ወያኔ አለማጣ ገባ፤ ተውት ይግባ

ጠላትህ ራሱን እያጠፋ ስታየው አታውከው።
“Never interfere with your enemy while he is in the process of destroying himself.”
(ናፖሊዮን ቦናፓርት፣ Napoleon Bonaparte)

“ጠላትህ ራሱን እያጠፋ ስታየው አታውከው።”

“Never interfere with your enemy while he is in the process of destroying himself.”

(ናፖሊዮን ቦናፓርት፣ Napoleon Bonaparte)

 

ወያኔ ወደ ሞቱ እየገሰገሰ ያለ ሟች ድርጅት ነው።  እንዳገሳገሱ ደግሞ እንደ ድርጅት ግብአተ መሬቱ በቅርቡ መፈጸሙ አይቀሬ ነው።  እንደ ድርጅት ከሞተ በኋላ ደግሞ ልክ እንደ ኢሕአፓ አባላቱ እየተንጠባጠቡ ሙተው እስከሚያልቁ ድረስ አለሁ ለማለት ያህል ብቻ በየጊዜው መግለጫ እያወጣ መንገታገቱን ይቀጥላል።  ኦነግም እየተከተለ ያለው ያስተማሪውን የወያኔን መንገድ ስለሆነ፣ ዕጣውም የወያኔ ዕጣ ነው።  ስለዚህም መነሻው አማራ መድረሻው ጦቢያ የሆነው ያማራ ሕዝብ ትግል ዋና ዓላማ እነዚህ ወያኔና ኦነግ የሚባሉ ይዞ ሟች ድርጅቶች አማራን ጨፍጭፈው ጦቢያን ይዘው ሳይሞቱ በፊት እንደ ድርጅት የሚሞቱበትን ቀን በተቻለ መጠን ማፋጠን ነው።

የወያኔ የሞት ሂደት ሀ ብሎ በይፋ የጀመረው የወያኔ አመራሮች (የራሳቸውን ጓዶች ካስገደሉና በሚሊዮን የሚቆጠሩ የትግራይ ወጣቶችን ካስጨፈጨፉ በኋላ) አዲሳባ ሂደው፣ ከጭራቅ አሕመድ ጎን ተቀምጠው በቴሌቪዥን መስኮት የታዩ ዕለት ነው።  ከዚያች ዕለት ጀምሮ ወያኔ በትግራይ ሕዝብ ዘንድ ያለው ድጋፍ በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል።  ለዚህ ደግሞ “ለየካቲት” ገለመሌ የሚባለው (ለወትሮው የከበሮ ድምጽ በታዳሚ የተጨናነቀን አዳራሽ ግድግዳ ይነቀንቅ የነበረበት) የወያኔ ምሥረታ በዓል፣ ዘንድሮ ግን ጥቂቶች ብቻ ታድመውበት፣ ከመቆየት ብዛት ጨርሶ ሊረሳ የተቃረበ 49ኛ የሙት ዓመት መስሎ ጭር ብሎ ማለፉን መጥቀስ ብቻ ይበቃል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በአሁናዊ ተራማጅ አስተሳሰቦች እየተመሩ ፍትሃዊ ለውጦችን  በማስመዝገብ እንጅ በታሪክ በመቆዘምና በመኮፈስ ኢትዮጵያን ማበልፀግ ቀርቶ ማስቀጠል አይቻልም

ሐበሻን ከምድረገጽ ሊያጠፋ ቆርጦ ከተነሳው ከጭራቅ አሕመድ ጋር የሚሞዳሞደውን ወያኔን አሁንም የሚደግፍ የትግሬ ሰው ካለ፣ ሰውየው ወይ በወያኔ ዘረፋ የተጠቀመ ዘራፊ ወይም ደግሞ ወያኔ በየዕለቱ ይገተው በነበረው ፀራማራ ትርክት የሰከረና ስካሩ አሁንም ድረስ ያልበረደለት ሰካራም መሆን አለበት።  ወያኔ ያማራን ክልል ዳግመኛ ለመውረር የተነሳበት አንደኛው ምክኒያት ደግሞ የነዚህን በፀራማራ ትርክት የሰከሩ፣ በዝቅተኝነት ስሜት የታወሩ ደጋፊወቹን ሞራል ለመገንባት ነው።

ወያኔ ያማራን ክልል ለመውረር በድጋሚ የተነሳበት ሌላኛው ምክኒያቱ ደግሞ ከኦነግ ጋር በመተባበር እድሜውን ለማርዘም ነው።  የወያኔ ሂወት የተንጠለጠለችው በኦነግ ገመድ ላይ ስለሆነ፣ የኦነግ ገመድ ሲበጠስ ወያኔ ተፈጥፍጦ ይሞታል።  በሌላ አነጋገር ወያኔ ራሱን በራሱ የኦነግ ተለጣፊ ድርጅት ስላደረገ፣ ወያኔን እንደ ድርጅት ለመግደል የሚያስፈልገው ኦነግን እንደ ድርጅት መግደል ብቻ ነው።  ስለዚህም ያማራ ፋኖ ሙሉ ትኩረቱን ማድረግ ያለበት ጭራቅ አሕመድን አስወግዶ አራት ኪሎን በመቆጣጠር ላይ ነው፣ አራት ኪሎን መቆጣጠር ማለት ሁለቱን ፀራማሮች ኦነግንና ወያኔ ባንድ ዲንጋ መግደል ማለት ነውና።

ባለፈው ወረራው ያማራን ሕዝብ ፍዳ እያስበላ ሐብትና ንብረቱን ያወደመውና የዘረፈው ያማራ ሕዝብ ዘላለማዊ ጠላት የሆነው ወያኔ፣ እንደገና ተመለሶ አለማጣን ወይም ሌላ ያማራ ከተማን ቢይዝ ጠላት ወረዳ ዘው ብሎ ገባ ማለት ስለሆነ፣ ውጤቱ አማራን አሸነፍኩ ብሎ ባማራ ጥላቻ የሰከሩትን ጥቂት ደጋፊወቹን እያስጨፈረ የራሱን ሞት ማፋጠን ብቻ ነው፣ ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነውና።  በተጨማሪ ደግሞ ያማራ ሕዝብ ባሁኑ ጊዜ በደንብ ስለታጠቀና ቀንደኛ ጠላቱን ወያኔን በደንብ ስላወቀ፣ ወያኔ የቱንም ያማራ ከተማ ቢቆጣጠር፣ ያማራን ሕዝብ እንደ ቀድሞው በቀላሉ ሊጨፈጨፈው፣ ልጆቹን ሊደፍር፣ ንብረቱን ሊያውድም፣ ሐብቱን ሊዘርፍ አይችልም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በውኑ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነውን? - ሰሎሞን ጌጡ

አብዛኛው የትግሬ ሕዝብ ደግሞ (ይህን ሁሉ መከራ ያወረደበትን) ወያኔን ቢደግፈውም የሚደግፈው አማራጭ ስላጣ ብቻ በመሆኑና በሙሉ ልቡ ስላልሆነ፣ ባሁኑ የድጋሚ ወረራ ወያኔ ሊያሰልፈው የሚችለው ሠራዊት ቁጥሩ የመነመነ፣ ወኔው የደበነ የውሻ ሞት የሚሞት ደመ ከልብ ሠራዊት ነው።  የወያኔ ሠራዊት አዝማች የጻድቃን ገብረተንሳይ አንድና ብቸኛ ችሎታ ደግሞ ሠራዊቱን ፈንጅ እያስረገጠና እያስጨፈጨፈ የሚያልቅው አልቆ የቀረው ወደፊት እንዲገፋ ማድረግ ብቻ ስለሆነ፣ ፈንጅ ረጋጭ ካጣ ምንም አያመጣ።

ስለዚህም ያማራ ሕዝብ ሆይ ትንሹ ጅብ ወያኔ የትም ገባ የትም ለጊዜው ንቀህ ተወውና ሙሉ ትኩረትህን በትልቁ ጅብ በኦነግ ላይ አድርግ፣ ትንሹ ጅብ ሂወቱን እያራዘመ ያለው ትልቁ ጅብ ዋናውን ሥጋ በልቶ በሚያስቅርለት ቁሪሳ ነውና። ወደ ትልቁ ጅብ የምታደርገውን ግስገሳ ትንሹ ጅብ ከኋላ ሁኖ እያወከ ከበጠበጠህ ደግሞ ብዙ ጦር ሳትመድብለት ስልታዊ መከላከል በማድረግ ተመልሶ ወዳማይወጣበት ቀጠና እየሳብከው ለጊዜው አቆየው።

 

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

1 Comment

  1. መስፍን አረጋ you are right and ወያኔ አለማጣ ገባ፤ ተውት ይግባ !
    Mistakes come at a high cost, and hard-working Ethiopians are bearing the burden because they placed their trust in Abiy’s deceitful tactics. It’s said that the best time to correct a mistake is before it happens. The reasons behind mistakes often boil down to three things: ignorance, negligence, or apathy.
    Consider this scenario: If Abiy were to announce tomorrow that he intends to change the constitution, professing love for Ethiopia, and claiming unity in the Orthodox Church, would you believe him? Absolutely not! When is Abiy lying? Whenever his lips are moving!
    The only talent Abiy has is starting and exploiting conflicts, and this ‘Welkait’ situation is just another one of his manipulations. Let me reiterate an analogy: Picture a jar containing 100 black ants and 100 red ants. Initially, they coexist peacefully. However, when the jar is shaken and placed on a table, the ants start attacking each other, leading to chaos and destruction.
    Likewise, in Ethiopia, before turning against each other, we must consider who is shaking the jar. It’s the boorish troublemaker, Abiy. Let’s use our rationality before surrendering to division and violence. The mistakes we make now are costly, and it’s the hard-working, impoverished Ethiopians who are paying the price for trusting Abiy’s deceit. It’s time to understand the modus operandi of the Boy King’s divide-and-rule strategy, so we don’t fall victim to the ignorant ways of Abiy again and again.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share