰውን አሰቃቂ በደል በመቃወም በከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል። ሌላው ደግሞ ማናቸውም ለሀገራችን ተቆርቋሪዎች ነን የሚሉ ኢትዮጵያዊያኖች ወገኖቻችንን በሙሉ የሚያሳትፍ (keep of fighting ethiopian youth forum KOFEYF) የሚል የፓልቶክ (paltalk room) ከፍቶ ዘውትር በየሳምንቱ እሁድ ከ15፡00 – 3፡00pm ሰአት ጀምሮ አንጋፋ የሆኑ የፖለቲካ ባለሞያዎችንና የሀገር ተቆርቋሪዎችን በመጋበዝ ትልቅ አስተዋጾ በማድረግ ላይ ይገኛል ። እርሶም ይህን እድል በመጠቀም ያለዎትን እውቀት ለማህበረሰቡ በማስተማርና በመማር ለሀገርዎ ትልቅ አስተዋጽኦ በማድረግ ዉድ ሀገራችንን ኢትዮጵያን ከገባችበት የድጥ ማጥ ውስጥ እናውጣት የሚል ተማጽኖዬን በማክበር እጠይቃለሁ።
ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር!!!
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያ ሀገራችንን በምህረቱ ይጎብኛት!!!
Dawit Abebe, April 2013. Oslo
ሁሉም ለሀገሩ ዘብ ይቁም!!
Latest from Blog
የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው እና አሁን ላይ በአማራ ፋኖ በጎጃም የሁለተኛ (ተፈራ ) ክፍለጦር ሰብሳቢ የነበረው ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በክብር ተሰዋ። የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህሎና አደጋ ለመቀልበስ ያለ
ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ የሐዘን መግለጫ ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል !
ዘመነ ካሴ በድሮን በቤተሰቡ ላይ ስለደረሰው ጥቃት/ የጎንደር ፋኖ አንድነት እና የቀጠለው ከባዱ ውጊያ / ፓርላማው በትግራይ ግምገው ያረጋገጠው
ዘመነ ካሴ በድሮን በቤተሰቡ ላይ ስለደረሰው ጥቃት/ የጎንደር ፋኖ አንድነት እና የቀጠለው ከባዱ ውጊያ / ፓርላማው በትግራይ ግምገው ያረጋገጠው
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ “ይድረስ ለእገሌ” ማለቱ ሰለቸኝና ተውኩት እንጂ ዛሬም መጻፍ የፈለግሁት የአማራን ዕልቂት ለመታደግና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር እየተዋደቁ ላሉት ወገኖቼ ነው – በፋኖም ይሁን በሌላ ስም፡፡ ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ የነገድና
ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!
[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ
ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)
January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ
ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ ታየማ ታየ ነው
አማራ ፋኖ አነጋጋሪው የኤርትራ ሙዚቃ Nahom Yohannes New Eritrean Music ክመረብ ማዶ አድማስ የመጣው ዝማሬ የሚለው ገብቶኛል መድህን ነው ላገሬ አንከፋፈልም በተገንጣይ ወሬ ሑለቱ አንድ ናቸው ጥንትም ሆነ ዛሬ —
አማራ ፋኖ አነጋጋሪው የኤርትራ ሙዚቃ Nahom Yohannes New Eritrean Music
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ” — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ ራሳችንን እንፈትሽ ። እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ
ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል። ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ
አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!
ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት
80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?
በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና