October 10, 2024
20 mins read

ትግሉ ይጥራ – ከጥሩነህ ግርማ

Fano2 2 1የህልውና ትግሉን ወደሚቀጥለው ምዕራፍ ለማሸጋገር የኦይዶሎጂ ብዥታን ማጥራትና በመሬት ላይ ያለውን ተንኮል መጋፈጥና ማፅዳት ያስፈልጋል

የህልውና ትግሉ በአማራ ብሄርተኝነት ላይ ያጠነጠነ እንደመሆኑ የመኖር አለዚያም እንደ ህዝብ  የመጥፋት ትግል ነው:

ሌላው ኢትዮዽያዊ ወገን ፍትሃዊነቱን ተረድቶ በሚችለው አቅሙ ቢተባበር ሰው መሆንን የሚያሳይበት ነግ ለእኔም ግንዛቤን የሚጨብጥበት ነው::

ትግሉ ለአማራ ህዝብም ሆነ ለሌላው ወገን ግልፅ  መሆን አለበት: የተምታቱ የብሄርተኝነት ግንዛቤወችን ማጥራት ይኖርበታል: በሌላ በኩል በአማራ ብሄርተኝነት ላይ የተመሰረተው ትግል እንዳይሰናከል ተዋንያንን አበጥሮ ማውጣት ፍፁም አስፈላጊ ነው:

በመጀመሪያ በብሄርተኝነት ዙሪያ ያሉትን ብዥታዎች እንይ:

የአማራ ብሄርተኝነት አማራ በአማራነቱ የተጠነሰሰለትን የሞት ፅዋ ከውዲሁ እድሜውን ለማሳጠር የተጣለበት ማንነት ነው: አማራ ማንነቱን ሳይገነዘብ ለሽህ አመታት ኢትዮዽያዊነትን ተሸክሞ የሃገር ግንባታን እውን አድርጏል- ቀለሙ የማይደበዝዝ የውሸት ትርክት የማይሽረው አኩሪ ታሪክ ሰርቷል: ነገር ግን በዘርና በቋንቋ የተቸነከሩ ሃያ አንደኛውን ክፍለ ዘመን ወደ አስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን ለመመለስ የኇሊት የሚደናቀፉ ባለጊዜዎች አማራነቱን በመግደልም በማሳደድም አይኑን ገልጠውለታል:: ምንም እንኳ ሌላውም ጊዜውን ጠበቆ የሚደርሰው ቢሆንም ዛሬ አማራው የሚሞተው በአማራነቱ ነው: መመከትና እራሱን ማዳን የሚችለውም በአማራነቱ ተሰባስቦና ተደራጅቶ ነው: ስለኢትዮዽያ የአዞ እንባ የሚያፈሰው የኦሮሙማው ቡድን ኢትዮዽያን ሃያል የሚያደርጋት በአማራ እሬሳ ላይ እንደሆነ ከቃሉ ብቻ ሳይሆን በተግባሩም እያሳየ ነው: የአማራ ብሄርተኝነት እራስን በህይዎት ከማቆየት የመጣ እንጂ ከኢትዮዽያዊነት ጋር ትስስሩ በእብሪተኞች የሚበጠስ አይደለም: አማራነቱ ኢትዮዽያዊነቱን አያሳንሰውም አይጋጭበትምም:

የአማራ ብሄርተኝነት ለኢትዮዽያ አደጋ የለውም እንዲያውም በእኩልነት ላይ የተመሰረተች ሃገር ለመግንባትና በጋራ ሃገረ መንግስትም ለመትከል የእራሱን ጉልህ ድርሻ ያመጣል እንጂ። ዛሬ በአማራ መሬት የሚደረገው የነፍስ አድን መዋደቅ አማራ በህልውናው ለመቆየት አልፎም በብሄሩ የተጫነበትን ቀንበር አውልቆ ለመጣል የሚደረግ ፍትሃዊ ትግል ነው:: ለዚህ ነው በኢትዮዽያ ብሄርተኝነት ተለጉመው የሚዋዥቁ እለፍም ሲል የአማራን ብሄርተኝነት የሚኮንኑ አማሮች ግልፅ ግንዛቤ እንዲገዙ የምንጠይቀው:።

አማራ ነህ ተብሎ የሚታረድን የኢትዮዽያዊነት ካባ አልብሶ ማዳን አይቻልም::

ግንዛቤ የጎደለው የዋህ አማራ ቢኖርም ከእንጀራ ጋር ተጣብቆ የአብይን መቅኑን የሚጠብቀውም ቀላል ቁጥር አይደለም:: አብይ ሲያስነጥሰው መሃረብ ለማቅረብ የሚገፋፉት አማሮች የአማራን ችግር ያውቁታል ግን አድር ባይነታቸው ስለሚበልጥባቸው እንዳጎበደዱ ይገኛሉ:

አገልጋዮች ጉልበታቸው እስከሚላላጥ ተንበርክከው ጌቶቻቸውን ያገልግሉ እንጂ የአማራ ተፈጥሯዊ እራስን የማዳን ትግል ምንም አይነት የኢትዮዽያ ብሄርተኝነት ስብከት አይመለሰውም::ዋናው ኢትዮዽያ ጠል ዛሬ ኢትዮዽያ ስላለ ኢትዮዽያን አፈቀረ ማለት አይደለም: አማራን ከምድረ ገፅ አጥፍቶ ኢትዮዽያን መገንባት የሚል ከተበከለ አእምሮ የሚወጣ ዝባዝንኬ ብቻ ነው::

በትርክት ኢትዮዽያ የምትባል ሃገር የለችም የሚለን ዙሩ ሲጠብበት ማንነቱን ቀየረ ብሎ ለማመን የአማራ ደንገጡር መሆንን ይጠይቃል::

የአማራ እንቅስቃሴ መገደልና መስደድ ያመጣው የማይጨመር የማይቀነስ የህልውና ትግል ነው: በኢትዮዽያዊነቱ አማራው በዘረኛች ውግዘት ሲወርድበት ነፍጠኛ- አግላይ ጨቋኝ ሲባል እንዳልኖረ በአማራ ብሄርተኝነቱ ዙሪያ ተሰባስቦና ተደራጅቶ ሞትን አልቀበልም ሲል ከእንቅልፍ በድንገት እንደነቃ ህፃን እየተወራጩ የኢትዮዽያ አምላኪ በመሆን መማል መገዘት እውነታውን አይቀይረውም: አማራን ገፍተው ወደ ብሄሩ ያስገቡት ከሃምሳ  አመታት በላይ ብሄርተኝነትን/ ዘውገኛነትን ምለውበታል ተገዝተውበታል: ችግሩ የተፈጠረባቸው በፈጠሩት የውሸት ትርክት  አማራን ሲያሳድዱና ሲገሉ አማራ በቃ ብሎ መነሳቱ ላይ ነው::

ዛሬ አማራ እንደ ህዝብ መኖር የሚችለው በብሄሩ ተደራጅቶ ሊያጠፉት ያሰፈሰፉ ዘረኞችን በአመፅ ሲመልስ ብቻ ነው:: ኢትዮዽያዊ ብሄርተኝነት ለሁሉም ኢትዮዽያውያን እንጂ ለአማራ ብች የተሰጠ ችሮታ አይደለም: አማራ ለህይወቱና ለክብሩ በአማራነት ይታገላል: ከሌሎች ጋር ደግሞ በጋራ ኢትዮዽያን ከዘረኞች መንጋጋ ለማውጣት ድርሻውን ያዋጣል::

መጀመሪያ መቀመጫየን ነውና ህልውናውን ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጦርነት በምንም በማንም አይለውጥም::

አማራ የገጠመው ፈተና ቀደም ሲል ከአማራ ጠሉ ወያኔ አሁን ደግሞ በታሪክ ድኩማኑ የኦሮሙማው ቡድን ብቻ አይደለም: ፈተናው ክእራሱ ከአማራ አብራክ የወጣው ምሁር ባይ ጭምር ነው: ይህ ቡድን የባህር ላይ ኩበት ሆኖ ሲንከራተት ይታያል: በአንድ በኩል አማራነቱን መቀበል እንደቆፈነነው ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ዘረኞች ስለማያስጠጉት እንዲያውም ስለሚጠረጥሩት/ስለሚጠሉት ከሁለት ያጣ ስደተኛ ነው: በምናውቃት ኢትዮዽያ ሳይሆን በምናብ በሚያያት ኢትዮዽያ ውስጥ ተደብቆ እየባነነ እንቅልፋን እንደተኛ ነው:

 

መስከረም አበራ በውብ ብዕሯና ብሩህ አእምሮዋ እንዲህ ትላለች—

““የአማራ ንቅናቄ አያስፈልግም፣የአማራ ህዝብ ኢትዮጵያ ማዕቀፍ ስር በሚገታሉ ፓርቲዎች ስር ሆኖ በመታገል ችግሩን መፍታት ይችላል” ብለው የተሰለፉ የአማራ ልሂቃን አውቀውትም ሆነ ሳያውቁት ለአማራ ጠሉ የዘውግ ፖለቲካ ጉልበት ሆነዋል፡፡እነዚህ ወገኖች ለአማራ ጠሉ የዘውግ ፖለቲካ ጉልበት የሚሆኑበት ወሳኝ ነገር ፖለቲካዋ ሁሉ ዘውግ በሆነችው ሃገራችን የአማራውን በዘውግ መደራጀት እንደ ዘረኝነትና ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንደመተባበር አድርገው በመቁጠር በአደባባይ ሊያወግዙ የሚቃጣቸው መሆኑ ነው፡፡በዚህ ሳቢያ አማራ ጠሉ የዘውግ ፖለቲካ በሄደበት መንገድ ሄደው፣ የአማራን ህዝብ መብት ሊያስከብሩ የሚችሉ የአማራ ልሂቃን ዘረኛ እና ኢትዮጵያን አፍራሽ ላለመባል ሲሉ ብቻ በህዝባቸው መከራ ላይ ፊታቸውን እንዲያዞሩ ሆነዋል፡፡

በተጨማሪም እነዚህ ወገኖች ኢትዮጵያን የረዱ መስሏቸው የኢትዮጵያን ስም እየጠራ አማራውን ለሚያርደው ስርዓት የድጋፍ እጅ ይዘረጋሉ፡፡እንዲህ ያለው የአማራ ልሂቃን አቋም ስልጣን ላይ ያለው አማራ ጠል የዘውግ ፖለቲካ የጥላቻውን ምሬት ያህል አማራውን ያለጠያቂ እንዲገድልና እንዲያሳድድ ረድቶታል፡፡ በመሆኑም የአማራው አሰቃቂ ሞት፣የስነልቦና ስብራት፣ጠበቃ አልቦ ተሳዳጅነት እንደ ተገቢ የአዘቦት ተግባር ተባብሶ ቀጥሏል፡፡” ትላለች መሰከረም:

 

የአማራ ሙሁራን ከኢትዮዽያዊነት  መውረድ ውድቀት ነው እንደሚሉት ያጡት ግን ኢትዮዽያዊነትንም አማራነትንም ነው:: ትልቁ ችግራቸው ሌላው አማራ ከነሱ ያላነሰ የኢትዮዽያ ፍቅር እንዳለው ነው: ልዩነቱ ሌላው አልተጨፈነምና በአማራ ላይ እየዘነበ ያለውን መዓት ተርድቶታል: ስለዚህም ከዚህ መዓት ለመዳን አይነተኛውና ብቸኛው  መንገድ በአማራነቱ ተደራጅቶ መታገል መሆኑን ይገነዘባል:

በኢትዮዽያ ማዕቀፍ ስር እየታገለ ምንም ውጤት አልማግኘቱን መስከረም እዲህ ትላለች–

“…ይልቅስ በዘውጉ ተለይቶ ለሚደርስበት ሁለንተናዊ በደል ዘውግ ዘለል በሆነ ማዕቀፍ ለመፍታት በኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት ስር እንታገላለን የሚሉ ፓርቲዎች እና ድርጅቶች ስር ታቅፎ ሲታገል ቆይቷል፡፡ይህም ቢሆን በአማራ ጠሉ የዘውግ ፖለቲካ ፓርቲ ልሂቃን ዘንድ አልተወደደለትም፤በኢትዮጵያ ብሄርተኝነት ማዕቀፍ ውስጥም ቢሆን የአማራው ህዝብ ህልውና ስጋት በተገቢው መንገድ የማታገያ አጀንዳ ሆኖ አልቀረበም፡፡ አማራው በዘውጉ ለመደራጀት መዘግየቱም ሌሎችን ብሄረሰቦች የመጨፍለቅ ፍላጎቱ፣”የበለጥኩ ኢትዮጵያዊ ነኝና የበለጠ ለኢትዮጵያ አስባለሁ የማለት ትምክህተኝነቱ” መገለጫ ተደርጎ ተወሰደ፡፡በአማራ ህዝብ ላይ የሚደርሰው መከራ እየበረታ ሲሄድ አማራውን ለማደራጀት የተደረጉ አንዳንድ ሙከራዎች ሲታዩም ደግሞ ለአማራ ጠሉ የዘውግ ፖለቲካ ምቾት የሚሰጥ አልሆነም፡፡የአማራ ጠሉ የዘውግ ብሄርተኝነት ዋነኛው ተፈጥሮ በየትኛውም የክርክር ገፅ አማራውን ማክፋፋት፣ማጣጣል፣መቃወምና መጠራጠር በመሆኑ ምክንያት ነው በዘውግ መደራጀቱም አለመደራጀቱም አማራውን እኩል የሚያስወቅሰው፡፡

በዘውግ መደራጀቱም፣ አለመደራጀቱም የሚያስወቅሰው የአማራው ልሂቅ ታዲያ ከሶስት አስርተ አመታት በላይ ስልጣን ላይ ያለው አማራ ጠሉ የዘውግ ፖለቲካ አማራውን እንዴት እንደሚመለከተው ለመገንዘብ ረዥም ጊዜን ወስዶበታል፡፡ በመሆኑም አማራው በዘውግ የመጣበትን ፈተና በዘውግ ተደራጅቶ ለመመከት የሚደረገው ሙከራ ከአማራ ጠሉ የዘውግ ፖለቲከኞች እኩል ከአማራው ልሂቅም ተቃውሞ ይገጥመዋል፡”

አማራው ሃገሩን ተነፍጎ ከታጠረበት የክልል አጥር እንዳይውጣ ታግቶ ብቻ ሳይሆን ባለበትም ሲታረድ በኢትዮዽያዊነት ድምፅ ያሰማ የሌላ ብሄር የለም። ታዲያ ይህን እያዩና እያዎቁ ነው የአማራ ልሂቃን አማራው በኢትዮዽያዊነት እንጂ በአማራነት መደራጀትን የሚኮንኑት:

የአማራው ልሂቅ አማራን ከሚጠሉ ጋር መሰለፋ ታሪክ የማይረሳው ክህደት ነው: ግማሹ ግራ ተጋብቶ ከጠላት ይውግናል ሌላው በፈቃዱ ጌቶቹን ያገለግላል: የጎባጣ አሽከር አጎንብሶ ይሄዳል ነውና አንዳንዶች እንዲያውም ካለቆቻቸው በባሰ አማራን  ያሳድዳሉ: ከጌቶቻቸው ቀድመው ለሞሞት ይሽቀዳደማሉ:

 

ት  ግ  ሉ  በ መ ሬ ት ም   ይ  ጥ  ራ

ሁለተኛው በመሬት ላይ ያለው ትግል ጥራትና ፅናትን የሚጠይቅ መሆኑ ነው: ፋኖ በአጭር ጊዜ ያስቆጠራቸው ድሎች ወደር የሚገኝላቸው አይመስለኝም: በብሶት ወኔን አንግቦ የወራሪውን ጦር ድባቅ እየመታው ነው: ይህን በውሸት ተጠንሰስው በውሸት ተወልደው በውሸት ያደጉት ወራሪዎችም ወደማመኑ የደረሱበት ሃቅ ነው: በሁለት ሳምንት፣ በሰላሳ ቀን ወዘተ እንጨርሳቸዋለን ድንፋታወች የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እስከሚመስል አናፍተውበታል:: ጦርነቱን ጨርሰን እየለቀምን ነው ከሚለው እስከ ስጋት ወደማይሆንበት እናደርሰዋለን ሲባል እንዳልነበረ ሰሞኑን ደግሞ ጨርሶ ማጥፋት አይቻልም ላይ ደርሰዋል::ይህ ሁሉ የፋኖን ገድል እነሱውም ቢሆኑ የማይክዱበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን የሚያሳይ የእምነት ቃል ነው: ውርደታቸውን ለማሳየት እንጂ የነሱን ምስክርነት ፈልገነው አይደለም: መሬት ምስክር ናትና::

የፋኖ እድገትና አኩሪ ታሪክ ግን አልጋ ባልጋ ነበር ማለት አይደለም: በፋኖ ስም የፋኖን ልብስ የኮረጁ አስመሳዮች በህዝቡ መካከል ውጥረት እየፈጠሩ ነው:  ህዝብ ይደበድባሉ ይዘርፋሉ:ወራሪው ባለባቸው ቦታዎችም ሆነ ፋኖ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ፋኖ ዞር ሲል  በጠራራ ፀሃይ ስው ማገትና ገንዘብ መጠየቅ የእየለቱ ተግባር እየሆነ ነው: አብዛኞች በወራሪው ሃይል ተመልምለው ህዝብንና ፋኖን ለማቃቃር የተሰገሰጉ ናቸው እየተባለ ነው: ወራሪው ሃይል በወራሪው አባወራ አብይ አህመድ ትዕዛዝ ህዝብንና ፋኖን ለማጋጨት የማያደርገውና የሚንቀው ነገር የለም: በአንዳንድ አካባቢዎች እየወጣ ያለው የህዝብ ቅሬታ ነገ ሌላ ሆኖ ሊመጣ ይችላል: ዋናው የኦሮሙማም ግብ ይህ ነውና:

ለዚህ ነው ፋኖ ከውስጥ ትግሉን ማጥራት አለበት የምንለው:በፋኖ አደረጃጀት ውስጥ እስከ ትንሿ ቡድን ድረስ በተዋረድ ማደራጀትና ቁጥጥር እንዲኖር ማድረግ ለሰርጎ ገቦች ትልቅ እንቅፋት ነው: ጥብቅ ቁጥጥርና ከበረት የጠነከረ ዲሲፕሊን በተዋጊው ውስጥ ማስረፅ ትግሉን ወደፊት ከመግፋቱም በላይ እነአብይ ለሚመኙለት ክፍፍል ታላቅ በትር ይሆናል: ድል በመሽኮርመም አይመጣምና ትግሉን የሚጎትቱ ቅጥረኞች ሲያዙም  አስተማሪ የሚሆን እርምጃ መውሰድ የግድ ይሆናል::

በሌላ በኩል ህዝቡን ማደራጀትና እራሱን ከሰርጎ ገቦች እንዲከላከል ማሰልጠን፣ ሲቻልም ማስታጠቅ የትግሉ ሌላው ገፅታ ነው::

 


 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/ ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ ላይ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
Go toTop