March 13, 2024
24 mins read

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ!

በላይነህአባተ(abatebelai@yahoo.com)

Diaspora fight

በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ የሚያስታውስና ዳግም የሚያስተርክ ነው፡፡

ጥንት ድሮ የአማራን ቋንጃ ለመስበር እንኳን ኢትዮጵያ ውስጥ የበቀሉ ጉዶች ምዕራባውያንም እቅድ ከማውጣታቸው ከአድዋው ጦርነት በፊት የጫጉላ ጊዜአቸውን ጨርሰው ጎጆ የወጡ ወጣት ባልና ሚስት ስለ “መነሻና መድረሻ” እቅድ ማውጣት ጀመሩ፡፡ መነሻቸው መሬት አርሰውና ጓሮ ቆፍረው እህል አምርተውና ሸጠው ገንዘም ማግኘት ሆነ፡፡ መዳረሻቸው ደሞ ላም መግዛትና ስትወልድ ጥጃውን እቤት ማሰር ሆኖ ተተለም፡፡ በመነሻቸውና ላሚቱን በመግዛቱ ላይ ተስማሙ፡፡ በመዳረሻው መጨረሻ ጥጃውን በሚታሰርበት ቦታ ግን ስላልተስማሙ ጉርንቦ ለጉርንቦ እስተሚተናነቁ ድረስ ተጨቃጨቁ፡፡ ባልዮው የጎጇቸውን የግራ ጓዳ በጣቱ እየጠቆመ “እዚህ ጋ ነው የሚታሰረው ሲል” ሚስቲቱ እሬሳዬ በእንጨት ሳይወጣ ጥጃው እዚያ ጋ አይታሰርም የሚታሰረው በቀኝ በኩል ነው ብላ!” ሽንጧን ገትራ ትከራከራለች፡፡ ቤቱ የተቃጠለ የሚያስመስለው ይህ ጭቅጭቅ ለሳምንታት ዘለቀና ዘመድ አዝማድም ጎረቤትም ሰምቶት አረፈ፡፡ ይኸንን የሰሙ ዘመድ አዝማዶችና ጎረቤቶችም ሁለቱን ለሽምግልና አስቀምጠው “ገና ዘንቦ ተባርቆ በሚወለደው ጥጃ ተምትከራከሩ መጀመርያ እርሻውን እረሱና ገንዘብ አፍሩ” ብለው ድንጋይ ተሸክመው ሊያስታርቁ ቢለምኗቸውም እምቢ ብለው ጥጃው በሚታሰርበት ቦታ አይናቸውን እንደ ልቅ አንጎልጉለው ክርክሩን ቀጠሉ፡፡ ሽማግሌዎችም ቁርጥ አወቁና የራሳችሁ ጉዳይ ብለው ትተዋቸው ሄዱ፡፡ ባልና ሚስቲቱም እንኳን ላሚቱ ተገዝታ ጥጃው እስቲወለድ ሊቆዩ ገና መሬቱም ሳይታረስ ተፋተው ጉልበታቸውን ታቅፈውን ችጋር የሞላበትን የጎናዴ ኑሯቸውን ጀመሩ፡፡

እንደነዚህ ያልበሰሉ ጮርቃ ከንቱ ባልና ሚስት ሁሉ አንዳንድ ከንቱ ዲያስፖራዎች “መነሻችን አማራ መዳረሻችን ኢትዮጵያ ወይም መነሻችን አማራ መዳረሻችን አማራ” በሚል እንቶ ፈንቶ ክርክር ራሳቸው ተደናብረው ሌላውንም ለማደናበር ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እኝኝ ይላሉ፡፡

እኛ ታላላቆቹ የቤት ስራችን ስላልሰራን መቀመቅ ውስጥ የከተትነው ወጣት ፋኖ የህልውና ትግልን መርሁ አድርጎ ሆ ብሎ ተነስቶ በሚዋደቅበት ሰዓት ከንቱ ዲያስፖራ እንደነዚያ ጮርቃ ተጫጉላ የወጡ ሙሽራዎች በመዳረሻ አታካራና ግብግብ ስብሰባውንም የመገናኛ መድረኩንም ሲያውከው ይውላል፡ እሮጠው ያልጠገቡ ልጆች በእኛ ከንቱነት የደረሰባቸውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለመቋቋም በሚዋደቁበት ሰዓት እንደዚህ አይነቱን አታካራ በዲያስፖራ ማየት ካላሸማቀቀ ሌላ ምን የሚያሸማቅቅ ነገር በዓለም ላይ ይገኛል? ሁለተኛ ጥርሳቸውን ገና አብቅለው ያልጨረሱ ልጆች ሳይቀር “የምንታገለው ተምድር ላለመጥፋትና አገር አልባ ላለመሆን ነው” ብለው በአዋጅ እየተናገሩ “ፋኖ መርህ አልባ ነው!” ወይም “መዳራሻችን ይህ ነው! ያ ነው! ቅብጥሶ ጂኒጃንካ …” እያሉ መቀባጠርና ሥም ማጥፋት እሳት እንደነካው ላስቲክ ጭምትር አርጎ ታላሳፈረ ሌላ ምን ሊያሳፍር ነው፡፡

እነአቶኤችዲያስፖራዎችሆይ፡ “የህልውናና አገርን ያለማጣት ትግል” ከሚል መርህ የበለጠ ምን መርህ ተገኝቶ የፋኖን አላማ ራሱን አዙሮ በማያየው ህሊናዎ ያጣጥሉታል፡፡ ለመሆኑ ወጣቱ ከዚህ የዘር መጥፋት መከራ የደረስው በእርስዎ “በአማራነትን መደራጀት ራስን ዝቅ ማድረግ ነው ወይም መደራጀት ለአማራ አይመጥንም” በሚለው ጅላጅል ድስኩርዎ መሆኑን ራሱን የማይፈትሸው ህሊናዎ ረስቷል? በጥጃ ማሰሪያ ሥፍራ ፉክክር ትዳራቸውን አፈር ድሜ እንዳስጋጡት ጮርቃ ወጣቶች በመዳረሻ ፍሬከርስኪ የፋኖን ደጋፊ ዲያስፖራ እንደ አሻሮ ሲያምሱት ትንሽ ይሉኝታ ይሰማዎታል?

የትኛውም አገር ወይም ሕዝብ ራሱን በአገርነት ወይም በሕዝብነት ሲገነባና ሲያደራጅ መዳረሻዬ እዚያ ብቻ ነው ብሎ ወስኖ አያውቅም፡ ጥንታዊ ግሪኮች አገር ሲመሰርቱ ከብዙ ዓመታ በኋላ በታላቁ አሌክሳንደር መሪነት ዓለምን እንገዛለን ብለው መዳረሻ አልተለሙም፡፡ ለዚያ ያበቃቸው በየጊዜው ያዳበሩት ጥበባቸው፣ ስልጣኔአቸውና የገነቡት አንድነንት ነው፡፡ ጥንታዊ ሮማውያንም አገርን ሲመሰርቱና ሕዝባችውን ሲያደራጁ ዓለምን እንቆጣጠለን በሚለው መዳረሻ ተከራክረው አልነበረም፡፡ ለዚያ ያበቃቸው በየጊዜው የገነቡት ስልጣኔ፣ ጥበብና አንድነት ነው፡፡ የእኛም ቅድመ አያቶች በዘመኑ የነበረው ስልጣኔአቸው፣ ጥበባቸውና አንድነነታቸው በጠነጠነበት ዘመን በሰሜን እስከ እየሩሳሌም በደቡብ እንደ ማደጋስካር አገር ገንብተንው አስተዳድረዋል፡፡ በአውጫጭኝ ስደተኞች የተመሰረተው አሜሪካም ሲመሰረት አላማው ከእንግሊዝ አገዛዝ ለመላቀቅ እንጅ አሁን የደረሰበትን ሐያልነንት አቅዶ አልነበረም፡፡

እነመነሻችንእዚህመዳረሻችንእዚያ!” ቦራቂዎችሆይ! መዳረሻችሁን የሚውስነው በየ አዳራሹና በእየ ሕዝብ መገናኛው መድረክ የሚደነፋው አፋችሁ ሳይሆን እግዚአብሔር እንደ አያቶቹ ለፋኖ የሰጠው ቁርጠኝነት፣ ደፋርነት፣ ጥበብ፣ አንድነትና ክንድ ነው፡፡ ቁርጠኝነት፣ ደፋርነት፣ ጥበብ፣ አንድነትና ክንድ ሲገናኝ መዳረሻው ሰማይም የሚደርስ ነው፡፡ ለዚህ ደሞ ለማንም ያልገበሩትና አገራቸውን ያላስደፈርቱ ቅድመ አያቶቻችን ምስክሮች ናቸው፡፡ ስለዚህ ወጡን ሳትወጠውጡ ወስከንባዩን ለማሮጥ መለፍለፍ ራሳችሁን አደናብራችሁ ሌላውንም ግራ ማጋባት ነው፡፡ ይልቁንስ እውነት ዘራችሁ እንዳይጠፋና ለነጻነትና ለክብር ተቆርቋሪ ተሆናችሁ በመዳረሻ መጨቃጨቃችሁዉን ተውና የራሳችሁን ቁርጠኝነት፣ አሞትና ወኔ ፈትሹ፡፡ ፋኖ ባህርዳር ገባ ሲባል መቦረቁን ለስልት አፈገፈገ ሲባል ጅራታችሁን መወተፉን አቁሙ፡፡ በእውነትን ለራስ ነጻነት፣ ለክብር፣ ሰው ሆኖ ለመኖር፣ ለሕዝብ፣ ለአገርና ለፍትህ የሚታገል ሰው ሞቅ ሲል የሚገነፍል በረድ ሲል አፉን ተምግብ ተክሎ እንደ አሳማ መኖር የሚመርጥ መሆን የለበትም፡፡

ዲያስፖራሆይ! አገራችንን በተለያዬ መንገድ ጥለን ወጥተን በውጪ አገር የምኖር ሁሉ ወዶ ገብ ዘመናዊ ባርያዎች ነን፡ ባርነትማለት ማገልገል የምንፈልገውን ወይም ማገልገል የሚገባንንሕዝብትተንሌላውንለሆድ፣ለጥቅምወይምለመኖርስንልማገልገልነው፡፡ባርነት የሚለካው በሚከፈለን የገንዘብ መጠን ሳይሆን አገልግሎትን በምንሰጠው የሕብረተስብ ክፍል ዓይነት ነው፡፡ በውጪ አገር በመሀንዲስነት፣ በጠብቃነት፣ በሐኪምነት፣ በፋርማሲስትነት፣ በነስርስነት፣ በምጣኔ ሐብት ባለሙያነት፣ በመምህርነት ወዘተርፈ የምናገለግል ሁሉ ማገልገል የምንፈልገውን ወይም ማገልገል የሚገባንን ሕዝብ ትተን ለጥቅም ስንል ጌቶቻችንን የምናገለግል ልሙጥ ዘመናዊ ባሪያዎች ነው፡፡ ይኸንን የባርነት ትርጉም የማይገነዘብ ወይም የማይቀበል ባርያ ደግሞ የባሪያዎችም ባርያ ነው፡፡ ከዚህ ባርነት ራሳችንን ለማውጣት፣ ዘራችን በጭራቆች ተጠርቆ እንዳይጠፋና አገር አልባ እንዳንሆን ከፈለግን እንደ ቅንቡር በልቶ ማለፍን መጠየፍ መልካም ነው፡፡

ቁርጠኝነት፣ ደፋርነንት፣ ጥበብ፡ አንድነትና ክንድ በሚወስኑት መዳረሻ እንደነዚያ ያልበሰሉ ከንቱ ባልና ሚስት ነጋ ጠባ መጨቃጨዉን ትተን በሚከተሉት ጉዳይዎች ላይ ብናትኩር ጠቃሚ ነው፡፡ የአማራ ፍጅት የአካል፣ የሃይማኖት፣ የባህል፣ የቅርስ፣ የእውቀት፣ የታሪክና ሌሎች እሴቶች ስለሆነ ሁሉም የሚሳተፍበት የተወሳሰበ ቋሚና ዘላለማዊ የትግል ዘርፍ ይጠይቃል፡፡ ለመንደርደሪያ ያህልም፡-

. የእምነት ምሁራን “እግዚአብሔር ሰውን በአምሳሉ ፈጠረው ከሚለው ትምህት በተጨማሪ እግዚአብሔር ስውን በአምሳሉ ቢፈጥረውም ከተፈጠ በኃላ ሰይጣን ሊነጥቀውና ዘር አጥፊ ሊያደርገው ስለሚችል ከዘር አጥፊ ራስን መከላከል የሙሴ የኢያሱና የሌሎችም የእግዚአብሔር ሰዎች የቅድስና ተግባር መሆኑን ማስተማር

. መስቀል የተሸከሙ የሃይማኖት የአማራ ምሁራን መስቀል እንደ እስጢፋኖስ ያሉ ምሁራን የተሰውበት የመስዋአትነት ምልክት መሆኑን ማመንና ለመስቀሉ መገዛት

. ዲግሪ አለን የሚሉ ምሁራን ዲግሪቸውን የምግብ መጠቅጠቂያን መንደላቀቂያ ተማድረግ አሳማዊ ባህሪ ተላቀው የሕዝባቸውን እልቂት ለማየት አይናቸውንና ጆሮዋቸውን በመክፈት የሰላሳ አመቱን እልቂት በጥናትና በምርምር ለሕዝባቸውና ለዓለም ማሳወቅ

.ምሁራን ባዳበሩት እውቀት

ህ. አማራ አሁን ብቻ ሳይሆን ወደፊትም የሚደርስበትን ችግር ከወዲሁ በተለያዬ መንገድ በማስተማር ማንቃት

ለ. አማራ ራሱን ከአካላዊና መንፈሳዊ ዘር ፍጅት ለመከላከል የሚያስችል ጥኑ ድርጅታዊ መዋቅር መዘርጋት

ሐ. በአለፉት ሰላሳ ዓመታትም ሆነ አሁን በዘራቸው የተጨፈጨፉትን፣ የተፈናቀሉትን፣ የተሰደዱትን፣ የተጠለፉትን፣ ሆነ ተብሎ ዩንቨርስቲ እንዳይገቡ የተከለለሉትን በምስል፣ በሥም፣ በእድሜ፣ በፆታና በሌሎችም መስፈርቶች ያካተተ ማህደር ማጠናቀር

መ. በውጪም ሆነ በአገር ቤት ይኸንን ጭፍጨፋ የሚያስታውሱ ማስታውሻዎች መገንባት

ሠ. የአማራን ዘር ፍጅት ወይም የህልውና ተጋድሎ የሚዘክር በበላሙያ ጋዜጠኞች የሚመራ የሕዝብ መገናኛ (ራዲዮ፣ ቴሌቪዥን፣ ዌብ ሳይትና ሌሎችም) ማቋቛም፡፡ የትያትር ሰዎችም የምዕራባውያንን ግሳንግስ እየቀዱ ወጣቱን ማዘናጋቱን ትተው የዘር ማጥፋቱን የሚመመለከት ታሪካዊ ሥራ ሰርተው እንዲያልፉ መወትወት፡፡

ረ. በአማራ ዘር ጭፍጨፋ የተሳተፉትን አረመኔዎች አጣሪና መዝጋቢ ቡድን መገንባት

ሸ. በዘር ጭፍጨፋ የተሳተፉትን ሕግ ፊት የሚያቀርብ ቡድን ማቋቋም

ቀ. የአማራን የዘር ጭፍጨፋና የህልውና ተጋድሎ ለዓለም ሕዝብ የሚያሳውቅ የዲፕሎማሲ ተቋም ማቋቋም

፭. ሕዝቡ ምሁራን በመከተል

ሀ. እንኳን ሙሉ አካል ያለው የሌለውም እያንዳንዱ አማራ ዘሩ፣ ሃይማኖቱ፣ ባህሉ፣ ታሪኩና ቅርሱ እንዳይጠፋ የሚያበረክተው አስተዋፅዎ እንዳለ ማመን

ለ. ምሁራን የሚያቋቁማቸውን ቋሚ ተቋማት በጉልበት፣ በሐሳብና በገንዘብ መርዳት

ሐ. ተጎልቶ አንድም ሰው ጠፋ እኮ እያሉ ማጣወር ራስን አንደ ሰው አለምቁጠርና ራስን ሰው መሆን የማይችል የአንግዲህ ልጅ አድርጎ መቁጠር መሆኑን ማጤን፡፡ አባቶች ይሉት እንደነበረው ግፍ ሲበዛና ልብ ስትቆርጥ ማንም ጀግና ሊሆን አንደሚችልና ሜዳውም ሆነ ከተማው ወደ ጫካነት ሊቀየር አንደሚችል ማመን

መ. ጀግና ሲፈጠር በመቅቡጥ፣ በአድርባይነት፣ በባንዳነትና በፍርሃት አየተሽመደመዱ አሳልፎ አለመስጠት

ሠ. ጊዜው የቴክኖሎጅ ስለሆነ ሁሉም አማራ በምስል፣ በድምጥና በጽሑፍ የተደገፈ እውነተኛ መረጃ በመሰብሰብ ሥራ መሰማራት

ረ. ተመዋሸት፣ ተስንፍና፣ ተስርቆት፣ ተክህደት፣ ግፍ ተመስራትና ሌሎችም እርኩስ ሥራዎች ራስን መጠበቅ

ሰ. ተጅብ ተርፎ የሰነበተ ጥንብ የአህያ ሬሳ የባሰ የሚከረፋውን መንደርተኝነት የሚባል ደዌ አንድ ሺህ ሜትር ጉድጓድ ቆፍሮ እስከ ዓለም ፍጣሜ አንዳይነሳ አርጎ መቅበር

ሸ. ዳግመኛ የዘር ጭፍጨፋ ኢላማ ሆኖ ላለመገኘት በዓለት ላይ የተመሰረት ኃይል መገንባት የአማራ ምሁራንና የአማራ ሕዝብ ሆይ! እንደምታውቁት የአማራ ዘር ፍጅት ቁማር ከሰላሳ ዓመታት ወዲህ በግልጥ ይፈጠም አንጅ የተሸረበው ከአውሮጳውያን የቅኝ ግዛት ሽንፈት በኋላ ነው፡፡ የአማራ ዘር ፍጅት በአንድና በሁለት ትውልድ ብቻ ይቆማል ብሎ ማሰብ በጠራራ ፀሐይ ቅቤ በራሱ ተሸክሞ ተሄደው ማሞ ቂሎም ማነስ ነው፡፡

የአማራ የአካል፤ የሃይማኖት፤ የባህል፤ የቅርስ፤ የትምህርትና የታሪክ ዘር ፍጅት ከውጪም ከውስጥም ሥር ያለው ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ዘላለማዊ ሰይጣናዊ አቅድ ነው፡፡ የአማራ ምሁራንና ሕዝብም እንደ አያቶቻቸው አራት አይና ሆነውና ይኸንን ተገንዝበው የጥፋት ሴራውን የሚቋቋም ጥኑ ዘላለማዊ ተቋም መገንባት አለባቸው፡፡ ዘር መጥፋትን መከላከል ሰውነት ነው፤ ምሁርነት ነው፤ ቅድስናም ነው፡፡

አመሰግናለሁ፡፡

ተጨማሪ ጽሑፎች፡

1. A Message to Amara Elites: Never Allow Ethnic Cleansing of Amara Again! https://www.zehabesha.com/a-message-to-amara-elites-never-allow-ethnic-cleansing-of-amara-again/?fbclid=IwAR39-VVEyK9B3K4qyv40xVyKLFAQ4yQd3NZ5gdVLLEIf-OL3BW8pyuuTAWI
Please Stop Predisposing Amaras to Continue Perishing in Cities and Rural Areas!

Please Stop Predisposing Amaras to Continue Perishing in Cities and Rural Areas!


The Ethiopian Elites Have Failed to Follow The Principles of Our Forefathers! https://www.zehabesha.com/the-ethiopian-elites-have-failed-to-follow-the-principles-of-our-forefathers/?fbclid=IwAR2vDSOkwZ2-A8HUa-iajOYFrvb49Z2rdD62jLkfLA_T7p2V6vWcco9gEIk
4. በስልጣን ሰክሮ ያበደን ካድሬ ውይይትና ምክር ሊፈውሰው ይችላልን? https://welkait.com/?p=19399&fbclid=IwAR1PGGrvShRVdWUA5_-QmXlhonXcdrFDR-J6pIJv3LWBYPyRq9vwJLcWYYY

5. አማራ ሆይ! ምን እስኪሆን ነው የምትጠብቀው?
https://welkait.com/?p=17552&fbclid=IwAR1eqGmFZYQ_aO5tKOaJXsFZzW–Hi6PULfLQMJuSvh067CnTy-MMzFduuo

6. ጨቋኙ አማራ ይኸው ነው!
http://amharic.abbaymedia.info/archives/29664?fbclid=IwAR0e_LnjBSS5a32RXriIAS3_laU5kG-7WR3yaAZLzygplOiqXGeGFxecv54

7. አማራ ዳግም አትታለል እንደ ላሜ ቦራ!
https://welkait.com/?p=16336&fbclid=IwAR3TucrZU-L98xi7BHvmfy72coFWall47VWRKXYQs3OAlGT3_yttzFuqEns

8. ወጣት ሆይ! እደግ! ተመንደግ! – በላይነህ አባተ https://www.zehabesha.com/amharic/archives/94987?fbclid=IwAR16KT0YJujEAGRuw2Qum3Thw7GD6WvIp8TfLCXeETm6ptbZ2BRBzqJiL2g

9. ወጣት ሆይ! ለህልውናህም ሆነ ለክብርህ ወደ ባህልህ! http://ethioforum.org/amharic/%E1%8B%88%E1%8C%A3%E1%89%B5-%E1%88%86%E1%8B%AD-%E1%88%88%E1%88%85%E1%88%8D%E1%8B%8D%E1%8A%93%E1%88%85%E1%88%9D-%E1%88%86%E1%8A%90-%E1%88%88%E1%8A%AD%E1%89%A5%E1%88%AD%E1%88%85-%E1%8B%88%E1%8B%B0/?fbclid=IwAR0tsEDbDAQaE5BkeeJpzHCv3j30RxoxKtsV4ybfgBg8PTatn0eJmmIQSz0
10. አማራ ሆይ! ሰው እንሰሳም ነው! https://welkait.com/?p=19311&fbclid=IwAR15eJVKUJ_b6SBFd-Sz8_mJ4wDOCGfJ4a6gVy8HQJdTigeXypyWG7KTwSc
11. የአማራ ጨቋኙ አቀንቃኞች እምቢኝ አረፋውን ባህሪ! http://ethioforum.org/amharic/%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%88%9B%E1%88%AB-%E1%8C%A8%E1%89%8B%E1%8A%99-%E1%8A%A0%E1%89%80%E1%8A%95%E1%89%83%E1%8A%9E%E1%89%BD-%E1%8A%A5%E1%88%9D%E1%89%A2%E1%8A%9D-%E1%8A%A0%E1%88%A8%E1%8D%8B%E1%8B%8D/?fbclid=IwAR06hGmzfyvYp0pamjEv2M4Oo3U4k5Lh1ucqE_NFHVb1MGmMet2mr-YUpeU
12. አማራ ከጅብ መንጋጋ ተላቆ ከእስስት አፍ ገብቷል! (በላይነህ አባተ) https://www.satenaw.com/amharic/archives/64345?fbclid=IwAR186W_UWnfZoS9_NhCKQ6hRHdx-c_W7HT3r0oLNVu1fzZhmad9LwyAsndY
ለአባትዮውለገሰቦንድ ለልጁ ፓስተር አቢይ ፈንድ! https://welkait.com/?p=19088&fbclid=IwAR1mqyYRoNVg3ZCVPhEbSzxYZU3FGf1QH5siUhRwKdaKla-0Q6Ly4lKx7dY
ሕዝብእንዲሰማህሰፊ አፍ ይኑርህ! http://www.zehabesha.com/amharic/archives/94149?fbclid=IwAR0531t6KCkF-TywMIFjVmqx-jZyabuh_Ourw5vqSlrFVACc8DH6ROXJgA8
15. በአማራ ሰማእታት የተፈጠመው ግፍ በቅዱሳን ሐዋርያት ከተፈጠመው ግፍ ይከፋል! (በላይነህ አባተ)
https://www.satenaw.com/amharic/archives/63706?fbclid=IwAR1Jz8X8rmn5Sxgbt9b-r_7VJ5P6stU0n79czhwp83hq9kB19i5_hiBhDRc
16. ይሁዳ ክርስቶስን በሰላሳ ዲናር ሸጠው! (በላይነህ አባተ )
https://www.satenaw.com/amharic/archives/61148?fbclid=IwAR2x5wsTnwsME1ckDTJJfBg1VI_TgjoH0Wvba8dq_PjEyqkEcm32hq2cu5I
17. Urgent Message to Amara Elites: Speak Up Against The Ethnic Cleansing of Amara!

Urgent Message to Amara Elites: Speak Up Against The Ethnic Cleansing of Amara!

መጋቢት ሁለት ሺ አስራ ስድስት ዓ.ም.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop