በመጽሐፈ መነኮሳት ሲመዘኑ ”አቡነ ኤርምያስ” ከድጡ ወደ ማጡ ሰመጡ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

ከመጻሕፍተ መነኮሳት አንዱ የሆነው ፊልክስዩስ  ገጽ 106 ላይ “እንኪያስ መነኮሳት ነውር ነቀፋ የሌለባቸው ሁነው በፍጹም ሥራ ሊኖሩ ይገባቸዋል” ይላል፡፡* ሌላኛው መጽሐፍ መነኮሳት ማር ይሳቅ እንደዚሁ ገፅ 106 ላይ “አቡነ” ኤርምያስ ስሙን የዘረፉትን ቅዱስ ኤርምያስን ከጠቀሰ በኋላ “ እግዚአብሔር ሳንፈራ ሳንበርድ ጸላታችንን (ሰይጣንን ማለቱ ነው) እንገጥመው ዘንድ ያዝዛልና” ብሎ “ሳይቀድምህ ቅደመው…ትወጋው ዘንድ መር ብለህ ቁንጮውን ያዘው”* እያለ ያዝዛል፡፡

ሰይጣን እግዚአብሔርን የከዳ ቀደም ሲል ከመላእክት አንዱ እንደነበር ይታወቃል፡፡ መላእክት ደሞ እንደ ሰው አካል ወይም እጅና እግር እንደሌላቸው ይታወቃል፡፡ ሰይጣን ወይም ሳጥናኤል የሚጠቀመው እጅና እግር ያላቸውን ዋሾዎች፣ ቀጣፊዎች፣ ከሃዲዎችትን፣ ዘራፊዎች፣ አረምኔዎችና ጭራቆችን  መሆኑን “አቡነ ኤርምያስና ጓዶቻቸው” የዘነጉት ይመስላል፡፡ ሰይጣን የእርጉዝ ሆድ በመቅደድ፣ ሰው ዘቅዝቆ በመስቀል፣ ሕዝብን ከነነፍሱ በማቃጠል፣ እሬሳ በመጎተት፣ ገዳማትና ቤተከርስትያንን በማቃጠል እንደሚከሰት ለማመን ለግመዋል፡፡ “ይሁን ይሁን፤ አይሆንምን አይሆንም በል” የሚለውን የመጣፍ ቃል ተላልፈው እንኳን ሰይጣንን ቁንጮውን ሊይዙ  ሰይጣንን ሰይጣን ለማለትም እንጀራ አንቋቸዋል፡፡

አደራቸውን ለመወጣት ከመልገምም አልፈው “አቡነ ኤርምያስ” የአማራን ሕዝብ በሚጨፈጭፉት ሰይጣን በተሰቀላቸው ወታደሮች ታጅበው ፋኖን ስለመወረፋቸው ሲጠየቁ ሕዝቡን እየራበው ስለሆነ ለሆዱ ሲል ላጀቧቸው ጪራቅ ገዥዎች እጅ ይስጥ ዓይነት ቃለ መልስ ሰጥተው አርፈዋል**፡፡

“ጳጳሱ” ቅዱስ ዳዊትን በጎልያድ ላይ ያነሳው እግዚአብሔር ፋኖን በጭራቆች ላይ እንዳስነሳው ለማመን ተቸግረው ፋኖን ተማብጠልጠል አልፈው ጳጳስ ነኝ በሚሉበት አገር እሬሳ እንደ ግንድ መሬት ለመሬት የጎተተውን አረመኔ ትተው በውጭ ያሉ የፋኖ ደጋፊዎችን “የሬሳ ነጋዴዎች” ብለው ትርፍ ቃል ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ይህ ስርዓት በፍጹም አይድንም

“ዶሮ ብታልም ጥሬዋን” ይባላል፡፡ ሆዳም እሚያልም ምግቡን እንጅ እውነትን፣ ፍትህን፣ ክብርንና እምነትን ስላልሆነ እንደ ”አቡነ” ኤርምያስ ምክር ወይም ትዕዛዝ ተሆነ አማራ ለሆዱና ለህክምና ሲል ክብሩን፣ ማእረጉን፣ እምነቱን፣ ፍትህና እውነትን መጣል አለበት፡፡ እኒሁ “ጳጳስም” ሆነ ሌሎች ጓደኞቻቸው የአማራ ሕዝብ ለግማሽ ክፍለ-ዘመን በእቅድ አገር አልባ እንዲሆን ከተቻለም እንዲጠፋ የተፈረደበት መሆኑን ያውቃሉ፡፡ መስቀል ጨብጠውና ቆብ ደፍተው ግን ይኸንን በአማራ ላይ እየደረሰ ያለውን መከራ የክቡር አቶ ታዲዎስ ታንቶን ያህል የመናገር የእምነትም ሆነ የሞራል ብቃት አላገኙም፡፡

ጳጳሳት ከወራት በፊት እነ ሄሮድና ጲላጦስ ስልጣናቸው ሊነጥቋቸው ሲሉ ለሕዝቡ የድረሱልን ጥሪ አቅርበውና ሕዝብ አስፈጅተው ስልጣናቸውን ታረጋገጡ በኋላ ሕዝቡን ከፈጁት አረመኔዎች ጋር መላላስ እንደ ጀመሩ የሚታወቅ ነው፡፡ ህፃናት ሳይቀር በሚያርዱት በእነ ሄሮድስ ተገደውም አሜሪካን አገር በአስገድዶ መድፈር ሙከራ የተከሰሱ “ መነኩሴ ነኝ” ባይ ጣኦተኛ ጳጳስ አድርገውን ስልጣን እንደሰጡ የሲኖዶስ ተብየው ስራ አስኪያጅ የተናገሩትን ልብ ያለው የሚያስታውሰው ነው፡፡ ይህ ሁሉ እየሆነ “አቡነ ኤርሚያስ” ቤተክርስትያኗን እየጠበቁ እንደሆነ ሲናገሩ መስቀላቸውን ያነገቱበት ማተብ ትንሽም አልገታቸው፡፡

ምእመናን ሆይ፡-ቤተከርስትያን ማለት የቤተክርስቲያናን አእዋፍ (ራስ) ክርስቶስን፣ ሕዝብና የአምልኮት ሥፍራን (ቤተክርስትያናትና ገዳማትን) የሚያጠቃልል ነው፡፡ እነደሚታወቀው ቤተክርስትያኗን ቀጥ አርጎ የያዘው የአማራ ሕዝብ የህልውና አደጋ የተጋረጠበትና  በድሮን በመጨፍጨፍ ላይ ያለ ሕዝብ ነው፡፡ የአምልኮት ቦታውም በአህዛብና በአውሬዎች እየተቃጠለ ነው፡፡ ክርስቶስም ከእርሱ ይልቅ ይህቺን ምድራዊ ዓለም በመረጡ ጳጳሳትና አቡን እየተከዳ ነው፡፡ ታዲያ ቤተክርስትያኗን እየጠበቅን ነው የሚሉት የትኛውን የቤተክርስትያን ክፍል ጠብቀውት ነው?

ፋኖን ያብጠለጠለው የአቡነ ኤርምያስ አንደበት ለምእመናኑም እውቅና ባይሰጥም እግዚአብሔር ምስጋና ይግባውና የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን እየተጠበቀች ያለችው ለምኖ ሳይቀር አስራት በሚከፍለው ጽኑ እምነት ባለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው፡፡ ቤተክርስትያኗ እየተጠበቀች ያለችው አንገቱን ለሰይፍ ሊሰጥ በተዘጋጀ አማኝና ሰማእት በመሆን ላይ ባሉ የቤተክርስትያን አገልጋይ ካህናት ነው፡፡ ጳጳሳትና አቡኑ ሰማእትነታቸውን የስልጣን ማደላደያ ያደረጓቸው የሻሸመኔ መእመናንና ካህናት ለዚህ ምስክር ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን እየተጠበቀች ያለችው በህይወት ሳሉ በተዋደቁላት ቅዱሳን በአቡነ ጴጥሮስ፣ አቡነ ሚካኤል፣ አቡነ ቴዎፍሎስ፣ መላከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬና በሌሎችም መንፈስ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰቀለ? (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም)

የዛሬዎቹ አቡንና ጳጵሳት ያልሰነፉት የምእመናን አስራት በደሞዝና ውሎ አበል ስም መላፍና ቁንጣን ሲይይዛቸውም ወደ ውጪ ሄደው መታከሚያ ማድረግ ነው፡፡ “አቡነ ኤርምያስ” የቤተ-ክርስትያኗ ግድግዳና ማገር የሆነው የአማራ ሕዝብ እየተራበና የህክምና አገልግሎት እንደማያገኝ በተናገሩበት ምላስ አንዱ ጓደኛቸው በአሁኑ ሰዓት ዘመናዊ ሕክምና ለማግኘት አሜሪካን አገር እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በፊቱም ብዙዎቹ አሜሪካና አውሮጳ እየሄዱ ህክምናውንም ሽርሽሩንም አድርገዋል፡፡ መታከሚያ ያጣ ቁስለኛ በቁስሉ እየለመነ አስራት ይከፍላል ጳጳስና አቡን ዶላሩን እንደ ሳር ነስንሶ አውሮጳና አሜሪካ ይታከማል፣ ይዝናናል፡፡ ቲኬት ቆርጦ፣ ለወራት ሆቴል ተከራይቶ፣ ካለምንም ኢንሹራንስ አሜሪካን አገር መጥቶ ለመታከም የሚያስፈልገው ገንዘብ ኢትዮጵያ ውስጥ ቢያንስ አንድ ሺህ ክሊኒክ አሰርቶ ሥራ ያስጀምራል፡፡  ጳጳስት ምእመናኑ ሲታመሙ ተጠመቁን እየሰበኩ ወደ ፀበል ሥፍራዎች እየላኩ የእነሱ ፀበል ቦታዎች ዘመናዊ የአውሮጳና የአሜሪካ ሆስፒታሎችና ክልኒኮች ሆነዋል፡፡ አስራት ከፋዩ ሕዝብ ሲኖድን በሚያሽከረክሩት ጭራቅ ገዥዎች በችጋርና በበሽታ ሲያልቅ ጳጳስና አቡን እንደሚሰግዱላቸው አረመኔ ገዥዎች ሁሉ አውሮጳና አሜሪካ እየነጎዱ ሆድ ቁርጠትና ራስ ምታት ሲታከሙ ይታያል፡፡ ይኸም ሆኖ ዓይናቸውን በጨው ታጥበው ምዕመናኗ እየተጨፈጨፈ ያለውንና ገዳሟና ሕንፃዋ የሚነደውን ቤተክርስትያን እየጠበቅን ነው ይሉናል፡፡

እንደ ሌሎች የሲኖድ ጓደኞቻቸው ሁሉ በትምህርት፣ በእምነትና በመንፈስ ልዕልና የበሰሉ የማይመስሉት “አቡነ ኤርምያስ” አንዲትም የመጽሐፍ ቃል ሳይጠቅሱ ቃለ መጠየቁን በካድሬ ቃላት ጨርሰዋል፡፡ ለሆዱ ሲል የአማራ ሕዝብ ክብሩን፣ እምነቱን፣ ማእረጉን፣ ህልውናውንና አገሩን ለሰይጣን አሳልፎ ይስጥ ዓይነት የሚያሳፍር ንግግር አድርገውን ተድጡ ወደ ማጡ ወርደዋል፡፡ እግዚኦ!

 

*ምእመናን ሆይ የመነኮሳት፣ ጳጳሳትና አቡኑን መለኮታዊ ግዴታ ለማወቅ እባክዎን መጻሕፍተ መነኩሳትን ያንብቡ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡ መጻሕፍተ መነኮሳት 1929 ብርሃንና ሰላም እትም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኦሮሞ ጠባብ ብሔርተኞች ለኦሮሞ ሕዝብ ያላቸው ጥያቄ ምንድ ነው? - በፈቃዱ ኃይሉ

 

**ቃለ መጠይቁ የአማራ ህዝብ ተበድሏል። ይህ መንግስት ለሁሉ ነገር ጥፋተኛ ነው። እኔ ፋኖን አልወቀስኩም። ይቅርታ እጠይቃለሁ” ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ – (amharic-zehabesha.com)

7 Comments

 1. በላይነህ አባተ መልካም ነገር ከዚህ በፊት አይተንባቸዋል አንተ ያየኸውን እኛም አይተናል ዘለው አቶ(ቀሲስ) በላይን ወይም ሳሮስን ከሚሆኑ በዚሁ ታልፈው ወደ ወገን ቢመለሱ መልካም ይሆናል። ትንሽ ስህተት ባየን ቁጥር እንዲህ ቱግ ብለን አይሆንም ዶር/አክሎግ ቢራራ የአባይ ጉዳይ ከፖለቲካ በላይ ነው ሃገሬን ከኢኮኖሚ ድህነት የሚያላቅቃት ነው ብለው ከዶ/ር ስለሽ ጋር ዋሽንግተን ኢትዮጵያ ኤምባሲ ተገኝተው ምክር በመስጠታቸው ያ ሁሉ ናዳ በደቂቃን ወረደባቸው ፤ዶር ዳኛቸው አሰፋም በቴዎድሮስ ጸጋዬና ጸረ ኢትዮጵያን ሃይሎች ወከባው ባይበዛበት እንዲህ ጭልጥ ብሎ ባልሄደ ነበር፡፡መልካም ወገኖች ላይ ዱላው ይበረታልና ትንሽ ቢንሸራተቱም ተመጣጣኝ ተግሳጽ ይበቃ ነበር፡፡ እንዲህ ካልሆነ ያለሰው መቅረታችን ነው ልብ በልልኝ ዳንኤል ክብረትን አላልኩም እሱ ለይቶለታል ወይ ተዙሮበታል፡፡

 2. Zubeda,
  አንተም/አንቺም ቀላል ነገር አርግሀው/ሽው? እንደበፊቱ የፋኖ መሪዎችን አዘናግተው ለማስበላት የሚያደርጉትን የውሸት ሽምግልና? ፋኖን ማስበላግት አማራን ማስጨረስና ዘሩን ማጥፋት ነው፡፡ ይህ ጸሐፊ አማራን ተሚፈጀው ባንዳ ጀኔራል ጋር ተቀምጠው ፋኖን የተሳደቡትን ፎቶ ቢጠቀም ጥሩ ነበር፡፡

  ስጋትሽ/ስጋትህ ይገባኛል ነገር ግን ይህ የአማራን ህልውና የሚፈታተንና አደጋ ውስጥ የሚከት ነገር ነው የፈጠሙት፡፡

 3. Wow! “መታከሚያ ያጣ ቁስለኛ በቁስሉ እየለመነ አስራት ይከፍላል ጳጳስና አቡን ዶላሩን እንደ ሳር ነስንሶ አውሮጳና አሜሪካ ይታከማል፣ ይዝናናል፡፡” True! True! True!

  How in the universe can they defend this? Glad I am not them.

 4. ሽምግልና ልቀመጥ ያሉ አልመሰለኝም ቀሳውስት ሲገደሉ አልሰማሁም አይነት ንግግር አድርገዋል ፋኖንም የሚገባውን ክብር እንዳልሰጡ እገምታለሁ የአገዛዙም ቅልቦች አጠገባቸው ቁጭ ብለው ሲገለባበጡና አይናቸውን ሲያጉረጠርጡ ተመልክተናል እንግዲህ የስጋቸውም ነገር አድልቶባቸው ሊሆን ይችላል፡፡ በእርግጥም የበጎች እረኛ ሁነው ከዛች ወጣት ባነሰ ሁኔታ ለህዝባቸው መቆማቸው ያሳዝናል ባይሆን እርምት ቢያደርጉ ቢመከሩ መልካም ነበር፡፡ ጎበዝ የሳርዮስ ደቀ መዝሙሮችን አብይ መሃመድ በጎቾን ይዤ መጥቻለሁ ብሎ ሲያላግጥ ነበር ተኩሎቾን ይዤ መጥቻለሁ ከማለት ይልቅ፡፡ በዚህ ላይ የአቶ በላይ ተከታዮች ጋር ደምረህ አቡነ ኤርምያስና ተከዮቻቸውን ስትጨምርበት ለቤተ ክህነቱ መልካም አይመስልም፡፡ አንዳንዴ ከትግሬዎችም እንማር አብረሃ በላይን፡ ሳእረ መኮንንን አንድ ቀን ሲዘልፉ ሰምተህ ታውቃለህ? ስብሃት ነጋ፤ጻድቃን ገ/ተንሳይ፤ሰየ አብረሃ…..።በትግሬ ስም አገር ምድሩን ሲግጡ ትናንሽ የትግሬ ዘራፊዎች ድርሻችንን ከፍ አድርጉት ሲሉ ሰምተህ ታውቃለህ? እኛ አካባቢ ግን ከፋብሪካ እንደወጣ ምርት ሁል ጊዜ ተመሳሳይ ነገር እንጠብቃለን ይሄንን ከሩቅ ሁኖ ማብጠልጥል ይቀላል በቦታው ሲገኙ ግን ሌላ ይሆናል፡፡ ቀሲስ (አቶ) በላይ ጁዋርን የማታውቅ ኦርቶዶክስ እኔም አላውቃትም ብሎ ሲናገር አንድም ተቃውሞ አልገጠውም፡፡ ጁዋር ግን በአንጻሩ ከእስልምና ውጭ አንገቱን ቀንጥሱ ብሎ ጂሃድ ያወጀ የፍርድ ቀን ሲመጣ እጁን በገመድ ታስሮ ለፍርድ የሚቀርብ ነው፡፡ ግለሰቡ አሜሪካዊ መሆኑ እየታወቀ አብይ መሃመድ፤ብርቱካን ሚደቅሳ፤መራራ ጉዲና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ተሳታፊ ከመሆን ባሻገር የፊት ወምበር እንዲይዝ አድርገውታል ጎበዝ ተበላልተን አንለቅ እንጅ፡፡

 5. በላይነህ አባተ ትችትህ ከወገን የመጣ አይደለም። አቡነ አኤርምያስን እስከዚህ መናገርህ ላሊበላ ላይ በተናሩት አለመሆኑን የንግግርህ ደረጃ አሳበቀበህ የዽዽስና ሥም ዘረፉ፣ እንደሌሎቹ ዻዻሳት በመንፈሳዊ እውቀት እእና ሞራል የለቸውም፣ በንግግራቸው አንድም የመጽሀፍ ቅዱስ ቋንቋ አልተጠቀሙም ወዘተ
  በአጠቃላይ አነሳስህ አጋጣሚውን ተጠቅመህ አባታችን ላይ ተጨማሪ ድጋይ የምትወረውር ጠላት ነህ እንጂ የፋኖም፣የአማራ ህዝብም ሆነ የኦርቶዶክስ ውግንና የለህም። አባታችን ዻዻስ ከመሆናቸው በፊትም አሁንም ለእውነት እና ለህዝብ ውግንና ያላቸው ፣ ዓለምን የናቁ አባታችን ናቸው የሴራ ፖለቲከኞች ሊያሳስቷቸው ቢሞክሩም እናንተ የሴረኞችጉዳይ አስደጻሚዎች አንገት ልታስደፉ እና ሁለተኛ ለአደባባይ እንዳይሟገቱ ለማፍረግ ብትሞክሩም እኛ በአገራችን በችግሩ ውስጥ አብረን የምንገዘኝ ልጆቻቸው እንረዳቸዋለን።እየተራረምን ለድል እንበቃለን።

 6. ሀይለሚካኤል በላይነህ አባተ ላይ ትችት ስታዘንብ በምክንያት መደገፍ በተገባህ ነበር። ከመጻፉ አልጠቀሱም ላለው የጠቀሱትን ጠቅሰህ ማስረዳት በተገባ ነበር ያ ካልሆነ እርግማን ይሆናል። አንተን ዛሬ ያወቅንህ በላይነህን ለመተቸት መጥተህ ነው በላይነህ አባተ ግን የሀገርን ጉዳይ በንቃት የሚከታተል ዜጋ ነው። ብጹእ አባታችን በክፉ ቀን ህዝብ ጋር ቁመዋል ለህዝብ ሲል ህይወቱን የሰጠ ፋኖ ወጥቶ ህዝብ ገዳዩ የአብይ ሰራዊት ይምጣልን ማለት አግባብነት የለውም። እሳቸውም በስህተት ይቀጥሉ አይነት እርዳታ ነው ያደረግህላቸው። ፍቃድህ ከሆነ ብትመልስልን ከተከዜ ወዲያ ነህ? ትግሬ ነህ ላለማለት ነው።

 7. ሀይለሚካኤል በላይነህ አባተ ላይ ትችት ስታዘንብ በምክንያት መደገፍ በተገባህ ነበር። ከመጻፉ አልጠቀሱም ላለው የጠቀሱትን ጠቅሰህ ማስረዳት በተገባ ነበር ያ ካልሆነ እርግማን ይሆናል። አንተን ዛሬ ያወቅንህ በላይነህን ለመተቸት መጥተህ ነው በላይነህ አባተ ግን የሀገርን ጉዳይ በንቃት የሚከታተል ዜጋ ነው። ብጹእ አባታችን በክፉ ቀን ህዝብ ጋር ቁመዋል ለህዝብ ሲል ህይወቱን የሰጠ ፋኖ ወጥቶ ህዝብ ገዳዩ የአብይ ሰራዊት ይምጣልን ማለት አግባብነት የለውም። እሳቸውም በስህተት ይቀጥሉ አይነት እርዳታ ነው ያደረግህላቸው። ፍቃድህ ከሆነ ብትመልስልን ከተከዜ ወዲያ ነህ? ትግሬ ነህ ላለማለት ነው። እዚህ ጎረቤት ትግሬዎች አሉ ሲፈልጋቸው ይሰልማሉ ጥቅም የሚያገኙ ሲመስላቸው ወይ ይከረስትናሉ ወይ ኦሮሞ ይሆናሉ ወይ ሱማሌ ወይ የመናዊ ይሆናሉ ። ብጹእ አባታችንን ከቀረብካቸው መንግስታት ይሄዳሉ ይመጣሉ እርሶ ግን ከተገፋው ጎን ይቁም በላቸው። በቀበሮ ከተከበቡ በሳቸውም መፍረድ ከባድ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share