November 9, 2024
93 mins read

ቆርቆርጦ ቀጥሎች! ሂሳባችሁ ፉርሽ ነው! የአዲስ አበባዋ “150 ዓመት” አሰልቺ ትርክቷ

ወንድሙ መኰንን UK 09 Novembere 2024

መግቢያ

ይኸንን ጉዳይ አንድ ጓደኛዬ አማክሮኝ እኔም ከንክኖኝ ከዓመት በፊት ነበር ለመጻፍ የጀመርኩት። ኦሮሞ ጓደኞቼ ይቀየሙኛል ብዬ በይሉኝታ ታሥሬ እስከዛሬ ተውኩት። ይሉኝታ አይደል የሚገለን? ዳሩ ግን፣ ውሸት በውሸት ላይ ተቆልላ አብጣ ዕውነት ልትሆን ምንም አለቀራት። በዚያም ብታቆም ባልከፋም። ሌላ አደጋ ይዛ ብቅ አለች። በብልጽግና ሥር የተሰገሰጉት የኦሮሙማ ፍልስፍና አቀንቃኞች፣ ጭርሶ አማራን ለማጥፋት በግልጽ አውጀው ተነሱ። በየቀኑ እየባሰባቸው ሲሂድ፣ በቃኝ። የፈሩት ይደርሳል፣ የናቁት ይወርሳል ይባል የለ? ከአዲስ አበባ፣ ኦሮሞ ያልሆነውን ጠራርገው ሊያስወጡን ያላንዳች ሀፍረት አውጀው እየተገበሩት ነው። ጅምላ ጭፍጨፋ በወለጋ ከጀመሩ ሰነባበቱ (BBC, በቄለም ወለጋ ሌላ ጭፍጨፋ መፈጸሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገለጹ, 2022)። “ወላሂ፣ ሁለተኛ አማራ አልሆንም” እያለች የታረደች ሕጻን አኢሻ ሠይድ ምንጊዜም ከልባችን አትጠፋም። 1600 አማሮች በቄለም ወለጋ በአንድ ጀምበር ተረፍርፈዋል። ይኸን ግድያ የፈጸሙት፣ “ሸኔ ነበር” ይበሉን እንጂ የብልጽግና የአካባቢው ባለሥልጣናት በጭፍጨፋው ላይ መተባበራቸውን የሚገልጹ መረጃዎች ሞልተውናል። የዘር ማጽዳት (ethnic cleaning) ዘመቻ ነበር ያካኼዱባቸው። በየጊዜው፣ ምክኒያት እየፈጠሩ፣ አማራውን በያለበት ጨፈጨፉት። 18 የአማራ ሴት ተማሪዎችን ጠልፈው ደብዛቸውን አጠፉ። ዝም አልናቸው። በትርክት ላይ ተመሥርተው፣ መጀመሪያ ሸገር የምትባል ነገር ቀርፈው አወጡና፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ የእሳት ግንብ ገጠገጡ። የኦሮሞ ያልሆኑ የመኖሪያ ቤቶችን ሲያፈርሱ መስኪድም አልቀራቸው። ዛሬ፣ አዲስ አበባ፣ ልክ እንደ ኮንስታንቲኖፕል፣ በሸገር የተከበበች ከተማ ናት። መውጣት ይቻላል። ኦሮሞ ያልሆነ ተመልሶ መግባት አይችልም። የእሳት አጥር ናት። ብሶባቸው፣ ዓባይን ተሻግረው፣ የአማራ ክልል የተባለውን በእግረኛ መድፈና፣ በሰማይ፣ በድሮንና በጄት ገበሬ፣ ሴት፣ ሕጻን ሳይሉ እየጨፈጨፉት ነው። ዝምታችን እስከመቼ ይቀጥል?

Addis Ababa 799

የሸገር አስተዳደር ሹመኝች ግን፣ አዲስ አበባ ላይ ጉብ ብልው ነው የሚያስተዳድሯት። ነባሩን አሻራ አጥፍተው፣ አዲስ “ፊንፊኔን” ለማዋለድ፣ የኦሮሞ ያልሆነውን ቤት እያፈራረሱት ነው። ምነው፣ የኦሮሞውን ቤት ዘለላችሁትሳ ሲባሉ፣ “የኢንዲጂኒየስ” ቤት አናፈርስም አሉን። አታምኑኝም? ይኸን ጉዳችሁን ስሙት!

https://www.facebook.com/story.php?story_fbid=10227324961092310&id=1309028939&rdid=nls47Vg4voWrB5d3

ድንቁርና ያጀግናል!

ሁለት አደገኛ ሰዎች በዚህች ምድር ይኖራሉ። አንዱ የዕውቀት ድሀ ነው። ሌላው አውቆ አበድ ነው። አውቆ አበዱ የዕውቀት ድኃውን ለእኵይ ዓላማው እንደ አቀጣጣይ ነዳጅ ይጠቀምበታል። ደንቁርና ያጀግናል። በአውቆ አበዱ ግፊት የሚነዳው የዕውቀት ድሀ፣ ልቡ የደነደነ ዕለት ግን ከቁጥጥራችው ሥር ይወጣና አደገኛ ይሆናል። ጠብመንጃ ጨበጦ፣ እንደዚህ ያለ ባለጡንቻ አንጎል ለሥልጣን ከበቃ አያድርስ ነው። አገሪቷ አለቀላት በሉ! የልብ ልብ ሲሰማው፣ ዕውቀት አልባው አውቆ አበዱንም ሲበላው በታሪክ አይተናል። “ሥራ ለሠሪው እሾህ ላጣሪው” ይባል የለ? በኛ ታሪክ ላለፉት 50 ዓመታት እነዚህ ናቸው አገሪቷን ሲያስተዳድሩ የኖሩት! አውቆ አበዱ፣ በወገንተኝነት እነዚህን ባለዕውቀት አልባ ሰዎችን ወደ ሰይጣናዊ መንገድ እየመራ ደም ያስፈስሳል። የኋላ ኋላ የሱም ደም ይፈሳል። የመኢሶንና የደርግን ጊዚያዊ ቅንጅት ልብ በሉ። እነሱን ራሳቸው ቅርጥፍ አድርጎ በላቸው። ወታደራዊ ደርግ፣ እነሱን ከጨረሰ በኋላ፣ ለ17 ዓመታት በፌሮ ረግጦ ገዛን። ወደ አሁኑ እንመልስ።

የትግራይ ልሂቃን አውቆ አበዶች፣ ገዳይ አውሬ አሰለጠኑብን። ወያኔዎች ከበረሀ የማረኳቸንና ኦነጎችን ይዘው ገቡ። ከተለያየ ብሔር ብሔርሰቦች የመደቧቸውን “ጀሌዎቻቸውን” አሰልጥነው እየመሩ መጡብን። አገሪቱን በቋንቋ/ዘር እንደገና ዘረዘሯት። ለያናድንዱ ዘረኛ፣ ካርታ ስለው ሰጡት። አማራም ክልል ተፈጠረለት። የአባቶች ርስት ተከፋፍሎ፣ ግማሹ ወደ ትግራይ ተጠቃለለ። መተከልን ቆርጠው ቤኒ ሽንጉል ግሙዝ ብለው ሌላ ክልል ፈጠሩ። ከፈጠሯቸው ክልሎች “ኦሮሚያ” የምትባለው የደም መሬት ሆነች። የክልሏ ፕረዝደንት፣ ሺመልስ አብዲሳ ይባላል። “አማሮችን ኮንቪንስም ኮንፍዩዝም” አድርገን ቁማሩን በላን” እያለ ይፎክርብናል። አታለልናቸው ማለቱ ነው። ታሪክን እንዳላየ አልፎ “ከኔ ወዲያ አዋቂ የለም” ባይ ነው። አዲስ ትርክትና የሌለ ታሪክ ፈጥሮ ፣ እንደመጣለት ይናገራል። እሱ ከሚለው ውጭ የሚናገሩ ኦሮሞ ኤሊቶች ከተገኙ፣ እየታደኑ ተቀፍድደው፣ ከሞት ካመለጡ፣ ተይዘው ዘብጥያ ይወርዳሉ። ታየ ደንደአን የገጠመው ይኸ ነው። ሽፍትነትና ህገ-ወጥነት በክልሏ ነግሧል። የሰው ልጅ በመያዥያነት ታግቶ፣ እስከ ሚሊዮን ብር ቤዛ የሚጠየቅባት ክልል ሁናለች። ማስለቀቂያ ገንዘብ ጠይቀው ተቀብለውም የታገተውን ሰው የሚግድሉበት ሁኔታዎች አይተናል። ይኽ የክልሉ ፕርዝደንት ፈላጭ ቆርጭ ሁኖ እያለ “ከደሙ ንጹህ ነኝ” ይለናል። በኦሮሚኛ  ጊዜው የኛ ነው ባይ ነው። የልብ ልብ የተሰማቸው የኦሮሞ ጽንፈኞች በየቦታው ያለተጠያቂነት ደም ያፈሳሉ። ኧረ ሰው አርደው ሲበሉም የተነሱትን ቪዲዮ አጋርተውናል። ይኸን ዓይነቱን ሰይጣናዊ ድርጊት ስንቃወም፣ “ኦሮሞ ጠል” እንባላለን። “ክፉን ከወደደ፣ የጠላ ነገደ” ወዳጄ!

ከዚህ በፊት፣ በመስከረም መጨረሻ 2012 ዓ.ም፣ በሆራ-አልባዋ አዲስ አበባ ውሀ በቦቴ ቀርቦ፣ እሬቻ ተከበረ። “ፊንፊኔ ሆራ” አሉን! ጉድ እኮ ነው። ሺመልስ አብዲሳ አፉን ሞልቶ፣ “የዛሬ 150 ዓመት በዚህች ቦታ አባቶቻችን ተሰበሩ። ዛሬ ግን በተራችን የሰበሩንን ሰብረናቸው ኢሬቻን አያከበርን ነው” ብሎ ደነፋብን። የዛሬ 150 ዓመት? የት? ደን ውስጥ? ሆራው የት ገባ? እንደ ቡርቃ ወንዝ “አፍሮ ስምጦ መሬት ውስጥ ተደብቆ ይሆን”? ወይስ አማሮች አደረቁት? ያለሆራ መቼስ ኢሬቻ ሲከበር አላየንም። ከዚያ በፊት መስቀል አደባባይ መስቀል በዓል ከጥንት ጀምሮ ይከበር ነበር። የባህል ሚኒስትራቸው፣ ቀጄላ ማርዳሳና አዳነች አቤቤ፣ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማው በበዓሉ ላይ ተይዞ እንዳይወጣ ከለከሉ። ይዞ የወጣውን ህዝብ ያለ ርህራሄ እየቀጠቀጡት፣ ቀሙት። ሰንደቅ ዓላማው ያለበትን የሴቶች ቀሚስ ጥለት ተረተሩባቸው። በተቃራኒው፣ የግብጽ ባንዲራ፣ የሚመስለውን ባንዲራቸውን በጉልበት በአዲስ አበባ ላይ ገጥግጠው ኤሬቻቸውን በኩራት አከበሩ። ማን ተናግሯቸው! እንደ ቄስ ቶሎሳ ጉዲና ያሉ፣ “ኧረ ተው! ኢሬቻ ባዕድ አምልኮ ነው” ቢሏቸው፣ ማን ሰምቷቸው? በየትምህርት ቤቱ፣ መዝሙራቸው እንዲዘመርላቸው፣ ባንዲራቸው እንዲውለበለብላቸው በጉልበት እየገፉ፣ መጡበት። የአዲስ አበባ ሕዝብ ተቃወማቸው። የኢትዮጵያው ዳግማዊው ጠቅላይ ሥቃይ፣ ጠቅላይ ሚኒስትራቸው ወጣና፣ “የአዲስ አበባ ሕዝብ ኦሮሞ ጠሊታ ነው” አለን። ቆይ እስቲ! ቤቱንን እያፈረሰ፣ እየገደለ፣ እያፈናቀለ፣ ሰውን ከነነፍሱ ቁልቁል ዘቅዝቆ የሚሰቅለውን እንዲወደድለት አልሟል? ሰሞኑን ደሞ “የሕልም ጉልበት፣ ለእምራታዊ ስኬት” እያሉ፣ እያደነቆሩን ነው። እሱን በሌላ መጣጥፍ እመጣበታለሁ።

ታሪክና ትርክት!

እንግሊዝኛ ተናጋሪዎች እንዲህ ይላሉ። “You will find that a lie has no legs. It has to be supported by other lies.” ሲተረጎም፣ ውሸት እግር የለውም። በሌላ ውሸት መደገፍ አለበት። የኢትዮጵያ ደንቆሮ፣ ዘረኛ ትርክተኞች፣ አንድ ውሸት ሲዋሹ፣ ክርስቲያኑ፣ “በስመአብ ወወልድ፣ ወመንፈስ ቅዱስ” ብሎ አማትቦ፣ ታዝቦ ያልፋቸዋል። ሙዝልማኑ፣ “አኡዝቢላህ ምሸጣ ሪጅ ሼይጣን!” ብሎ ንቆ ወደ ሌላ ያያል። የናቁት ይወርሳል፣ የፈሩት ይደርሳል ይባላል። የመጀመሪያውን ውሸት ሲታለፍላቸው፣ ያን መሠረት ያደርጉትና፣ በሌላ ውሸት ይደግፉታል። ውሸት በውሸት ላይ ሲገነባ፣ የውሸት ካብ ሰማይ ጠቀስ ፎቅ ሁኖ ቁጭ! ዕውነት መውጣት አቅቷት ታቃስታለች። ውሸታቸው ነግሳ፣ ውላ ታድርና፣ ተረት ትሆናለች። ተረት ቆይታ ሊፕ ስቲክ ተቅብታ፣ ታሪክ ሁና በቁቤ ተሰንዳ ትቀርብልናለች። ዋጧት እንባላለን! እምቢ!

ኧረ ዝም አንበል! “ዝምታ ለበጓም አልበጃት፤ አስራ ሁለት ሆና አንዱ ነብር ፈጃት” ይባል የለ? እየፈጁን ነው! መቼ ነው በድፍረት የ’ዕውነት ጋሻን አንግበን፣ የዕውቀት ጦር ሰብቀን የምንጋፈጣቸው? ሲፍጨረጨሩ፣ ድል ይገኛል። ያሁኑ ትውልድ ሞኝ ነው፣ ቁጭ ብሎ ሞቱን ይመኛል። አዲስ አበባ ተዋርደሻል! እምቢ በይ!

ታሪክና ትርክት ይለያያሉ። ታሪክ አንድን የተፈጠረ ክስተትን ተከታትሎ መዝግቦ ለሚቀጥለው ትውልድ ያስተላልፋል። መመዝገብ አለበት። ካልተመዘገብ ዝም ብሎ ወሽካታ ትርክት ይሆናል። ትርክት ከታሪክ በተቃራኒው፣ የሆነ ክስተትን በተመለከተ፣ በአፈታሪክ ብቻ በየጊዜው እንድሚያመቸው ሀቁንና ውሽቱን ሁሉ እየቀላቀለ፣ እንደሚፈልገው አደባልቆና አዘበራርቆ ያስተላልፋል። የዓለም ታሪክ ምሑራን፣ የሚሉት ሌላ! ትርክተኞቹ የሚያወሩን ሌላ! አንዳንዴም ተረት አፈታሪክ ሁኖ ይቀርባል። የሚገርመው ግን፣ አንተ “ዕውነቱ ይኸውና! ማስረጃውም ይኸውና” ብለህ ስታቀርብለት ሊያሸማቅቅህ፣ “ተረት ተረትህን ወዲያ ጣለው” ይለሀል፣ ሺ ቦታ ይተርተርና፣ ሊያሸማቅቅህ እኮ ነው። የሱ አፈ-ታርክ ታሪክ ሁኖ፣ የኔ የተጻፈ ታሪክ ተረት ሲሆን ይታይህ።!

አዲስ አበባን በተመለከተ ታሪክ የሚነግረን ሌላ! የኦሮሞ ልሂቃን የሚነግሩን የውሸት ትርክት ሌላ። ኧረ እንዲያውም አንዱ ጀብራሬ፣ ደረቱን ነፍቶ፣ በተለምዶ “ለገሀር” ተብሎ የሚጠራውን ስፍራ ድሮ በኦሮሚኛ “ላጋ ሀሬ” ይባል ነበር ብሎናል። “ለገሀር” የምንለው ሰፈር፣ “La Gare” ከሚለው ከፈረንሳይኛ መሆኑን የት አውቆ! “La Gare” ባቡር ጣቢያ ማለት ነው። ድንቁርና ያጀግናል አላልኳችሁም?! ስም መቀየር ሲችሉበት። ሞጋሳ በሞጋሳ ታሪክን ለማጥፋት የማይቆፍሩት ጉድጓድ የለም። ባሊን ባሌ ብለዋታል። አባ ባህርይንና (ትርጉም ጌታቸው ኃይሌ 1995)፣ Almeida (1954) አንብቡ። ምን ያልለወጡት አለ? ኢትዮጵያን በጠቅላላ ከወረሩ በኋላ እናሪያን ኢሉ አባቦራ አሉት። ግራርያን ሰላሌ አሉት። ገሙን ጂማ አሉት። ቢዛሞን ቄለም ወለጋ አሉት። ዳሞትን ሌቃ ወለጋ አሉት። ፈጠጋርን አርሲ አሉት። ደዋሮን ጭሬ (ሐረር) አሉት። ምድረ ግኝን ከሚሴ አሉት። ቤተ ሳባን ዋራ ኢመኑ አሉት። ቤተጊዮርጊስን ዋራ ኢሉ አሉት። ወለቃን ቦረና አሉት። ጭቃ በረትን ባቲ አሉት። ቢራሮን ቃሉ/ኮምቦልቻ አሉት። አንጎትን ራያ አሉት። ገነቴን የጁ አሉት…። ያኔ አመድ ሁና ስላገኟት አልፈዋት ሂደው ነው እንጂ፣ በረራ ላይ ቢሰፍሩ ኑሮ ሌላ ስም በሞጋሳ ባከናነቧት ነበር። ዛሬ ላይ አዲስ አበባ ተብላ አሸብርቃ አምራ ሲያግኟት፣ “ፊንፊኔ” ካላልናት እያሉ እየተጋጋጡ ነው።

ታሪክ ምን ይለናል?

ስለአዲስ አበባ፣ ትንሽ የታሪክ መዛግብትን እንቃኝ። መዛግብቱ እንደሚመሰክሩ ከሆነ፣ በዛሬዋ አዲስ አበባ ስፍራ፣ ከ1521 በፊት በረራ የምትባል፣ ታላቅ ከተማ ነበረች! ከደብረ ብርሀን በኋላ፣ ከጎንደር በፊት የኖረች የመጨረሻዋ የዳግማዊ አጼ ዳዊት (ልብነ ድንግል ወይም ወናግ ሰገድ) መናገሻ ከተማ ነበረች። በመጋቢት 1521 (March 1529) በኢማም  አህመድ ቢን ኢብራሂም አል ጋዚ (ግራኝ አህመድ) ተቃጥላ ወድማና ባድማ ሆነች እያሉ እነ (Pankhurst, 2008), (Arab Faqih, Lester Stenhouse, 2003) ይነግሩናል። በተላይ Faqih በFUTÙH AL-HABAŠA በሚለው መጽሕፉ ከገጽ 165 እስክ 168 ድረስ እንዴት በረራን እንደበዘብዙ፣ ኗሪውን እንዴት አንድገደሉ፣ ከተማዋን እንዴት እንዳቃጠሉ፣ በዓይን ምስክርነት ይነግረናል። ከዚያ በፊት፣ እንዳሁኑ የጠቅላላ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔርሰቦች መነሀሪያ ስትሆን ኦሮሞ የተባለ ብሔር ድራሹም አልደረሰባትም። የኦሮሞ ወራሪዎች የመጡት በኋላ ነው። እዚያ ጨርሶ አልሰፈሩም። የኢማሙን እግር እየተከተሉ ሲቃርሙ የነበሩት ወራሪዎቻቸው፣ በረራ በደረሱበት ጊዜ፣ ተቃጥላ ዶጋመድ ሁኖ አገኟት። የሚቃርሙት ነገር ስለሌለ፣ ትተዋት የግራኝ አህመደን ጦር ተከትለው፣ በየመንገዳቸው የሚያጋጥማቸውን ቅሪት የኢትዮጵያ ተዋጊዎችን እያጸዱ፣ ወደ ሰሜን ነጎዱ። በረራ ለ350 ዓመታት ጠፍ ሆና ወደ ደን ተለወጠች። ንግሥናው ከበረራ ጎንደር፣ ከጎንደር መቀሌ ሂዶ ወደ ሸዋ ከተመለሰ በኋላ ዓጼ ምኒሊክ ክቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ፣ ከድንኳን ድንኳን ይኳትኑ ነበር። በአንድ ወቅት እንጦጦ ደረሱና ድንኳናቸውን ተክሉ።  ቤተሰባቸውን እንጦጦ ትተው ለዘመቻ ወደ ሐረር ሄዱ። እስኪመልሱ ድረስ፣ እቴጌ ጣይቱ፣ ወደ ፍልውህዋ እየወረዱ ጠበል ሲጠመቁ ስፍራዋን ወደዷት። ባለቤታቸው ከሐረር ሲመለሱ፣ “ዋና ከተማችን እዚህቺው ጠበሏ ዙሪያ ብንመሠርትስ” ብለው ሀሳብ አቀረቡ። ዓጼ ምኒልክም፣ “ይኸማ አካባቢ እኮ፣ ጥንትም አባቶቼ ይነግሡበት የነበረ ስፍራ ነው” በማለት፣ በኢቴጌዪቱ ሀሳብ ተስማሙ። ዕውነቱ ይኸ ነው። ታሪኩ ይኸ ነው። ሌላ የለም! የዛሬ 150 አውሬ እንጂ ሰው አልነበረባትም። በምን ሂሳብ ነው፣ አዲስ አበባ ላይ አባቶቻችን ተሰበሩ የሚሉት? አንበሳው ሰብሯችው ይሆን፣ ወይስ ጅቡ? ሂሳባቸው ፉርሽ ነው። ወደ ቀመር ሰሌዳው ይመለሱ።

ከዚህ በኋላ፣  1879 ዓ.ም (November 1886) በእቴጌ ጣይቱ ብጡል፣ አዲስ አበባ ተብላ ተሰይማ፣ ዳግም ከአመድ ተነሳች። የዛሬ 138 ዓመት መሆኑ ነው። ዳግማዊ ትንሣኤ በሉት! ጫካው ተመንጥሮ፣ እንደገና ተቆርቁራ፣ የዓጼ ምኒልክ ባለሟሎች መሬት ተመረተው አበልጽገው፣ ከባድማነት ወደዘመናዊ ከተማ ተቀይራ፣ እንደገና የነገሥታቶቻችን መናገሻ ሆነች! አማረች! ተንቆጠቆጠች! ከኢትዮጵያ አልፋ ተርፋ የአፍሪካ መዲና ሆነች! ቆንጆን ማን ይጠላል?! ባል ገድለው ሚስት መቀማት በደም ሥራቸው አልነበር ድሮውንም? ኦሮሙማዎች በዚህ አይታሙም። አዲስ አበባ ዳግመኛ ስትቆረቆር፣ የተፈናቀለም ህዝብ አልነበረም፣ የተደረገም ጦርነት አልነበረም። ይልቁንም መፈናቀል፣ ቤት ማፍርስ የተጀመረው፣ ባሁኖቹ የኦሮሙማ አሞሮች፣ በልጽግና ዘረኛ ዓይናውጣ አገዛዝ መሆኑ፣ ይሠመርበት!

የዘመኑ ባለተረኞች፣ ሁሉንም “ኬኛ” ባዮች፣ ትርክተኞች ምንድነው የሚያወሩት? ትርክተኞቹ “አዲስ አበባ ላይ አባቶቻችን የተሸነፉት የዛሬ 150 ዓመት ነበር ይሉናል። ይህቺ 150 ዓመት ተደጋገመችብንሳ! ከየት አመጧት? ከብብታቸው ስር እንደፈለጉ መዠረጧት እንዴ? ወይስ የታሪክ ጭብጥ አለው? የሚገርመው ቢቢሲ (BBC) የአማርኛ ክፍል ዝግጀት ዘጋቢ፣ በዚያ ኢሬቻ ላይ ተገኝቶ ነበር። እንዲህ ብሎ ዘገበ። (BBC, 2019)።

በዓሉ በአዲስ አበባ መከበር ካቆመ 150 ዓመታት እንዳለፉት የሚናገሩት አባገዳዎች ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በከተማዋ ላይ ሊከበር መሆኑ ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል።

ይገርማል! በምን ሂሳብ? እንዴት ተደርጎ? የዛሬ 150 ዓመት አዲስ አበባ እኮ ጠፍ ነበረች። የምን ድርቅና ነው? ቢቢሲ ያወራው፣ በኢትዮጵያ አቆጣጠር መስክረም 29 ቀን፣ 2012 ዓ.ም. መሆኑ ነው። ከዚያ ተነስተን 150 ዓመት ወደ ኋላ ብንቆጥር፣ 1862 ዓ.ም ላይ እራሳችንን እናገኛለን። “ያን ጊዜ ማን ሥልጣን ላይ ነበረ?” ብላችሁ ብትጠይቁ፣ ዓጼ ተክለጊዮርጊስ የሚባሉ ለትንሽ ጊዜ ነግሠው ዙፋን ላይ ጉብ ብለው ታገኟቸዋላችሁ። ተክለጻዲቅ መኩሪያ የኢትዮጵያ ታሪክ (1960)። “ርዕሰ መኳንንት ደጃዝማች በዝብዝ ካሳ ሐምሌ ፮ ቀን 1863 ዓ/ም ዓፄ ተክለ ጊዮርጊስን አድዋ አካባቢ አሳም የሚባል ሥፍራ ላይ ወግተው ድል ካደረጉ በኋላ ጥር 13 ቀን 1864 ዓ/ም አክሱም ላይ ሥርዓተ ንግሣቸው ተፈጽሞ ዓፄ ዮሐንስ ፬ኛ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብለው ነገሡ” ይለናል። ጉድ ፈላ! የትግራዩ ንጉሥም ገና አልነገሡም ማለት ነው። ዓጼ ዮሐንስ የገዙት ከ1864 እስክ 1882 መሆኑ ነው። እና፣ የኛን ኬኛ አባ ገዳ አባቶችን ማን ነበር ከአዲስ አበባ ተዋግቶ ያፈናቀላቸው? ትንሽ እንኳን የሚያገናዝብ አዕምር የላቸውም? ሒሳቡ እኮ አይገጥምም! ድምሩ ፉርሽ ነው። ሚዛን ይደፋል። The maths doesn’t add up ይሉታ ፍረንጆችል። በእርግጥ አባ ገዳዎች እንዲህ ብለዋቸው ከሆነ፣ የኦሮሞን ምስኪን ህዝብ በውሸት ትርክት ተጫወተውበታል። እንደ አኖሌ ትርክት መሆኑ ነው።

“ኡኡቴ!” አለች ማሚቴ! ኧረ ከዚያ በፊት አንድም ቀን በዛሪዪቱ አዲስ አበባ በምትባለው ቦታ ኢሬቻ ተከብሮ አያውቅም! ኧረ አትዋሹ በሉልኝ እነዚህን ወናፎች! ውሸት ኃጢአት ነው! “እዚህ ኢሬቻ እንዳታከበሩ ማን ሰባራችሁ?” እንዳልኳችሁ ሒሳቡ አይሠራም! “ምንጫችው?” ስንላቸው፣ “አፈታሪክ!” ይሉናል። ዘንድሮ በአፈታሪክ ጀመረውን በአፈታሪክ ሊጨርሱን ነው። እንደግምላቸው! ለ350 ዓመታት እኮ ጠፍታ፣ ደን ሁና፣ የአውሬ መጨፈሪያ ነበረች አዲስ አበባ!  ከማን ጋር  እዚያ ቦታ ላይ የዛሬ 150 ዓመት ተዋጉ? መቼም ተክለጊዮሪስ መጥተው ደን ውስጥ አልገጠሟቸውም? ከጅቡ ጋር ይሆን የተዋጉት? ወይስ ከአንበሳው ጋር? ከዝንጀሮው ጋር? ከዝሆኑ ወይስ ከቀጭኔው ጋር ነው የተዋጉት? ያለሆነ፣ ያልነበረ፣ ያልተከሰተ ተረት ላይ ተመሥርተው፣ ባለጊዜዎቹ “ጉድ!” እያሰኙን ነው። የተጻፈ ታሪክ የላቸው፣ ፊደል አልነበራቸው። በወረራ ኢትዮጵያ እስኪደርሱ፣ ምንም አልተማሩም ነበር። ለዚህ ነው ፕሮፌሰር ኡለንዶርፍ (Ullendorff, 1960, ገጽ 75)፣ ለኢትዮጵያ ሥልጣኔ ምንም አላዋጡም፣ እንዲያውም ወደ ኋላ ጎተቷት ያሉት።  እንዲያው በ16ኛው መቶ ክፈለ ዘመን በዚያቺው መጀመሪያ በተማሯት የኢትዮጵያ ፊደል እንኳ ታሪካቸውን ጽፈው፣ ማስቀመጥ ይችሉ አልነበረ? ዕድሜ ለጋሞው አባ ባህርይ (1965) ይበሉ እንጂ እስከነጭራሹ ታሪክ አልባ ህዝብ በሆኑ ነበር። ስለኦሮሞ ታሪክ የጻፉት አውርፓውያን በሙሉ መነሻቸው ከአባ ባህርይ ነበር። ደሞ ተረት ተረት ይሉናል! አያፍሩም!

ኦሮሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ጭቁን ብሔርሰብ ነበር?

የአሁኖቹ ምሑር ተብዬ ልሂቃናቸው ከሌሎቹ 86 ብሔር ብሔርሰቦች ይልቅ ድምጻቸውን ክፍ አድርገው ኦሮሞ በኢትዮጵያ ሁለተኛ ዜጋ ነው ይሉናል። አንደኛ ዜጋ ማን ሆነና? በቅርቡ እንኳን ጋሞዎችን ከቡራዩ እንዴት ጭፍጭፍ አድርገው እንዳባረሯቸው አላየንም? እንዲያም ግፍ ተፈጽሞባቸው፣ጋሞዎቹ እንኳን ሁለተኛ ዜጎች ነን ብለው ሲጮኹ አይሰሙም። መጨቆንን እርሱት፣ ላለፉት 495 ዓመታት፣ በግድም ይሁን በወድ ረግጠው ሲገዙን የኖሩ የዝሁ ሕብረተሰብ አባላት ነበሩ። ኦሮሞዎች በመጀመሪያ ዘላኖች ስለነበሩ፣ ለከብቶቻችው ግጦሽና ውሀ ፍለጋ በየጊዜው አዲስ መሬት ለመንጠቅ ኦሮሞ ያልሆነውን ህዝቡ ወግተው መያዝ ስለነበረባቸው፣ በቀጥታ ወራሪነት፣ እየጨፈጨፉ፣ የደቡብ ብሔር ብሔርሰቦችን እያጠፉ ነው መሀል ኢትዮጵያ የደረሱት። አሁንም የቀሩትን ሊሰለቅጧቸው ጀማምሯቸዋል። ድመት መንኩሳ ዐመሏን አትረሳ ይባል የለ?

566677io

በኩሽ ትርክት መልሰው ባሪያ ሊያደርጓቸው ይዝታሉ። አማራን ለማንበርከክ አሁን ዓባይን ተሻግረዋል። ያኔ በጦርና በገጀራ ነበር ሲዋጉ የነበሩት። ዛሬ ላይ ድሮንና ጄት ታጥቀው አማራውን እያጋዩት ነው። አማራው ግን የሞት ሽረቱን እየተዋደቀ ነው። አማራው ከተሸነፈ፣ ወላይታ ወየውልህ፣ ጋሞ ወየውልህ፣ ሲዳማ ወየውልህ፣ ጌደዮ ወየውልህ፣ ጉራጌ ወየውልህ፣ ካምባታ ወየውልህ፣ ከፋ ወየውልህ! ኧረ ከኢትዮጵያም አልፈው ኬኒያም፣ ሶማሊያንም እንሰለቅጣለን እያሉን ነው። ከተሳካላቸው፣ የሚቀጥለውን ኤሬቻ ቀይ ባህርና የህንድ ውቂያኖስ ላይ እንደሚያከብሩ፣ ፕረዝደንት ሺመልስ አብዲሳ ዝተዋል። የኬኒያውን ዊሊያም ሩቶን ሰሞኑን ያሳሰባቸውና የራስ ምታት የሆነባቸው ይኸው ትርክታቸው ነው።

ወደ ሁለተኛ ዜግነት እንጉርጉሯቸው እንመለስ። ጎንደር ደርሰው ከተረጋጉ በኋላ የመደበኛ መንግሥት አካል ሁነው ለ450 ዓመታት ሲገዙን ነው የኖሩት። ነግሠውም ንጉሠ ነገሥት እስከመሆን ደርሰዋል። እቴጌ ጣይቱ ብጡልም ከየጁ ኦሮም ዲናስቲ ናቸው። እንሱም አይክዱም። ቀዳማዊ ኃይለሥላሴም፣ የጉዲሳ የልጅ ልጅ ናቸው። እነሱም ይመሰክራሉ። እቴጌ መነንም በቅርቡ ከነሱ እንደሰማነው፣ የራስ አሊ የልጅ ልጅ የሆኑ ኦሮሞ ናቸው። ከአማሮች ጋር ሰላም ከፈጠሩ በኋላ፣ የቀሙትን እንደያዙ ቀርተው ለማንኛውም ተደበላልቀናል። እንዴት ጎንደር ደረሱ? ያ ሀቅ አይደበቅ! ከንግዲህ ዝም አንልም!

የኢማም አህመድን ኢብን ኢብራሂም አል-ጋዚ (ግራኝ አህመድ) ወታደሮች እግር-እግር እየተከተሉ፣ እንደ ጥንብአንሳ አሞራ ሲቃርሙ ጎንደር ድረሱ። ጎንደርን ከያዟት በኋላ ቀጥቅጠው ለ103 ዓመታት ብቻችውን ገዝተውናል! ቋንቋቸው ጽሑፍ ስለሌለው፣ አማርኛን የሥራ ቋንቋ አድርገው ተጠቅመውበት ኢትዮጵያ ሲግዟት ነው የኖሩት። የሚገርመው ግን እየገዙን “ተጨቆን” ይሉናል። ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሀል ማለት ይኸ ነው። ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ እኮ ሳይቀሩ በአባታቸው የጉዲሳ የልጅ ልጅ ናቸው ብዬ ጠቁሜያለሁ። የራስ መኰንን ሀውልት ሐረር ላይ መንጋቸው ግርርርር ብለው ሲያፈርሱ፣ አንድ ዳር ቁም ሲታዘብ የነበረ ሰው፣ ከአፍራሾቹ አንዱን እንዲህ ሲል ጠየቀው። “እኚህ እኮ የኦሮሞ ባላባት ልጅ ናቸው። ለምን አፈረሳችሁት አለው። የምኒልክ ሀውልት አይደለም እንዲ ብሎ በድንጋጤ መለሰለት። ይኸ የሆነው እንግዲህ ሀጫሉ ሁንዴሳን እራሳቸው ገድለው “ናፍጣኛ” ገደለው ብለው መሬቱን ባገለባበጡት ጊዜ ነው። የድፍረታቸው ድፍረት፣ እንግሊዝ አገር በጥገኝነት የሚኖሩ መንጋዎች ለንደን ላይ ወዳለው ዊምብልደን ፓርክ  ሂደው የቆመውን የቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ሐውልት አፍርሰዋል። ድንቁርና ያጀግናል። ዞሮ ላለማየት አንገት ያደነድናል። ወይ ጥጋብ! ስንት ሰው ገደሉ ሐረር? ስንት ሰው ገደሉ አርሲ? ስንት ሰው ገደሉ፣ ዝዋይ …?

ሌላው የሚገርመው፣ ጥሩ ጥሩው ነገር የነሱ ነው። መጥፎ መጥፎው የሌላ ነው። ሁሉን ነገር “የኛ” ነው። መቼና ከየት እንደመጡ እየታወቀ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታዩትን ቅርሶች በሙሉ የኛ ነው ማለትን አብዝተዋል። አንድ ቁጭ ብሎ ሲያወጋን፣ የግብጽን ፒራሚድ የሠራን እኛ ነን ሲል አዳመጥነው። ፒራሚዱ ላይ ኦሮሞ የሚል ኤሮግሎፊክስ ይኖር ይሆን? ጎጃምንም የመሠረቱት እነሱ እንደሆነ ያው ሰው ይነግረናል። “ጉጀም” ብለው ስም ያወጡለት ኦሮሞች እንደሆኑ ይነግሩናል። ወደ በላይ ዘለቀ ጠጋ ጠጋ ለማለት? ትግራይ ውስጥ የሚገኙትን ቅርሶች በሙሉ እነሱ እንደሠሯቸው ይነግሩናል። መቀሌ በኦሮሚኛ መገንጠያ ማለት ነው ተብለናል። አዲግራት፣ “ከአዳ ጋራ” የኦሮሞ ቃል የተገኘ ነው ተብለናል። ሽሬ ከኦሮሚኛው ሲሬ የተገኘ ነው ብለዉናል። አክሱም በንጉሡ በዓጼ አክሱም (የንግስተ አዜብ፣ ወይም ንግሥተ ሳባ) አያት ስም የተሰየመ መናገሻ ከተማ ሳይሆን አካሱማ ከሚለው ቃል ነው ተብለናል። የኦሮሞን መኖር የማያውቁት ክ505 እስከ 571 የኖሩት ባለዜማው ቅዱስ ያሬድ የመደባይ ኦሮሞ ናቸው ተብለናል። እሺ! እሱስ ይሁንላቸው፣ ግን ዛሬ ላይ ለምን ሰላም ይነሱናል?

የአገራችንም ታሪክ ተመራማሪዎች ሆነ፣ የውጪ ሥራ ቁጭ ብለው ቢያጠኑ፣ ከዛሬ 150 ዓመት በፊት አዲስ አበባ፣ ምን እንደምትመስል ቢረዱ ያፍሩ ነበር። ግን እፍረት የምትባል ነገር በዘረመላቸው (DNA) አልተፈጠረችባቸውም። ፈጣጣዎች ናቸው። ንጉሡ ራቁታቸውን መሆናቸውን የሚንግራቸው፣ እንደኔ ያለ እብድ መኖር አለበት። ዕውነተኛዋን ታሪካቸውን ከየት ያምጧት? አያውቋትማ! ያዩትን ሁሉ እንደ ሕጻን “የኛ” ነው – ወይም “ኬኛ” እያሉ ይበጠብጡናል። ለምንድነው ወለይታውና ጋሞው “ አዲስ አበባ ኖሲ” ያላሉን? ፈትለው የሚያለብሱን እነሱ ናቸው። ለምንድነው ጉራጌው “ኢናን አአር” ወይም “የኞየኞ” የማይለው? የትውልድ አገሩም ነው፣ በንግድም ወይም ጠቃሚ ሥራዎችን እየሠራ አዲስ አበባን ቀጥ አድርጎ የሚያገለግለው ህዝብ ነው። ለምንድነው አባቶቹ የቆረቆሩትን ከተማ አማራው “የኛ” ብሎ ሙጭጭ የማይለው? ሲዳማው ለምንድነው “የናሓና” ወይም “ኒንኬቴ” የማይለው? ዛሬ ላይ፣ ልንል የምንችለው፣ አዲስ አበባ የሁሉም  ኢትዮጵያዊ ከተማ መሆኗን ነው።

ጥንት መረጃዎችን ሳገላብጥ ያገኘሁት መረጃ፣ ኦሮሞዎች ሸዋ ከመድረሳቸው በፊት፣ ሸዋ ውስጥ ይኖሩ የነበሩት አማሮች፣ ሃዲያዎች፣ ከንባታዎች፣ ጉራጌውምችና የሞችና ሌሎች አናሳ ጎሳዎች ነበሩ። አብዛኞቹ አናሳ ጎሳዎች በኦሮሞዎች ተውጠው ደብዛቸው ጠፋ። በረራ የሁሉም ኢትዮጵያ መነሀሪያ ነበረች። እንግዳ መጥቶ ከቤትህ  አድሮ አመስግኖ እንደመኼድ አስወጥቶህ “የኔ ነው! ከዚህ ጥፋ” ሲልህ አያድርስ ነው!  ምን ዓይነቶቹን ነው እግዚአብሔር የጣለብን?

ከዚህ በፊት፣ የኦሮሞ አክቲቪስቶች፣ “አዲስ አበባ ዋጠችን”  እያሉ ‘ኡኡ ይሉ ነበር። አሁን ደሞ ካልዋጥናት ኡኡ እያሉ ያደነቁሩናል። ምንድናቸው እነዚህ? ከየትኛው ፕላኔት ነው የመጡት? ዕውነትም፣ የኦሮሞ ልሂቃን የምሑራን ወይም የአዋቂዎች አዕምሮ ሳይሆን ያላቸው፣ የሕጻናት ሁሉንም “ኬኛ” ጸባይ የተጠናወታቸው ይመስላሉ። መሀይም ባይሆኑማ፣ ሰው ያልነበረባት፣ ጠፍ፣ ዝሆን፣ ጅብ … ድኵላ፣ ሚዳቋ የሚጨፍርባት ደን መሆኗን ተረድተው ዛሬ፣ በ21ኛ መቶ ክፍለ ዘመን፣ ሊቀሙን የሚያሰፈስፉትን አሳፋሪ ተግባር፣ የሚያስገምታቸው መሆኑን በተረዱና፣ በተሸማቀቁ ነበር። መሸማቀቅማ አለተፈጠረችባቸውም። ድንቁርና ያጀግናላ! አዲስ አበባ፣ ወደ ጠፍ ደን ከመቀየሯ በፊት ለመሆኑ ምን እንደነበረች ያውቃሉ? ያንን የማወቅ አቅም የላቸውም። የሚያውቁት ዛሬ በምናባቸው ያለችውን “የኔ” ስግብግብነት ቀማኛነት ነው። አንዱን አሜሪካ ነዋሪ አክቲቪስታችውን፣ አንድ ኦሮሚኛ መናገር የሚችሉ መምህር “ምንድነው በኢትዮጵያ ውስጥ የተጨንቆንከው” ሲሉት፣ አማሮች ቋንቋችንን እንዳንናገር ከለከሉን አለ። ልጆች እንዳሉት ጠየቁት። “አዎን” አላቸው። “ልጆችህ ኦሮሚፋ ይችላሉ? ሲሉት፣ “አይችሉም” ነበር መልሱ። ግብዞች!

ኦርማኒያ (Ormania) እና “ቡርቃ ጅረት” ትርክቶች

የሚገርመው፣ እነሱ ተመራምረው የደረሱበትን ታሪክ ሳይሆን ሁልጊዜ የሚንጠለጠሉበት የኢትዮጵያ ጠላቶች የጻፉላቸውን ትርክት ላይ ነው። ሁለት ሰው ለዋቢነት ላቅርብላችሁ። አንዱ ጀርመናዊው የቅኝ ግዛት ሰላይ፣ ዮሐን ሉድዊግ ክራፕፍ (Johann Ludwig Krapf) የተባለው ጠላት ሲሆን፣ ሁለተኛው ተስፋዬ ገብረአብ የተባለው፣ ኢትዮጵያ ጠል ኤርትራዊ ነው።

ደረጀ ተፈራ (2009) ስለዮሐን ክራፕፍ እንዲህ ይለናል።

 

ወለጋ አካባቢ ለረጅ ጊዜ በመኖሩ የኦሮምኛ ቋንቋ መናገር የሚችል ዮሐን ክራፍት የሚባል የጀርመን ፕሮቴስታንት ሚሽነሪና ሰላይ መጽሐፍ ቅስን ጀርመንኛን በሚጽፍበት በእንግሊዘኛ ፊደል (በላቲን ፊደል) በመጠቀም በኦሮምኛ ቋንቋ ተረጎመ (በነገራችን ላይ የቁቤ መነሻው ይህ ነው)። ይህ ዮሐን ክራፍት የተባለ ሚሽነሪ (ወንጌላዊ) ለተወሰነ ጊዜ ሸዋ ተቀምጦ በነበረበት ሰዓት ለአውሮፓ ቀኝ ገዢዎች ሲሰልል ተደርሶበት ከሃገር የተባረረ ቢሆንም ዳግም በኬንያ ሞምባሳ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የገባ ነው። ከተወሰነ ጊዜ ሃገር ውስጥ ከቆየ በኋላ ተመልሶ ወጣ።

 

 

88999

ዮሐን ክራፕፍ፣ እስከነአካቴው፣ ወደተለያዩ የኢትዮጵያ በወረራ የተሠማሩትን የቦረና ሰዎችን፣ ከኢትዮጵያ ነጥሎ፣ በምሥራቅ አፍሪካ ወኪሎች ሊያደርጋቸው እንደፈለገ ለጀርመን መንግሥት እንዲያድሩ መልምሏቸው ነበር። ዎልበርት ስሚት (Wolbert Smidt (SMIDT, München, 19 October 1840)) የተባለ ጸሐፊ ዮሐን ክራፕፍን ሥራ መርምሮ እንዲህ ይገልጸዋል።

 

The first one to try was Johann Ludwig Krapf, who was convinced that the Oromo were similar to the ancient Germanic tribes. He hoped, that a Christian reform movement could start with them and later encompass whole Africa, similar to Germany, from where Protestantism had originated. He constructed the idea of a unified country ‘Ormania’, as a new centre of Protestantism in analogy to ‘Germania’, where the Protestants formation had been initiated three.”

ስንተረጉመው፣

ይኸንን ጉዳይ መጀመሪያ የሞከረው ሰው ዮሐን ሉድዊግ ክራፕፍ ነበር። በትክክል ለማለት ኦሮሞዎች ከጥንታውያን ጀርመኖች ጋር ተመሳሳይ ዘረመል ያላቸው ጎሳዎች ናቸው ብሎ ያምናል። ስለዚህ፣ የመጀመሪያው የክርስቲያናዊነት ንቅናቄ በነሱ ተጀምሮ፣ ከዚያ በኋላ፣ ጠቅላላ አፍሪካን እንደሚያጥለቀልቃት፣ ተስፋ ነበረው። ልክ ከጀርመኒ የፕሮቴስታንት ዕምነት እንደፈለቀው ማለት ነው። ከዚህም ሀሳብ የተነሳ፣ “ኦርማኒያ” የምትባል አገር ተፈጥራ፣ ልክ እንደጀርመኒያ፣ ከሦስት መቶ ዓመታት በፊት የፕሮቴስታንት ዕምነት ማዕክል እንደሆነችው ኦርማኒያም ትሆናለች።

ዮሐን ክርፕፍ ጀግናቸው ነው። መሆንም አለበት። “ኦሮሚያ” እንዲሉም ከኦርማኒያ ቃል እሱ ነበር ያስጨበጣቸው። ከዚያ በፊት ጋላ ነው የሚባሉት። ዛሬ እንደሚንግሩን ጋላ ስድብ አልነበርም። ለነሱ አዝኖ እንዳይመስላችሁ። እነሱን ተጠቅም ኢትዮጵያን ሊያወድማት ነበር እንጂ! ነጭማ ጥብቅና ቁሞላቸው እንዴታ!

ስለገዳ ሥርዐታቸውም፣ ጽፎ ያገነነው፣ የራሳቸው ሰው ሳይሆን፣ የኤርትራው ዩኒቨርሲቲ ፕረዝደንት ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሠ ነው። እነሱማ፣ ታሪካቸውን የት ያውቁና ይጽፋሉ። ትርክቶቹን መለቃቀም ነው እንጂ ሪሰርች አካሂደው፣ ከውሀ ወጣን የሚል መደምደሚያ ያለፈ ታሪክ መጻፍ አይችሉም። መዋሸት ግን ማን ብሏቸው! ቆርጦ ቀጥሎች ናቸው። ማን ነበር፣ “አንድ ሰው ከውሀ ወጥቶ ቆመ። ጾታ አልነበረውም። ዋቃ እንዲህ ዓይቶት ለሁለት ከፈለው። ኦሮሞ አለው።” ያለን? እዝቂኤል ገቢሳ! ያውም ፕሮፌሰር!

ሌላው ጀግናቸው፣ ደብረዘይት ተወልዶ ደብረ ዘይት ያደገው፣ አማርኛን እንደናቱ ቋንቋ የሚያቀላጥፈው ኤርትራዊው ተስፋዬ ገብረአብ የተባለው የቦርቃ ዝምታ ጸሐፊ ነው። ተስፋዬ፣ ልቦለድ መሆኑን አልደበቀም። የሱን የፈጠራ ድርሰትን፣ ታሪካቸው አድርገው ወስደውታል። ኦሮሞ ከአማራው ተዋግቶ ስለተሸነፈ፣ ቡርቃ የሚባለው የኦሮሞ ወንዝ አፍሮ ምድር ውስጥ ሰምጦ እስከዛሬ ቀረ ይለናል። እንዲህ ያለውን ፈጣራ የኦሮሞ ልሂቃን አምነው ዓይናቸውን ጨፍነው ያለማሰብ ተቀብለውታል። ሲቀጥል እዚያ መንደር የነበሩ ኦሮሞዎች በሙሉ ተገድለው አልቀው “አኖሌ እና ሐዊ” የተባሉ ሁለት ሕጻናት ተርፈው ተገኙ” ይለናል፣ ተስፋዬ ገብረ አብ። ሌሎች የኦሮሞ ሕብረተሰብ አባሎች እነዚህን የተረፉትን ሁለት ሕጻናት አንስተው በእንክብካቤ አሳደጉ ተባልን። መቼ እንደሆነ አይነግረንም። መመራመር የተሳናቸው የኦሮሙማ ፖሊቲከኞች በምኒልክ ጊዜ እንደ ተፈጸመ አድረገው ወሰዱት። በውስጠ ታዋቂነት ነዋ። የሚገርመው እዚህ ጋ ነው። ጭንቃላት ላለው ሂሳቡ ፉርሽ የሚሆንባቸው። እነዚህ በምኒልክ ጊዜ ተወለዱ ከተባለ፣ ልጆቹ በምን ዓይነት ዘገምተኛ ዕድገት ነው፣ የንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱን ዘመነ መንግሥት ተሻግረው፣ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ዘመን ዘልቀው፣ በደርግና በወያኔ ዘመነ መንግሥት የደረሱት? በትንሹ እኮ 120 ዓመት አለፋቸው፣ አኖሌና ሀዊ! ድምሩ ፉርሽ ነው። ምክንያቱም፣ አኖሌ በወያኔ ዘመን መንግሥት አምጾ፣ ተዋግቶ፣ ለሀየሎም አርአያ እጁን ሰጥቶ ወደአሥመራ ተሻግሮ እስከዛሬም ከሀዊ ጋር በሰላም እዚያ ይኖራል ተብለናል። የማቱሳላ ዕድሜ ተችሯቸው ነበር ማለት ነው? ወያኔ ግልብነታውን አውቃ የተቆረጠ ጡት የያዘ “አኖሌ” የሚል ሐውልት ሠርታላቸው፣ አዲስ አበባ አቆመችላቸውና ይሰግዱበታል። አሁን የኦሮሚያ ሕጻናት የውሸት ትምህርት መርዝ እየተጋቱ፣ በየዓመቱ አኖሌ የምትባል መንደር መንፈሳዊ ጉዞ (piligrimage) ይዘጋጅላቸዋል። “እዚህ ቦታ ነው፣ አማሮች አንድ ሙሉ የኦሮሞ መንደር ከነህዝቡ ያወደሙት” እየተባለ ይነገሯቸውል። ምስኪን ሕጻናትን በውሸት ትርክት ስቅስቅ አድርገው ያስለቅሷቸዋል። ይኸ እኮ የኦሮሞ ህዝብን የማሰብ ችሎት መስደብ ነው። “Insulting the intelegence of all Oromo people!” ኦሮሞ ተናቀ! ዓላማቸው በሙሉ ኦሮሞን ወደ 16ኛው መቶ ክፍለዘመን የወራሪነት ባህላቸው ለመመልስ ነው የሚጋጋጡት። ይኸስ ለጤና አይደለም።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰሞኑን በአሰማው አስገራሚ ንግግር፣ ታሪክ ላይ እንዳንንጠለጠል ነግሮናል። ለኦሮሙማ አቀንቃኞች፣ ለነ ሺመልስ አብዲስ እያመቻቸን ነው። አሁን ፋኖን መሣሪያውን ሊያስፈታ ሲዘምት እኛ ደሞ ታሪካችንን እንድንጥል ሊያጃጅለን ነው። የኋላችንን ካላወቅን እንዴት ወደፊት እንኼዳለን? እነሱ የሌለ ታሪክ ፈጥረው ስለአኖሌ ሰቆቃ ሲያወሩ እኛን “ዝም በሉ” ሊለን ይዳዳዋል። ብልጥ መሆኑ ነው? ታሪክ ተሽክመህ አትዙር ካለ፣ አጥብቆ የአርሱን ትርክተኞች ይቆጣጠር። የሚያኮራ ታሪክ አለን። ኩርርርር! ትሰማ እንደሆን ስማ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሥቃይ

 

የዛሬይቱ አዲስ አበባ፣ ከ450 ዓመታት በፊት! በረራ፡ ፍጥረትና ዉድመት

80jjokይህቺ ሥፍራ ወደ ደንነት ከመቀየሯ በፊት፣ የዱር አዉሬ ነግሶ ሳይጨፍርባት፣ የዛሬ 450 ዓመት ምን ትመስል ነበር? እሷማ፣ በወረብ አውራጃ ሥር የምትተዳደረው፣ የነገሥታት መናገሻ ከተማ የነበረችው ታላቋ “በረራ” ነበረቻ። በረራን የኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ ያደረጓት ዓጼ በዕድማርያም (1468-1478) ነበሩ። ዓጼ እስክንድር (1478-1495)፣ ዓጼ አምደጽዮን (1495)፣ ዓጼ ናዖድ (1495-1508) እና በስተመጨረሻ ዳግማዊ ዓጼ ዳዊት (1508-1540) ተራ በተራ የተወለዱባት፣ ያደጉባት እና የነገሡባት ከተማ ነበረች።

እንደ መሪራስ አማን በላይ አገላለጽ (2000፣ ገጽ 441) ፣ የልብነ ድንግል (የክርስትና ስማቸው) ወይም ዳግማዊ ዳዊት (የንግሥና ስማቸው)፣ ወይም ወናግ ሰገድ፣ የአጼ ናኦድና የእቴጌ አትጠገብ ወንድወስን፣ የአፄ አምደጽዮን የልጅ ልጅ፣ የአፄ ዘርዓያዕቆብ የልጅ ልጅ ልጅ፣ ነበሩ። ያ ማለት፣ 15ኛው እስክ ከ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በረራ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መናገሻ ከተማ እንደነበረች ያለምንም ማወላወል የተረጋገጠ ሀቅ ነው።  ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፕንክረስትም፣ ሳሙኤል ዎከርም (Walker, 2019), ፕሮፌሰር ሀብታሙ መንግሥቴ ተግኘም (2012)፣ በተጨባጭ መረጃ፣ አዲስ አበባ ጥንታዊቷ በረራ እንደ ነበረች አረጋግጠውልናል። በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን፣ በዳግማዊ አጼ ዳዊት ዘመነ መንግሥት፣ ምን ተፈጥረ? ያንን በአጭሩም ቢሆን እንመልከት።

የመጀመሪያዎቹ የዳግማዊ ዓፄ ዳዊት የአገዛዝ ዘመን የሰላም ዘመን ነበር፣ ይሉናል የታሪክ መጻፍት። ዳሩ ግን፣ አህመድ ኢብን ኢብራሂም አል ጋዚ (Ahmad ibn Ibrahim al-Ghazi)፣ በተለምዶ ግራኝ አህመድ የተባለው የጂሀድ ተዋጊ፣  ከዘይላ አካባቢ ተነስቶ፣ ኢትዮጵያን በሙሉ ጠቅልሎ በመያዝ፣ የሙዝሊም አገር ለማድረግ አቅዶ ተንሳ ይሉናል ታሪክ አዋቂዎች። ብዙ ከተሞችን፣ ገዳማትን፣ አድባራትን፣ አቢያተ ቤተክርስቲያኖችን እያወደመ፣ ሽምብራ ኩሬ ደረሰ። ሽምብራ ኩሬ ማለት፣ በዱከምና በደብረዘይት መሀል የምትገኝ ሥፍራ ነበረች። ንጉሱ፣ የጦር ሠራዊታቸውን ይዘው፣ ከበረራ ወደ ሽምብራ ኩሬ ወረዱ። የግራኝን ጦር ገጠሙ:: በዚያ ጦርነት፣  ዳግማዊ ዓጼ ዳዊት አልቀናቸውም ነበር። በግራኝ በኩል፣ የተሰለፉት፣ ኢሳ ሱማሌዎች፣ አዳሎችና ዘመናዊ ጦር መሣሪያ የታጠቁ ቱርኩችና አረቦች ጂሀዲስቶች ነበሩ። ኢትዮጵያውያን አይተው የማያውቁት ከቱርክ የመጡ እንደ መድፍ ያሉ ተተኳሽ ጦር መሣሪያዎች፣ ሲጮሁባቸው፣ ተደናግጠው ሸሹ፣ ይለናል፣ ታሪክ። እጥፍ ቁጥር የሌለው ሠራዊት ይዘው፣ የተሸነፉበት ዋናው ምክንያት ይኸ ነበረ።

አረብ ፋቂ  የተባለው የጦርነቱ ውሎ የዘጋቢ፣ “Futuh Al-Habesha”, (The Conquest of Abyssinia) የሚባል መጽሐፉ ብዙ ቁምነገሮችን ጽፏል። የጦርነትን ውሎ አንድ በአንድ ዘገቧል። ድል በሽንብራ ኩሬ የቀናው የግራኝ ጦር ማባረሩን ተያያዘው። በረራ ደረሰ። ንጉሡ ባድቄ የነበረቸውን ቤተመንግሥታቸውን አቃጥለው ሠራዊታቸውን ይዘው ወደ ስሜን አፈገፈጉ። በሰላዮቹ አማካኝነት በረራ ያለጥበቃ እንደቀረች ተረዳ። ያኔ ወደ በረራ ከነሙሉ ኃይሉ ያለምንም ተከላካይ እንደ ገባ ይተርክልናል፣ መጽሐፉ። ኢማሙ፣ ካቴድራል ውስጥ የነበረውን ወርቅና ብር በሙሉ ዘርፎ ከጫነ በኋላ፣ መነኮሳቱንና ካህናቱን አርዶ፣ ካቴድራሉን፣ አቃጠለው። ለተዋጊዎቹ የሰጠው ትዕዛዝ ያገኙትን ንብረት ሁሉ እንዲበዙብዙ ነበረ። ተዋጊዎች የዘረፉትን ዘርፈው፣ ያገኙትን አቃጥለው ዶጋመድ አደረጓት። ሴት፣ ሕጻን፣ ሽማግሌ ሳይሉ ገደሉ። የንጉሡ መናገሻና ዋና ከተማ የነበረችውን በረራ በእሳት ጋይች። ለዚህ ዋቢ ለማቅረብ፣ በአገር ውስጥ ከተጻፉት የታዋቂው ኢትዮጵያዊ መሁር፣ የኢትዮጵያ እንዱስትሪ ሚኒስትር የነበሩ፣ የአቶ ይልማ ዼሬሳንና፣ በጊዜው የተጻፉትን የብራና መጻህፍት ማንበብ ካልፈለጉ፣ እንዲሁም ኢትዮጵያን ያኔ የጎበኟትን የአውሮፓም ሆነ የአረብ አገራት ተዋጉዊች የጻፉትን፣ (ኡስታዝ አህመዲን ጀበል እነሱን በመጥቀስ የጻፈውን በፊስቡክ ላይ ሒዳያ የተባለች እህት ያጋራችውን) ማየት ይቻላል። ቢያንስ ቢያንስ የሚከተሉትን ጽሑፎች ለማንበብ እንዲሞክሩ፣ እመክራለሁ። ብረተርኒትዝ እና ፓንክረስት (2009)፣ ሀብታሙ መንግሥቴ ተገኘ (2012) እና አረብ ፋቂ (2003)።

ከዚያም በተረፈ፣ ከዚህ በፊት British አርኪዮሎጂስቶች በቁፋሮ፣ የዳግማዊ ዓጼ ዳዊትን ቤተመንግሥት ፍርስራሾች አግኝተዋል። ከነዚህ ተመራማሪዎች አንዱ ዎከር (Walker, 2019) ይባላል። ባገኘው ምርምር እንድህ ይለናል።

Accounts of the destruction of Barara and other cities and churches, accurately depict that demolition was total. Our search to identify lost cities was exacerbated by a paucity of scholarship related to these eras. Additionally, the perception, given Addis Ababa’s modern status, seems to have tacitly colored the idea that it must have had medieval importance as well; a perception buttressed by various medieval sites on its fringes. But that does not mean it is hiding Barara, and it is hard to hide cultural materials, such as ceramics, stone tools, occupational soils, etc.

ስንተረጉመው፡

ባራራ፣ በአጠቃላይ፣ ሙሉ በሙሉ መውደሟን የሚገልጹ ዘገባዎች፣ በተጨባጭ ይታያሉ። የጠፉ ከተሞችን ለመለየት ያደረግነው ፍለጋ ከዘመናት ጋር በተገናኘ የስኮላርሺፕ እጥረት ተባብሷል። በተጨማሪም፣ አዲስ አበባ ከደረሰችበት ለማዘመን በሚደረጉት ጥረቶች አንፃር ሲታይ፣ የመካከለኛው ዘመን ጠቀሜታ ሊኖረው ይገባል የሚለውን ሐሳብ በዘዴ ያደበዘዘው ይመስላል። በዳርቻው ላይ በተለያዩ የመካከለኛው ዘመን ጣቢያዎች ምንም ይሁን ምን ይታያሉ። የአዳዲስ ህንጻዎች መገጥገጥ ግን ጥንታዊት ባራራን ይደብቃል ማለት አይደለም።, የሽክላ ስብርባሪዎችን የድንጋይ መሳሪያዎች፣ የመሥሪያ ዕቃዎች  የመሳሰሉ ባህላዊ ቁሳቁሶችን ለመደበቅ አይቻልም”።

ይኽ ተመራማሪ የኦሮሙማን ግዥዎች፣ ሕንጻዎችን ማፈራረስ፣ ሰማይ ጠቀስ ፎቆችን መሥራት፣ የአዲስ አበባን፣ የነዋሪውን ዲሞግራፊ ለመቀየር የሚጋጋጡት፣ ጥንታዊነቷን ለመደበቅ ከሆነ ሙክራቸው ዋጋ ቢስ መሆኑን በጎን እየነገራቸው ነው።

አንባቢ  ሆይ! አንድ ጭብጥ ያዙልኝ። እሱም ለምን የኦሮሞ ወራሪዎች ከ400 ዓመታት በፊት፣ ዛሬ እንደሚሉት፣ ታላቋን ኦሮሚያን አልመሠረቱም? በዚያን ጊዜ በጦርነት ስኬታማ ነበሩ። ሁለት ነገር ተገጣጥሞላቸው ነበር። እንዱ እንዳየነው፣ ግራኝ አህመድ የመሀል መንግሥትን አዳክሞላቸው ነበር። ሌላ ምስጢር ግን፣ መቶ በመቶ በሚባል ደረጃ፣ እያንዳንዱ የኦሮሞ ወንድ ልጅ፣ ከሕጻንነቱ ጀምሮ፣ በገዳ ሥርዓት ተዋጊ ለመሆን ይሰለጥናል። ያ ማለት፣ ወንዱ ሁሉ ተዋጊ ነው ማለት ነው። ከብት አርቢ በመሆናቸው እርሻ የሚባል ነገር አያውቁም ነበር። ጀስዊት የሚባሉ የካቶሊክ ካህናትን ጉዞ ስናነብ፣ አኗኗራቸውን እንረዳለን። ምግባቸው በአብዛኛው የክብት ሥጋና ወተት ብቻ ነበር። ስለዚህ ትርፍ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት፣ በተዋጊነት ሥልጠና ላይ ነበር። ሌላ የኦሮሞ ያልሆነ መሬትና ንብረት ተዋግተው ካልቀሙ፣ ፎሌዎቹ ቆንዳላ አይባሉም ።

የጦርነት ስኬታቸውን በተመለከት፣ አባ ባሕርይ እንዲህ ይላሉ። “ጋላ ያልሆን ቁጥራችን ብዙ ይሁን እንጂ ውጊያ የሚችሉ ጥቂቶች፣  ወደ ውጊያ የማይቀርቡ ብዙዎች ናቸው” (ገጽ 89)። ይኸንንም ሲያብራሩ የኦሮሞ ወንዶች በሙሉ ተዋጊዎች ሲሆኑ፣ የኢትዮጵያው ወንዶች ግን ከአሥሩ ዘጠኙ በተለያየ ሙያ የተሰለፈ ነው ይሉናል። ዘጠኙ እጅ እዝባችን፣ እንደሳቸው ያለ እግዚአብሔርን ለማገልገል የመነኮሰ፣ ወይም ጦርነት በመፍራት እንዳይዋጋ የመነኮሰ ነው ይሉናል። ሌሎቹ ቀሳውስትና ካህናት ናቸው። አይዋጉም። ሌላው በዳኝነት ላይ የተሰማራ ነው። ሌሎቹ የመኳንንቱ ሚስቶች ሎሌውች ናቸው። ሌሎቹ ሽማግሌዎች በመሆናቸው፣ አይዋጉም። ሊሎቹ ገበሬዎች ናቸው። መዋጋት አይጠበቅባቸውም። ሌሎቹ ነጋዴዎች ናቸው። አንጥረኞች፣ ጸሐፊዎች፣ ሸማኔዎች፣ ፋቂዎች፣ አናጢዎች፣ በጠቅላላው የእጅ ባለሙያዎች ውጊያ አይጠበቅባቸውም። ሌሎች እንደ አዝማሪዎች፣ በገና ደርዳሪዎች ባለከበሮዎች አይዋጉም ይሉናል አባ ባሕርይ።

ኦሮሞ ያልሆኑት ኢትዮጵያውያን ተዋጊዋጊዎች ከአሥሩ አንዱ ብቻ ነው። መጽሐፍን ስንመረምር፣ እነዚህ ተዋጊዎች፣ ለነጉሠ ነገሥቱ የሚታዘዙ፣ አማሮች የሚባሉ ናቸው። አማሮች፣ በሰላም ጊዜ፣ ንጉሠ ነገሥት ያስቀመጣቸው ቦታ ሁነው፣ መሬት ተሰጥቷቸው እያረሱ እራሳቸውንና ቤተስባቸውን ይቀልባሉ። ጦርነት ከተነሳ፣ ንጉሡ ባወጁ ጊዜ ጨርቀን ማቄን ሳይሉ፣ በመሀላቸው መሠረት ወጥተው አገር ይከላከላሉ። ለዚህ ነው ወጥቶ አደር (ወታደር) የተባለው። ለዚህም ይመስላል፣ ወደ ጥንቱ የገዳ ሥርዓት ለመመለስ የሚሞክሩት የዘመኑ ኦሮሙማ አቀንቃኞች፣ አማሮችን ጥምድ አድርግ ይዘው፣ ከምድር ላይ ሊያጠፉቸው የሚባዝኑት።

በነገራችን ላይ፣ ወጣቶቻቸውን (ኢልማኖች) ለማሰልጠን ከሚጠቀሙባችው ቅሪት የጨዋታ ዘዴዎች እኔም በዚህ ዘመን በልጅነቴ አይቻቸዋለሁ። ወላጅ አባቴ ለብዙ ጊዜ የመንግሥት ሠራተኛ በመሆናቸው፣ ከቦታ ቦታ እየተቀየሩ ይሠሩ ነበር። ከነዚህ ውስጥ፣ አንዷ ያከማ የምትባል፣ በኢሉባቦር ጠቅላይ ግዛት፣ በሞቻ አውራጃ፣ በሰሌ ወረዳ የምትገኝ ሥፍራ ናት። የኦሮሞ “ኢልማኖች” ከብት ሲጥብቁ፣ የትም ቦታ ያላየሁት፣ አንድ ጨዋታ ነበራቸው። ጌንጎ ይባላል። ከሚለጠጥ እንጨት ወይም ጠንካራ ሐረግ የሚሠራ ትልቅ ቀለበት መሳይ፣ ሲወረውሩት መሽከርከር የሚችል ነው። ከኦሮሞ “ኢልማኖች”፣ ጉልበት ያለው ይመረጥና፣ ያንን ጌንጎ (ቀለበት) ባለ በሌለ ኃይሉ፣ ያምዘገዝገዋል። ሌሎቹ ቄሮዎች፣ ኡሌ በተባለ ሹል በትር፣ ያንን ተምዘግዛጊ ጌንጎ ቀለበት፣ ወግቶ ከመሬት ማጣበቅ ነው። በኋላ ላይ እንደተረዳሁት፣ ጦር በመወረወር የሚሮጥ የዱር አውሬን ወግቶ ከመሬት አጣብቆ መግደልን ነበር የሚያስተምረው። ሌሎቹ ብሔር ብሔርሰብ ጋ የትም አላየሁትም።

ጀስዊትስ የተባሉ፣ ኢትዮጵያን ወደ ካቶሊክ ክርስትና ለመለወጥ የመጡ ፖርቱጋሎች ነበሩ። ብዙ የኦሮሞዎችን ጭካኔዎች አስተውለው ጽፈዋል። እንደነ ፓየስ (Páez,, 1622 Vol. I & Vol. II), ፌርናንዴዝ (Fernandez 1954, pp 143-148) በዓይናቸው ያዩትን የኦሮሞ ተዋጊዎችን ጭካኔ ጽፈዋል። እንዚህ የፖርቱጋል ጀስዊት ካቶሊኮች፣ ሌሎችም በጊዜው የነበሩት፣ ኢትዮጵያውያን ወደ ካቶሊሲዝም ለመመልስ እምቢ በማlለታቸው፣ እግዚአብሔር ለቅጣት ኦሮሞዎችን ሰደደባቸው ብለው ይደመድማሉ። እኛ ያንን ጭካኔ ረስተነው ትተናል። እነሱ ግን ዳግም ዙር እልቂት አውጀውብናል።

ኦሮሞዎች ያን ሁሉ ወረራ ሲፈጽሙ፣ አንዳንድ ነገሮችን ከነባሮቹ ኢትዮጵያውያን ተምረዋል፣ አባ ባሕርይን  (ገጽ 83) ስናነብ፣ ፍረስ መጋለብና በቅሎ ላይ መቀመጥን ተምረዋል።

“… ይኸ ምሳሌ (በጋሎች ዘንድ) ከሱ በፊት ያልተደረገውን በፈርስና በበቅሎ መቀምጥ ጀመረ። … ‘ፊተኞቹ ሉባዎች በሁለትና በሦስት እግር የሚሂዱትን፣ በአራት እግር እንዲሄዱ አደረግኋቸው እስኪላቸው ደረሰ። በሦስት እገር ማለቱ መንገድ በመንገድ ሲደክሙ፣ ጦራቸውን ስለሚመርኮዙ ነው”

ጎንደር ሲደርሱ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ተረጋጉ። ፊደል ቆጠሩ፣ ንባብ ተማሩ። ዳዊት ደገሙ። ከኢትዮጵያውያን እኵል ሊቅ ለመሆን በቁ። ገዳ ሥርዓታቸውን ወደዚያ አሽቀንጥረው ጣሉ። ግማሾቹ ክርስቲያን ሆኑ፣ ግማሾች ሙዝሊም ሆኑ። በዚህ ዓይነት የአብሮ መኖር ዜድዎች ነበር፣ ተረጋግተው፣ የመንግሥትን አስተዳደር ተምረው፣ ከጎንደር ለመቶ ሦስት ዓመታት ለመግዛት የበቁት። ከዚያ በኋላማ፣ የኢትዮጵያ እሴቶች ተምረው፣ ከሌላው ጋር ተቀላቅለው በሰላም መኖርን ተማሩ። ኢትዮጵያውያን ሆኑ። በአገር አስተዳደርም ሆነ፣ በትምህርትም ሆነ፣ በጤና፣ በሁሉም መስክ እኵል ተሳታፊ ሆኑ። በሰላም እስከቅርብ ጊዜ ኖሩ።

ዶ/ር ዐብይ የተባለ የኦህዴድ አመራር አባል፣ እንደ ሽለምጥማጥ ተሽሎክሉኮ፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሆን፣ የቀድሞው የወራሪነት ጠባያቸው አገረሽቶባቸው መሰል፣ ህዝብን ወደ መጨፍጨፍ ተሸጋገሩ። አያዋጣችሁም እያልናቸው ነው።

አስታውሱ! ዛሬ ብዙ የተማሩ፣ የኦሮሞ ኤሊቶች (ልሂቃን) ሞልተዋል። ዕድሜ ለቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ይበሉ። እንደ አቶ አማኑኤል አብራሃም (Abraham 2009) የአዲስ አበባው ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት የመጀመሪያዎቹ አዳሪ ተማሪዎች በመሆን በ1918 ዓ.ም ከወለጋ መጥተው ከገቡት 23 ተማሪዎች አንዱ ናቸው። ተማሪዎቹን በስም ስያስታውሱ፡ አባተ ቀነአ፣ አብዲሳ ጉደታ፣ አቦሴ ዱፌራ፣ አጋ ነገዎ፣ ወ/ማርያም ነመራ፣ ወዳጆ ሾካ፣ ዋቅጅራ ሰርዳ፣ ዋቅጅራ ኤጀታ፣ አለማየሁ ቂጣታ፣ ደስታ ወልደኢየሱስ፣ ጃለታ እፋ፣ ጃለታ ዴቲ፣ ገለታ ነገዎ፣ ጎበና አያና፣ ሙሉጌታ ገ/መስቀል፣ በቀለ ማሙዬ፣ በቀለ ቴሶ፣ ባህሩ ካባ፣ ተገኝ ኪ/ማርያም፣ ተፈራ በየነ፣ ተፈራ እስጢፋኖስ፣ ተፈራ ጉታና አማኑኤል አብርሃም ነበርን አሉ፡

ከእዚህ እላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ ባህሩ ካባ የአውሮፕላን አብራሪ ሁኖ ነበር፡፡ ወ/ማርያም ነመራ የፊታውራሪነት ማእረግ ተሰጥቶት በአገር ግዛት ሚኒስትር የማዘጋጃ ቤቶች ክፍል ዋና ዳይሬክተር ሆኖ አገልግሏል፡፡ ዋቅጅራ ሰርዳ እስከ ሜጀር ጄኔራልነት በመድረስ ልዩ የታማዦር ሹምና በእስራኤልን ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆኖ እስከመሾም ደርሷል፡፡ አለማየሁ ቂጤታ በፊታውራሪነት ማእረግ የደቡብ ክፍላተ አገራት ምክትል እንደራሴ ሆኖ አገልግሏል፡፡ ጎበና አያና ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ፈረንሳይ አገር ተልኮ ትምህርቱን አጠናቆ በመመለስ የባሌ አውራጃ ገዢ የነበሩት የደጃዝማች ነሲቡ ዛማኔል ረዳት ሆኖ አገልግሏል፡፡ አማኑኤል አብርሃም በተለያዩ አገራት በአምባሳደርነት ያገለገሉ ሲሆን የተለያዩ የሚኒስቴር መ/ቤቶችንም በሚኒስትርነት መርተዋል፡፡ ዋቅጅራ ኤጀታ ትምህርቱን አጠናቆ ወለጋ በመመለስ የውትድርና ትምህርት ሲሰጥ ቆይቶ በጠላት ወረራ ዘመን ከታሰረበት ለማምለጥ ሲሞክር ተገድሏል፡፡ አብዲሳ ጉደታ በወልጋ ከደጃዝማች ሐብተማርያም ጋር በመሆን ሰርቷል፡፡ አቦሴ ዱፌራ የሕክምና ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ በአሰበ ተፈሪ ከአዛዥ ወርቅነህ ጋር ሰርቷል፡፡ በፋሽስት ወረራ ዘመንም በድሬደዋ ምድር ባቡር እየሰራ በጅቡቲ ካሉ የኢትዮጵያ አርበኞች ጋር በመጻጻፍ በውስጥ አርበኝነት አገልግሏል፡፡ ለምንድነው፣ ጃንሆይ ያንን ያህል፣ ለኦሮሞ ወጣቶች ተጭንቀው አስተምረው ለቁምነገር ያበቁት? የኢትዮጵያ ብርቅዬ ልጆች በመሆናቸውና፣ በአባታቸው በኩል የሐረር ኦሮሞ ስለነበሩ ነው! እና ኦሮሞ ተጨቆነ? ጭቆና እንዲያ ከሆነ፣ ኦሮሞ ልሁን። እና በዘረኝነት ተቀፍድደው ያጎረሰቻቸውን እጅ መንክስን ዋቃ ይወድ እንደሆን አላውቅም፣ እኔ የማመልክበት እግዚአብሔር አይወድም።

እንደነዚህ ያለ አሳፋሪ ትውልድ ከመብቅሉ በፊት፣ የኦሮሞ አባቶች፣ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በፍቅር በሰላም በትንሹ ለ400 ዓመታት ኑረዋል። ክፉንና ደጉን አብረው አሳልፈዋል። መሪዎቻችን አንድም ከኦሮሞ ያልተወልዱ አይገኙም። እነ ጎበና ዳጬ፣ ዘመነ መሳፍንት ካራኮታት የጥንታዊቱ ኢትዮጵያ ፍርስራሾች ዘመናዊቱን ኢትዮጵያ የገነቡ አባት ናቸው። ውለታቸው እንዴት ይረሳል? የአድዋ የጦር መሪዎቻችን እነ ፊታውራሪ ሁብተጊዮርጊስ ዲናግዴ፣ ራስ መኮንን ጉዲሣ ዳባ (የጃንሆይ አባት – ግማሽ ኦሮሞ)፣ እነደጃዝማች ባልቻ አባ ነብሶ (ግማሽ ኦሮም) ነበሩ። የእነዚያን ስመጥሩ አርበኞች ታሪክ ሳጠና፣ ብታምኑም ባታምኑም፣ አንድም የኦሮም ደም የሌለብት አጣሁ። ምኒልክን የሚወድ ኦሮሞ አንድም በቤቱ አልቀርም። አባ ጂፋር ብቻ ነበሩ፣ አገር እንዲጠብቁ በጃንሆይ ትዕዛዝ እንዲመለሱ የተደረጉት።

በማይጨው ጦርነትም ድል መጅመሪያ ላይ ባይቀናቸውም፣ የኦሮሞ አርበኞች ብዙ ጀብዱ የፈጸሙ ናቸው። ነጻነታችንን በተነጠቅንበት አምስት ዓመታት ስንት ጀግና የኦሮሞ ልጀ ታሪክ ሠርቷል። የበረሀው ተኵላ አብዲሳ አጋ፣ ጣሊያንን በገዛ አገሩ ያርበደበደ ታሪክ የማይዘነጋው ጀግና ነበረ። አገር ውስጥ እነ ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ጣሊያንን መግቢያ መውጫ ያሳጡ አርበኛ ነበሩ። “አይጎነጎንም የፈረሱ ጭራ፣ ለማንዲራው ታማኝ ገረሱ አባ ቦራ ተብሎ የተገጠመላቸው ናቸው። የፍቼው ተውላጅ፣ ሰማ’ዕቱ አቡነ ጴጥሮስ አሁን ይረሳሉ? እጃችንን ኢትዮጵያ ላይ ካነሳን፣ ወየውልን፣ የአቡነ ጴጥርስ ግዝት አለብን። በወጣት አርበኞች የተገነባው የጥቁር አንበሳ ወጣት አርበኞች በብዛት የኦሮሞ ተዋጊዎች ነበሩ። ጀኔራል ጃካማ ኬሎ እንዴት ይረሳሉ? ጄኒራል አበባ ገመዳስ? ተጫነ ጀምበሬ በተረጎመው “የሀበሻ ጀብዱ በተበለ መጽሐፍ የሸዋው አቢቹ ጀግንነት በቼኩ ዜጋ የዓይን ምስክርነት ሲነገር ልብ ያንጠለጥላል። አበበች ዳራራ “አቢቹ ናጋ ናጋ፣ ቆሬን ሲዋራኒኖ” እያለች ታዜም የነበረው ለዝያ ወጣት አርበኛ መታሰቢያ ነበር። ስማቸው ግኖ ያለወጣው ስንት ጀግና አርበኞች አሉ መሰላችሁ? እኔስ፣ የአርብኛ ለማ ደግፌን ስም ባልጠራ ሒሊናዬ ይወቅሰኛል።

ትንሽ ከአሁኑ ትውልድ ቀድም ብሎ፣ ስመጥር ኢትዮጵያውያን የኦሮሞ ተውላጆች ነበሩ፣ አሁንም አሉ። ጀኔራል ካሣዬ ጨምዳን የማያውቅ ሰው ይኖር ይሆን? ጀኔራል ደሚሴ ቡልቶንስ? ጀኔራል ረጋሳ ጂማንስ? ስንቱን አንስቼ ስንቱን ልተው። ይኸ እንግዲህ የቀድሞና የአሁኖቹን አትሌቶቻችንና ደራሲዎቻችንን ስም ሳልጠቅስ ነው። ከዋሚ ቢራቱ እስከ የዲባባ ቤተሰቦች የሉትን ባለውለታዎቻችንን እናስተውል። ዛሬ፣ በዘረኝነታችሁ ተገፍታችሁ፣ የነዚያን ብርቅዬ አባቶች ልፋት ላይ ውሀ የምታፈሱት፣ ወደቀልባችሁ ተመለሱ። አለበለዚያ አጥንታቸው ይወጋችኋል። እንዳትረገሙ ተጠንቀቁ።

ማጠቃለያ

አዲስ አበባ ሲጀመር የኦሮሞዎች አልነበረችም አይደለችም። የጉራጌዎች፣ የካምባታዎች፣ የሀዲያዎች፣ የወላይታዎች፣ የየሞችና፣ የአማሮች አጽመ ርስት ነበረች። የናንተ ነገር ኋላ የመጣ ዓይን አወጣ ነው። ድሮውንም አገር መሥርታችሁ አታውቁም። ኦሮሙማዎቹ ጠቅላይ ሚኒስትራቸው እና ሹሞቻቸው፣ አይዟችሁ ባይነት የትም አያደርሳችሁም። ሰሞኑን በኦሮሚኛ ንግግር ሲያደርግ ጠቅላይ ሚኒስሩ፣ ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎች በኦሮሞዎች መያዙን አብሰሮዋቸዋል። የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ቦታ የያዘው፣ ኦሮሞ ነው። የጦር ኃይሎች ዋና አዛዥ ኦሮሞ ነው። የጦር ኃይሎች ኤታ ማጆር ሹሙ ኦሮሞ ነው። የአየር ኃይሉ አዛዥ ኦሮሞ ነው። የኢትዮጵያ አይር መንገድም የቦርዱ ሊቀመንበር ኦሮሞ ነው። ጊዜው የናንተ ነው ተብለዋል። ሁሉንም ኬኛ እያሉን ነው። ቡና መጀመሪያ የተገኘው፣ ካፋ ሳይሆን ኦሮሚያ ነበር በማለት እንድ አኖሌ ሐውልት ጂማ ላይ ሕውልት ሠርተውለታል። የቡና ሲኒ!

 

990ojj

ይኸ ግፍ በዚህ አይቀጥልም ባይ ነኝ። የኢትዮጵያ ሕዝብ እዳር ቁሙ የ16ኛ መቶ ክፍለ ዘመን ወረራ ሲደገም ዝም ብሎ አያያቸውም። ሆ ብሎ ተነስቶ ወያኔዎችን እንዳባረራቸው አሁንም ሆ ብሎ ተንስቶ የኦሮሙማ ብልጽግናንም ይሸኘዋል። ንብረቱ፣ ወድሞበት፣ ቤቱ ፈርሶበት፣ ተፈናቅሎ ለጎዳና ተዳዳሪነት ተዳርጎ፣ ግፍ ለመሸከም ትከሻ የለውም። የጥፋት መንገድ ይዘው እየነጎዱ ነውና ሀይ ሊባሉ ይገባል። አያዋጣቸውም። ወንድማዊ ምክሬን ልለግሳቸው ነው። እንደፈርኦን ልባቸው ከደነደን፣ ወደ ጥፋት መንገድ ነው የሚመራቸው።

በ15ኛው እና 16ኛው መቶ ክፍለ ዘመናት፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ወግተውታል፣ አድምተውታል፣ ሰልበውታል። መሬቱንም ነጥቀውታል። ቢሆንም፣ ከ450 ዓመታት በኋላ ግን በስለላም ጎን ለጎን በመኖራችን፣ የተለየ የአብሮነት ሁኔትዎችን ፈጥሯል። የያዙትን ይዘው ከተረጋጉ በኋላ አብረን ኑረናል። ተቀላቅለውናል። ለዘመናት በጋብቻ ተቀላቅለን ደማችን ተዋህዷል። አብረንም ክፉ ቀናትን አሳልፈናል። ቢያንስ ቢያንስ ሁለት ከባደ የወጭ ወረራዎችን አባቶቻችን አብረው ተቋቁመናል። ኢትዮጵያን ከቅኝ ገዥነት አትርፈዋል። አባቶቻችን ጎን ለጎን ቁመው ደማችውን አፍሰው አጥንታቸውን ከስክሰው፣ አደዋ ላይ ቅኝ ገዥዎችን በማሸነፍ፣ ለጥቁር ሕዝብ ጭምር አብሪ ኮከብ ሁነዋል። በሁለተኛ የዓለም ጦርነትም ጊዜ እንዲሁ አብረው ከአባቶቻን ጋር ተዋድቀው አገራችንን አትርፈውልናል። ነጻነታችንን ጠብቀውልናል። አንድ ሕዝብ ሁነናል። ያንን የሚይረጋግጥ ሳይንሳዊ የዘረመል ምርመራ የሚያሳይው ይኸንኑ ነው። እስቲ ልብ በሉት።

o878789hgh

ይኸ የምርመራ ውጤት እንደሚያሳየው፣ አንድ ንጹህ ኦሮሞ የለም። ከሁሉም ኢትዮጵያውያን ጋር ተደበላልቀዋል። የሌሎቹ ኢትዮጵያውያን ደም በደምሥራቸው ይዘዋወራል። ቋንቋ መግባቢያ ነው። በቋንቋ መለያየት የለብንም። አንድ ሕዝብ ነን። እውነቱ ግን በወሸት ላይ ተንተርሰው ሊያንበረክኩን የሚሞክሩት ሳይሁን ይኽቺ በትንሹ ያቀረብኳት ዕውነት ናት። ዕውነት አንድ ናት!

የኦሮሞ ልጅ እንዲማር አድርገው ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የእነ አቶ አማኑኤልን አብርሀምን ዓይን ሲክፍቱ፣ የተማረ ኢትዮጵያዊ ለማፍራት ነበር እንጂ፣ በዘር፣ በጎሳ ተለያይተን ለመኖር አልነበረም። የያዛችሁት መንገድ ለማንም አይበጅም። ወደ አዕምሯችሁ ተመለሱ ሊባሉ ይገባል!

ኦሮሚያ ውስጥ ሽማግሌዎች አልቀዋል ልበል? ልጆቹን ተው የሚል የለም? ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እንደሆነ እነ ሺመልስ አብዲሳን ተጠቅሞ ሊበታትነን ዕቅድ አሳዝሎ ሉሲፌር የላከው መልዕክተኛ እንጂ ኦሮሞን ሊያደን የመጣ መልአክ አይደለም። “ጠቅላይ ሚንስትሩን ኦሮሞ ነው፣ የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች አዛዥ ኦሮሞ ነው፣ የአየር ኃይሉ ጠቅላይ አዛዥ ኦሮሞ ነው” እያለ፣ “በአገሪቱ፣ ቁልፍ ቁልፍ ቦታ በኦሮሞ ተይዟል” ቢላችሁ አትጃጃሉ። የመንግሥት ቁልፍ ቁልፍ ቦታ መያዝ፣ ወያኔንም አላተረፈውም። ጠቅላላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይነሳባችኋል። ከገፋችሁት፣ ግዑዙ ግድግዳም መልሶ ይጋፋል። በዚህ ከቀጠለ መጨረሻው ለማንም አይበጅም።

“የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት” የሚባለው አካል ለመሆኑ እስከመቼ ነው ሥልጣን ላይ ለወጡት እያጎበደደ የሚዘልቀው? የአገር መከላከያ እንደስሙ ከውጭ ወራሪና አገርን ሊያፈርስ ከተነሳ የውስጥ ቦርቧሪ፣ አገርን ከጠላት እንዲያድን እንጂ፣ የአምባገነኖችን ወንበር ለመጠበቅ አልነበርም። የአገር መከላከያው የአገር መከላከያ የሚሆንበትን ጊዜ ለማየት እጓጓለሁ።

አበቃሁ።

 

ዋቢ ሥራዎች


መሪ ራስ አማን በላይ፣ (2004) ፣ መጽሐፈ አብርሂት፣ አብርሂ ኢትዮጵያ እዮብለዩ (፫፼) የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙርት ቅዱሳን በኢትዮጵያ

ይልማ ዴሬሳ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ፡ በአሥራ ስድስተማው ክፍለ ዘመን፣ 1967

https://www.facebook.com/AbubekerrAhmed/photos/a.856021951122955/1410026442389167/?type=3

Breternitz, Harwig and Richard Pankhurst. “Barara, the royal city of 15th and early 16th century (Ethiopia): medieval and other early settlements between Wechecha Range and Mt Yerer: results from a recent survey.” Annales d’Ethiopie 24 (2009): 209-249. Also found at https://www.persee.fr/doc/ethio_0066-2127_2009_num_24_1_1394

ተገኝ፣ ሀብታሙ መንግስቴ (2012) በረራ ቀዳሚት አዲስ አበባ

VI ተክለጻዲቅ መኩሪያ “የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ከዓጼ ትዎድሮስ እስክ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ፣ 1960፣ አዲስ አባባ

VII ኃይሌ፣ ጌታችው “ዜናሁ ዘጋላ” (1995) በአብ ባይርይ ድርሰቶች ውስጥ ገጽ 75 – 93

VII Almeida, Manoel de (1954) in Some Records of  Ethiopia 15193-1646, pp 133-139

VII Walker, Samuel C: Revealing Barara—the long-lost African medieval city, 23 April 2023, https://www.ethiopia-insight.com/2019/04/23/revealing-barara-the-long-lost-african-medieval-city/

IX  Sihab ad- Din Ahmed bin Abd al – Qāder bom Sa;e, bom ‘ Utmān. Also known as Arab Faqih

“Futuh  AL-Habasha, The Conquest of Abyssinia (16th Century), 2003, Translated by Stenhouse, Paul Lester

X ተፈራ፣ ደረጃ (2009) ያለፉትን 500 ዓመታት በሃገራችን የተከናወኑ ዋና ዋና ክስተቶችን፣ 2009፣ ኢትዮ ፓናራማ፣ https://ethiopanorama.com/?p=43325

XI Pedro Páez’s History of Ethiopia, 1622 / Volume, 1622 VI and VII

XII Fernandez, Father Antonio: “The Journey of Antonio Fernandes 1613 – 14, in Some Records of Ethiopia 1593 – 1646, pp 143 – 148

XII *Ullendorff, Edward: “The Ethiopians – an introduction to country and people,” London I96O

XIII Abraham, Emmanuel: Reminiscences of My Life, 2011,

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/ ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ ላይ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
Go toTop