In the early 1970s, a growing student movement sought to overthrow the Ethiopian Emperor Haile Selassie and usher in democratic rule. The emperor was instead replaced by a military dictatorship. (Submitted by Tamara Mariam Dawit)

የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ እና የ1966ቱ ሕዝባዊ አብዮት (ክፍል -፩-)

In the early 1970s, a growing student movement sought to overthrow the Ethiopian Emperor Haile Selassie and usher in democratic rule. The emperor was instead replaced by a military dictatorship. (Submitted by Tamara Mariam Dawit)
እ.ኤ.አ. በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ የኢትዮጵያን ንጉሠ ነገሥት ኃይለ ሥላሴን ከሥልጣን ለማውረድ እና ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ለማምጣት የተማሪዎች እንቅስቃሴ እያደገ መጣ። በምትኩ ንጉሠ ነገሥቱ በወታደራዊ አምባገነንነት ተተኩ። ( ታምራት ማርያም ዳዊት አቅርቧል)

በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን)

(ይህ ጽሑፍ ማስታወሻነቱ፤ በቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን መስሪያ ቤት የማይዳሰሱ ቅርሶች /Intangible Heritage/ ከፍተኛ ኤክስፐርት፤ የኢትዮጵያና አፍሪካ ታሪክ ተመራማሪ፣ ተቆርቋሪ ለነበረው ለወዳጄ፤ ለነፍሰ ኄር አቶ ኃ/መለኮት አግዘው እና በቅርቡ በሞት ለተለየን፤ ‹ለታሪክ አዋቂውና ለታሪክ ነጋሪው› ለነፍሰ ኄር፣ ገነነ መኩሪያ/ሊብሮ ይሁንልኝ)፡፡

Walelign Mekonnen (left) and his brother Getachew Mekonnen 1967
ዋለልኝ መኮንን (በግራ) እና ወንድሙ ጌታቸው መኮንን

 

‹‹… ይኸው ትታያለች ለሕዝብ በይፋ፣
ጥቁር ተከናንባ ጥቁር ተጎናጽፋ፡፡
እኔስ መስሎኝ ነበር ዘመድ የሞተባት፣
የእናት ሞት የአባት ሞት፣
የልጅ ሞት ያጠቃት፣
ለካ እሷስ ኖራለች ዘመን የሞተባት…!!››

Birhanmeskel reda,walelegne, Getachew maru and Martha Mebratu- all mrtyers.

(አንጋፋው ፖለቲከኛ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር፣ አዛውንቱ ዶክተር ኃይሉ አርዓያ- በዛን ጊዜው የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ/የአሁኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ በነበሩበት በ1950ዎቹ ስለኢትዮጵያ ከቋጠሩት ስንኝ/እንጉርጉሮ የተወሰደ፤)

በዘንድሮው፣ በያዝነው ወርኻ የካቲት የ1966ቱ የኢትዮጵያ፣ ሕዝባዊ አብዮት ከፈነዳ 50ኛ ዓመቱን ይደፍናል፡፡ ይህን ተከትሎም አንዳንድ ሰዎች፤ ‹‹ይህ ሕዝባዊ የኾነ የኢትዮጵያ አብዮት ተገቢው ታሪካዊ ስፍራና ክብር ተሰጥቶት በቅጡ ሊዘከር፣ ሊታሰብ ይገባዋል እኮ…?!፤›› የሚል እንድምታ ያለው አሳብ እዚህም እዚያም ሲነሳ ታዝቤያለሁ፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ የፖለቲካ ሳይንስና የዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ፣ ዮናስ አሽኔ (ዶ/ር)፤ የዚህ የ66ቱ፣ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮት በቅጡ ለማሰብና ለመዘከር እምብዛም እንቅስቃሴ ባለማስተዋሉ ነገርዬው አብከንክኖት ይመስላል፤ በአማርኛው ቢቢሲ ድረ-ገጽ ላይ፤ ‹‹የኢትዮጵያ አብዮት 50ኛ ዓመት ኢዮቤልዩ በዓልን የመዘከር ፋይዳ›› በሚል አርእስት ቁጭት አዘል ሰፋ ያለ ጽሑፉን አስነብቦናል፡፡

የአብዮቱ ጉዞ ፍጻሜ ምንም ይሁን ምንም ይህ አብዮት በአገራችን ትልቅ የኾነ የታሪክ ምዕራፍን የከፈተ፣ ከፍተኛ የኾነ ሕዝባዊ መሠረት የነበረው፣ የብዙ እልፍ ወገኖቻችንን እንባ፣ ላብና ደም ያስገበረ አገር አቀፍና ስር ነቀል የለውጥ እንቅስቃሴ መሠረት፤ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ የታሪክ አካል ስለኾነ በቅጡ ሊዘከር፤ ሊታወስ ይገባዋል፤ የሚል የመከራከሪያ አሳቦችን በጥቂቱም ቢሆን ሲዘዋወር እያስተዋልን ነው፡፡

Students protest in Addis Ababa, Ethiopia, September 17, 1974, against the military committee that seized political power last week. Photograph: AP
ባለፈው ሳምንት የፖለቲካ ስልጣን የተቆጣጠረውን ወታደራዊ ኮሚቴ በመቃወም በአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፣ መስከረም 17 ቀን 1974 ተማሪዎች ተቃውሞ አሰሙ። ፎቶ፡ ኤፒ

ከ10 ዓመታት በፊት የ1966ቱ አብዮት 40ኛ ዓመትን አስመልከቶ ይህ ሕዝባዊ አብዮት በተለያዩ ዝግጅቶች መዘከር ወይም መከበር እንደሚገባው ይሟገቱ የነበሩ ሰዎችንና ጸሐፊዎችን አስታውሳለሁ፡፡ እንዲሁም በማኅበረሰብ ድረ-ገጾች ይህንኑ የኢትዮጵያ አብዮት ለመዘከር አንዳንድ ሰዎች አዲስ ድረ-ገጽን ያስተዋወቁም ነበሩ፡፡

እነኚህን ሰዎችና ሐሳባቸውን የደገፉ ሌሎችም ይህን ገጽ በመቀላቀል፣ በማስተዋወቅና እንዲሁም የ1966ቱ አብዮት በተመለከተ በእጃቸው የሚገኙትን ማንኛቸውንም ዓይነት የጽሑፍ፣ የምስል፣ የኦዲዮና የቪዲዮ መረጃዎችን በመለጠፍና በመለዋወጥ ፈቃደኛ መሆናቸውን ከመግለጽም ባሻገር፤ ስለዚሁ ሕዝባዊ አብዮት ያለንን እውቀትና መረጃ ከፍ ለማድረግ በማሰብ ይህን ገጽ መክፈታቸውን በስፋት አስነብበውን ነበር፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከፓርላማዊ ዲሞክራሲ ወደ ፕሬዚደንታዊ ዲሞክራሲ . . . . ለምን? እንዴት? በማን ውሳኔ?

እንደ ታሪክ ተማሪነቴም እንዲህ ዓይነቱ እንቅስቃሴ፤ ይህ ትውልድ የትናንትናው ትውልድ ለውድ አገሩና ለወገኑ ስለነበረው ተቆርቋሪነት፣ ሕልምና ርእዩ፣ ብሩሕ ተስፋው፣ ስለከፈለው መሥዋዕትነት፣ ስለ መንፈስ ጽናቱና ብርቱ ተጋድሎው፣ ስለ ጀብደኝነቱና ቆራጥነቱ፣ ስለ አንድነቱና ልዩነቱ፣ ስለልማቱና ጥፋቱ፣ ስለሕይወት ፍልስፍናው፣ ርዕዮተ ዓለሙና እምነቱ፣ ስለ ተጓዘበት ረጅምና ውስብስብ የታሪክ ጉዞው.. ወዘተ. በሚገባ ለማወቅ መልካም አጋጣሚን እንደሚፈጥር ብዙዎችን ያስማማል ብዬ አምናለሁ፡፡

እናም ያገባናል፣ የታሪኩ አካል ነን የሚሉ ሁሉ አብዮቱንና የትናንትናውን ትውልድ በተመለከተ የዛሬው ትውልድ በሚገባ የሚያውቅበትና በሰከነና በረጋ መንፈስ፣ በቅንነት፣ በጨዋነት የሚወያይበት የተለያዩ መድረኮች ደግመው፤ ደጋግመው ቢያዘጋጁ በግሌ መልካምና የሚገባም ነው እላለኹ፡፡ የምክክር ኮሚሽኑም በሀገራችን ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ የ66ቱ ሕዝባዊ አብዮት ካለው ትልቅ ስፍራ አንፃር ይህን የ66ቱን አብዮትና ተያያዥ ጉዳዮችን በትልቁ ከግምት ውስጥ እንደሚያስገባው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

 

የ‹‹ያ ትውልድ›› የታሪክ ማስታወሻዎች

ባለፉት ሠላሳና ዐርባ ዓመታት ውስጥ፤ የዛን ትውልድ ትግልና አብዮታዊ እንቅስቃሴ በተመለከተ የዛ ትውልድ አባላት ለመጻፍ ሞክረዋል፡፡ የኢሕአፓው ክፍሉ ታደሰ፤ ‹‹ያ ትውልድ›› ቅጾች፤ የአንዳርጋቸው አሰግድ፤ ‹‹የመኢሶን ታሪክ በአጭር የተቀጨው ረጅሙ ጉዞ››፣ የሕይወት ተፈራ፤ ‹‹ታወር ኢን ዘ ሰካይ››፤ የአምባሳደር ታደለች፤ ‹‹ዳኛው ማነው››፤ የባቢሌ ቶላ፤ ‹‹ቱ ኪል ዘ ጄኔሬሽን/የትውልድ እልቂት››፤ በሚል ርእስ ያስነበቡን መጻሕፍት በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

እንዲሁም በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የሚገኙ የዛ ትውልድ አባላት ምሁራንም በዩኒቨርስቲዎች፣ በበርካታ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችና የውይይት መድረኮች ላይ፤ የኢትዮጵያ ተማሪዎችን እንቅስቃሴንና ያን ተከትሎም ስለተከሰተው የ66ቱ ሕዝባዊ አብዮት በርካታ የጥናት ወረቀቶችን አቅርበዋል፡፡

እንደእነ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ፕ/ር አንድርያስ እሸቴ፣ ዶ/ር ኃይሉ አርዓያ፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፣ ተሻለ ጥበቡ (ዶ/ር)፣ ገብሩ ታረቀኝ (ዶ/ር)፣ ኢንጀነር ኃይሉ ሻውልን የመሳሰሉ ምሁራንና ፖለቲከኞች የተማሪውን እንቅስቃሴና ይህንንም ተከትሎ ስለተከሰተው የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮት ያለንን መረጃና ዕውቀት ሊያሰፋ የሚችል የራሳቸውን የኾነ ከፍተኛ የሆነ ምሁራዊ አስተዋፅዖ አድርገዋል ማለት ይቻል ይመስለኛል፡፡

በተጨማሪም፤ ‹‹ከፈረሱ አፍ›› እንዲሉ፤ የደርጉ ዋና ሊቀመንበርና የኢሕዲሪ ፕሬዚደንት የነበሩት ጓድ፣ ኮ/ል መንግሥቱ ኃ/ማርያም፤ ‹‹ትግላችን፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ የትግል ታሪክ››፤ ቅጽ. 1 እና 2 መጻሕፍት፤ የደርግ አባልና በወቅቱ የአብዮታዊት ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚ/ር የነበሩት ሻምበል፣ ፍቅረ ሥላሴ ወግደረስ፤ ‹‹እኛና አብዮቱ››፤ የጓድ/የአቶ ፋሲካ ሲደልል፤ ‹‹የሻምላው ትውልድ›› በሚል ርእስ ለንባብ ያበቋቸው መጻሓፍትም- ታላቅ ሕዝባዊ መሠረት ስለነበረው ስለ 1966ቱ ሕዝባዊ አብዮት ለዛሬውና ለመጪው ትውልድ ሰፊና ጥልቅ የሆነ መረጃን የሚሰጡን ናቸው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  “አደፍርስ ! ካልደፈረሰ አይጠራምና” መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

የእርስ በርስ መወቃቀሱና መፈራረጁ ማብቂያው መቼ ይሆን…?!

ተነሳ ተራመድ ክንድህን አበርታ፤

ለሀገር ብልጽግና ለወገን መከታ፡፡››

(በዘመኑ ይዘመሩ ከነበሩ አብዮታዊ/ሕዝባዊ መዝሙሮች አንዱ)

በእርግጥ በአብዛኛው ስለትናንትናው አብዮተኛ ትውልድ ሲነሳ በአንዳንዶች ዘንድ ጎልቶ የሚሰማው አፍራሽነቱ፣ የጥላቻና የእርግማን ድምፅ ነው፡፡

በአንጻሩም ደግሞ፤ የትናንትናው ትውልድ አባላቶችም፤

‹‹… ይህ ወኔ ቢስ ትውልድ›› በምን ሂሳብ ነው ያን ተራራ፣ ቁልቁለትና ዳገት ሳይበግረው፣ የመከራ ውርጅብኝና ናዳ ወኔውን ሳያላላው፣ ረሃቡና ጥሙ፣ ስደትና መንገላታቱ ሳይፈታው፣ የአምባ ገነኖች ጭካኔና ‹የቀይ ሽብር ይፋፋምብን!› ዘግናኝ እልቂትና የጠራራ ፀሐይ ነፃ ርምጃ ቅንጣት ሳያስፈራው፣ ከሞት ጋር ፊት ለፊት እየተጋፈጠ፣ እንባውን፣ ላቡንና ደሙን ለአገሩና ለወገኑ የከፈለን፣ ያን ለነፍሱ እንኳን ያልሳሳውን ‹ተራራን ያንቀጠቀጠ› ጀግና ትውልድ በጎሪጥ ለማየት፣ ለመተቸትና ለመውቀስ ምን የሞራል ብቃት አለው፤ እንደምንስ ይህን ለማለት ይደፍራል?!›› የሚል ድምፅ አብዝቶ ይሰማል፡፡

‹የጥላቻና የመጠፋፋት ፖለቲካ› በእጅጉ የሰለቸውና ያማረረው የዛሬው የእኔ ትውልድም፤

‹‹እናንተና ትውልዳችሁ ምን አተረፋችሁልን? ከእልቂትና ከመከራ በስተቀር፣ ምድሪቱን የደም ምድር/አኬልዳማ፣ የእልቂትና የራብ ምድር የሚል ቅፅል እንድትጎናጸፍ ከማድረግ ባሻገር… ዛሬ እንኳን በሽምግልናችሁ ዘመን ‹ለይቅርታና ለዕርቅ› ልባችሁ ገና እንዳልተከፈተ ነው በአደባባይ እሳያችሁን ያለው፡፡ ዛሬም ከነጋሪታችሁ የሚሰማው ‹የበቀል፣ የጥላቻ፣ የፅንፈኝነትና የመለያያት ድምፅ› እንጂ ‹የሰላምና ዕርቅ ድምፅ› አይደለም…፤›› ሲል በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ዛሬም እጃቸው ረጅም የሆኑትን የዛን ትውልድ አባላቶች በብርቱ ይወቅሳል፤ ይኮንናል፡፡

ለዚህ እጅግ በመረረ ስሜት፣ ምሬትና ቁጭት ትውልዱ ለሚሰነዝረው ትችትና ወቀሳም የትናንትናው ትውልድ አባላቶች ምላሻቸው በአብዛኛው ‹‹ታሪክን የማያውቅ፣ ውለታ ቢስ፣ ምስጋና የለሽ ትውልድ›› በሚል ቁጣና ኃይለ ቃል የተቀላቀለበት እንደሆነ ነው በተደጋጋሚ የተስተዋለው፡፡

ዛሬም የትናንትናው አንጋፋ ትውልድ የዛሬውን ትውልድ ‹‹የመከነ ዘር፣ የጨነገፍ፣ ከንቱና የባከነ ትውልድ›› የሚል አንድምታ ካለው ምሬትና ቁጭት የተላቀቁ አይመስሉም፡፡ እናም በነጋ ጠባ በትውልዱ ላይ ያላቸው ምሬታቸውና ብሶታቸው ነው ጎልቶና አይሎ የሚሰማው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የነዳንኤል ክብረትና የኔ - ሁለት አቢይ አህመዶች! - ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

በአንፃሩ ቁጭትና እልህ በሚያንገበግባቸው በሌሎች በትናንትናው ትውልድ አባሎች ዘንድ ደግሞ፤

‹‹ለፍሬ ይሆናል ያልነው የደከምንበት ዘራችን ዋግ፣ ኩብኩባና ተምች መታው፤ ተስፋ ያደረግነው ቡቃያችን በአረምና በአርማሞ ተውጦ፣ በእሾህ ታንቆ ከንቱ ሆነ… መና ቀረብን…›› የሚሉና በዘሩት ዘር መምከን፣ በትውልዱ መጨንገፍ/መክሸፍ ነጋ ጠባ የኀዘን፣ ቁጭትና የእሮሮ ድምፃቸውን ሲያሰሙ ይደመጣሉ፡፡

በአንፃሩም ደግሞ የዛሬው ትውልድ ለአባቶቹ ወቀሳም ሆነ ምሬትና ቁጭት የራሱን መልስ እንካችሁ ከማለት ወደኋላ አላለም፡፡ ዘርታችሁ ያበቀላችሁን እናንተው ናችሁ፤ መቼም ‹‹ያልዘሩት አይበቅልምና›› ዘራችሁ መልካም በሆነ እኛም መልካም በሆንን ነበር፡፡ ‹‹ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮኻል›› አሉ በሚል አገሪኛ ብሒል ለአባቶቹ ወቀሳና ምሬት ዋጋ ቢስነትንና ከንቱነት ላይ በመሳለቅ ዛሬም ድረስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መልስ ከመስጠት አልደከመም፣ አልቦዘነምም፡፡

የበእውቀቱ ስዩም፣ ‹‹ኗሪ አልባ ጎጆዎች›› የምትለው ግጥሙ የተሰደሩ ስንኞች  በትናንትናውና በዛሬው ትውልድ መካከል ያለውን ይኸውን ሙግት የምታጎላ ሳትሆን አትቀርም፡፡

‹ኗሪ አልባ ጎጆዎች›

‹‹አያቶች!

በባዶ መስክ ተመራምረው

ጥበባቸውን

ዕድሜያቸውን

ገብረው

የጎጆ ንድፍ ሲያበጁ

አረጁ

ዘመናቸውን ፈጁ

አባቶች!

መላ ዘመናቸውን

ጎጆ በመቀለስ አሳለፉ

ሳይኖሩት አለፉ

ልጆች!

ጎጆውን ለመውረስ ሳይከጅሉ

እንዲህ አሉ

ያ’ባቶቻችን ጎጆ

ይኹን ባዶ ይኹን ኦና

በ’ኛ ቁመት

በ’ኛ መጠን

አልተቀለሰምና፡፡››

ይሄ የትናንትናውን ትውልድ ተጋድሎና ሕዝባዊ መሠረት ነበረውን የ1966ቱን አብዮት ክስተት 50ኛ ዓመቱን አስመልክቶ ‹ከታሪካችን ማስታወሻ› በመጠኑ ለመፈተሽ የሚሞክረው ይህ ጽሑፍ ዋንኛ ዓላማ አድርጎ የተነሳው ከትናንትና ታሪካችን እርስ በርስ እንድንማማርና የዛሬው ትውልድ ከትናንትናው ትውልድ ከዛሬው ትውልድ ጋር መማር የሚችልበት መድረክ ሊመቻች ቢችል በሚል ቅን ምኞት ነው፡፡ ‹‹ታሪክ የትውልድ መገናኛ ድልድይ ነው፤›› እንዲሉ የታሪክ ሊቃውንቱ፡፡

በቀጣይ ጽሑፌ የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴንና የ1966ቱን ኢትዮጵያን ሕዝባዊ አብዮት በተከታታይ በአጭሩ ለመዳሰስ እሞክራለሁ፡፡

(ጸሐፊው ተረፈ ወርቁ (ዲ/ን)፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ፤ በደቡብና በምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ዋና ጸሐፊ ሆነው ያገለገሉ ሲሆኑ፤ በአሁን ሰዓት ደግሞ በጥናትና ምርምር ዘርፍ ከፍተኛ ተመራማሪ/ሪሰርቸር፤ የታሪክና የቅርስ አስተዳደር ባለሙያ ናቸው፤ እንዲሁም Universal Peace Federation/UPF የሰላም አምባሳደር ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ፤ የሪፖርተር ጋዜጣ የረዥም ጊዜ ጸሐፊና ደንበኛ ናቸው)፡፡

 

 

7 Comments

 1. እንደው በድፍረት ሌላውን ለመተንኮስ በሚል መልኩ ደህና ነገር እንደሰራ ሁሉ ያ ትውልድ በሚል አርእስት አስታውሱት ተብሎ እንዲህ ያለ ነገር ይልኩልናል? እኛ ከአእምሯችን ለማሸሽ እነሱ ዳግም ለመትከል ግብግብ ይዘዋል። አረ ተውን የናንተን ነገር። በቅርቡ እንኳን አብዩ ብርሌ የተባለው አባላችሁ ከአንድ ሻቢያ ጋር ቀርቦ በነበረው ውይይት ሻቢያው ኢትዮጵያዊ እስኪመስል አብዩ ግን ከኢሳይያስ በልጦ ነበር የተገኘው እንዲህ ነው የዛ ትውልድ ነገር። ኢትዮጵያ መልሳ ስትቋቋም እንደ እናንተ አይነት ታሪክ አጣማሚዎች ለፍርድ ትቀርባላችሁ የሚል እምነት አለን። አገርን ባናቱ ተክላችሁ አብሮ የሚኖረውን ህዝብ አበጣብጣችሁ፣ ያልገባችሁን ርዮት ህዝብ ላይ ጭናችሁ፣ ገንጣይ አስገንጣይ ሁናችሁ ዛሬም ተበዳይና የሀገር አሳቢ ሁናችሁ ቀርባችሗል በሰራችሁት ስህተት አንድም ጊዜ ስትጸጸቱ አትታዩም። የምን የህዝብ አብዮት ነው የምታወሩት? ዩኒቨርስቲ ውስጥ ሻቢያና ምእራብ መር ተንኮል በአማራ ጥላቻ ተጎነጎነ የዩኒቨርስቲውን ያን ትውልድ ጫኑት፣ ለአቅመ ማሰብ ያልደረሰውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርት ይዘጋልሀል ረብሽ አላችሁት፣ አገር ባናት ተከተለ አገሩ የጨረባ ተዝካር ሆነ ዛሬም ከዛ አዙሪት አልተወጣም። የታገላችሁለት ሻቢያ አገር ይዞ ወጣ ትግሬ እየተንደረደረ ነው አገር ለመሆን ፣ ኦሮሞም በስልጣንንላይ በመሆኑ ነው እንጅ ምቾቱ ሲቀንስ ተገንጣይ ነው። አንዳንድ ምሁራኖቻችሁ በህይወት የተረፉት ባስተሳሰብ የተጎዳውን ጀሌ ግፋ በለው ብለው እነሱ ላይብሬሪ መሽገው ነው። ያ ባይሆን በህይወት አይተርፉም ነበር። አሁን ማን ያምናል ዋለልኝና ኢህአፓ በዚህ መልኩ ታሪክ ይዘከርለት ሀውልት ይቁምለት አይነት ድፍረት ይነገራል ተብሎ? አዎ ከላይ በስም የጠቀስካቸው ሁሉ በስም ይለያዩ እንጅ በተግባር አንድ ናቸው መለሰ ዘራዊንና ስብሀት ነጋን አይነቶች ዘለልካቸው እንጅ። እንዲህ ያለ ጽሁፍ ብትችሉ በራሳችሁ መጽሄት አንባቢ ካገኛችሁ በመጽሀፍ አትሙት እንጅ ወደዚህ አትምጡብን።

  • ተባረክ የሚታፈርበት እንጂ የሚኮራበት ትውልድ አይደለም:: ውጤቱ እኮ በእደባባይ አሁን ይታያል:: የሚያሳዝነው የበለጠ ጨካኝ የዐቢይ የአረመኔ ዘመን ተካው ምስኪን ሀገርና ህዝብ

 2. The Stalinist inclination of the writer is seen when he shamelessly inserts this suggestion.

  ” የምክክር ኮሚሽኑም በሀገራችን ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ የ66ቱ ሕዝባዊ አብዮት ካለው ትልቅ ስፍራ አንፃር ይህን የ66ቱን አብዮትና ተያያዥ ጉዳዮችን በትልቁ ከግምት ውስጥ እንደሚያስገባው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡”

  What Commision? The same one that Abiy Ahmed composed ahead of time so when he is done with his project genocide he could be absolved of all his crime and sins in the style of Rwanda and South Africa? That commission is constituted with avowed Stalinists including hand-picked OLF veteran Zegeye Asfaw. Yeah Zegeye Asfaw a decorated and stellar member of the sixties generation. You want this generation to once again determine the fate of Ethiopia? You must be a very cruel person.
  Abiy Ahmed is dreaming to have the fate of Kagame, who despite initiating the Rwanda Genocide on behalf of US mining interests, conducted a fake “Truth and Reconciliation’ drama and managed to stay in power for three decades.

  What the generation accomplished was to undermine Ethiopian from within, paving the way for the dismantling of the monarchy, the weakening of the church and the destruction of the military leadership. The likes of Walelign parroted what was handed to them by secessionist Jebha, itself an agent of colonial and neocolonial forces.
  Once the fragmentation of Ethiopia is achieved, the political movements initiated by foreign agents in the sixties would have accomplished all they set out to do.
  One thing that the sixties movement is not is an organic, home-grown patriotic movement of Ethiopia. It was alien in its ideology, alien in its modus operandi and alien in the culture it introduced into this ancient land.
  The generation of Ethiopians that was politicized in the sixties, directly jumped from a decadent life of western worship and partying to one of celebrating the leftist world and revolution overnight.
  Our nation is still reeling from the mortal blow dealt by that generation. Still, the blame is on the system that produced that generation – the system that divorced it from its foundational culture and knowledge base.

  Yes it is very valuable to record and reminisce on history. But with honesty. It fails to be history when you are using it to yet cause another damage.

  If the writer is of religious background, then maybe he should tell us about the magnitude of the devastation the hijacked generation brought on the spiritual life of our spiritual nation.

 3. ከላይ የተሠጡትን ሁለት አስተያየቶች አነበብኩና፤ ጸሐፊው ምንኛ ትክክል እንደሆነ ገባኝ። የእውቀት መሠረቱ፤ የምፈልጉትን ወይንም ግለሰቡን ደስ የሚያሰኘውን ብቻ መርጦ መስማት ማለት አይደለም። የነበረውን ከተለያዩ ምንጮች መረዳትና፤ ትክክለኛ ኝዛቤ መውሰድ ነው። በርግጥ ሁሉም አንባቢ ተመሳሳይ መደምደሚያ ላይ ይደርሳል የሚል ቅዠት የለኝም። ነገር ግን፤ የተለያዩ ግንዛቤዎች እንዳሉ መረዳት ግደኢታ ነው። አለያማ መቼ አሁን ለደረሰንበት እንበቃ ነበር። ጸሐፊው ገና መጀመሩ ነው። እኔ የምወደውን ላያቀርብ ይችላል። ለመማር ግን ዝግጁ ነኝ። ስላለፈው ትውልድ ስንጽፍና ስንናገር፤ ይሄ ትውልድ በተመሳሳይ ሁኔታ እየራመደ መሆኑን መዘንጋት አይገባም። ያኔ በዳይና ተበዳይ እንደነበሩ ሁሉ፤ ዛሬም በዳይና ተበዳይ አሉ። ያኔ ለሕዝብ ብለስ ሕይወታቸውን የገበሩ እንደነበሩ ሁሉ፤ ዛሬም አሉ። ሕይወት ቀጣፊዎችም የየትውልዳቸው አባል እንደነበሩ መዘንጋት አይገባም። ያኔ ኢሕአፓን ለመውቀስ ያሰበ። ዛሬ ዐብን ምን አያደረገ እንደሆነ ማሰብ ይገባዋል። የዐብን ጥቂት አመራር የዐማራን እንቅስቃሴ ክደው ለብልፅግና አንዳደሩ ማሰብ ይገባል። ያ ደግሞ መላ የዐብን ደጋፊዎችን ከሃዲ አያደርጋቸውም። ከሁለት አንጻር አንባቢ እንዲመለከት እፈልጋለሁ። አንደኛ፤ ያን ጊዜ ምን እንደነበር መረዳት አልሰሚያስፈልግ፤ ከሁሉም አቅጣጫ የነበረውን እንረዳ። ለፍርድም የሚያመቸው፤ ሁኔታውን ከሁሉም አቅጣጫ ስንረዳው ነው። ሁለተኛ ደግሞ፤ ከዚያ ወዲህ ለተከሰተው ሂደት ትክክለኛውን ተጠያቂ ክፍል ማወቅ አስፈላጊ በመሆኑ ነው። ተማሪዎች ሥልጣን ይዘው ሰው አልገደሉም። የራሳቸውን የፖለቲካ አስተሳሰብ ለመተግበር መንግሥታዊ ሥልጣን አልነበራቸውም። በሃሳብ ደረጃ የፈለጉትን ቢሉ፤ መጥፎ አያደርጋቸውም። ሥልጣን ይዞ አገራችንን ለዚህ ያበቃትን ክፍል ለይቶ ማወቅና ያንን ለፍርድ እንዲቀርብ ማድረግ ተገቢ ነው። እንዲያው ይሄን ወይንም ያንን ዓይነት አመለካከት አለውና ይወቀስ ማለት ተገቢ አይደለም። በርግጥ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ነኝ ባዩ ድርጅት ያገራችንን የፖለቲካ መድረክ ስላመሰቃቀለውና ተማሪዎች ባላሰቡት መንገድ ወስዶ ፍዳ ስለስከተለብን፤ ያንን ወገን የተማሪዎች ትግል አካል አድርጎ መውሰድና በዚያ ላአይ ፍርድ መጣል፤ ይጎዳል። የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር አነሳስ፣ አድገትና ለሥልጣን መብቃት፤ ከአፄ ሚኒሊክ ጊዜ ጀምሮ ሲብጠለጠል የነበርና በኃይለ ሥላሴ ጉግሳ፣ በመለስ ዜናዊ አባት ባንዳው አስረስ ተላልፎ፤ የትግራይ ተበደለች ትርክት መሆኑን አንዘንጋ! በኦነግም ቢሆን የቆዬ በራሱ ትርክት የሄደ ነው። ሁለቱን ከተማሪው ትግል ጋር አይተሳሰሩም። የሚያገናኛቸው ቢኖር ጥቂት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከመሪዎቻቸው መካከል መገኘታቸው ብቻ ነው። ዛሬም ከመሪዎች ጋር የሚያቆልበው ወጣት የዛሬው ትውልድ አካል ነው። በያንዳንዳ ትውልድ፤ በጎና በጎ ያልሆኑ ክንውኖችን ያስተናገዱ ግለሰቦች አሉ። ያንን መረዳት ያስፈልጋል። ከሁሉ በላይ ያለፈን ለመማሪያ ስናገናዝብ፤ መርጥዕን አይደለም። ሁሉንም ነው።

 4. የተስተካከለ፤
  ከላይ የተሠጡትን ሁለት አስተያየቶች አነበብኩና፤ ጸሐፊው ምንኛ ትክክል እንደሆነ ገባኝ። የእውቀት መሠረቱ፤ የሚፈልጉትን ወይንም ግለሰቡን ደስ የሚያሰኘውን ብቻ መርጦ መስማት ማለት አይደለም። የነበረውን ከተለያዩ ምንጮች መረዳትና፤ ትክክለኛ ግንዛቤ መውሰድ ነው። በርግጥ ሁሉም አንባቢ ተመሳሳይ መደምደሚያ ላይ ይደርሳል የሚል ቅዠት የለኝም። ነገር ግን፤ የተለያዩ ግንዛቤዎች እንዳሉ መረዳት ግዴታ ነው። አለያማ መቼ አሁን ለደረሰንበት እንበቃ ነበር። ጸሐፊው ገና መጀመሩ ነው። እኔ የምወደውን ላያቀርብ ይችላል። ለመማር ግን ዝግጁ ነኝ። ስላለፈው ትውልድ ስንጽፍና ስንናገር፤ ይሄ ትውልድ በተመሳሳይ ሁኔታ እየተራመደ መሆኑን መዘንጋት አይገባም። ያኔ በዚያ ትውልድ በዳይና ተበዳይ እንደነበሩ ሁሉ፤ ዛሬም በዳይና ተበዳይ አሉ። ያኔ ለሕዝብ ብለው ሕይወታቸውን የገበሩ እንደነበሩ ሁሉ፤ ዛሬም አሉ። ሕይወት የቀጠፉም የየትውልዳቸው አባል እንደነበሩ መዘንጋት አይገባም። ያኔ ኢሕአፓን ለመውቀስ ያሰበ፤ ዛሬ ዐብን ምን አያደረገ እንደሆነ ማሰብ ይገባዋል። የዐብን ጥቂት አመራር የዐማራን እንቅስቃሴ ክደው ለብልፅግና አንዳደሩ ማሰብ ይገባል። ያ ደግሞ መላ የዐብን ደጋፊዎችን ከሃዲ አያደርጋቸውም። ከሁለት አንጻር አንባቢ እንዲመለከት እፈልጋለሁ። አንደኛ፤ ያን ጊዜ ምን እንደነበር መረዳት ስለሰሚያስፈልግ፤ ከሁሉም አቅጣጫ የነበረውን እንረዳ። ለፍርድም የሚያመቸው፤ ሁኔታውን ከሁሉም አቅጣጫ ስንረዳው ነው። ሁለተኛ ደግሞ፤ ከዚያ ወዲህ ለተከሰተው ሂደት ትክክለኛውን ተጠያቂ ክፍል ማወቅ አስፈላጊ በመሆኑ ነው። ተማሪዎች ሥልጣን ይዘው ሰው አልገደሉም። የራሳቸውን የፖለቲካ አስተሳሰብ ለመተግበር መንግሥታዊ ሥልጣን አልነበራቸውም። በሃሳብ ደረጃ የፈለጉትን ቢሉ፤ መጥፎ አያደርጋቸውም። ሥልጣን ይዞ አገራችንን ለዚህ ያበቃትን ክፍል ለይቶ ማወቅና ያንን ለፍርድ እንዲቀርብ ማድረግ ተገቢ ነው። እንዲያው ይሄን ወይንም ያንን ዓይነት አመለካከት አለውና ይወቀስ ማለት ተገቢ አይደለም። በርግጥ “የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር” ነኝ ባዩ ድርጅት ያገራችንን የፖለቲካ መድረክ ስላመሰቃቀለውና ተማሪዎች ባላሰቡት መንገድ ወስዶ ፍዳ ስላስከተለብን፤ ያንን ወገን የተማሪዎች ትግል አካል አድርጎ መውሰድና በዚያ ላይ ፍርድ መጣል፤ ይጎዳል። “የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር” አነሳስ፣ ዕድገትና ለሥልጣን መብቃት፤ ከአፄ ሚኒሊክ ጊዜ ጀምሮ ሲብጠለጠል የነበርና በኃይለ ሥላሴ ጉግሳ፣ በመለስ ዜናዊ አባት ባንዳው አስረስ ተላልፎ፤ የትግራይ ተበደለች ትርክት መሆኑን አንዘንጋ! በኦነግም ቢሆን የቆዬ በራሱ ትርክት የሄደ ነው። ሁለቱ ከተማሪው ትግል ጋር አይተሳሰሩም። የሚያገናኛቸው ቢኖር ጥቂት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከመሪዎቻቸው መካከል መገኘታቸው ብቻ ነው። ዛሬም ከመሪዎች ጋር የሚያቆልበው ወጣት የዛሬው ትውልድ አካል ነው። በያንዳንዳ ትውልድ፤ በጎና በጎ ያልሆኑ ክንውኖችን ያስተናገዱ ግለሰቦች አሉ። ያንን መረዳት ያስፈልጋል። ከሁሉ በላይ ደግሞ፤ ያለፈን ለመማሪያ ስናገናዝብ፤ መርጠን አይደለም። ሁሉንም ነው።

  • ይሄ መለጥዕፍ አልነበረበትም። የታረመው ከታች ተለጥፏል። ይሄ ምን ያስፈልጋል።

 5. Alemu thank you for your, I call it deep analysis. I wish if you add a little bit and send the Amharic and the English version to the media. I am a bit confused about the writer is he university Dean or religious title. I believe a man called Bahiru zewde may learn from your writing.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የአቶ አረጋ ከበደ መኪና በፋኖ እጅ ገብታለች አሁን በአማራ ህዝባዊ ሀይል ቃል አቀባይ አርበኛ ፋኖ ማርሸት ፀሐይ እየተሾፈረች ነው | “ፋኖ ገሎ ጨረሰን አንዋጋም” ጄኔራሎች

Next Story

ስለ ዐድዋው ጦርነት እና ድል በኢትዮጵያ ቤ/ክ አባቶች/ሊቃውንቶች አስቀድሞ ትንቢት መነገሩን እናውቅ ይሆን?! የዐድዋ ድልን፤ ያለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ማስብ ፈጽሞ የማይቻል ነው!!

Latest from ነፃ አስተያየቶች

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት

የፋኖ አደረጃጀቶች አንጻራዊ ወሳኝነትና የእስክንድር ነጋ ወሳኝ ሚና

ጭራቅ አሕመድ ያማራን ሕዝብ ለመጨፍጨፍ የተነሳው  በእስክንድር ነጋ ላይ ግልጽ ጦርነት እከፍታለሁ ብሎ በመዛት ስለነበር፣ ያ ማራ ሕዝብ ደግሞ ጭራቅ አሕመድን  ጨርቅ በማድረግ ቅኔያዊ ፍትሕ  (poetic justice) ሊሰጠው የሚገባው  በእስክንድር ነጋ መሪነት ነው።    ________________________________________ ያማራ ፋኖ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የቤታማራና የሸዋ

Share