‹ልጅ ያቦካው —- › እንዲሉ! (ልጅ ተክሌ ‘የኢሳት 3ኛ አመት ክብረ-በዓል የሙስሊሞች ብቻ ነው እንዴ?’ በሚል ላቀረበው ጽሁፍ የተሰጠ ምላሽ)

ቶፊቅ ጀማል – ቼክ ሪፑበሊክ(ፕራግ)

ሰላም ጤና ይስጥልኝ! ይህ ጽሁፍ ልጅ ተክሌ የኢሳት 3ኛ አመት ክብረ-በዓል የሙስሊሞች ብቻ ነው እንዴ? በሚል ርእስ ላወጣው ጽሁፍ (ባለ 12 ነጥብ የአቋም መግለጫ) የተሰጠ ምላሽ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ጽሁፍ የግል አስተያየቴ መሆኑን ማንኛውም አንባቢ ከመረዳት በተጨማሪ በየትኛውም መልኩ የጎሳዬን፣ ሃይማኖቴን እንዲሁም የቤተሰቤን አመለካከት እንደማያሳይ ይታወቅልኝ፡፡
1. ውድ ልጅ ተክሌ ከልቤ አመሰግንሃለሁ፡፡ ጽሁፍህ አበሳጭ ወይም አስጨብጫቢ ስለሆነ ግን አይደለም፡፡ ድብቁ ማንነትህን እና ኋላ ቀር አስተሳሰብህን በዚህ ጽሁፍ ምክንያት ገሃድ ስላወጣኸው ነው፡፡ በእርግጥ ለእያንዳንዱ ነጥብ 12 የሚያስጨበጭቡ መልሶችን ልሰጥህ በቻልኩ ነበር ግና ልጅ ስለሆንክ አንድ አንድ ብቻ ይበቃሃል፡፡ በአንደኛው ነጥብህ የምትጽፋው ለማበሳጨት/ለማስጨብጨብ እንደሆነ ገለጽክ፡፡ ግን አስፈላጊ ነው? እንደ እኔ ግን መጻፍ ያለብህ ደጋፊ ወይም ነቃፊ ለማፍራት ሳይሆን የተሳሳቱትን ለማረም፣ ጥሩ የሰሩትን ለማሞገስ እንዲሁም የህብረተሰቡን ችግር መፍትሄ ለመሻት መሆን ነበረበት፡፡ በእርግጥ በዚህ ጽሁፍህ ሁለቱንም አላማዎችህ አሳክተሀል፡ ምክንያቱም አንተን በጭፍን የሚከተል ክርስቲያን ካለ አርእስቱን ብቻ በማንበብ ያጨበጭብልሃል፡፡ ያነበበው ሙስሊም ደግሞ ስንትና ስንት ወንድሞቼ፣ እህቶቼ፣ አስተማሪዎቼ እንዲሁም ጓደኞች ታስረው እንዴት ይቀልዳል በሚል ይበሳጭብሃል፡፡ ልጅነትህን ሲያውቅ ግን ይቅር ይልሃል እኔም ‹የሚያደርገውን አያውቅም እና ይቅር በለው!› እላለሁ፡፡ የህብረተሰቡን ችግር አንስተው የሚፅፉ፣ በዳዮችን ሣይወግኑ የሚነቅፉ፣ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የራሳቸውን አመለካከትና የመፍትሄ ሀሳቦችን የሚሰጡ ፀሐፍት ሁል ጊዜ ይጨበጨብላቸዋል፡፡ የአማርኛ ተናጋሪዎችን ጉዳይ ሌሎች ስለፃፉት ተውኩተ አልክ? በጣም ትገርማለህ እረ ታበሳጫለህ፡፡ ከስልሳ በላይ ሰዎች የሞቱበትና ብዙመቶዎች የተንገላቱበትን ጉዳይ እንዲ በቀላሉ ሌሎች ፅፈውታል ብለህ ስትተወው(የመፅሃፍ አቅሙ ካለህ ማለቴ ነው) በጣም ነው ምታሳዝነው፡፡
2. በነጥብ ሁለት ላይ አምስት የእስልምና ሃይማኖት መሪዎች መጋበዛቸውን ብልሃት ያነሰውና ያልተጠና ውሳኔ እንደሆነ ታስረዳለህ፡፡ እኔም ልጠይቅህ፡ ግን በዚህ ፀሁፍህ ምን ያህል የኢሳትን ምስል የማጠልሸት ስራ እንደሰራህ ይታወቅሃል? እንደምትለው የኢሳት አሰተዳደር ቢሳሳት ለኢሳት ካለህ ቀረቤታ ማረም አይቀልም ነበርን ወይስ ጥቅም ተነክቶብሃል ማለቴ ጋብዙኝ ስትላችው አይ አንተ ልጅ ነህ አሉህ? በእርግጥ እንደ ኢሳት ደጋፊ ሳየው የተከተሉት መርህ ይህንን ይመስላል፡፡ እነዚህን የሙስሊሙን የሃይማኖት መሪዎች በመጠቀም በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ የተፈጠረውን መነሳሳት ለኢሳት ማጠናከሪያነት ለማዋል፡፡ ደግሞስ የግል ሚድያ የሚቆመው ለተበዳዮች ከመሆኑም በላይ ትግሉ በተጧጧፈበት ማዘምበሉም የሚዲያ ባህሪይ አይመስልህም? ወይስ ኢሳት የግል ሚዲያ ሳይሆን የፖለቲካ ፓርቲ ድምፅ ነው እያልከኝ ነው?፡፡
3. በዚህኛው ነጥብህ ሙስሊሞች የፖለቲካ ፓርቲ ሆነው የመውጣት አላማ እንዳላችውና አንተ እንደማትደግፍው ገለፅክ፡፡ እረ ልጅ ተክሌ ቶሮንቶ ተቀምጠህ ከኢቲቪ ትኮርጃለህ? በመጀመሪያ አነዚህ ሰዎች የሙሰሊሙን አንቅስቃሴ ሲያቀጣጥሉ አይደለም ኢሳት ሽፋን የሰጣቸው አንዲያውም ኢሳት መጠቀሚያ ነው ያደረጋቸው በዚህም አኔ በግሌ በኢሳት ቅር ብሎኛል የህዝቡን ትግል ለግል ወይም ለድርጅት ጥቅም አንደማዋል ቆጥሬዋለሁ፡፡ ድንገት አንኳን አነዚህ ሰዎች አድሉን አግኝተው ትግሉን ቢያቀጣጥሉ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ህገ-መንግስቱን ለማስከበር ሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚሄደውን ሰላማዊ አካሄድ ከመደገፍ አንጻር ልታየው ለምን አልቻለህም? ደሞ በ2013ትም ሙስሊም፣ ክርስቲያን እንባባል? አረ brain washed መሆን የለብንም፡፡
4. እዚህ ጋ አንድ ያልተረዳኸው ወይም ልትረዳው ያልፍለከው/ያልሞከርከው ጉዳይ ያለ ይመስለኛል፡፡ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ችግሮቹ የፖለቲካ አይደሉም፤ የሃይማኖት ናቸው፡፡ እንደዚህ ተደራጅቶ የሚንቀሳቀሰውም እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ሲሆን የየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ድጋፍና እርዳታ አይፈልግም፤ አሚሮቹም አላዘዙትም፡፡ነገር ግን በሃገሪቱ ያለውን የፖለቲካ ችግር እንደግለሰብ ከሚመርጠውና ከሚመጥነው የፖለቲካ ድርጅት ጋር በመሆን የሌሎች ወገኖቹን ፈለግ ሊከተል ይችላል፡፡ ግን ሞኝ መሆን የለብህም፤ በየትኛውም ሁኔታ ይህንን ትግል ለጋራ ጥቅማችን (መንግስትን ለማውረድ) እናውለዋለን ብለህ አታስብ፡፡ በግሌ ያንተን የፖለቲካ አካሄድ አልደግፍ ይሆናል ከዛ በተጨማሪ እነ አቶ ነጂብም ቢሆን ዛሬ ሃይማኖትህን አስከብር እንደሚሉት ሁሉ ነገ ‹ይህንን የፖለቲካ ፓርቲ በመምረጥ ህዳሴህን አብስር› ቢሉ የሚሰማቸው አይኖርም፡፡ ምክንያቱም በአንድ ሃይማኖት ውስጥ ያሉ ሁሉ ተመሳሳይ የፖለቲካ አስተሳሰብ (በተለይ ከ 80 በላይ ዘር ባለበትና የዘር ፖለቲካ ስር በሰደደበት በአሁኑ ስዐት) ስለሌለው፡፡
5. ለዚህ መልስ መስጠት ያለብኝ አይመስለኝም፡፡ ነገር ግን ስትፅፍ የሰዋሰው ስህተት ይታይበታል፡፡ ይኸውም ይህ የግል አስተያየትህ እንደመሆኑ መጠን ነጠላ(singular) አገላለፅ ተጠቀም፡፡ ምን አልባት እኔ የምደግፈው በመጅሊስ ውስጥ ስልጣን ፈልጌ ይሆናል፣ ሌላው ደግሞ የሚደግፈው ጥያቄው ለሙስሊሞች ከተመለሰ ለተቀረውም በእኩል እንደሚረጋገጥ ስለገባት ይሆናል እንዲሁም አንዱ ደግሞ በትክክል ሃይማኖቱ አስጨንቆት ይሆናል፡፡ በመሆኑም ልጅ ማነህ? በሞቴ አትዘባርቅ የራስህን እምነት ወይም ግላዊ አስተሳሰብ በሚያሳይ መልኩ አስቀምጥ፡፡
6. በዚህ ነጥብ በእርግጥ ምን ለማለት እንዳወብህ አልገባኝም፡፡ ‹መንግስትና ሀይማኖት አይለያዩ ማለታችን ነው …› ስትል በእርግጥ ማለት የፈለከው ይህንን ከሆነ በጣም አዝንብሃለሁ፡፡ ገዢው መንግስት የቀድሞ ስርአት ናፋቂ እያለ የሚጠራችው እንዳንተ አይነቱን መሆን አለበት፡፡ የአማርኛ ችግር አለብህ ብዬ እንዳልል የቄስ ትምህርት እንደቀሰምክ ከሌላኛው ስምህ ተረድቻለሁ(ደግሞ የራስህን ፅሁፎች በራስህ ስም ፃፋቸው፡፡ አታወዛግበና!) ፡፡ ሙስሊሙ እንደ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ይወጣል ስትል እስቲ አንድ ምልክት ስጠኝ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ያለህን ጥላቻ እና የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ወደ ሌላ ጎራ የመውሰድ ፍላጎት በግልፅ አሰቀምጠሃል፡፡
7. ይህንን የልጅ ራዕይ ብዬ ነው ማለፍ ያለብኝ
8. እነዚህን ሰዎች እንደዜጋ ነው እዚህ ዝግጅት ላይ የተገኙት ብሎ መውሰዱ ለምን እንደከበደህ በእርግጥ አልገባኝም (ሙስሊም ቢሆኑም ዜጋ መሆናቸው ልትክድ ካልሆነ በስተቀር) ወይስ ከእነዚህ ሰዎች አንዱ ቢቀነስ አንተ አንደ ዜጋ (ወይም እንደ ኦርቶዶክስ) የመጋበዝ እድሉ ነበረህ እማፀንሃለሁ የግል ጥቅማችንን በዚህ መልኩ ለማስጠበቅ መጣር አደገኛ መሆኑን የሚመክር ጓደኛ አፍራ፡፡
9. በእርግጠኝነት ታማኝ ይህንን ፅሁፍ ሲያነብ ያንተን ወዳጅ እንዳልሆነ በግልፅ ይነግርሃል ብዬ ጠብቃለሁ፡፡ ግን እውነትን ለመናገር የዋህ መሆን ያለብህ አይመስለኝም፡፡ እውነት አንተ የዋህ ሆንክም ሌላ እውነትነቱን የሚሽርበትም ሆነ የሚሸረሸርበት ሁኔታ አይኖርም፡፡ በእርግጥም ይደረግ የነበረውን ነገር ተናገረ እንጂ ክርስቲያኑ ጥፋተኛ ነበር እናም በግሌም ሆነ ክርስቲያኑን ወክዬ ይቅርታ እጠይቃለሁ አላለም፡፡ ደግሞ ታማኝ አጥፍቶአል ብለህ የምታስብ ከሆነ ለምን አልፃፍክም ‹የምንጋብዘው ….›አልክ አንተም ጋባዥ ነበርክ ከነበርክ ለምን ጋበዝክ ወይስ ኢሳትን ወክለህ መናገርህ ነው አይገርምህም ኢሳት ውስጥ አንድ እንደ አንተ የሚያስብ ‹ልጅ› ካለ ‹ኢሳት የኢትዮጵያውያን አይንና ጆሮ› የሚለው በጣም የተሳሳተ እንደሆነ ሁሉም ይገባዋል፡፡
10. አይ የልጅ ነገር ቅድም ኢሳት የሁሉም ነው እንዳላልክ አሁን ደግሞ የሙስሊም፣ የኦርቶዶክስ እና የጴንጤዎች ነው ብለን እናስባለን አልከን፡፡ ደግሞስ የትኛውን ጥናት ተመርኩዘህ ነው ‹ጴንጤዎች ስለሃገር ያላቸው ተቆርቋሪነት ጎደሎ ቢሆንም › የምትለው? በመጀመርያ እኛ ሃገር ውስጥ ያሉት ሃይማኖቶች እነዚህ ብቻ አይደሉም በተጨማሪም ኢሳት የኢትዮጵያውያን ነው ብዬ ስለማስብ ጠበህ ማጥበብ የለብህም የሚል ተግሳፅ ያሻሃል፡፡ ደግሞ በተለያየ አጋጣሚ የተዘጋጁ ቢሆኑ የማይገርም ከሆነ በአንድ ላይ ታስቦበት ከተዘጋጀ ለምን አልዋጥ አለህ?
11. ይህ ነጥብ በእርግጥ ከነጥብ 6 የተለየ አይደለም፡፡ የቅርፅ ለውጥ አድርገህ ተመሳሳይ ሃሳብ ነው ያቀረብከው፡፡ ይህም ምን አልባት ነጥቦችህ ደርዘን እንዲሞሉ ካለህ ፍላጎት ይመስለኛል፡፡ ኢሳት ለእኔ እንደሚገባኝ (አንተ በእርግጥ የበለጠ ልታውቃቸው ትችላለህ) በህዝብ ድጋፍ የሚተዳደር ነፃ ሚዲያ ይመስለኛል፡፡ እንደዚህ አይነት ሚዲያዎች ደግሞ የራሳቸውን ህልውና ለማስጠበቅ እና ለማስቀጠል በእያንዳነዱ እንቅስቃሴ ውስጥ ያሉ ቁልፍ(figure head) የሆኑ ሰዎችን ግድ ይላቸዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች ግን የተሰጣቸውን እድል ተጠቅመው እንዳንተ ብዥታ ያለባቸውን ሰዎች ስለ ሙስሊሙ ትግል ምንነት ግልፅ ካደረጉ እሰየው ነው፡፡ ካላደረጉም እነሱን ብሎ ለሚመጣው ማህበረሰብ አብሮ የተገኘው የኢሳት ሰው ስለ ኢሳት አላማ፣ ራዕይ እንዲሆም በምን መልኩ መደገፍና መሳተፍ እንዳለባችው የሚያስረዳ አይመስልህም?
12. በእርግጥ እነዚህ ሰዎች(እነ አቶ ሌንጮ) እቅዳቸውን/አዋጃቸውን እንዲያሰተዋውቁ እድል መስጠቱ ጥሩ ነው ባይ ነኝ፡፡ ግን ልጠይቅህ! ተጠይቀው ዝግጁ እንዳልሆኑ ቢናገሩስ፣ ወይም እቅዱ የወጣው እነሱ ውሳኔያቸውን ከማሳወቃቸው በፊተ ቢሆንስ፣ እነ አቶ ነጅብ ጠይቀው፣ለምነው፣ ከፍለው(በከፊልም ይሁን በሙሉ) ወይም ተነሳሽነት አሳይተው ቢሆንስ?

ለማጠቃለል ያህል፡
ልጅ ተክሌ(ተክለማርያም ሣህለማርያም/ ተክለሚካኤል አበበ)፤ በእርግጥ የኢሳትን መልክ ለማጠልሸት አልመህ ከሆነ ከሞላ ጎደል ተሳክቶልሃል፡፡ ቢያንስ እኔ እንድጠራጠር አድርገሃልና፡፡ ካልሆነ ግን ፅሁፍህ ብስለት የጎደለው፣ ልጅነትህን አጉልቶ የሚያሳይ ባጠቃላይ የጋዜጠኝነት ስነምግባርን ያልተከተለ ከመሆኑም በላይ የአማርኛም ክፍተት ይታይብሃል፡፡ በተጨማሪም የሙስሊሞችን የሃይማኖት ጥያቄ ለፖለቲካ አላማ ማስፈፀምያነት ለማዋል ቁርጥ አላማ እንዳለህ ከማሳየቱም በላይ ለምትሰራለት ድርጅት(ኢሳት) ምስል(image) ምንም አይነት ደንታ የሌለህ መሆኑን ተረድቻለሁ፡፡ ሌላው ልትረዳው እምፈልገው ጉዳይ ቢኖር እንደው ግላዊንት ካልሆነ በስተቀር ምንን ምክንያት አድርገው ነው የሌላው የሃይማኖት አባቶች ሊሳተፉ የሚችሉት በብዙ ሺህ የታሰሩት ሙሰሊሞች፣ ከአመት በላይ ደምፃቸውን ያለማቋረጥ በሰላማዊ መልኩ እያሰሙ ያሉት ሙሰሊሞች፣ ከትምህርት ገበታቸው በጅምላም በችርቻሮም እየታፈኑ ያሉት ሙሰሊሞች፣ በምሽት እየተዋከቡ የሚገኙት ሙሰሊሞች ወንድሜ ቆም ብለህ ማሰብ ያሻሃል፡፡

ቶፊቅ ጀማል

ቼክ ሪፑበሊክ(ፕራግ)

8 Comments

 1. Tekle got an issue and that issue has to be confronted without fear. There are a lot of people with his mentality. ESAT should organize dialogue so that all of us have clear stand.

 2. Tekle want going to weyanny like Selomon Tekalgn.Many times he wrote this kind article on Ethiopia zare to confus the people.ESAT must give reply for this bad article if they want the people support.

 3. የተክሌን ሀሳብና ስጋት ኢጋራለሁ። ኢሳት ለሙሰሊሞች ጥያቄ የሚሰጠው ጭፍን ሁኔታ የክርስቲያን ኢትዮጲያውያንን ስጋትና ነገ ሊከተል የሚችለውን ስጋት ያላገናዘበ ነው። ችግሩ በጣም የተወሳሰበና ወደፊት ከዘርና ከቋንቋ የበለጠ የሀገሪቱን አንድነትና ሰላም ሊፈታተን የሚችል ነው። ችግሩ የአህባሽ አስተምህሮ ለምን በምንግስት ይጫንብናል የሚል ብቻ ሳይሆን እጅግ አክራሪ የሆነውን ወኻቢያ ካልተገበርን የሚል ነው። በመሰረቱ ህገመንግሰቱ የሀይማኖት ነፀነትን ቢፈቅድም ማንኛውም የሀይማኖት አስተምህሮ በህግ ተቀባይነት የሚኖረው የልሎችን መብት እስካልተጋፋ ድረስ ብቻ ነው። ህገመንግስቱን የመጣስ ህገመንግስታዊ መብት ሊኖር አይችልም።

 4. Facts on Tekle articles,
  1. Tekle repeatdly writes articles hostile articles against amhara society like EPRDF.
  Ex. He wrote article supporting Tesfaye Gebreab, Yeburka zimita ,hostile book on amhara society in support of massmasacre on amharas at arbagugu.
  2.He specially supports ethnic organization like OPDO,OLF,ODF
  3.Hidden hate on amhara people,uses ESAT as a hide.ex. His answers on Ye hud weg.
  4.He attacks ESAT from the inner side works against its credibility and acceptancy like writing articles on muslims.
  5.Esat must take adminstration measures on this idiot.

 5. Mulu bemulu Yeteklen hasab egaralehu bene emnet Tekle sereat balew menged kume negerun kuch aderegotal. bachiru YELEBEN new yetenagerew. sereate balew meneged liberetata yigebawal.

 6. በኢትዮጵያ ውስጥ የኢስላም አክራሪዎች በክርስቲያኑ ማህበረሰብ ላይ ያደረሱትን የግድያና ድብደባ፣አስገድዶ የማስለም፥ የተቃጠሉ ቤተ ክርስቲያኖችን በማስረጃ የተደገፈ የኢ-ሜልና የስልክ መልእክቶች ለኢሳት ብደርሱትም ፥ ኢሳት በአንድ በኩል የኢዮጵያ ህዝብ ድምጽ ነኝ እያለ የብዙሀኑን ድምጽ ማፈኑ ያሳዝናል::VOA ከአህባሽ እና ከውሀቢስ ተወካዮችን በመጋበዝ እኩል እድል በመስጠት ህዝቡ ጥሩ ግንዛቤ እንዲያገኙ ያደረገ ቢሆንም ኢሳት ግን የአንድ አክራሪ ሴክት ፕሮፓጋንዳ ማሰራጫ ሜዲያ መሆኑ ብዙዎችን አስገርሟል:: በኢትዮጵያ የሸሪያ ህግ ተግባራዊ እንዲሆን አብዛኛው ሙስሊሙ ዲያስፖራ በPaltalk Cyber ያልተፈጠረውን ተፈጠረ እያሉ ክርስቲያኑ እና ሙስሊሙ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ተቻችለው እንዳይኖሩ ሌት ተቀን ሲያሴሩ ይታያሉ:: ከነዚህ አክራሪ ሀይላት መካከል ኢሳት በእንግድነት የሰላም ተምሳሌት አድርጎ ይዞአቸው ሲዞር በበኩሌ የተክሌን ስጋት በሚገባ እጋራለው፥ ኢሳት በእርግጥም ትልቅ ኪሳራ ላይ ወድቋል:: እናም ኢሳት ነገሩን ለማስተባበልና ያለውን እውነታ ከመሸፋፈን ከአሁኑ እርምጃ እንዲወስድ በማሳሰብ ያለኝን ሀሳብ እቋጫለሁ::

 7. Who actulally a great terror to the people of ethiopia?
  Ethnic Racist deology like of Tekle’s or Muslim Ethiopians?
  What is the cause of Evacuation and genocide on amharas,dislocation of gambela people ,afar people,somali? Are they Muslims or Ethnic polititians and their ideologies like Teklie?If Muslimism is a threat why not Ethnisism or ethnic racism a threat? Who is a terror, Lencho Leta ( Bedeno genocide responsible OLF polititian) or the ethiopian innocent muslims? His article was intended for the following facts,
  1.Ceation of terror on christian society to stop funding ESAT
  2.Creat a division between muslim and christians

  You idiots try stop your fullish idea.

 8. To Lij Tekle

  It is good to write what you feel but also better to read a lot befor you pick your pen. you may find an answer to your illusion.many of your writings and also your discussion on Esat Shows that you need to read alot and learn manner. Some time also good to give to a freind your writtings for critics befor you come to the public.

Comments are closed.

Teklemichael Abebe
Previous Story

ከማግለል ማሳተፍ ይቅደም! (ልጅ ተክሌ በኢሳት ላይ ላቀረበው አስተያየት የተሰጠ ምላሽ)

ESA
Next Story

የሚኒሶታ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበር ለ18ኛ ያዘጋጀው የባህል ምሽት የፊታችን ቅዳሜ ይደረጋል

Latest from Blog

አገራችን አሁን ያለችበት እጅግ አጣብቂኝ ሁኔታ (እውነቱ ቢሆን)

በዚህች አጭር ጽሁፌ ሁለት ነገሮች ላይ ብቻ አተኩራለሁ፡፤ በወልቃይትና ራያ መሬቶች ጉዳይና ስለአብይ አህመድ የማይሳካ ቅዠትና ህልም ዙሪያ፡፡ ስለወልቃይትና ራያ፦ እነዚህ ቦታወች ዱሮ የማን ነበሩ? በማን ስርስ ይተዳደሩ ነበር?  አሁንስ የማን ናቸው?? ለምንስ ይህንን ያህል ደም ያፋስሣሉ… ወዘተ ወደሚለው ጥያቄ ከማምራታችን በፊት መሬቶቹ በውስጣቸው ምን ቢይዙ ነው? አቀማመጣቸውና ጠቀሜታቸውስ ምንና

ሳሙኤልም እንደ እስጢፋኖስ!

 በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ሳሙኤል አወቀ እንደ ቅድመ አያቶቹ ዝቅዝቅ መታየትን ያልተቀበለና በጥናት የታገለ ከመጀመሪያዎቹ ፋኖ ሰማእታት አንዱ ነው፡፡  ሰማእታትን መዘንጋት አድራን መብላት ነው፡፡ አደራን መብላትም እርምን መብላት ነው፡፡ እርምን መብላትም መረገም ነው፡፡እርማችንን

በትሮይ ፈረስነት የመከራና የውርደት አገዛዝን ማራዘም ይብቃን!!!   

June 16, 2024 ጠገናው ጎሹ በሥልጣነ መንበር ላይ የሚፈራረቁ ባለጌ፣ ሴረኛ፣ ሸፍጠኛና ጨካኝ ገዥ ቡድኖች መከረኛውን ህዝብ ከአስከፊ ድንቁርና እና ከሁለንተናዊ የመከራና የውርደት ዶፍ ጋር እንዲለማመድ  ከሚያደርጉባቸው እጅግ በጭካኔ  የተሞሉ ዘዴዎቻቸው መካከል ኮሚቲ፣

ኑሮ የከበዳቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓትን በቤተ እምነቶች እያሳለፉ መሆኑ ተነገረ

ሲሳይ ሳህሉ / ቀን: June 16, 2024 የቤት ኪራይ መክፈል ያልቻሉ ተደብቀው ቢሮ ውስጥ ያድራሉ ተብሏል መንግሥት የሚከፍላቸው ወርኃዊ ደመወዝ አልበቃ ያላቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓታቸውን ወደ ቤት እምነቶች በመሄድ፣ እንዲሁም ቤት

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት
Go toTop