August 24, 2024
16 mins read

ግራ ገብቶ ግራ የሚያጋባው የዲያስፖራ ውዥንብር እና ትርምስ!!

Diaspora ethiopia 1 1 1 1 1
#image_title

በዚህ ፅሁፍ “ዲያስፖራ” የሚለውን ጥቅል ቃል በውስጡ ግን ብዙ ታሪካዊ እና ጥናታዊ ትንታኔ ያለውን ቃል ትርጉም ለመተንተን አንሞክርም። ነገር ግን ስደተኞችን ተቅብላ የጥገኝነት መኖሪያ ፍቃድ ለመጀመርያ ጊዜ የሰጠችው የኛይቱ ሃገር ኢትዮጵያ ሁና ሳለ “ታሪክ ተለውጦ” ዛሬ ዛሬ እኛው የሰደተኝነት ፍልሰት በሽታ ተጠናውቶን እየታመስን እንገኛለን።

በዚህ ፅሁፍ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ( ትውልደ አማራ ዲያስፖራው) በስደት በሚኖርበት ሃገር ያለው ህጋዊ ቁርኝት ምን መምሰል አለበት? ፣ ጥሎት ከመጣው ከዕትብቱ ሃገሩ ጋር ያለው ግንኙነትስ በምን በምን ላይ ማተኮር አለበት?፣ ሃገር ቤት ካሉት የፖለቲካ ድርጅቶች ሆነ ነፍጥ አንስተው ከሚፋለሙ ድርጅቶች ጋር ሊኖረው የሚገባው ትስስር እና አስተዋፅኦው ምን መምሰል አለበት? የሚለውን ማወቅና አደጋ እና አስተዋፅኦውን ጥያቄ ውስጥ በማይስገባ መልኩ መጓዝ እንዳለብን ልብ ይሏል።
ከዚህ ባሻገር ጥበብ በተሞላበት መንገድ በሃገር ቤት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲሰፍን ፣ የለውጥ ድባብ እንዲመጣ ዲያስፖራው ምን መከናወን አለበት ፣ አፋፍ ላፋፍ እና ገደል ለገደል እየተዋደቀ ካለው ፋኖ  ጋር ያለው ትስስር እና የግንኙነቱ ገደብ (Boundary) እስከ የት መሆን አለበት የሚለውን ለመንገዘብ እና ለመረዳት መሞከር የግድ የሚል እና የኢትዮጵያ ዲያስፖራ(አማራው ዲያስፖራ) ቅርቃር ውስጥ ገብቶ ሃገር ቤት ያለውን የለውጥ ኃይል እንዳይጎዳው ሙያዊ ምክራችን እንለግሳለን።
ኢትዮጵያዊያን የመጀመሪያዎቹን  ከእየሱስ ክርስቶስ መወለድ በኋላ በ7ኛው (615 ከክርስቶስ መወለድ በኋላ) ወይም በ9ኛው ምህተ ዓመት (613 ከክርስቶስ መወለድ በኋላ ከአረቢያ ምድር ስደተኞችን ተቀብላ የንዋሪነት ፍቃድ የሰጠች ሃገር ናት።
በዚያን ጊዜ አክሱምን ያስተዳድር የነበረው የአማራ አጋዚያን ነገድ እንደነበር ልብ ይሏል።
“The first group of migrants, which comprised twelve men and four women, who fled Arabia in the year 7 BH (615 CE) or 9 BH (613 CE) according to other sources, and was granted asylum by Najashi, the Negus of the Kingdom of Aksum, a Christian state that existed in modern-day Ethiopia”.
ከላይ የተዘረዘረው ፅንሰ ሃሳብ መሰረት አድርጎ መጀመሪያ በታሪክ አክሱምን ያስተዳድር የነበረው ኢትዮጵያዊው ክርስቲያን ንጉስ ነጋሽ ከአረቢያ ምድር ለተሰደዱት የእምነታቸውን ጥንካሬ ፣ ፅናታቸውን ፣ በራስ መተማመናቸውን እና የአንድንታቸውን ጥግ ከግንዛቤ ውስጥ እስገብቶ ጥገኝነት ሰጥቷቸው መኖር እንደጀመሩ ይታወቃል። እንዲህም ተብሎ በዓለም አቀፍ ቋንቋ እንግሊዝኛ ተመራማሪዎች ከተበውታል:
“king Negash (Nejash) confirmed to thm, ‘for you are safe in my country”. He then returned the gifts to the envoys and dismissed them’.[11]them”
 በዓለም ላይ በሌሎች ሃገራት ተበትነው የሚገኙት ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራ (Diaspora) ተብለው ይጠራሉ።
ይህ ነጥብ የተነሳው በውጭ ሃገራት የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊው እና በተለይ አማራው በሰው ሃገር ሲኖር ምን ማድረግ እንዳለበት ፣ ምን አለማድረግ እንዳለበት እና ሃገር ለቆ በጥገኝነት በሰው ሃገር ሲኖር ሊያውቃቸው የሚገቡ ጉዳዮች ፣ ሃገርን ፣ ወገነንም እና እራሱንም እንዳይጎዳ ሊጠነቀቅ ይጋብል እንላለን።
፩) ትውልደ ኢትዮጵያዊው / ትውልደ አማራው ቀየው ወይም ሃገሩ ሰላም ከሆነች የሚከተሉትን ሊያከናውን እንደሚችል ሰነዶች ያሳያሉ:
“Diasporas build bridges between home land host countries. Diaspora also promote trade and foreign direct investment, create businesses and spur entrepreneurship, and transfer new knowledge and skills.”
ከላይ እንደተፃፈው የዲያስፖራው ሚና በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች (UNITED NATION FOR MIGRATION) ድርጅት ሕግ መሰረት በተወለደበት ሃገር እና ጥገኝነት ባገኘበት ሃገር መካከል መልካም ግንኙነት ይፈጠር ዘንድ ድልድይ መሆን ፣ በተወለደበት ሃገር የውጭ ዜጎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ መገፋፋት ፣ የንግድ ዘርፎች የጋራ ጥቅምን መሰረት ባደረገ መልኩ እንዲስፋፉ አስተዋፅኦ ማድረግ እና የእውቀት ሽግግርን ማሳለጥ ናቸው።
፪) ትውልደ ኢትዮጵያዊው ማድረግ የሌለበት ጉዳዮች ሲዘረዘሩ ፣
ከላይ የተዘረዘረው የትውልደ ኢትዮጵያዊው ( ዲያስፖራ) በሕግ አግባብ የተፃፈ ሊታወቅ የሚገባው በግልቡ የተቀመጠ በሃገሩ እና ጥገኝነት አግኝቶ በሚኖርበት ሃገር ሊያከናውነው የሚቻሉ አወናታዊ የሆኑ ጉዳዮች እንዳለ ሁሉ :
“Diasporas can also actively be involved in nation-wrecking when there is violence and war in the homeland. Diasporic groups have played major roles in fomenting and supporting conflict in places as diverse as Ethiopia, Kosovo, Nagorno-Karabakh, Kashmir, Israel, and Palestine.” Steven Vertovec.
ትውልደ ኢትዮጵያዊው(Ethiopian Diaspora) ዕትብቱ በተቀበረበት ሃገር ግጭት ፣ ጦርነት እና የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲኖር እነዚህን አሰቃቂ መከራዎች የማባባስ እና የማናር አካሄዶች ሊያደርስ እንደሚችል ከላይ የተዘረዘረው ሙሁራዊ ጥናቶች ያመለክታሉ።
እሁን አሁን በአማራ ዲያስፖራው (በትውለደ አማራው) እየታየ ያለው የአሳብ አለመጣጣም ፣ ቡድንተኝነት ፣ አንዱን የአማራ ፋኖ መሪ ደግፎ ሌላውን የመንቀፍ ፣ የሚደግፉትን የአማራ መሪ በገንዘብ አባብሎ ከሌሎች መሪዎች ጋር ቅራኔ ውስጥ እንዲገቡ የማድረግ አካሄዶች ብቅ ብቅ እያሉ መጥትዋል። ይህ ደግሞ የአማራን ፋኖ ትግል የድሉን ጊዜ የሚያራዝም ፣ የአማራው ማህበረሰብ የስልጣን ባለቤት እንዳይሆን እንቅፋት የሚሆን እና በትግል ሜዳ ያሉት ታጋዮች የእርስ በርስ መጠራጠር የሚፈጥር ከመሆኑ ባሻገር ትውልደ አማራውን ( The Amhara Diaspora) በተነሳሳሽነት እና በግለት የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲቀዘቅዝና እርስ በርሱ እንዲጠራጠር ያደርገዋል።
ከዚህ ባሻገር ቀጠል ብሎ የተፃፈው የምርምር ጥናት እንደሚያመለክትው:
“Different diaspora-based associations may lobby host countries to shape policies in favour of a homeland or to challenge a homeland government; influence homelands through their support or opposition of governments; give financial and other support to political parties, social movements, and civil society.” Yeshi Choeodn.
የተለያዮ የዲያስፖራ ማህበራት ዕትብታቸው የተቀበረበት መንግስታት የሚያወጡት ፖሊሲዎች ላይ ምክንያትዊ በሆነ መንገድ ፣ የህዝብን ፍላጎት እና መብት ባካተተ መልኩ እንዲቀረፁ ተፅህኖ ማሳደር ፣ በሕዝብ ላይ የመብት ጥሰት ፣ መገደል ፣ እስር እና እንግልቶች ካሉ ጥያቄዎችን በአግባቡ ማስጮህ ፣ አስፈላጊ ከሆነ መንግስት ይወርድ ወይም ይለወጥ ዘንድ ለተቃዋሚ ፖርቲዎች ፣ ለንቅናቄ ቡድኖች እና ማህበራዊ ተቋማት የገንዘብ እና አስፈላጊ ድጋፎችን ማድረግ እንደሚችል ሃገራዊ ተሞክሮዎች እና ጥናቶች ያሳያሉ።
እንግዲህ ይህን ካልን ዘንዳ በዓለም የተቋቋሙ የአማራ ዲያስፖራ ማህበራት ሊያውቁት የሚገባ ጉዳይ በምንም መልኩ ከዚህ ውጭ ሊያከናውኑት የሚችሉት አንዳች ነገር የለም።
ይህ ማለት “ከኔ በላይ ላስር “ ብሎ መወራጨት ለመጋጋጥ ወይም እቅምን እና መዳረሻን አለማወቅ ነው።
በጣም የሚገርመው ጉዳይ ምድር ላይ ያለው ፋኖ የዲያስፖራው ቅጥ ያጣ አካሄድ ያሰለቸው ፣ “እርካብ ያጣ ፈረስ” ስለሆነበት “መስሚያው ጥጥ ሁኗል ፣ የእርስ በርስ ጭቅጭቁ” ስላደከመው ፀጥ ብሎ ትግሉን ወደ ግብ ለማድረስ በራሱ እና በሚያዋጣው መንገድ ለዲያስፖራው ንትርክ ፣ ግራ የገባው አካሄድ እና ትርምስ ጀሮ ሳይሰጥ እየተፋለመ ይገኛል።
አንዳንዶቹ  በዲያስፖራ ያሉ ማህበራት አባላት ምድር ያለውን ፋኖ ሊመሩ የሚዳዱ ፣ እነሱ በሚያስቡት መንገድ እንዲጓዝ ፣ “እንዲህ መሆን አለበት እንዲያ መሆን የለበትም” እያሉ መቃዥት ፣ ስልጣን ሰጪ እና ነሽ የመሆን “ የኛ እናውቅልሃለን አካሄድ” እየታየባቸው እንዳለ እያየን ነው።
ይህ “እንደ እርጎ ዝንብ” ዘው እያሉ መፈናጠር እና አካሄድ በስደት የሚኖርበት ሃገር ሳይቀር የማይሻው ፣ አሰልች እና ህጋዊነትን የጣሰ እየሆነ ሲመጣ የዲያስፖራውን ስደተኛ ተቀባይ ሃገራት የተቃውሞ እንቅስቃሴውን  ከመደገፍ ይልቅ ስልጣን ላይ ላለው ጨቋኝ እና ገዳይ ቡድን አጋርነታቸውን እያሳዮ ሊመጡ እንደሚችሉ ጥናቶች ያሳያሉ።
ከዚህ ባሻገር በሚፈጠሩ ሽኩቻዎች ፣ የሰፋ ልዮነቶች ፣ እሰጥ አገባዎች ንትሮኮች ፣ በማያገባውም እና በሚያገባውም ጣልቃ የመግባት ፣ ትርምሶች እና ውዝግቦች ምክንያት አፈንጋጭ የዲያስፖራ አመራሮች ይፈጠሩና ሚስጥሮችን ለጠላት አሳልፎ ከመስጠት ባሻገር የዲያስፖራውን ማህበረሰብ ትግል ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ኩነት ከመፍጠር አልፎ ሃገር ቤት ለሚደረጉ ትግሎች የሚሰባሰቡት ምዋህለ ንዋዮች እና ድጋፎች አግባብነት ባለው መልኩ ለተፈለገው ዓላማ እንዳይደርስ ፣ የስደት ተቀባይ ሃገር ደህንነቶች እና የሚመለከታቸው ተቋማት የተዋጣውን ገንዘብ ከማገድ አልፎ አላስፈላጊ የሆነ ቁጥጥር ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ ልምዶች ያሳያሉ።
ማጠቃለያ
የኡትዮጵያ ዲያስፖራ የተቃውሞ ትግል የቆየ ታሪክ እንዳለው የሚታወቅ ሲሆን በተለይ ደርግን እና ህውሃትን ይቃወሙ የነበሩ የዲያስፖራ አደረጃጀቶች በሳል ፣ ምሁራን የበዙበት ፣ ሰፊ የመከፋፈል አባዜ ያልተጠናወታቸው ፣ ግርማ ሞገስ ያላቸው፣ እርስ በርስ የሚከባበሩ ሃገር ቤት የተደራጁ ተፋላሚዎችን ያለምንም ልዮነት የሚደግፉ እንደነበረ ታሪካቸው ያትታል።
ለምሳሌ ህወሃት ደርግን ይፋለም በነበረበት ወቅት የሌላው ብሔር ተቃዋሚ ዲያስፖራ ቡድን የተሸወደው እና ግልፅ ያልሆኑለት የህውሃት ደባ ቢጊዜው ቢኖርም ሁሉ ባንድ ላይ “ሆ” ብሎ በመነሳቱ ደርግ ሊፍረከረክ ችሏል።
ለጊዜው ጥቃቅን ችግሮችን ፣ የስልጣን መገፋፋቶችን ወደ ጎን አድርጎ በፅናት እና ሚስጥርን “የባቄላ ወፍጮ” ሳያደርጉ መታገልን የአማራው የዲያስፖራ አደረጃጀት ክህውሃት አልመማሩ ድንግር የሚል ፣ የማይገባ እና ግራ የሚያጋባ ኩነት ነው። ያሳዝናልም ፣ ያበሳጫልም።
በትግል ውስጥ ሰንኮች ይኖራሉ ነገር ግን እነዚህ ሰንኮች ፣ ያልሰፉ መከፋፈሎች እና የግል መፋተጎች ከትግሉ ዋና ዓላማ ጋር ሲነፃፀሩ ኢምንት በመሆናቸው ቦታ ሊሰጣቸው የማይገባ በመሆኑ ትውልደ አማራው (Diaspora) ግራ ገብቶ ግራ ከማጋባት እና እርስ በርስ በማህበራዊ በይነ መረብ ፣ ፌስ ቡክ ፣ ዋትስ አፕ መናረቱን፣ መቆራቆሰን ሊያቆም እና ሊታቀብ ይገባል እንላለን።
ተዘራ አሰጉ

ከምድረ እንግሊዝ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/ ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ ላይ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
Go toTop

Don't Miss

263967418 910622529847944 6927065551309196375 n

ዲያስፖራ ሆይ! ዘራፊዎች እንደገና ሊያፈርሱት ተሚችሉት ጎጆ በፊት ፋኖን ገንባ!

በላይነህ አባተ ([email protected]) ታሪክ እንደሚያስረዳውና እንደምናውቀው ፋኖ አገር ስትወረር፣ የሕዝብ