አቡነ ኤርምያስ ሆይ፣ ቅድስት ቤተክሲያን አቡን (ማለትም የሐይማኖት አባት) ያደረገችወት ፍርድ ጠፋ፣ ግፍ ተንሰራፋ፣ ፍትሕ ጎደለ፣ ሕዝብ ተበደለ እያሉ ለተገፉ፣ ለተበደሉና ለተጨቆኑ መዕምኖችወ እንዲጮሁ መሆኑን ለርስወ መንገር አያስፈልግም። ርዕት ቤተክሲያን መንፈሳዊ አባት ያደረገቸወት በሂወትወ ቆርጠው፣ ለመስዋዕትነት ራስወን አዘጋጅተው፣ ለፍትሕ ርትዕ በመቆም ግፈኞችን ያለ ምንም ፍራቻ አጥበቀው እያወገዙ በመንፈሳዊ መንገድ አጥበቀው እንዲዋጓቸው ነው።
እርስወ እያደረጉ ያሉት ግን በዳይም ተበዳይም እንዳይቀየሙወት ከበዳይም ከተበዳይም ጋረ የቆሙ እያስመሰሉ፣ እንደ ሸማኔ መወርወሪያ እዛና እዚህ እያሉ፣ እርስወን በማይመጥን በሚያሳፍር ሁኔታ መለሳለስና መቅለስለስ ነው። ልወደድ ባይነት ደግሞ የሐይማኖት አባት ሳይሆን የፖለቲከኛ ባሕሪ ነው። ስለዚህም የርስወ ተግባር ሙሉ በሙሉ የሚመሰክርብወት የሐይማኖት አባትነት ሳይሆን የፖለቲከኛነት ሚና እየተጫወቱ መሆኑን ነው።
ሙሉ ፖለቲከኛ በመሆን የሚፈልጉትን ቡድን ሙሉ በሙሉ መደገፍ ሙሉ መብትወ ነው። የሐይማኖት ካባ ለብሰው የፖለቲካ ደባ የመፈጸም መብት ግን የለወትም። አለበለዚያ የሐይማኖት አባት በማድረግ ያከበረችወትን ቅድስት ቤተክሲያን ማራከስ ይሆንብወታል። ስለዚህም እያራከሷት ያሉት ቅድስት ቤተክሲያን አውግዛወት የደፋችልወትን ቆብ ሳታወልቅበወት በፊት እስወ ራስወ በገዛ እጅወ እንዲያወልቁት ይመከራሉ። በወያኔና በኦነግ የተዋረደቸው የቅድስት ቤተክሲያን ልዕልና እርስወ ከሚገምቱት በላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየተቃረበ ስለሆነ፣ ቆብወን በገዛ እጀወ አውልቀው የቀረቸወትን እንጥፍጣፊ ክብር ለመጠበቅ ያለወት ጊዜ በጣም አጭር ነው። ሳይመሽ ገሽሽ ይበሉ።
መስፍን አረጋ
mesfin.arega@gmail.com