Hiber Radio: “ከሁሉ አገር በታች ሕግ የሌለበት በደመ ነፍስ የሚመራ አገር የእኛ አገር ብቻ ነው” – ታማኝ በየነ (ቃለምልልስ)

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
Hiber Radio: "ከሁሉ አገር በታች ሕግ የሌለበት በደመ ነፍስ የሚመራ አገር የእኛ አገር ብቻ ነው" - ታማኝ በየነ (ቃለምልልስ) 1
የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ሚያዚያ 6 ቀን 2005 ፕሮግራም

<<...ይሄን በደል ማስቆም የእያንዳንዳችን ግዴታ ነው።...ከሁሉ አገር በታች ሕግ የሌለበት በደመ ነፍስ የሚመራ አገር የእኛ አገር ብቻ ነው። ይሄንን አስቁመን ቢያንስ ልጆቻችን እንዳይሰደዱ ለማድረግ በአገራቸው ተስፋ የሚያደርጉበት አገር እንዲሆን ሁሉ ሰው ጥረት ማድረግ አለበት...>>

አክቲቪስትና አርቲስት ታማኝ በየነ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው አጭር ቃለ መጠይቅ የተወሰደ

<<...በሲና በረሃ የኢትዮጵያውያኑንና የሌሎዩንም አካል በቁማቸው ቀደው ኩላሊታቸውንና ልባቸውን ወስደው እንዲሞቱ ይጥሏቸዋል። ከዚያ አንስተው በርካታ ሬሳ ካለበት ጉድጉዋድ ይትሏቸዋል። የሰውነት አካል ግብይቱ ልክ የመኪና መለዋወጫ እንደመግዛት ያህል መሆኑን በስራው የተሰማራ ገልጻል...>>

በሲና በረሃ በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው ስቃይና በበረሃ ወድቀው የሚቀሩበትን አስከፊ ሁኔታ የ ከቃኘንበት ልዩ ዘገባ የተወሰደ

<<...ከሱዳን በሽፍቶች ተጠልፋ ሲና በረሃ ያለችው ባለቤቴ የተወሰነ ገንዘብ አፍነው ከሸጡላቸው ለገዙዋትና ሲያሰቃዩዋት ለነበሩት ተሰጥቶ ድብደባው ለጊዜው ቆሞላታል። እስክትለቃቅ ግን እየጠበቅን ነው ... >>

አቶ መልካሙ ባዬ ከሱዳን ሸገረ አብ ስደተኞች ጣቢያ ባለቤታቸው ታፍነው ተወስደው ተሽጠው በወቅቱ ስላሉበት ሁኔታ ሲያስረዱ

<<አልደራደርም ያለው አሰሪ ለድርድር መጥቷል።ይሄ በጥንካሬ ስለቆምን ነው። ይዞት ያመጣው አዲስ ነገር ስለሌለ ጥያቄውን ውድቅ አድርገነዋል። የስራ ማቆም አድማ ትግላችን ውጤት እስክናገኝ ይቀጥላል...>>

አቶ ሽመልስ ደረሱ ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑት የቬጋስ የየስራ ማቆም አድማ ተሳታፊ የታክሲ አሽከርካሪዎች መሪ ከሰጡን ቃለ ምልልስ የተወሰደ

<<ያሰሩን ፍርሃት ለመፍጠር ነው። ከእስር ቤት ስወጣ ፖሊሱን ነገ ተቃውሞው ቦታ ትመጣለህ ወይ አልኩት አዎ ሲለኝ እንግዲያው እዚያው እንገናኝ ነበር ያልኩት እንዳሰቡት ጥቂቶችን አስረው ፍርሃት ለመፍጠር አልቻሉም...>> ከቬጋስ የታክሲ ሾፌሮች የስራ ማቆም አድማ አስተባባሪዎቹ አንዱ የከተማው ፖሊስ ለተቃውሞ ወጥተው ቀይ ከበራ በሁዋላ ተሻግራችሁዋል በሚል አስሮ ከለቀቃቸው አንዱ ስለሁኔታው ለህብር ከገለጸው(ዝርዝሩን ያዳምጡ) ሌሎችም ቃለ መጠይቆች አሉን

ዜናዎቻችን

– ኤርትራዊው ምሁር ኢትዮጵያ አሰብን በሊዝ ትጠቀም ሲሉ ሀሳብ አቀረቡ

– የወ/ሮ አዜም መስፍን ከንቲባ ሊሆኑ ይችላሉ የሚለው ግምት አነጋጋሪ ሆኗል

– ጃዋር መሐመድ እሳቸው ከንቲባ ቢሆኑ ውድቀት መሆኑን ገልጿል

– በየመን የአገሪቱ ጦር የታገቱ 180 ኢትዮጵያውያንን ነጻ አወጣ

– የሙስሊሙ ሕ/ሰብ ፍትሕ ሲል በመላው አገሪቱ ድምጹን አሰማ

– በኢትዮጵያ ገዢው ፓርቲ ራሱ ተመራጭና አስመራጭ ሆኖ ምርጫ አካሄደ

Medhani
Previous Story

ደብረ ዘይትና አባ ማትያስ (ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ)

AP681748281334 1
Next Story

ኢትዮጵያዊው ላሊሳ ዲሳሳ ባሸነፈበት የቦስተን ማራቶን ቦምብ ፈነዳ

Go toTop